2021 (እ.አ.አ)
ልትሆኑ የምትችሉትን ከሁሉም የተሻለውን ማንነታችሁን መገንባት።
መስከረም 2021 (እ.አ.አ)


“ልትሆኑ የምትችሉትን ከሁሉም የተሻለውን ማንነታችሁን መገንባት፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ መስከ. 2021 (እ.አ.አ)፣ 6–7።

ወርሀዊ የ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ መስከረም 2021(እ.አ.አ)

ልትሆኑ የምትችሉትን ከሁሉም የተሻለውን ማንነታችሁን መገንባት

ደስተኛ ህይወትን ለመገንባት የሚረዱ አምስት መንገዶች።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥13–14

የወጣት ሴት ራጅ፣ የቤተመቅደስ ብሉ ፕሪንት

ሥዕል በጁሊዬት ፐርሲቫል

የከርትላንድ ቤተመቅደስን እንዲገነባ ጌታ ጆሴፍ ስሚዝን ሲያዘው የሚገነባበትን መንገዶች በራሱ እንዲፈልግ አልተወውም። ወደስኬት የሚመራውን እቅድ ገለጸ።

ጌታም “በአለም በሚሰሩበት ሳይሆንም፣ ቤት ይሰራ” በማለት ተናገረ። “በማሳያችሁ ስርዓት ይሰራ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥13–14)። ከዚያም ጌታ ቤተመቅደሱ እንዴት እንደሚሰራ መመሪያዎችን ሰጠ ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥15–17ይመልከቱ)።

ምስጋና ይግባውና ጌታ ቤተመቅደሶችን ከመገንባት የበለጠም ነገር አሳይቶናል። እንዲሁም ልንሆን የምንችለውን ከሁሉም የተሻለውን ሰው እንድንሆን የሚረዳን መመሪያም ሰጥቶናል። ስንከተላቸው “አለም በሚሰሩት ሳይሆን” በጌታ ንድፍ መሰረት ህይወታችንን እንገነባለን።

ደስተኛ ህይወትን ለመገንባት የሚረዱ ኢየሱስ ክርስቶስን ማዕከል ያደረጉ አምስት መንገዶች እነሆ።

የተረጋገጠ መሰረት ገንቡ

ማንኛውም አርኪትክት ወይም ገንቢ ጠንካራ መሰረት ለሁሉም ህንጻ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ይነግራችኋል። ለህይወታችን ከሁሉም የተሻለው መሰረት “አዳኝ በሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በክርስቶስ ዓለት መሰረታች[ን]ን መገንባት” ነው ሲል ሄለማን አስተምሯል (ሄለማን 5:12)። ወደእርሱ በመምጣት እና ትምህርቶቹን በመከተል ክርስቶስን መሰረታችን ማድረግ እንችላለን። የህይወታችሁን መሰረት ክርስቶስን በማድረግ ረገድ እንዴት እየሰራችሁ እንደሆነ ይሰማችኋል?

ሌሎችን ማገልገል

እግር

በወቅቱ በቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ በነበሩት በፕሬዚዳንት ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ መሰረት ህይወታችንን ለመገንባት ያለው ሌላኛው ታላቅ መንገድ “ጌታን እና በዙሪያችን ያሉትን ስናገለግል” ይመጣል።1 ሌሎችን ስታገለግሉ ኢየሱስ ያደረገውን እያደረጋችሁ ነው እንዲሁም ይበልጥ እንደእርሱ መሆንን እየተማራችሁ ነው። እንዲሁም የምትባርኩት የምታገለግሏቸውን ሰዎች ብቻ ሳይሆን እናንተም ትባረካላችሁ።

መደበኛ የጸሎት እና የቅዱስ ጽሁፍ ጥናት ልምድ ፍጠሩ።

የሚጸልዩ እጆች

ደስተኛ ህይወት የሚገነባበት ሌላኛው መንገድ ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ዝምድና መመስረት ነው። ያንን የማድረጊያ ትልቁ መንገድ ጸሎት እና የቅዱስ ጽሁፍ ጥናት ነው።

ፕሬዚዳንት ኡክዶርፍ እንዲህ ብለዋል “ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር፣ ከእርሱ ጋር ትርጉም ያለው ጊዜ ሊኖረን ይገባል። በርጋታ በቀን ተቀን የግል ጸሎት እና የቅዱስ ጽሁፍ ጥናት … ላይ በማተኮር ወደሰማያዊ አባታችን ለመቅረብ ጊዜያችንን እና ጥረቶቻችንን በጥበብ ስራ ላይ እናውላለን።”2

ጸሎት በሰማይ ካለው አባታችን ጋር የመነጋገር አድል ነው። እርሱም ያውቀናል፣ ይወደናል፣ እናም እኛን መስማት ይፈልጋል። በቅንነት ስንጸልይ፣ ምስጋና ስናቀርብ እና የሚያስፈልጉንን ነገሮች ስንጠይቅ ያዳምጠናል እንዲሁም በራሱ መንገድ እና ጊዜ ሁልጊዜ ይመልሳል።

የቅዱስ ጽሁፍ ጥናትን በተመለከተ አንድ ትክክለኛ መንገድ የለም። አስፈላጊው ነገር ማንበባችሁ ነው። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል “በየቀኑ የእግዚያብሄርን ቃል በጥልቅ ማጥናት መንፈሳዊነትን ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው። ”3 በያንዳንዱ ቀን ቅዱሳን ጽሁፎችን ለማንበብ ጊዜ መስጠት ያለጥርጥር የእምነት እና የጥንካሬ ህይወት እንድትገነቡ ይረዳችኋል።

ራሳችሁን መልካም እንድታደርጉ በሚያበረታቷችሁ ሰዎች ክበቡ።

እጆቹን የዘረጋ ልጅ

ሰማያዊ አባት ከሌሎች ጋር እንድንገናኛ እና ዝምድና እንድንመሰርት ይፈልጋል—በተለይ ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር አብዛኛውን ጊዜ አብረናቸው በምንውላቸው ሰዎች እንቀረጻለን። የቤተክርስቲያን አባላት ሆኑም አልሆኑ ራሳችሁን ወንጌልን እንድትኖሩ፣ የጌታን መስፈርቶች እንድትጠብቁ እንዲሁም የተሻለ ሰው እንድትሆኑ በሚረዷችሁ ሰዎች ክበቡ። በዙሪያችሁ ያሉትም ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ መርዳትም ትችላላችሁ፡፡ የትኛው ጓደኛችሁ ነው መሰረታችሁን በጽድቅ ላይ እንድትገነቡ እየረዳችሁ ያለው፡፡

መሰረታችሁን በመገንባት ደስታ አግኙ፡፡

ቤተክርስቲያን መሄድን እና ቅዱስ ቁርባን መውሰድን፣ ቃልኪዳኖችን መግባትን እና መጠበቅን እንዲሁም የህያው ነቢያትን ምክሮች መከተልን ጨምሮ ህይወታችሁ በመንፈሳዊ ጠንካራ እና ደስታ ያለው እንዲሆን ለመገንባት የምትችሉባቸው ሌሎች ብዙ መንገዶች አሉ፡፡

እነዚህ ነገሮች ሁሉ ስራ እና ጊዜ እንደሚጠይቁ ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ ሁልጊዜ መገንባት እና መማር አለ ነገር ግን ያንን ብቻችሁን ማድረግ አይጠበቅባቸሁም፡፡ እናንተ እና እርሱ የምትኮሩበትን እና ደስታ የሚያመጣላችሁን ህይወት ለመገንባት የተቻላችሁን ስታደርጉ ጌታ በየቀኑ ይረዳችኋል፡፡

ማስታወሻዎች

  1. ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “Waiting on the Road to Damascus፣” ሚያዝያ 2011 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 76)።

  2. ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “Of Things That Matter Most፣” ጥቅምት 2010 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2010 (እ.አ.አ)፣ 21)።

  3. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ ”Hear Him፣” ሚያ.2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ (ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 89)።