“የከርትላንድ ቤተመቅደስ፣” ጓደኛ፣ መስከረም 2021 (እ.አ.አ)
ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ መስከረም 2021 (እ.አ.አ)
የከርትላንድ ቤተመቅደስ
እግዚያብሄር ቤተመቅደስ እንዲገነባ ለጆሴፍ ስሚዝ ነገረው። መገለጡ ምን እንደሚመስል አሳየ። የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል።
የቤተመቅደሱን ግንባታ ለመርዳት ቅዱሳን በህብረት ሰሩ። ሰዎች ረዣዥም ግንቦችን ሰሩ። ሴቶች መጋረጃዎችን እና ምንጣፎችን ሰሩ። ልጆች መሳሪያዎችን እና ውሃ ለሰራተኞች በማምጣት ረዱ።
ቤተመቅደሱ ሲያልቅ ቅዱሳኑ ወደውስጡ ገቡ። መዝሙር ዘመሩ እንዲሁም እየጮሁ “ሆሳዕና!” አሉ። ቤተመቅደሱን ለመመረቅ(ለመባረክ) ጆሴፍ ጸሎት አደረገ።
ከሳምንት በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ ጆሴፍ ስሚዝን እና ኦሊቨር ካውድሪን በቤተመቅደሱ ጎበኘ። ኢየሱስ ቤተመቅደሱን እንደቤቱ እንደተቀበለው ተናገረ።
ዛሬ በአለም ዙሪያ ቤተመቅደሶች አሉ። እያንዳንዱ ቤተመቅደስ ቅዱስ ቦታ ነው። አንድ ቀን ወደውስጥ እገባለሁ ከእግዚያብሄርም ጋር ቃልኪዳን አደርጋለሁ።