2021 (እ.አ.አ)
አጠቃላይ ጉባኤ፦ዓለም ዓቀፍ የቤተክርስቲያን ስብሰባ
መስከረም 2021 (እ.አ.አ)


“አጠቃላይ ጉባኤ፦ዓለም ዓቀፍ የቤተክርስቲያን ስብሰባ፣ ” ሊያሆና፣ መስከረም 2021 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ መስከረም 2021(እ.አ.አ)

አጠቃላይ ጉባኤ፦ዓለም ዓቀፍ የቤተክርስቲያን ስብሰባ

በአጠቃላይ ጉባኤ ነቢያትን እና የቤተክርስቲያን መሪዎችን እናደምጣለን። እግዚያብሄር እንድንሰማ የሚፈልገውን ያስተምሩናል።

የጉባኤ ማዕከል የውጪኛው ክፍል

በሚያዝያ እና በጥቅምት ቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ ጉባኤ የተሰኘ ተከታታይ ስብሰባዎችን ታካሂዳለች። መሪዎች ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለወንጌሉ ያስተምራሉ እንዲሁም ይመሰክራሉ። አጠቃላይ ጉባኤ የሚካሄደው በሶልት ሌክ ስቲ፣ ዩታ፣ አሜሪካ ውስጥ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ከ80 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ይሰራጫል። ሁሉም የቤተክርስቲያኗ አባሎች እና ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ንግግሮቹን እንዲያዳምጡ ተጋብዘዋል።

የጉባኤ ማዕከል የውስጠኛው ክፍል

የመጀመሪያዎቹ የቤተክርስቲያን ጉባኤዎች።

ቤተክርስቲያኗ በይፋ የተቋቋመችው ሚያዝያ 6፣1830 በተካሄደ ስብሰባ ወቅት ነበር።( ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 20)። የመጀመሪያው አጠቃላይ ጉባኤ የተካሄደው ሰኔ 9 ቀን 1830 ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት አመራር አባላት ሊሰበሰቡ በሚችሉባቸው ቦታዎች አጠቃላይ ጉባኤዎች ሲካሄዱ ነበር። በ1840ዎቹ መሪዎች ጉባኤዎችን በአመት ሁለት ጊዜ ማድረግ ጀመሩ።

ፕሬዚዳንት ሞንሰን በመነጋገሪያ አትሮኖስ ፊት

በአሁኑ ጊዜ ጉባኤዎች እንዴት እንደሚዘጋጁ

የቀዳሚ አመራር፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን እና ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች በአጠቃላይ ጉባኤዎች ንግግር ያደርጋሉ። በቤተመቅደስ አደባባይ የሚገኙ የታበርናክል ዘማሪዎች እና ሌሎች የቤተክርስቲያን ዘማሪዎች መዝሙር ያቀርባሉ። እያንዳንዱ ጉባኤ አምስት ክፍለ ጊዜዎች አሉት፦ቅዳሜ ሶስት እና እሁድ ሁለት። በሚያዝያ፣ ቅዳሜ የሚደረገው ሶስተኛው ክፍለ ጊዜ ለአሮናዊ እና ለመልከጸዲቅ ክህነት ቡድን አባላት ነው። በጥቅምት ለሴቶች መረዳጃ ማህበር እና ለወጣት ሴቶች አባላት ነው።

የመሪዎች ትምህርቶች

ከጉባኤ በፊት ባሉት ወራት የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ስለምን እንደሚያስተምሩ ይጸልያሉ። ጌታ ምን መናገር እንደሚገባቸው እንዲያውቁ ያነሳሳቸዋል። የወንጌልን እውነቶች ያስተምራሉ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንድንጠብቅ ይጋብዙናል፡፡ ስለኢየሱስ ክርስቶስም ይመሰክራሉ እንዲሁም እንድንከተለው ያበረታቱናል፡፡

ከጉባኤ መማር

ከአጠቃላይ ጉባኤ በፊት ጌታ እንድንማር የሚፈልገውን እንድንሰማ ልንጸልይ እንችላለለን፡፡ ንግግሮቹን ስንሰማ መንፈስ ልናውቅ የሚገባንን ያስተምረናል። ከጉባኤው በኋላ ንግግሮቹ በChurchofJesusChrist.org ላይ፣ በወንጌል ቤተ-መጽሐፍት መተግበሪያ ውስጥ እና በ ሊያሆናውስጥ ይገኛሉ። ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለወንጌሉ ይበልጥ ለመማር ንግግሮቹን በጸሎት መንፈስ ልናጠና እንችላለን።

ከቅዱሳን መጻህፍት

ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር እንድንገናኝ አስተምሯል( 3 ኔፊ 18፥22ይመልከቱ)።

የቤተክርስቲያን አባላት በአንድነት ሲያመልኩ ጌታ ከእነርሱ ጋር ይሆናል ( ማቴዎስ 18፥20ይመልከቱ)።

የቤተክርስቲያን አባላት ”እርስ በራሳ[ቸው] [ይ]ማማሩ እና [ይ]ተናነጹ ዘንድ” አዟል(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 43፥8ይመልከቱ)።

የቤተክርስቲያን አባላት በክርስቶስ እምነት ሲያሳዩ በሚሰበሰቡ ጊዜ የእርሱ መንፈስ ከእነርሱ ጋር ይሆናል( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 44፥2ይመልከቱ)።