“ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያኑን ሰየመ፣” ጓደኛ ጥቅምት 2021 (እ.አ.አ)።
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ ጥቅምት 2021 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያኑን ሰየመ
ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያኗን ምን ብሎ መሰየም እንዳለበት ለጆሴፍ ስሚዝ ነገረው። “የኋላኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን“ ተብላ ትጠራለች አለው።
ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሉት ቃላት ከቤተክርስትያና ስም እጅግ አስፈላጊው ክፍል ነው። ይህችም የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በመሆኗ፣ በእርሱ ስም ተሰይማለች።
የኋላኛው ቀን ቅዱሳን ማለት የዚህ ዘመን የቤተክርስትያን አባላት ማለት ነው።
ነቢያት እና ሐዋርያት የቤተክርስትያኗን ትክክለኛ ስም መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ አስተምረዋል። በኢየሱስ ክርስቶስ እንደምናምን ሌሎች እንዲያውቁ ይረዳል።
ሌሎች በምን እንደማምን ሲጠይቁኝ፣ “በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ። እኔ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ነኝ” ብዬ መመለስ እችላለሁ።
© 2021 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, October 2021 ትርጉም። Amharic. 17474 506