2021 (እ.አ.አ)
የቤተመቅደስ ስራ
ጥቅምት 2021 (እ.አ.አ)


“የቤተመቅደስ ስራ” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2021 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ጥቅምት 2021 (እ.አ.አ)

የቤተመቅደስ ስራ

ቤተመቅደሶች የጌታ ቤቶች ናቸው። በቤተመቅደሶች ውስጥ ስርአቶችን መቀበል እና ከጌታ ጋር ቃል ኪዳኖችን መስራት እንችላለን። በቤተመቅደስ ውስጥ ለቅድመ አያቶቻችን ስርአቶችን መፈፀምም እንችላለን፡፡

ቤተመቅደስ

የባራንኪያ ኮሎምቢያ ቤተመቅደስ ፎቶ በብሩኖ ሊማ

በዘመናት ጌታ ህዝቡ ቤተመቅደሶችን እንዲገነቡ ያዝዛቸው ነበር። ቤተመቅደሶች የእግዚአብሔር ፍቅር ሊሰማን የሚችልባቸው፣ ስርአቶችን የምንቀበልባቸው እና ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳኖችን የምንፈጽምባቸው የተቀደሱ ቦታዎች ናቸው። እነዚህን በረከቶች ብዙ ሰዎች እንዲያገኙ ቤተክርስትያኗ በአለም ዙሪያ ቤተመቅደሶችን እየገነባች ነች።

አንዲት ሴት ከቤተመቅደስ ፊት ለፊት

በኦከር ማውንቴን ቤተመቅደስ ፊት ለፊት የቆመች የአንዲት ሴት ፎቶ በነክሲኦ እና ማቲው ረየር

የመንፈስ ስጦታ

በቅድስና የሚኖሩ የቤተክርስትያን አባላት ስርአቶችን ለመቀበል እና ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖች ወይም የተስፋ ቃላትን ለመፈጸም ወደ ቤተመቅደስ ይሄዳሉ። ከቤተመቅደስ ስርአቶች መካከል አንዱ የመንፈስ ስጦታ ነው። Endowment [የመንፈስ ስጦታ[ የሚለው የእንግሊዘኛ ቃል “ስጦታ” ማለት ነው። የመንፈስ ስጦታ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። በዚህ ስርአት ለደህንነታችን የሰማይ አባታችን ስላለው እቅድ እንማራለን እና የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለመጠበቅ ቃል ኪዳኖች እንገባለን። ለምንገባው ቃል ኪዳኖች ታማኝ ከሆንን እግዚአብሔር ይባርከናል።

ጥንዶች በቤተመቅደስ ፊት

ጥንዶች በማኒላ ፊሊፒንስ ቤተመቅደስ በኩል ሲራመዱ ፎቶ በክርስቲና ስሚዝ

ቤተሰቦችን በአንድ ላይ ማተም

በቤተመቅደስ ውስጥ የሚካሄድ ጋብቻም መታተም ተብሎ ይጥራል። ጥንዶች በቤተመቅደስ ውስጥ ሲታተሙ እና ቃል ኪዳኖቻቸውን ሲጠብቁ ለዘለአለም የተጋቡ ይሆናሉ። ልጆች ካሏቸውም፣ ልጆቻቸው ከእነርሱ ጋር የታተሙ ይሆናሉ። ልጆች ከወለዱ በኋላ የታተሙ ወላጆች ልጆቻቸው ከእነርሱ ጋር እንዲታተሙ ማድረግ ይችላሉ። በጽድቅ የሚኖሩ ከሆነ፣ ለዘላለም ቤተሰቦች ይሆናሉ።

የሊዝበን ፖርቹጋል ማጥመቅያ ቦታ

የሊዝበን ፖርቹጋል ማጥመቅያ ቦታ ፎቶ በለስሊ ኒልሰን

የቤተመቅደስ ስራ ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች

ስለ ቤተሰቦቻችን የዘር ሃረግ ስራ የምንሰራው ስለአያቶቻችን ለማወቅ ነው። ከዚያም በእነሱ ፈንታ የቤተመቅደስ ስራ እንሰራለን። በህይወት ያሉት የሚያስፈልጋቸውን ስርአቶች በሙሉ ለእነርሱ እንፈጽማለን፦ ጥምቀት፣ መንፈስ ቅዱስን መቀበል፣ ክህነትን መቀበል (ለወንዶች)፣ መንፈሳዊ ስጦታን መቀበል እና መታተም። ከዚያም እነርሱ እንዚህን ስርአቶች ለመቀበል ወይም ላለመቀበል መምረጥ ይችላሉ። በዚህ መንገድ የእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ የወንጌልን በረከቶች ሊካፈሉ ይችላሉ።

ቤተሰብ በቤተመቅደስ ፊት

በፊላደልፊያ ፐንሰልቨኒያ ቤተመቅደስ ፊት የቤተሰብ ፎቶ በኮዲ ቤል

የቤተመቅደስ ስራ በረከቶች

በቤተመቅደስ ውስጥ የምንገባቸውን ቃል ኪዳኖች የምንጠብቅ ከሆንን እንባረካለን፣ እንጠበቃለን፣ እና እንበረታለን። የክህነት ሃይል ከኛ ጋር እናገኛለን። ቤተሰቦቻችን ለዘለአለም አንድ ላይ ይሆናሉ።

በተጨማሪም ቤተመቅደስ የሰላም እና የመገለጥ ቦታ ነው። የቤተመቅደስ ስራ ስንሰራ፣ መንፈሳዊ ምሬት እናገኛለን እናም የእግዚአብሔር ፍቅር ይሰማናል።