2021 (እ.አ.አ)
የእርሱ ቤተክርስትያን ስም
ጥቅምት 2021 (እ.አ.አ)


“የቤተክርስትያኗ ስም፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ጥቅምት 2021 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ጥቅምት 2021(እ.አ.አ)

የእርሱ ቤተክርስትያን ስም

ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተክርስትያኑ ከሰጠው ስም ጀርባ ትርጉም አለ።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ መልካሙ እረኛ

የእኔ ቤተክርስትያን

ቤተክርስትያን—በአንድ አይነት ነገሮች የሚያምኑ እና በአንድነት የሚያመልኩ ሰዎች ስብስብ። ይህች ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ናት። እርሱ ጀምሯታል። እርሱ ይመራታል። የእርሱ ናት።

የተጠራችሁ ሁኑ

ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝብ የእርሱን ቤተክርስትያን ምን ብለው እንዲጠሯት እንደሚፈልግ ነግሮናል። ስለዚህ እንደዚያ ብለን ነው ይህችን መጥራት ያለብን—እናም ሌሎችም በትህትና እንዲህ እንዲጠሩ መጠየቅ አለብን። ይህ ስም የመጣው ከኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

የመጨረሻ ቀናት

የመጨረሻ ቀናት— አሁን የምንኖርበት ቀን፤ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት በፊት። ለዚህ የመጨረሻ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያኑን ወደ ምድር መልሶ አምጥቶታል። ይህም አለምን ለዳግም ምፅዓቱ እንዲዘጋጅ ይረዳል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን

(“ቤተክርስትያኔ”ን ተመልከቱ) ይህም አዳኙ ለቤተክርስትያኑ የሰጠው ስያሜ የመጀመሪያ ክፍል ነው። “ቤተክርስትያን” ብሎ ጠርጧታል ምክንያቱም እርሷን አደራጅቷታልና። በእርሷም ላይ ስሙን አኑሮታል።

ኋላኛው ቀን

(“ኋላኛው ቀናት”ን ተመልከቱ) ይህ የቤተክርስትያኗ ስም የሚቀጥለው ክፍል ነው። ይህ የሚያሳየው በቀደሙት ዘመናት የጀመረውን ሳይሆን በእነዚህ ቀናት ውስጥ በዳግም መልሶ ያስመለሳት ቤተክርስቲያን መሆኗን ነው።

ቅዱሳን

ቅዱሳን—ቃሉ “ቅዱሳን የሆኑ ህዝቦች” የሚል ትርጉም ያለው ነው። ይህ የቤተክርስትያኗ ስም የመጨረሻ ክፍል ነው። ይህም ስለ ቤተክርስትያኗ አባላት ይናገራል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያጠራን እና ሊያነጻን ይችላል። እናም ያዘዘንን ልንፈጽም ስንሞክር እንዲያበረታን መንፈስ ቅዱስን ይሰጠናል። በእርሱ ላይ እምነት ካለን እና መሞከራችንን ከቀጠልን፣ የተቀደስን ያደርገናል። ቅዱሳን ያደርገናል።

አትም