2021 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 1991(እ.አ.አ)፦ የዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ እና ዝምባቡዌ ቡራኬ
ጥቅምት 2021 (እ.አ.አ)


ወሩ በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ

ጥቅምት 1991(እ.አ.አ)፦ የዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ እና ዝምባቡዌ ቡራኬ

በጥቅምት 1991(እ.አ.አ) መጨረሻ ላይ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን አባል የነበሩት ሽማግሌ ጄምስ ኢ. ፋውስት (1920-2007) ዩጋንዳን፣ ኬንያን እና ዝምባቡዌን ለወንጌል ስብከት እና ለቤተክርስቲያኗ ምስረታ ቡራኬ አደረጉ።

በጥቅምት 23 ሽማግሌ ፋውስት የአፍሪካ አካባቢ ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለግሉ ከነበሩት የሰባዎቹ አባል ከሆኑት ከሽማግሌ ሪቻርድ ፒ.ሊንድሰይ ጋር በመሆን (1926–2010) ከዋና ከተማዋ ካምፓላ ለዩጋንዳ ቡራኬ አደረጉ።

በቡራኬው ጸሎት ውስጥ ሽማግሌ ፋውስት እንዲህ ብለው ጌታን ጠየቁ በዩጋንዳ ምድር ውስጥ “ሁሉም ልጆችህ እንደፈቃዳቸው ማምለክ ይችሉ ዘንድ ሰላማዊ ብዝሃዊነት ያለው ህብረተሰብ ይኑር።

በሚቀጥለው ቀን ጥቅምት 24፣ ሽማግሌ ፋውስት፣ ሽማግሌ ሊንድሰይ፣ እና የኬንያ ናይሮቢ ሚስዮን ፕሬዚዳንት ሌሪ ብራውን አንድ መቶ የቤተክርስቲያን አባሎች ለውጪ አገልግሎት ወደተሰበሰቡበት ወደ ኬንያ ናይሮቢ ተጓዙ።

በቡራኬው ጸሎት ውስጥ፣ ሽማግሌ ፋውስት እንዲህ አሉ፣ “ይህን እንደ ተባረከ ምድር አድርገን እንወስደዋለን።” ጸሎቱ ስለኬንያ ውበት፣ ታላቅነት እና የተትረፈረፉ የእፅዋት እና የእንስሳት ሕይወትን አካተተ።

ቅዱሳኑ ቤተመቅደስ እንዲኖራቸውም ጸለዩ።

በጥቅምት 25፣ ሽማግሌ ፋውስት እና ሽማግሌ ሊንድሰይ ዝምባቡዌን ለመባረክ ከዝምባቡዌ ሀራሬ ሚስዮን ፕሬዚዳንት ቨርን ማርብልን ጋር ተገናኙ።

“ከስብሰባው በፊት የዝምባቡዌ ቅዱሳን ዝናብ እንዲዘንብ ፆም ጸሎት ላይ ነበሩ” ብለው ሽማግሌ ሊንድሰይ ተናገሩ።

“የቡራኬው ጸሎት በሽማግሌ ፋውስት ሲጠናቀቅ ዝናብ መዝነብ ጀመረ፣ ከዚያ በኋላም ለቀናቶች እየጨመረ መዝነቡን ቀጠለ።”

አትም