የቃልኪዳኔ መንገድ
ውስን አጠቃቀም ያለው የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ
ውስን አጠቃቀም ያለው የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን መቀበል ለብዙ የቤተክርስቲያኗ አዳዲስ አባሎች እና ወጣቶች አስደሳች ጊዜ ነው። ከኤጲስ ቆጶሳችሁ ጋር በምታደርጉት ቃለ መጠይቅ ወቅት በጥምቀታችሁ ጊዜ ከተጠየቃችሁት ጋር የሚመሳሰል ጥያቄዎችን ይጠይቃችኋል። እነዚህ ጥያቄዎች ትዕዛዛትን ስለመጠበቃችሁ እና ስለወንጌል ያላችሁን ምስክርነት ያካትታሉ። የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያችሁን ስትቀበሉ ከቤተሰባችሁ እና ከአጥቢያ ጓደኞቻችሁ ጋር ወደ ቤተመቅደስ ለመጓዝ ማቀድ ትችላላችሁ።
በጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሚገኝ በኮስሞ ሲቲ ቅርንጫፍ ውስጥ ያለችው ሞሳ በቤተመቅደስ ለመካፈል ለሚጨነቅ ሰው ምን ብላ እንደምትናገር ስትጠየቅ እንዲህ ብላ መልሳለች፣ “ምንም የሚያስጨንቅነገር የለም። በዛ ቤት ውስጥ—በቤተመቅደስ ውስጥ ሰላም አለ። ሁሉም ፍርሃታችሁ እና ፈተናችሁ በቤተመቅደስ ውስጥ ቀሊል ይደረጋሉ። ቤተመቅደስ አስደናቂ፣ ሰላማዊ ቦታ ነው … በምድር ላይ የሚገኝ ደህንነት ያለው ቦታ ወይም ህንፃ ነው። ሁላችንም ተጋብዘናል። ሁኔታዎች ራሳችንን ከመሆን እንዲሁም ከሰማይ አባታችን ጋር ህብረት ከመፍጠር ሊያግዱን ይችሉ ይሆናል። ቤተመቅደስ መድሃኒት ነው፣ ብርሃናችን ከመደብዘዝ ስፍር ቁጥር ወደሌለው ብሩህነት የሚለወጥበት የነፍሳችን ሆስፒታል ነው። ‘እኔ ካንተ ጋር ነኝና አትፍራ’ (ኢሳያስ 41:10)።”
ውስን አጠቃቀም ያለው የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ በቤተመቅደስ በሚደረግ ጥምቀት ውስጥ እንድታገለግሉ እና በሞት ለተለዩ የቤተሰብ አባላችሁ እና በሞት ለተለዩ ሌሎች ሰዎች የጥምቀት እና የማረጋገጫ ስርዓቶችን እንድታደርጉ ይፈቅድላችኋል። ቤተመቅደሱ የጥምቀት አልባሳትን እና ፎጣ ያቀርባል። ከቤተክርስቲያን አለባበስ ወደ ነጭ አለባበስ ለመቀየር እያንዳንዱ ሰው የግሉ ሳጥን እና መቀየሪያ ክፍል ይኖረዋል።
ሞሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተመቅደስ ስትሄድ የነበራትን ስሜት እንዲህ ታስታውሳለች፤ “ወደ ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሄድ እና በቤተክርስቲያን ስርዓት ላይ መሳተፍ ስችል የነበረው ጊዜ መቼም አይረሳም። ለሞቱት ሰዎች መጠመቅ ስችል የነበረኝን ደስታ መግለፅ አልችልም። የቤተክርስቲያን አባል ለመሆን ወይም ለመጠመቅ እና እውነትን ለማወቅ እድል ያላገኙ ሰዎችን ለመርዳት መቻሌ ልቤን አሞቀው።… መንፈስ ቅዱስ ከእኔ ጋር ሆኖ ተሰማኝ።”
ወደ ጌታ ቤት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመግባት መዘጋጀት የምትችሉባቸው መንገዶች አሉ። ነብያችን ረስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፣ “ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተመቅደስ የሚሄዱት አባሎች በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ የተዘረዘሩትን ሰባት ርዕሶች አጭር የማብራሪያ አንቀፆች እንዲያነቡ ለመጋበዝ እወዳለው፤ ርዕሶቹም ‘መቀባት፣’ ‘የሃጢያት ክፍያ፣’ ‘ክርስቶስ፣’ ‘ቃል ኪዳን፣’ ‘የአዳም ውድቀት’፣ ‘መስዋዕቶች’ እና ‘ቤተመቅደስ’ ናቸው። ይህን ማድረግ ጠንካራ መሰረት ይሰጣል።”1
ወደ ጌታ ቤት ውስጥ ለመግባት ብቁ መሆን በሕይወታችሁ ውስጥ ትልቅ በረከት ነው። ውስን አጠቃቀም ያለው የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን 12 ዓመት በምትሆኑበት ዓመት መጀመሪያ ላይ መቀበል ትችላላችሁ። ወንዶች ቤተመቅደስ ከመግባታቸው በፊት አሮናዊ የክህት ስልጣንን መቀበል ይኖርባቸዋል። የቤተመቅደስ ቀጠሮ ለመያዝ ቀደም ብላችሁ ስልክ መደወል ሊኖርባችሁ ይችላል። ቤተሰባችሁ ወይም የቤተክርስቲያን መሪዎች የቤተመቅደስ ሰራተኞችን በስልክ ለመገናኘት እንዲረዷችሁ አድርጉ።
ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፣ “ቤተመቅደስ የጌታ ቤት በመሆኑ ምክንያት የመግቢያ መስፈርቶቹ በእርሱ ነው የተዘጋጁት። አንድ ሰው እንደ የጌታ እንግዳ ነው የሚገባው። የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን መያዝ በዋጋ የማይታመን እድል እንዲሁም ለእግዚአብሔር እና ለነብያቱ ያለ ታዛዥነት ተጨባጭ ምልክት ነው።”
ለአምልኮ እና ለማገልገል ወደ ቤተመቅደስ ስትመጡ ሕይወታችሁ በሰላም ይሞላል።