ሊያሆና
ሊያሆና
የካቲት 2024 (እ.አ.አ)


“ሊያሆናው፣” ጓደኛ፣ የካቲት 2024 (እ.አ.አ)፣ 26–27።

ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ የካቲት 2024 (እ.አ.አ)

ሊያሆናው

alt text

ስዕል በአንድሪው ቦዝሊ

ጌታ ሌሂ ከቤተሰቡ ጋር ወደ ቃል ኪዳን ምድር እንዲሄድ ነገረው። ነገር ግን እዚያ እንዴት እንደሚደርሱ እርግጠኛ አልነበሩም።

alt text

ጌታ ለሌሂ ልዩ መሳሪያ ሰጠ። እንደ ኮምፓስ ነበር። መሄድ ወዳለባቸው መንገድ ይጠቁም ነበር። ሊያሆና ብለው ሰየሙት።

alt text

ትእዛዛቱን ሲጠብቁ፣ ሊያሆናው ይሰራል። ወደ ምግብ እና ደህንነት መራቸው። ሲጨቃጨቁና ሳይታዘዙ ሲቀሩ ግን መስራት አቆመ።

alt text

የሌሂ ቤተሰብ ወደ ቃል ኪዳን ምድር መድረስ እንዲችሉ ሊያሆናውን ተከተሉ። ትክክለኛውን ስንመርጥ የሰማይ አባት እኛንም ይመራናል።

የሚቀባ ገፅ

እኔ እንደ ኢየሱስ መጠመቅ እችላለሁ

Alt text

ሥዕል በአደም ኮፎርድ

ለመጠመቅ እንዴት መዘጋጀት ትችላላችሁ?