ሊያሆና
በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ የመሆን ዓርአያ
ጥቅምት 2024 (እ.አ.አ)


“በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ የመሆን ዓርአያ፣ “ ሊያሆና፣ጥቅምት 2024 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ ሊያሆና መልዕክት፣ ጥቅምት 2024 (እ.አ.አ)

በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ የመሆን ዓርአያ፣

በ 4ኛ ኔፊ ውስጥ እንዳሉት ህዝቦች በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ስንሆን፣ የአንድነት ፍላጎታችን ልዩነቶቻችንን በመተካት ወደ ደስታ ይመራናል።

የክሪስተስ ሃውልት

የምንኖረው አለመግባባቶች እና የክርክር ማዕበሎች በዓለም ዙሪያ ሁሉ እየተዛመቱ ባሉበት ጊዜ ነው። በቴክኖሎጂ እና ልባቸው እየቀዘቀዘ በሄደ ሰዎች በመታገዝ፥ እነዚህ የመከፋፈል ኃይሎች ልባችንን በንቀት ለመሙላት እና ግንኙነቶቻችንን ሁሉ በክርክር ለማበላሸት ይዝቱብናል ። የህብረት ትስስሮች እየተበጠሡ ነው። ጦርነቶች በኅይል እየተካሄዱ ነው።

በዚህ አውድ ውስጥ፥ እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ሰላምን ይሻሉ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ላይ የተመሠረተ ሌላ አይነት ማህበረሰብ— ለመገንባት በንቃት ይሰራሉ። ይህንን ግብ እናሣካ ዘንድ፥ ጌታ ፥ “እንዲህ እላችኋለሁ፣ አንድ ሁኑ፤ እናም አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም።”ትምህርት እና ቃልኪዳኖች ፣ 38;27በማለት አዞናል። በእርግጥም፥ አንድነት እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ገላጭ ባህርይ ነው።

የመከፋፈል እና የክርክር ሀይልን በመቃወም መስራት የምንችለው እንዴት ነው? አንድነትን ማሳካት የምንችለው እንዴት ነው ?

ደግነቱ፥ በመጽሐፍ ሞርሞን ውስጥ የሚገኘው 4ኛ ኔፊ ምሳሌ ይሰጠናል። ይህ ምዕራፍ አዳኙ ህዝቡን ከጎነኛቸው፣ ካስተማራቸው እና ቤተክርስቲያኑን በመሀከላቸው ከመሰረተ በኋላ እንዴት ሲኖሩ እንደነበረ በግልጽ መዝግቦ ይዟል። ይህ ታሪክ እነዚህ ህዝቦች እንዴት ደስተኛ እና ሰላማዊ የሆነ አንድነትን ማሳካት እንደቻሉ ያሳያል፣ እንዲሁም በዚያ መሰረት እኛም ተመሳሳይ አንድነትን እንድናገኝ መከተል ያለብንን ዓርዓያ ይሰጠናል።

መለወጥ

4ኛ ኔፊ 1:1፥ የሚከተለውን እናነባለን : “ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በምድሪቱ ዙሪያ በሁሉም ስፍራ የኢየሱስን ቤተ ክርስቲያን መሰረቱ።” እናም [ህዝብ] ወደ እነርሱ መጡ እናም በእውነትም ለሀጢያታቸው ንሰሀን ገቡ።”

በጌታችን እና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዙሪያ አንድ እንሆናለን። ሁሉም ሰው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ወንጌሉ እና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ በሚማርበት ጊዜ፥ መንፈስ ቅዱስ በእያንዳዱ ሰው ልብ ውስጥ በጥልቅ እና በቅንነት እውነትን ይመሰክራል። ከዚያም በእርሱ እምነት እንዲኖረን እና ንስሀ ገብተን እንድንከተለው እያንዳንዳችን የአዳኙን ጥሪ እንቀበላለን።

ስለዚህ ከራስ ወዳድነት እና ከኃጢአተኝነት ምኞቶች በመራቅ እና ወደ አዳኙ በመቅረብ —የአንድ ግለሰብ የመለወጥ ጉዞ ይጀምራል ። እርሱ የእምነታችን መሰረት ነው። እናም ሁላችንም በሙሉ ሀሳባችን ወደ እርሱ ስናተኲር (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 6:36ይመልከቱ)። እርሱ በህይወታችን ውስጥ አንድ የሚያደርገን ህይል እና ተፅእኖ ይሆናል።

ቃል ኪዳኖች

በ4ኛ ኔፊ ውስጥ ያለው መዝገብ እነዚያ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የመጡት እና ለሀጢያታቸው ንሰሃን የገቡ “ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፣ እናም ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ” (4ኛ ኔፊ 1:1በማለት ይቀጥላል። ከእግዚአብሄር ጋር— ልዩና የሚያስተሳስር ጽኑ ዝምድና—ያለውን ቃል ኪዳን ገብተዋል ።

ቃልኪዳን ስንገባ እና ስንጠብቅ፣ እንደ አንድ ግለሰብ የጌታችንን ስም በራሳችን ላይ እንወስዳለን። በተጨማሪም፥ እንደ ህዝብ ስሙን በራሳችን ላይ እንወስዳለን። ቃልኪዳን የገቡ እና ለመጠበቅ የሚጥሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ህዝቦች ተባሉ፥ ለእርሱም የተመረጡ ርስቱ ሆኑ ( ዘፀአት 19:5ይመልከቱ)። እነሆ፥ የቃል ኪዳኑን መንገድ በግለሠብ ደረጃም ሆነ በጋራ እንጓዝበታለን። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የቃል ኪዳን ግንኙነት የጋራ የሆነ ምክንያት እና የጋራ የሆነ ማንነት ይሰጠናል ። እራሳችንን ከእግዚአብሔር ጋር በምናንስተሳስርበት ጊዜ፥ “ልባችን በአንድ ላይ በአንድነት አንዱ ሌላኛውን ባላው ፍቅር እንዲጣበቅ ያግዘናል” (ሞዛያ 18:21)።

ፍትሃዊነት፣ እኩልነት እና ድሆችን መርዳት

በ4ኛ ኔፊ ውስጥ ያለው ዘገባ እንዲህ በማለት ይቀጥላል፡“ በመካከላቸው ክርክርና አለመግባባት አልነበረም፣ እናም እያንዳንዱ ሰው እርስ በርሱ ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ተግባራቸውን ያደርጉ ነበር።

“እናም ሁሉም ነገሮች በጋራ ነበሩአቸው፣ ስለዚህ ድሃና ሃብታም፣ ግዞተኛና ነፃ አልነበረም፣ ነገር ግን ሁሉም ነፃና፣ ሰማያዊውን ስጦታ ተቀባይ ነበሩ” (4ኛ ኔፊ 1:2-3)።

በምድራዊ ህይወታችን በምናደርጋቸው ግንኙነቶቻችን፣ ጌታ እርስ በእርሳችን ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ እንድንሆን ይፈልጋል እንጂ አንዳችን ሌላውን እንዳናታልል እና ሌሎችን ለግል ጥቅማችን እንድንጠቀምባቸው አይፈልግም። (1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4;6ይመልከቱ)። ወደ እግዚአብሔር በማደግ በምንቀርብበት ጊዜ፥ “ እናም በሰላም ለመኖርና፣ ለእያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ለመስጠት እንጂ፣ እርስ በርሳችሁ የመጎዳዳት ሃሳብ አይኖርባችሁም(ሞዛያ 4:13)።

ደግሞም ጌታ ድሆችን እና የተቸገሩትን እንድንንከባከብ አዞናል። እናም ደግሞ አቅማችን በሚፈቅደው መልኩ ምንም ሳንፈርድባቸው ያለንን [የእራሳችንን] ሀብት ልናካፍላቸው ይገባናል (ይመልከቱ ሞዛያ 4:21-27

እያንዳንዳችን “ወንድማችንን እንደራሳችን [እንመልከት]”(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38;24)። እኛ የእግዚአብሔር ህዝቦች ለመሆን እና አንድ ለመሆን ፣ እርስ በርሳችን እኩል መሆን ብቻ ሳይሆን ፣ ነገር ግን እርስ በርሳችን በእውነት እኩል እንደሆንን እና በልባችንም እኩል መሆናችንን— በእግዚአብሔር ፊትም ዋጋችን እና አቅማችን እኩል እንደሆነ በልባችን ሊሰማን ይገባል ።

ታዛዥነት

ቀጣዩ ትምህርት ከ4ኛ ኔፊ የመጣው ቀለል ባለ አገላለጽ ሲሆን፡ “ከጌታቸውና ከአምላካቸው በተቀበሉአቸው ትዕዛዛት [መሰረት]፣ ይራመዱ ነበር። (4ኛ ኔፊ 1:12)

እግዚአብሔር እነዚህን ሰዎች ትምህርቱን አስተምሮአቸው ፣ ትእዛዛትን ሰጥቷቸው እንዲሁም እንዲያገለግሏቸው አገልጋዮችን ጠርቶ ነበር። ይህን ካደረገበት ዓላማዎች አንዱ በመካከላቸው ምንም ዓይነት ልዩነት እንዳይኖር ለማድረግ ነበር ( 3ኛ ኔፊ 11:28-29; 18:34)ይመልከቱ።

ለጌታ እና ለእርሱ አገልጋዮች ትምህርቶች መታዘዛችን አንድ ለመሆናችን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህም፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ከመጠበቅ በምንዘናጋበት እና በምንሳሳትበትም ጊዜ ሁሉ ንስሐ እንድንገባ የተሰጠንን ትእዛዝ ለመፈጸም ያለንን ቁርጠኝነት ማሳየት እና ዕለት ተዕለት የተሻልን ለመሆን በምንጥርብት ጊዜ ሁሉ እርስ በእርስ መረዳዳትን ያካትታል።

በስብሰባ ላይ ሰዎች ቅዱሳት መጽሐፍትን ሲመለከቱ

በህብረት መሰብሰብ

ቀጥሎም፥ በ4ኛ ኔፊ ውስጥ ህዝቡ “[ያለማቋረጥ] በፆማቸውና፣ በፀሎታቸው፣ እንዲሁም በየወቅቱ ለመፀለይና የጌታን ቃል ለመስማት በመሰብሰብ ይራመዱ እንደነበር እንማራለን።(4ኛ ኔፊ 1:12).

በህብረት መሰብሰብ ያስፈልገናል። በየሳምንቱ የምናደርጋቸው የአምልኮ ስብሰባዎች በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ ጥንካሬን የምናገኝባቸው ጠቃሚ አጋጣሚዎች ናቸው። ቅዱስ ቁርባንን እንካፈላለን፣ እንማራለን፣ እንጸልያለን፣ አብረን እንዘምራለን፣ እናም እርስ በርሳችን እንረዳዳለን። በተጨማሪም ሌሎች ስብሰባዎች የተፈላጊነትን ስሜት፣ ወዳጅነትና የጋራ የሆኑ ዓላማዎች እንዲጠናከሩ በማድረግ ያግዛሉ።

ፍቅር

በ 4ኛ ኔፊ ውስጥ ያለው ታሪክ ምናልባት ለዚህ ሁሉ ዋና ቁልፍ የሆነውን ነገር ይሰጠናል—ያለዚህም ነገር እውነተኛ አንድነት ሊገኝ አይችልም፡- ”እናም እንዲህ ሆነ በህዝቡ ልብ ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር ፍቅር የተነሳ በምድሪቱ ፀብ አልነበረም (4ኛ ኔፊ 1:15)።

የግል ውስጣዊ ሰላምን የምናገኘው ፥ ትሁት በመሆን፣ አምላክን ከልብ ስንወድ ነው። “ይህች ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትዕዛዝ ናት። ከማንም ወይም ከምንም ነገር በላይ እግዚአብሔርን መውደድ እውነተኛ ሰላም፣ መጽናኛ፣ መተማመንና ደስታ ሊያስገኝ የሚችል ቅድመ ሁኔታ ነው። ለእግዚአብሔር እና ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን ፍቅር እያዳበርን ስንሄድ ለቤተሰብና ለጎረቤታችን ያለንን ፍቅር ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ይከተላል።

ከምንጊዜውም በላይ ታላቁን የደስታ ስሜት ልንጋራ የምንችለው ለእግዚአብሔር እና ለልጆቹ ሁሉ ባለው ፍቅሩ ስንሞላ ነው።

ንፁህ የክርስቶስ ፍቅር የሆነው ልግስና ፣ ለክርክር ፍቱን መድኃኒት ነው። ያም የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታይ ዋነኛ ባህሪ ነው። ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት ስናዋርድ እና በሙሉ ልባችን ስንጸልይ እርሱ ልግስና ይሰጠናል (ይመልከቱ ሞሮኒ 7:48)።

ሁላችንም በልባችን ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲኖር እና እንዲሰማን በምንፈልግበት ጊዜ፣ የአንድነት ተዓምራት ፍጹም ተፈጥሯዊ ሆነው ይታዩናል።

መለኮታዊ መርሆዎች

በመጨረሻም፣ በ 4ኛ ኔፊ ያሉ ህዝቦች ትኩረት ሊንሰጠው የሚገባንን የአንድነት ተምሳሌት አሳይተዋል፡- “ሌቦችም ሆኑ ገዳዮች፣ ላማናውያንም ሆኑ ማንኛውም ዓይነት በመደብ የተለዩ ሰዎች አልነበሩም፤ ነገር ግን ሁሉም በአንድነት የክርስቶስ ልጆች፣ እናም የእግዚአብሔርንም መንግስት ወራሾች ነበሩ” (4ኛ ኔፊ 1:17)።

ሕዝቡን ለብዙ መቶ ዓመታት ሲከፋፍሉት የቆዩት የከፋይነት መደቦች ጸንተውና የማንነት ነፀብራቅን ሳይዙ በመቅረት ጠፍተዋል። ራሳቸውንም ሆነ —ሌሎችን ሁሉ —ይመለከቱ የነበረው ከሰማይ አባትና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባላቸው ግንኙነት መልክ ነበር ።

የሐሳብ እና የማንነት ልዩነቶቻችን ለእኛ መልካም እና ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ከሁሉ የላቀው ማንነታችን ከመለኮታዊ አመጣጥና ዓላማ ጋር የሚዛመድ ነው።

ከሁሉ በላይ ደግሞ እያንዳንዳችን የእግዚአብሔር ልጅ ነን። ሁለተኛ፣ እንደ ቤተክርስቲያኗ አባል፣ እያንዳንዳችን የቃል ኪዳን ልጅ ነን። ሦስተኛ ፥ እያንዳንዳችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ነን። ሌላ ማንኛውንም አይነት ነገር የተዘረዘሩትን ከእነዚህ ሶስት ቋሚ ስያሜዎች ማለትም “የሚያፈናቅል ፣ የሚተካ ወይም ቅድሚያውን ሊወስድ የሚገባ ምንም አይነት ከፋፋዮችን እንዲገቡ መፈቀድ እንደሌለብን ሁላችንንም ላሳስብ እፈልጋለሁ።”

ቤተሰብ አንድላይ ወለል ላይ ተቀምጠው

አንድ ሁኑ

ኢየሱስ ክርስቶስ ሁላችንም ወደ እርሱ እንድንቀርብ ይጋብዘናል። ለሁሉም ሰው የሚሆን ቦታ አለ። በባህላችን፣ በፖለቲካችን፣ በጎሳችን፣ በልምዶቻችን እና በሌሎች በርካታ ምርጫዎቻችን እንለያያለን። ይሁን እንጂ በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ በምንሆንበት ጊዜ እንዲህ ዓይነቶቹ ልዩነቶች ያን ያህል የጎላ ትርጉም አይሰጡም— የእርሱ ለመሆን ከመፈለጋችን የተንሳ ውስጣችን ባለው አንድ የመሆነ ጽኑ ፍላጎት እየጠፉ ይሄዳሉ።

በ 4ኛ ኔፊ ያለውን ትምህርት በቁም ነገር አስቡት እናም ተግብሩት። እያንዳንዳችን እነዚህን የአንድነት ወሳኝ ክፍሎች በህይወታችን ውስጥ ለማካተት ስንጥር፣ ስለ እነርሱ እደተባለው ስለ እኛም ሰዎች እንዲህ በማለት ይገልጻሉ “በእርግጥ በእግዚአብሔር እጅ ከተፈጠሩት ሰዎች መካከል እንደዚህ ያለ ደስተኛ ሊሆን የቻለ ህዝብ አልነበረም” (4 ኔፊ 1:16)።

ማስታወሻዎች

  1. ረስልኤም ኔልሰን፣ “As We Go Forward Together [ወደፊት አብረን ስጓዝ]፣” ሊያሆና፣ ሚያዝያ፣ 2018 (እ.አ.አ)፣ 7፤ ራስል ኤም ኔልሰን “The Everlasting Covenant [ዘለአለማዊው ቃል ኪዳን]]፣” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) 4፣ 11።

  2. Russell M. Nelson, “Choices for Eternity [የዘለአለማ ምርጫዎች]” (worldwide devotional for young adults, May 15, 2022), Gospel Library.