2024
ኢየሱስ አንድ በአንድ ባረከ
ጥቅምት 2024 (እ.አ.አ)


“ኢየሱስ አንድ በአንድ ባረከ፣” ጓደኛ ጥቅምት 2024 (እ.አ.አ) 26–27.

ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ጥቅምት 2024 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ አንድ በአንድ ባረከ

ነብያት ኔፋውያንን ሲያስተምሩ

በአንድሩ ቦዝሊ የተሳለ

ነቢያት ለኔፋውያን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ምልክቶች አስተማሩ። በሞተ ጊዜ በምድር ላይ ሦስት ቀን ጨለማ ሆኖ ነበር። በኋላ፣ ሰዎቹ የሰማይ አባትን ድምጽ ከሰማይ ሆኖ ሲናገር ሰሙ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ኔፋውያንን እየጎበኘ

የሰማይ አባት፣ “እነሆ የምወደው ልጄ” አለ(3ኛ ኔፊ 11:7)። ኢየሱስም ለኔፋውያን ታየ እርሱ ከሞት ተነሥቷል! ለኔፋውያን ብዙ ነገሮችን አስተማራቸው። ንስሐ እንዲገቡና እንዲከተሉት ነገራቸው።

ኢየሱስ ኔፋውያንን ሲፈውስ

የታመሙት እንዲፈወሱ ሕዝቡን ወደ እርሱ እንዲያመጡዋቸው ጠየቃቸው። እርሱ ባረካቸው።

ኢየሱስ ህጻናትን ሲባርክ

እርሱም ልጆቻቸውን አንድ በአንድ ባረካቸው። መላእክት ህጻናትን ከበው.

የሚቀለም ገፅ

አዳኙ እያንዳንዱን የሰማይ አባት ልጆችን ይወዳል።

የሚቀለም ገፅ

በአደም ኮፎርድ የተሳለ

የሰማይ አባት ፍቅር እንዴት ይሰማችኋል?