2024
ሁላችንም የተለያየን ከሆንን አንድ ልሆን የምንችለው እንዴት ነው?
ጥቅምት 2024 (እ.አ.አ)


“ሁላችንም የተለያየን ከሆንን አንድ ልሆን የምንችለው እንዴት ነው ?፥” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ጥቅምት 2024 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ጥቅምት 2021(እ.አ.አ)

ሁላችንም የተለያየን ከሆንን አንድ ልሆን የምንችለው እንዴት ነው?

የቀስት ምልክት ያለበት አራት ማዕዘን ኩብ

ሁላችንም እንለያያለን። ጌታ ግን “አንድ እንድንሆን” ይፈልጋል።(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38;27)። ነቢያትና ሐዋርያት ያስተማሩን ጥቂቶቹ የአንድነት መሰረታዊ መርሆዎች እነሆ፥

በኢየሱስ ክርስቶስ ፣ በወንጌሉ ፣ እና በቤተክርስቲያኑ አንድ ነን። “አንድ ለመሆን ተስፋ ማድረግ የምንችለው ለኢየሱስ ክርስቶስ ባለን የግል ታማኝነትና ፍቅር ብቻ ነው ።”

አንድነት መዋደድን ይጠይቃል። “የተለያየ ቋንቋና ማራኪ ባሕል ቢኖረንም እንኳ ልባችን በአንድነትና በፍቅር ሊጣበቅ ይገባል።”

አንድነት ማለት በሁሉ መመሳሰል ማለት አይደለም። “አንድነት እና ልዩነት ተቃራኒዎች አይደሉም። የአብሮነትን ስሜት እና የብዝሃነት መከባበርን ስናጎለብት የላቀ አንድነት ማምጣት እንችላለን። “አንድነት መመሳሰልን አይጠይቅም፣ ግን መስማማትን ይጠይቃል።”

አንድነት ጭፍን ጥላቻን እና መጥሌን ማስወገድን ይጠይቃል። “ለሁሉም ሰው የሚሆን ቦታ አለ። ሆኖም፣ ለማንኛውም ዓይነት ጭፍን ጥላቻ፣ ውግዘት ወይም ክርክር ቦታ የለም ።”