ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 8–14፦“እነርሱ ‘መንገዳቸውን አልሳቱም ነበር።’” አልማ 23–29


ሐምሌ 8–14፦“እነርሱ ‘መንገዳቸውን አልሳቱም ነበር።’” አልማ 23-29፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

“ሐምሌ 8–14። አልማ 23-29፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

ምስል
አንቲ ኔፊ ሌሂዎች ጎራዴያቸውን እየቀበሩ

አንቲ ኔፊ ሌሂዎች የጦር ጎራዴዎቻቸውን ሲቀብሩ፣ በጆዲ ሊቪንግስተን

ሐምሌ 8–14፦“እነርሱ ‘መንገዳቸውን አልሳቱም ነበር።’”

አልማ 23–29

አንዳንድ ጊዜ እውን ሰዎች መለወጥ ይችላሉ በማለት ትጠይቃላችሁ? ምናልባት ያደረጋችኋቸውን መጥፎ ምርጫዎች ወይም የተለማመዳችኋቸውን መጥፎ ልማዶች ማሸነፍ ትችሉ እንደሆነ ልታስቡ ወይም ስለምትወዷቸው ሰዎች ተመሳሳይ ጭንቀት ሊኖርባችሁ ይችላል። እንደዚያ ከሆነ የአንቲ ኔፊ ሌሂዎች ታሪክ ሊረዳችሁ ይችላል። እነዚህ ሰዎች የኔፋውያን ደመኛ ጠላቶች ነበሩ። የሞዛያ ልጆች ወንጌልን ለእነርሱ ለመስበክ በወሰኑ ጊዜ ኔፋውያን “በማሾፍ ሳቁባ[ቸው።]” ላማናውያንን መግደል እነሱን ከመቀየር የበለጠ አሳማኝ መፍትሄ ይመስል ነበር። ( አልማ 26፥23–25 ይመልከቱ።)

በኢየሱስ ክርስቶስ የመለወጥ ሃይል—ላማናውያን ተለወጡ። አንዴ “ልበ ጠጣሮችና አስፈሪ ሰዎች” በመሆን የታወቁ ነበር (አልማ 17፥14) ነገር ግን “ለእግዚአብሄር ባላቸው ቅናዓት [የተ]ለዩ ነበሩ” (አልማ 27፥27)። በርግጥ እነርሱ “መንገዳቸውን አልሳቱም ነበር” (አልማ 23፥6)።

ምናልባት የምትለውጧቸው አንዳንድ ሃሳቦች ወይም ድርጊቶች ወይም ማስቀመጥ የሚኖርባችሁ “የ… የአመፅ መሳሪያዎች” ሊኖሯችሁ ይችላሉ (አልማ 23፥7)። ወይም ደግሞ ለእግዚአብሄር ትንሽ የበለጠ ቅንዓት ሊኖራችሁ ይገባ ይሆናል። ምንም አይነት ለውጦች የሚያስፈልጓችሁ ቢሆን አልማ 23–29 በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ሃይል ዘላቂ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል ተስፋ ሊሰጣችሁ ይችላል።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

አልማ 23–2527

ምስል
seminary icon
ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወደወንጌሉ መለወጤ ህይወቴን ይቀይራል።

ላማናውያን ለመለወጥ ሊታጩ የማይችሉ ይመስሉ ነበር፤ ነገር ግን ብዙዎቹ በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ተዓምራዊ ለውጦችን አድርገዋል። እነዚህ የተለወጡ ላማናውያን ራሳቸውን አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ብለው ይጠሩ ነበር።

አልማ 23–2527 ማንበብ የራሳችሁን ለውጥ እንድታሰላስሉ ሊገፋፋችሁ ይችላል። አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች እንዴት እንደተለወጡ ፈልጉ—እንዴት “ወደ ጌታ” እንደተለወጡ (አልማ 23፥6)። ለማስጀመሪያ ያህል የሚሆኑ ጥቂት ጥቅሶች ቀጥሎ ቀርበዋል፦

ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌሉ ሊለውጧችሁ ይችላሉ። ወደ እርሱ እንደቀረባችሁ የተሰማችሁ መቼ ነው? ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየተለወጣችሁ መምጣታችሁን እንዴት ለማወቅ ትችላላችሁ? መንፈስ ምን እንድታደርጉ እየገፋፋችሁ ነው?

በተጭማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “Converted unto the Lord,ሊያሆና፣ ሕዳር 2012 (እ.አ.አ)፣ 106–9፤ ዴል ጂ. ረንለንድ፣ “Unwavering Commitment to Jesus Christ፣” ሊያሆና፣ ሕዳር 2019፣ 22–25፤ የወንጌል አርዕስቶች፦ “Become like Jesus Christ፣” ወንጌል ላይብረሪ።

አልማ 24፧7–1926፧17–22

እግዚአብሄር ይቅር ባይ ስለሆነ ንስሐ ስገባ ይቅር ይለኛል።

አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ያደረጉት ለውጥ የባህሪ ለውጥ ብቻ አይደለም—በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እና ከልብ ከመነጭ ንስሐ የተፈጠረ የልብ ለውጥ ነበር። ምናልባት በአልማ 24፧7–19 በእያንዳንዱ ጥቅስ ውስጥ ስለ ንስሐ አንድ እውነትን ልታገኙ ትችሉ ይሆናል። እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔር ንስሐ ለሚገቡ ሰዎች ስለሚያደርገው ምሕረት ምን ያስተምራሉ? ከአልማ 26፥17–22ምን ተጨማሪ እውነቶች ታገኛላችሁ?

እግዚአብሄር በሕይወታችሁ ውስጥ ምህረቱን እንዴት እንዳሳየ አሰላስሉ። ለእርሱ ያላችሁን ምስጋና እንዴት መግለፅ ትችላላችሁ?

አልማ 2629

ወንጌልን ማካፈል ደስታን ያመጣልኛል።

ደስታ የሚለው ቃል በአልማ 23–29 24 ጊዜ ተጠቅሷል፤ ይህም እነዚህን ምዕራፎች —የአዳኙን ወንጌል በመኖር —እና በማካፈል ደስታን እንዴት መቀበል እንደሚቻል ለመማር ጥሩ ቦታ ያደርጋችዋል። አሞን፣ የሞዛያ ልጆች እና አልማ የተደሰቱበትን ምክንያት በመፈለግ አልማ 26፡12–22፣ 35–37 ፤ እና 29:1–17 ማጥናትን አስቡ። ከእነዚህ ምንባቦች በሕይወታችሁ የበለጠ ደስታን ሊያመጡ ስለሚችሉ ነገሮች ምን ትማራላችሁ?

ሽማግሌ ማርከስ ቢ. ናሽ እንዲህ አስተምረዋል “ወንጌልን ማካፈል በሰጪውም ሆነ በተቀባዩ ነፍስ ውስጥ ደስታን እና ተስፋን ያጭራል። … ወንጌልን ማካፈል በደስታ ላይ ደስታ፣ በተስፋ ላይ ተስፋ ነው (“Hold Up Your Light፣” ሊያሆና፣ ሕዳር 2021(እ.አ.አ)፣ 71)። ወንጌልን ለሌሎች በማካፈል ረገድ ምን ተሞክሮዎች አሏችሁ? ወንጌልን ለማካፈል በምትፈልጉ ጊዜ ምን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ያጋጥሟችኋል? የሰማይ አባት እነዚህን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ለመቋቋም እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?

ወንጌልን እንዴት እንደምናካፍል—እና እሱን በማድረግ ደስታን እንዴት እንደምናገኝ ትንቢታዊ መመሪያ ለማግኘት—የፕሬዚዳንት ዳልን ኤች. ኦክስ መልዕክትን “Sharing the Restored Gospel፣” (ሊያሆና, ሕዳር 2016 (እ.አ.አ)፣57–60) ማጥናትን አስቡ። በእርሱ መልዕክት ምን ጥቆማዎችን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም “The Bush Family Story፣” “Sharing Your Beliefs፣” “Sharing the Gospel” (ቪዲዮዎች)፣ ወንጌል ላይብረሪ።

ለአንድ ጓደኛ ሰለ መፅሐፈ ሞርሞን የምታካፍሉትን ነገሮች ዝርዝር መፃፍን አስቡ። የመፅሐፈ ሞርሞን መተግበሪያን በመጠቀም መፅሐፈ ሞርሞንን ለማካፈል ሞክሩ

የተለመዱ መንገዶችን እና ጭብጦችን ፈልጉ። ቅዱሳት መጻሕፍትን በምናጠናበት ጊዜ የተደጋጋሙ ቃላትን፣ ሐረጎችን ወይንም ሐሳቦችን በመፈለግ ውድ እውነቶችን ማግኘት እንችላለን። እነዚያን የተደጋገሙ ሐሳቦች ለማየት ቀላል ለማድረግ በቅዱሳት መጻህፍቶቻችሁ ውስጥ ማጣቀሻ ወይም የገጽ ማገናኛ ሊሠራላቸው ይችላል።

አልማ 26፥5–7

በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ መጠለያን ማግኘት እችላለሁ።

በመኸር ወቅት እህል ብዙውን ጊዜ ነዶ በሚባሉ ጥቅልሎች ውስጥ ይሰበሰብና በማከማቻ ውስጥ ይቀመጣል፣ ይህ አንዳንዴም ጎተራ ይባላል። በአልማ 26:5–7 ውስጥ ነዶዎች፣ ጎተራዎች እና ማዕበሎች በህይወታችሁ ምን ሊወክሉ እንደሚችሉ አስቡ። በኢየሱስ ክርስቶስ መጠለያ የምታገኙት እንዴት ነው?

በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “The Temple and Your Spiritual Foundation,” ሊያሆና፣ ሕዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 93–96፤ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “Honorably Hold a Name and a Standing፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2009፣ 97–100፤ “Jesus, Lover of My Soul፣” መዝሙር፣ ቁ. 102 ይመልከቱ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ሳምንት የሊያሆና ዕትም እና የ ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄትን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

አልማ 24፥6–24

ከእርሱ ጋር የገባኋቸውን ቃልኪዳኖች ለመጠበቅ ስጥር ጌታ ይባርከኛል።

  • ምናልባት ልጆቻችሁ እንደ አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች “መሳሪያዎቻቸውን” በመቅበር ሊደሰቱ ይችሉ ይሆናል። አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች አዳኙን ለመከተል ሰለገቡትን ቃል ኪዳን ልጆቹን ለማስተማር የተወሰኑ ቁጥሮችን በ አልማ 24፥6–24 ውስጥ ለማንበብ ትችላላችሁ። ከዚያም እርሱን ለመከተል ሊቀይሩት የሚችሉትን አንድ ነገር ማሰብ፣ በዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ላይ መጻፍና ጉድጓድ ቆፍረው መሳሪያቸውን እንደሚቀብሩ ማስመሰል ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁ አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች “እንደእግዚአብሄር ምስክር” ምን እነዳደረጉ በመፈለግ አልማ 24፥15–19 ሊያነቡ ይችላሉ። ከዚያም ቃል ኪዳኖቻችን እንዴት “ለእግዚአብሔር ምስክር” ሊሆኑ እንደሚችሉ ከእነሱ ጋር ልትነጋገሩ ትችላላችሁ (ቁጥር 18)። ልጆቻችሁ እርሱን መከተል ስለሚፈልጉበት መንገድ እንዴት ለእግዚአብሔር እንደሚያሳዩት እንዲናገሩ አድርጉ። እንደ “I Want to Live the Gospel፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣148 ሊያሉ መዝሙሮችን መዘመር እንዲነሳሱ ሊረዳቸው ይችላል።

አልማ 24፥7–1028፥23–3427፥27–30

ንስሐ መግባት እችላለሁ።

  • ንስሐ በምንገባበት ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንድንለወጥ ሊረዳን እንደሚችል ልጆቻችሁ እንዲያዩ ለመርዳት ስለአንቲ-ኔፊ-አንቲ-ሌሂዎች ልታስተምሯቸው ትችላላችሁ። ይህንን ለማድረግ ሁለት ጎድጓዳ ሳህኖች ላይ “በፊት” እና “በኋላ” ብላችሁ ልትለጥፉባቸው ትችላላችሁ። ከዚያም ልጆቻችሁ አልማ 17፥14–15 እና 27፥27–30 ሊያነቡ እና ከንስሐ በፊት እና በኋላ ላማናውያን ምን እንደሚመስሉ ሊጽፉ እና በትክክለኛው ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ጨምሩ። በአልማ 24፥7–10መሠረት እንዲቀየሩ የረዳቸው ምንድን ነው? ስለምህረቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናችንን የምናቀርበው አንዴት ነው?

አልማ 2629

ኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋ ይሰጠኛል እናም ይህንን ደስታ ማካፈል እችላለሁ።

  • ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ ስላሉ ደስታን የሚሠጡ ነገሮች ሥዕሎችን በመሳል ልትደሰቱ ትችላላችሁ። ሥዕላችሁን ለልጆቻችሁ አሳዩ እነርሱም አንድ ሰው እንዲደሰት ለመርዳት ሥዕላቸውን ለዚያ ሰው እንዲያሳዩ አበረታቷቸው።

  • ልጆቻችሁ ደስታ እና መደሰት የሚሉትን ቃላት በበአልማ 26 እና 29 ውስጥ እንዲፈልጉ እርዷቸው። ለአሞን እና ለአልማ ደስታን የፈጠረላቸው ወይም እንዲደሰቱ ምክንያት የሆናቸው ምንድን ነው? ይህ ጥያቄ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመኖር ወይም በማካፈል ስለሚመጣው ደስታ ወደመወያየት ሊያመራ ይችላል።

አልማ 27፥20–30

ጓደኞቼ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲኖሩ ልረዳቸው እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁ፣ አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎችን ከንግዲህ ላለመዋጋት የገቡትን ቃልኪዳን እንዲጠብቁ ለመርዳት ምን እነዳደረጉ በመፈለግ አልማ 27፥22-23 ሊያነቡ ይችላሉ። ጓደኞቻችን ቃል ኪዳኖቻቸውን እንዲጠብቁ ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት ነው? ልጆቻችሁ የትወና ሚናዎችን ሊጫወቱ ይችላሉ። ለምሳሌ ለመዋሸት ወይም ጨካኝ ለመሆን የሚፈልግን ሰው ምን ልንለው እንችላለን?

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች መሳሪያዎቻቸውን ሲቀብሩ

አንቲ ኔፊ ሌሂዎች መሳሪያዎቻቸውን ሲቀብሩ የሚያሳይ ምስል በዳን በር

አትም