“ሐምሌ 15–21፦ ‘የእግዚአብሔር ቃል በጎነት።’ አልማ 30-31፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])
“ሐምሌ 15–21። አልማ 30-31፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])
ሐምሌ 15–21፦ “የእግዚአብሔር ቃል በጎነት።”
አልማ 30–31
በአልማ 30–31 ውስጥ ያሉት ዘገባዎች የቃላትን ሃይል በግልጽ ያሳያሉ—ለክፉም ለደግም። ቆሪሆር የተባለ የሐሰት አስተማሪ “በሽንገላ” እና “ጮክ ባሉ ቃላት” “ብዙ ነፍሳትን ወደ ጥፋት” እንደሚያመጣ ዝቶ ነበር አልማ 30፥31፣47)። በተመሳሳይ መልኩ፣ የኔፋውያን ተቃዋሚ የነበረው የዞራም ትምህርቶችም የህዝቡ ሥብሥብ ሁሉ “በታላቅ ስህተት ውስጥ” እንዲወድቁ እና “የጌታን መንገድ እንዲበክሉ” አድርጓቸዋል (አልማ 31፥9፣ 11)።
በአንጻሩ፣ አልማ የእግዚአብሔር ቃል “ከጎራዴ ወይም ከሚሆንባቸው ማንኛውም ነገር የበለጠ በአዕምሯቸው ላይ ውጤት [እንደሚኖረው] የጸና እምነት ነበረው” (አልማ 31፥5)። የአልማ ቃላት ዘላለማዊ እውነትን ይገልጹ ነበር እንዲሁም ቆሪሆር ጸጥ እንዲል የሚያደርገውን ( አልማ 30:39–50 ይመልከቱ) የኢየሱስ ክርስቶስን ሃይል ያስገኙ እና ዞራማውያንን ወደ እውነት ለመመለስ ከእርሱ ጋር በሄዱት ላይ የእርሱን በረከት ይጋብዙ ነበር ( አልማ 31:31–38)። የሐሰት መልዕክቶች በሚበዙበት በዛሬው ጊዜ እነዚህ ለክርስቶስ ተከታዮች ውድ ምሳሌዎች ናቸው። አልማ እንዳደረገው “በእግዚአብሔርን ቃል በጎነት” በማመን እውነትን ማግኘት እንችላለን (አልማ 31:5)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ተቃዋሚው በሐሰት ትምህርት ሊያታልለኝ ይሞክራል።
በአልማ 30 ውስጥ ቆሪሆር “ጸረ ክርስቶስ” ተብሎ ተጠርቷል (ቁጥር 6)። ማንኛውም ኢየሱስ ክርስቶስን እና ወንጌሉን የሚቃወም ግለሰብ ወይም ነገር ጸረ ክርስቶስ ነው። በአልማ 30:6–31 ውስጥ ቆሪሆር ከዚህ መግለጫ ጋር እንደሚስማማ የሚያሳዩት የትኞቹ ጥቅሶች ናቸው? የቆሪሆርን የሐሰት ትምህርቶች ማጥናት ተመሳሳይ ትምህርቶችን እንድታውቁ እንዲሁም እንዳትቀበሉ ሊረዳችሁ ይችላል። የሚከተሉት አክቲቪቲዎች ጥናታችሁን ሊረዱ ይችላሉ፥
-
በአዳኙ ትምህርቶች እና በሰይጣን የሐሰት ኩረጃዎች መካከል ያለውን ልዩነት የበለጠ ለመረዳት የሚያስችሉ የትኞቹን የተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ትምህርቶች ልታስቡ ትችላላችሁ? ዓሣ ለማጥመድ፣ ለሐሰት ገንዘብ እና ለሐሰት ማስታወቂያ የሚያገለግሉ ማጥመጃዎች የዚህ አንዳንድ ምሳሌዎች ናቸው። አንድ ነገር የሐሰት መሆኑን እንዴት ማወቅ ትችላላችሁ? እውነት የሆነውን ልታውቁ የምትችሉት እንዴት ነው?
-
በአልማ 30፡6–31ውስጥ የሚገኙትን ቆሪሆር ያስተማራቸውን የሐሰት ትምህርቶች መዘርዘርን አስቡ። ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል ዛሬ የሚስብ የሚመስለው የትኛው ነው? ( 30:12–18, 23–28 ይመልከቱ)። እንደዚህ ያሉትን ሃሳቦች በመቀበል ምን ዓይነት ጉዳት ሊከተል ይችላል? ጠላት ዛሬ ሊያታልላችሁ የሚሞክረው ምን ዓይነት የውሸት መልእክትን በመጠቀም ነው?
-
ለቆሪሆር ትምህርቶች እውነተኛ ምላሽ ለመስጠት አልማ ምን አደረገ? (አልማ 30፥31–54 ይመልከቱ) እነዚህን መርሆች በህይወታችሁ ውስጥ እንዴት ማየት ትችላላችሁ?
እንደ አልማ ሁሉ፣ የዘመናችን ነቢያት እና ሐዋርያት በእውነት እና በሰይጣን ውሸቶች መካከል ያለውን ልዩነት እንድናውቅ ይረዱናል። በእነዚህ መልዕክቶች ውስጥ ምን ዓይነት ምክሮችን ታገኛላችሁ፣ ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን “Deceive Me Not፣” ሊያሆና፣ ሕዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 00-00፤ ዳለን ኤች. ኦክስ “Be Not Deceived፣” ሊያሆና፣ ሕዳር 2004 (እ.አ.አ)፣ 00።
በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች “Seek Truth and Avoid Deception፣” ወንጌል ቤተመፅአህፍት፤ “Oh Say, What Is Truth?፣” መዝሙር, ቁ. 272 ይመልከቱ።
ሁሉም ነገሮች ስለእግዚአብሄር ይመሰክራሉ።
ዛሬ ብዙ ሰዎች እግዚአብሄር እንደሌለ ያምናሉ። እግዚአብሄር እውን እንደሆነ እንድታውቁ የሚረዳቸሁ በ1 ቆሮንቶስ 30፥39-46 ላይ ምን ታገኛላችሁ? እርሱን ከማወቅ የሚያግደን ምንድን ነው? እግዚአብሄር ህያው እንደሆነ ሌላ ምን ምስክርነት ሰጥቷችኋል።
ጠላት ተከታዮቹን አይረዳቸውም።
ሰይጣን ተከታዮቹን ስለሚይዝበት መንገድ ከአልማ 30:56–60 ምን ትማራላችሁ? ቤታችሁን ከተፅዕኖው ለመከላከል ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
በተጨማሪም አልማ 36:3 ይመልከቱ።
የእግዚአብሄር ቃል ሰዎችን ወደ ጽድቅ የመምራት ኃይል አለው።
ዞረማውያን ከኔፋውያን የመለየታቸው ችግር ለአንዳንዶች ፖለቲካዊ ወይም ወታደራዊ መፍትሄ የሚያስፈልገው መስሎ ታይቷቸው የነበረ ሊሆን ይችላል ( አልማ 31:1–4ይመልከቱ)። ነገር ግን አልማ “በእግዚአብሔርን ቃል በጎነት” ማመንን ተምሮ ነበረ (አልማ 31:5)። ከአልማ 31:5 ስለእግዚአብሄር ቃል ሃይል ምን ትማራላችሁ? በተጨማሪም ( ዕብራውያን 4:12፤ 1 ኔፊ 15:23–24፤ 2 ኔፊ 31:20፤ ያዕቆብ 2:8፤ ሄለማን 3:29–30 ይመልከቱ)
አልማ 31 ስታጠኑ ለህይወት ተሞክሮዎቻችሁ የሚሆኑ ምን ሌሎች የወንጌል እውነቶችን ታገኛላችሁ? ለምሳሌ፦
-
የእግዚአብሔር ቃል ሰዎችን ወደ መልካም ነገር ሲመራ ያያችሁት እንዴት ነው? ( ቁጥር 5 ይመልከቱ)።
-
አልማ ለሌሎች ያለውን አመለካከት፣ ስሜት እና ድርጊት ( ቁጥር 34–35 ይመልከቱ) ከዞረማውያን ጋር አነጻጽሩ ( ቁጥር 17–28 ይመልከቱ)። እንደአልማ ልትሆኑ የምትችሉት እንዴት ነው?
-
በ1 ቆሮንቶስ 31፥30-38 ውስጥ ሌሎች ላደረጉት ሃጥያት ለሚያዝኑ ሰዎች የሚረዳ ምን ታገኛላችሁ?
በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት እያንዳንዱ ሊለወጥ ይችላል።
አልማ ወንጌልን ለዞረማውያን ለመስበክ ሲሄድ ከእርሱ ጋር የወሰዳቸውን ህዝቦች ሥብሥብ አስተውሉ ( አልማ 31:6 ይመልከቱ)። በሞዛያ 27:8–37፤ 28:4፤ አልማ 10:1–6፤ 11:21–25፤ 15:3–12 ውስጥ ስለእነዚህ ሰዎች ህይወት ምን ትማራላችሁ? በእነርሱ ተሞክሮዎች ውስጥ ለእናንተ የሚሆን ምን አይነት መልዕክት ሊኖር ይችላል?
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
መፅሐፈ ሞርሞን ከሃሰት ትምህርቶች ያስጠነቅቀኛል።
-
እንደ ገንዘብ እና ምግብ ያሉ ነገሮችን እንዲሁም እነዚህን ነገሮች በአሻንጉሊት መልክ ማሳየትን አስቡ። ይህ እውነተኛ በሆኑ እና የውሸት በሆኑ ነገሮች መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ ስለሚቻልባቸው መንገዶች ወደሚደረግ ውይይት ሊያመራ ይችላል። ከዚያም በአልማ 30:12–18 ቆሪሆር ስለእግዚአብሔር ያስተማራቸውን ውሸቶች ወይም የሐሰት ትምህርቶች ልጆቻችሁ እንዲለዩ መርዳት ትችላላችሁ። በአልማ 30:32–35 ውስጥ አልማ ለእነዚያ ውሸቶች ምላሽ የሰጠው እንዴት ነው? ከእርሱ ምሳሌ ምን እንማራለን?
ሁሉም ነገሮች ስለእግዚአብሄር ይመሰክራሉ።
-
አልማ በሰማይ እና በምድር ያሉ ነገሮች እግዚአብሄር እንዳለ እንዴት እንደሚመሰክሩ ተናግሯል። የሚቻል ከሆነ ከልጆቻችሁ ጋር ከቤት ውጭ የእግር መንገድ አድርጉ ወይም በምታነቡበት ጊዜ መስኮቱ አጠገብ ቁሙ አልማ 30፥44። እግዚአብሄር እውን እንደሆነ እና እንደሚወዳቸው እንዲያውቁ የሚረዷቸውን ነገሮቸ እንዲዘረዝሩ ጠይቋቸው። የሚያገኟቸውን ነገሮች ሥዕል መሳልም ይችላሉ ( የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ይመልከቱ)።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ “የሰማይ አባቴ ይወደኛል” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 228–29)፣ የሚለውን መዝሙር ስትዘምሩ ኳስ ወይም ሌላ ነገር እንዲቀባበሉ ማድረግም ትችላላችሁ። በየጊዜው ሙዚቃውን እያስቆማችሁ ኳሱን የያዘውን/ችውን ልጅ የሰማይ አባት ከፈጠረው አመስጋኝ ከሆነበት/ችበት አንድ ነገር እንዲያካፍል/ድታካፍል ጠይቁ።
የእግዚአብሔር ቃል ሀይለኛ ነው።
የሰማይ አባት ፀሎቴን ይሰማል።
-
በአልማ 31:8–35 ውስጥ ካሉት ጥቅሶች በመጠቀም የአልማን እና የዞራማውያንን ታሪክ በአጭሩ አጠቃልሉ (በተጨማሪም “ማዕራፍ 28: ዞራማውያን እና ራሜዩምጵቶም፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 78–80) ይመልከቱ። ልጆቻችሁ የራሜዩምጵቶም ግንብ በጡብ ወይም በድንጋይ እንድትገነቡ በሚረዷችሁ ጊዜ ዞራማውያን በጸሎታቸው ውስጥ (አልማ 31:15–18 ይመልከቱ) የተናገሯቸውን ነገሮች እንዲለዩ እርዷቸው። መፀለይ ያለብን እንደዚህ እንዳልሆነ አስረዱ። እናንተ እና ልጆቻችሁ እንዴት መጸለይ እንዳለብን ስትነጋገሩ ድንጋዮቹን ወይም ጡቦቹን አንድ በአንድ እንዲያነሱ አድርጉ። ሁልጊዜ ጠዋት እና ማታ እንዲጸልዩ ለማስታወስ ይችሉ ዘንድ ከድንጋዮቹ አንዱን በአልጋቸው አጠገብ ሊያስቀምጡት ይችሉ ይሆናል። ድንጋዮቻቸውን ማስጌጥ ያስደስታቸው ይሆናል።