ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መስከረም 30–ጥቅምት 6 “እኔ ህግ እንዲሁም ብርሃን ነኝ።” 3 ኔፊ 12–16


መስከረም 30–ጥቅምት 6 “እኔ ህግ እንዲሁም ብርሃን ነኝ።” 3 ኔፊ 12-16፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

“መስከረም 30–ጥቅምት 6፣ 3 ኔፊ 12-16፣ ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

አኢየሱስ ወደ አስራ ሁለቱ ሐዋርያት እየጠቆመ

Third Nephi: These Twelve Whom I Have Chosen፣ በ ጋሪ ኤል. ካፕ

መስከረም 30–ጥቅምት 6 “እኔ ህግ እንዲሁም ብርሃን ነኝ።”

3 ኔፊ 12-16

በገሊላ የተራራውን ስብከት ለመስማት እንደተሰበሰቡት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በለጋስ ምድር በሚገኘው ቤተመቅደስ የተሰበሰቡት ሰዎችም የሙሴን ህግ ይኖሩ ነበር። ነፍሳቸውን ወደ ክርስቶስ ይመራ ስለነበረ ተከትለውት ነበር። (ያዕቆብ 4:5 ይመልከቱ)፣ አሁን ደግሞ ክርስቶስ ከፍ ያለ ሕግ እያወጀ በፊታቸው ቆመ። ሆኖም እኛ የሙሴን ህግ ያልኖርነውም እንኳን ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ያስቀመጣቸው መሥፈርቶች ከፍ ያሉ እንደሆኑ መገንዘብ እንችላለን። “ፍጹም እንደሆነው አባታችሁ ፍጹም [ሁኑ]፣” ሲል ተናግሯል። (3 ኔፊ 12:48)።. ይህ ብቁ እንደማትሆኑ እንዲሰማችሁ ካደረጋችሁ አኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህም እንዳለ አስታውሱ፣ “አዎን፣ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ወደ እኔም የሚመጡ ብፁአን ናቸው፣ መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና” (3 ኔፊ 12:3)። ይህ ከፍ ያለ ህግ “ወደ እኔ ኑ፤ እናም ዳኑ፤” የማለት ሌላ መንገድ ነው (3 ኔፊ 12:20)። እንደሙሴ ሕግ ሁሉ ይህ ሕግም እርሱ በቻ ሊያድነን እና ፍጹም ሊያደርገን ወደሚችለው ወደ ክርስቶስ ይመራናል። “እነሆ፣እኔ ህግ እንዲሁም ብርሃን ነኝ። ወደ እኔ ተመልከቱ፣ እናም እስከመጨረሻው የጸናችሁ ሁኑ፣ እናም ህያው ትሆናላችሁ” ብሏል (3 ኔፊ 15:9)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

3 ኔፊ 12–14

የሴሚናሪ ምልክት
የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀ መዝሙር መሆን እችላለሁ።

3 ኔፊ 12–14አዳኙ ያስተማረውን ለማጥናት እና በተገባር ላይ ለማዋል የሚያስችል አንድ መንገድ እነሆ፦ የጥቅሶችን ሥብሥብ ምረጡና “የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት…” ብሎ በሚጀምር አንድ ዓረፍተ ነገር ማሳጠር ትችሉ እንደሆነ ተመልከቱ። ለምሳሌ፣ 3 ኔፊ 13:1–8 ሲያጥር እንዲህ ሊሆን ይችላል “የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት ስላደረጉት መልካም ነገር በህዝብ ፊት እንዲሞገሱ አይፈልጉም።” በእነዚህ ምንባቦች ሞክሩት፦

  • 12:3-16:

  • 12:38–44:

  • 1:19–24:

  • 14:1–5:

  • 2:21–27:

  • ሌሎች የሚያነሳሷችሁ ምንባቦች

እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ አኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ይሰማችኋል?

3 ኔፊ 12:48 ውስጥ ያሉት ትዕዛዛት ከባድ ከዚያም አልፎ የማይቻሉ ሊመስሉ ይችላሉ። “Be Ye Therefore Perfect—Eventually” (ሊያሆና, ህዳር. 2017(እ.አ.አ) 40–42) በሚለው የሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ መልዕክት ውስጥ በነዚህን ጥቅሶች ውስጥ ያሉትን የአዳኙን ቃላት እንድትገነዘቡ የሚረዳችሁ ምን ትማራላችሁ? በሞሮኒ 10:32–33፣ መሰረት እንደ አዳኙ ፍፁም ለመሆን የሚረዳው ምንድን ነው?

The Challenge to Become፣” ኢንዛይን፣ ሕዳር፣ 2000 (እ.አ.አ)፣ 32–34፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “Become like Jesus Christ,” ወንጌል ቤተመፃሕፍት፤ “Lord, I Would Follow Thee,” መዝሙር፣ ቁጥር. 220፤ “ኢየሱስ ክርስቶስ ከፍ ያለውን ሕግ እንዴት መኖር እንደሚቻል ያስተምራል” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ላይ ተመልከቱ።

ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮችን ተጠቀሙ። አዳኙ ስለተለመዱ ነገሮች በመናገር ታላላቅ እውነቶችን አስተምሯል። ስለ 3 ኔፊ 12 ስታጠኑ ወይም ስታስተምሩ ተመሳሳይ ነገሮችን ልታደርጉ ትችላላችሁ። ጥቂት ጨው፣ ሻማ ወይም ኮት መመልከት ወይም መያዝ አዳኙ ስላስተማራቸው ዘላለማዊ እውነቶች የሚደረግን ውይይት ሊያዳብር ይችላል።

3 ኔፊ 12:1–2፤ 15:23–24፤ 16:1–6

ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው።

እንደ ለጋስ ምድር ሰዎች አዳኙን ያዩት እና ድምፁን የሰሙት በጣም ጥቂት የእግዚአብሄር ልጆች ናቸው። ብዙዎቻች በ3 ኔፊ 12:215:23፤ እና 16:4–6 ውስጥ እንደተገለጹት ሰዎች ነን። እንደዚህ ላሉ ሰዎች በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ምን ዓይነት ተስፋዎች ተሰጥተዋል? እነዚህ ተስፋዎች በሕይወታችሁ ውስጥ እየተሟሉ ያሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም ዮሐንስ 20:26–292 ኔፊ 26:12–13አልማ 32:16–18 ይመልከቱ።

3 ኔፊ 12:21–3013:1–8፣ 16–1814:21–23

የልቤን ፍላጎቶች ለማጥራት የልቤን ጥረት ማድረግ እችላለሁ።

በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ልታስተውሉ የምትችሉት አንድ ጭብጥ አዳኙ ከፍ ያለውን ሕግ ስለመኖር ይኸውም በድርጊቶቻችን ብቻ ሳይሆን በልባችንም ጻድቅ እንድንሆን ያቀረበው ግብዣ ነው። አዳኙ ስለ ክርክር (3 ኔፊ 12:21–26)፣ ብልግና (3 ኔፊ 12:27–30)፣ ጸሎት (3 ኔፊ 13:5–8)፣ እና ጾም (3 ኔፊ 13:16–18) በሚናገርበት ጊዜ ይህንን ጭብጥ ፈልጉ። ሌሎች ምን ምሳሌዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ? የልባችሁን ፍላጎቶች ለማጥራት ምን ማድረግ ችላለሁ።

3 ኔፊ 14፥7–11

የሰማይ አባት ስለምን፣ ስፈልግ እና ሳንኳኳ መልካም የሆኑ ነገሮችን ይሰጠኛል።።

3 ኔፊ 14:7–11 ውስጥ ያለውን እንድትለምኑ፣ እንድትፈልጉ እና እንድታንኳኩ የቀረበላችሁን የአዳኙን ግብዣ በምታነቡበት ጊዜ፣ ምን “መልካም ነገሮችን” እንድትጠይቁ እንደሚፈልግ አሰላስሉ። ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡትት ተጨማሪ ቀዱሳት መጻህፍት እንዴት እንደምትለምኑ፣ እንደምትፈልጉ እና እንደምታንኳኩ እንድትገነዘቡ ሊረዷችሁ ይችላሉ። አንዳንድ ጸሎቶች እናንተ በጠበቃችሁበት መንገድ ለምን እንደማይመለሱ ለማስረዳት ሊጠቅሙም ይችላሉ ኢሳይያስ 55:8–9ሔለማን 10:4–5ሞሮኒ 7:26–27, 33, 37፤ እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 9:7–988:64። እነዚህ ምንባቦች በምትለምኑበት፣ በምትፈልጉበትና በምታንኳኩበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም ሚልተን ካማርጎ “Ask, Seek, and Knock፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 106-8 ይመልከቱ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

3 ኔፊ 15፥23–16

ኢየሱስን በመከተል ረገድ መልካም ምሳሌ መሆን እችላለሁ።

  • አንዳንድ ጊዜ ለጆች ምሳሌነታቸው ምን ያህል ሌሎችን ሊባርክ እንደሚችል ላይገነዘቡ ይችላሉ። 3 ኔፊ 12:14–16 ብርሃናቸውን እንዲያበሩ ለማበረታታት ተጠቀሙበት። ለምሳሌ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “እናንተ” ወይም “የእናንተ” የሚለውን ቃል ስታነቡ ልጆቻችሁ ወደ ራሳቸው እንዲጠቁሙ ጠይቋቸው። ኢየሱስ ክርስቶስን በሚከተሉበት ጊዜ ስለምታዩባቸው ብርሃን እና እናንተም እሱን እንድትከተሉ እንዴት እንደሚያነሳሳችሁ ለልጆቹ ንገሯቸው። እንደ “I Am like a Star” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 163) ያለ ልጆቹ እንደ ብርሃን እንዲያንጸባርቁ የሚያበረታታ መዝሙር አብራችሁ ልትዘምሩም ትችላላችሁ።

  • ልጆቻችሁ ብርሃናቸውን እንዳይደብቁ ለማበረታታት (3 ኔፊ 12:15 ይመልከቱ) አንድን አምፖል ወይም መብራት በየተራ ይደብቁ ወይም ይሸፍኑ። ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ ለመሆን ሊያደርጉ ስለሚችሉት አንድ ነገር በጠሩ ቁጥር ብርሃኑን ሊገልጡ ይችላሉ።

3 ኔፊ 13:19–21

“ሃብትን በሰማይ አከማቹ”

  • እነዚህን ጥቅሶች ማንበብ ዋጋ ስለምንሰጣቸው ነገሮች እንድንወያይ ሊያነሳሳን ይችላል። ምናልባት ልጆቻችሁ ዘላለማዊ ዋጋ ያላቸውን ሀብቶች የሚያስታውሷቸውን ነገሮች ለማግኘት ወደሚደረግ የሀብት ፍለጋ ልትመሯቸው ትችላላችሁ።

3 ኔፊ 14፥7–11

የሰማይ አባት ለፀሎቴ መልስ ይሰጣል።

  • 3 ኔፊ14:7 በምታነቡበት ጊዜ ልጆቻችሁ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን የአዳኙን ግብዣዎች የሚወክሉ ተግባራትን ሊያከናውኑ ይችላሉ። ምናልባት እጃቸውን ሊያወጡ (ለምኑ) በእጆቻቸው አጉሊ መነፅር ሊሰሩ (ፈልጉ) እንዲሁም በር እንደሚያንኳኳ ሰው ሊያስመስሉ(አንኳኩ) ይችላሉ። ልጆቻችሁ በጸሎቶቻቸው ውስጥ ሊናገሩ እና ሊጠይቁ ስለሚችሏቸው ነገሮች እንዲያስቡ እርዷቸው።

  • ልጆቻችሁ አንድ የሆነ ነገር ጠይቀው ከዚያ ሙሉ በሙሉ የተለየ ነገር የሚቀበሉበትን አንድ የጨዋታ ዓይነት በመጫወት ሊደሰቱ ይችላሉ። በ3 ኔፊ 14:7–11 ውስጥ አዳኙ በሰማይ ስላለው አባታችን እንድናውቅ የፈለገው ምን ነበር።?

3 ኔፊ 14:21–2715:1

አዳኙ የሚያስተምረውን እንድሰማ እና እንዳደርግ ይፈልጋል።

  • ልጆቻችሁ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉትን ምሳሌዎች በዓይነ ህሊናቸው እንዲያዩ ልትረዷቸው የምትችሉባቸውን መንገዶች አስቡ። ምናልባት ሥዕሎችን ሊስሉ፣ ተግባራትን ሊያከናውኑ ወይም በጠንካራ እና በሸዋማ ቦታዎች ነገሮችን ሊገነቡ ይችላሉ። 3 ኔፊ14:24–27ን በሚያነቡበት ወይም The Wise Man and the Foolish Manን” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 281) “በሚዘምሩበት ጊዜ “ጠቢብ ሰው” በሚለው ቦታ ስማቸውን ሊተኩም ይችላሉ። ወይንም በ3 ኔፊ 14:21–27 እና 15:1 ውስጥ “የሚያደርጉ” የሚልን ቃለ በሚሰሙበት ጊዜ ሁሉ ሊነሱ ይችላሉ።

  • ልትሞክሩት የምትችሉት ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገር እነሆ፦ልጆቻችሁ አንደኛው እግራቸው የአዳኙን ቃል መስማትን እንዲሁም ሌላኛው እግራቸው አዳኙ ያስተማረውን ማድረግን የሚወክሉ እንደሆኑ አድርገው እንዲያስቡ ጠይቋቸው። ልጆቻችሁ “በመስማት” እግራቸው ብቻ ተስተካክለው ለመቆም እንዲሞክሩ ጋብዟቸው። ሃይላኛ ነፋስ ወደቤት ቢነፍስ ምን ይከሰታል? ከዚያም እናንተ እና ልጆቻችሁ አዳኙ እንድናደርጋቸው ያስተማራቸውን የተለዩ ነገሮች ልትፈልጉ ትችላላችሁ: 3 ኔፊ 12:3–12, 21–2613:5–8 ይመልከቱ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ኢየሱስ ኔፋውያንን ሲያስተምር

የአዳኙ ይአሜሪካ ህዝቦች ጉብኝት በግሌን ኤስ. ሆፕኪንሰን