ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 14–20፦ “እናንተ የኪዳን ልጆች ናችሁ።” 3 ኔፊ 20–26


“ጥቅምት 14–20፦ እናንተ የቃል ኪዳን ልጆች ናችሁ።’ 3 ኔፊ 20-26፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

“ጥቅምት 14–20 3 ኔፊ 20–26፣ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

ክርስቶስ ለኔፋውያን ሲገለጥ

Illustration of Christ appearing to the Nephites[ክርስቶስ ለኔፋውያን ሲገለጥ የሚያሳይ ምሥል፣ በአንድሪው ቦስሊ

ጥቅምት 14–20፦ “እናንተ የኪዳን ልጆች ናችሁ።”

3 ኔፊ 20-26

ሰዎች የእስራአኤል ቤትእንደሚለው ያሉ ቃላትን ሲጠቀሙ ስትሰሙ ስለእናንተ እየተናገሩ እንደሆነ ያህል ይሰማችኋል? ኔፋውያን እና ላማናውያን ቃል በቃል “የእስራአኤል ዛፍ ቅርንጫፍ፣” የእስራአኤል ዘሮች ነበሩ ሆኖም “[ከአካሉ እንደጠፉ]” ተሰምቷቸው ነበር (አልማ 26:36፤ በተጨማሪም 1 ኔፊ 15:12 ይመልከቱ)። ነገር ግን አዳኙ በእርሱ ዘንድ እንዳልጠፉ እንዲያውቁ ፈለገ። “የእስራኤል ቤት ናችሁ” እናም “የቃል ኪዳን ልጆች ናችሁ” (3 ኔፊ 20:25)። ለእናንተም ዛሬ ይህን የሚመስል ነገር ሊናገር ይችላልል፤ የተጠመቀ እና ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን የሚገባ ሁሉ “የእስራኤል ቤት ነው።” በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ስለ እስራኤል ቤት በሚናገርበት ጊዜ ስለእናንተ እየተናገረ ነው። “የምድርን ወገኖች ሁሉ ”ለመባረክ የተሰጠው ተዕዛዘ ለእናንተ ነው (3 ኔፊ 20:27)። “በድጋሚ ንቂና፣ ጥንካሬሽን ልበሺ” በማለት የተደረገው ግብዣ ለእናንተ ነው (3 ኔፊ 20:36)። እንዲሁም “ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አያልፍም፣ የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም” የሚለው ውድ ተስፋ ለእናንተ ነው (3 ኔፊ 22:10)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

3 ኔፊ 20–22

በኋለኛው ቀናት እግዚአብሄር ታላቅ ሠራ ይሠራል።

3 ኔፊ 20–22፣ አዳኙ ስለ ቃል ኪዳኑ ሕዝብ የወደፊት ዕድል ተንብዮአል (በተለይ 3 ኔፊ 20:30–32፣ 39–4121:9–11፣ 22–29 ይመልከቱ)። እነዚህን ጥቅሶች በምታነቡበት ጊዜ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም.ኔልሰን ያሉትን አስታውሱ፦“እኛ የጌታ ቃል ኪዳን ህዝብ [ነን]። የእኛ እድል ደግሞ እነዚህ ቃልኪዳኖች እንዲሟሉ በግል መሳተፍ ነው። ለመኖር እንዴት አስደሳች ጊዜ ነው!” (“The Gathering of Scattered Israel,” ሊያሆና፣ ሕዳር 2006 (እ.አ.አ) 79)። በተለይ አስደሳች የሆኑት የትኞቹ ትንቢቶች ናቸው? እንዲሟሉ ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

የሚያነሳሱ ቃላትን እና ሃረጎችን ፈልጉ። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ቃላት እና ሀረጎች በተለይ ለእናንተ የተጻፉ በሚመስል መልኩ ያስደንቋችሁ ይሆናል። እነዚህንም በቅዱሳት መጻህፍትዎ ላይ ምልክት ማድረግን ወይም በጥናት ደብተርዎ ውስጥ መፃፍን ያስቡ።

3 ኔፊ 22፤ 24

ጌታ ወደ እርሱ የሚመለሱ ሠዎችን ይምራል።

3 ኔፊ 22 እና 24፣ አዳኙ ኢሳይያስ እና ሚልክያስ የተናገሯውን በግልፅ ምስል እና በንፅፅር የተሞሉት ቃላት ጠቅሷል—ፍም፣ የተጣራ ብር, ጋብቻ፣ የሠማይ መስኮቶች (በተለይ 3 ኔፊ 22:7–8፣ 10–1724:10–12, 17–18 ይመልከቱ)። እነዚህ ንጽጽሮች እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር እንዲሁም ከእናንተ ጋር ስላለው ግንኙነት ምን ያስተምሯችኋል? በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ያሉት እነዚህ ተስፋዎች በሕይወታችሁ ወይም ብቤተሰባችሁ ህይወት ውስጥ እየተሟሉ ያሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም “The Refiner’s Fire” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

3 ኔፊ 23፥6–13

መንፈሳዊ ተሞክሮዎችን መመዝገብ ቤተሰቤን ሊባርክ ይችላል።

3 ኔፊ 23፥6–13 ውስጥ አዳኙ ክኔፊ ጋር ስለነበረው ግንኙነት ምን ያስደንቃችኋል? አዳኙ የፃፋችኋቸውን መዝገቦች የሚመረምር ቢሆን ኖሮ ምን ጥያቄዎችን ሊጠይቃችሁ ይችላል? ምን ዓይነት ጠቃሚ ሁኔታዎችን ወይም መንፈሳዊ ተሞክሮዎችን ትመዘግባላችሁ? ይህንን ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው ( 3 ኔፊ 26:2ይመልከቱ)?

3 ኔፊ 2326:1–12

አዳኙ ቅዱሳት መፃህፍትን እንድመረምር ይፈልጋል።

3 ኔፊ 20:10–122326:1–12 በምታነቡበት ጊዜ አዳኙ ስለቅዱሳት መፃህፍት ምን እንደሚሰማው አሰላስሉ። ቅዱሳት መፃህፍትን በመመርመረ እና ዝም ብሎ በማንበብ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? ( 3 ኔፊ 23:1 ይመልከቱ)።

3 ኔፊ 24፥7–12

የሴሚናሪ ምልክት
አስራትን መክፈል የሰማይን መስኮቶች ይከፍታል።

የእግዚአብሔር ሰዎች ሁል ጊዜ አሥራት እንዲከፍሉ ታዝዘዋል (ዘፍጥረት 14:17–20ሚልክያስ 3:8–11)። 3 ኔፊ 1:1-12፣ በምታጠኑበት ጊዜ እግዚአብሄር ሕዝቡን ለምን አሥራት እንዲከፍሉ እንደሚጠይቃቸው አስቡ። እነዚህ ጥያቄዎች ጥናታችሁን ሊመሩላችሁ ይችላሉ፦

  • የንጽህና ህግ ምንድን ? (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 119 በዚህ ራዕይ “ትርፍ” ማለት ገቢ ማለት ነው። ገቢ ያላቸው አባላት በሙሉ አሥራት መክፈል አለባቸው።) አሥራት ከሌሎች ሥጦታዎች የሚለየው በምንድን ነው?

  • አሥራት ጥቅም ላይ የሚውለው በምን ላይ ነው? ከእፊል ዝርዝሩን በወንጌል አርዕስቶች “አሥራት” (ወንጌል ላይብረሪ).ውስጥ መፈለግ ትችላላችሁ። የቤተክርስቲያኗ አባላት አስራት በመክፈላቸው ምክንያት በየትኞቹ መንገዶች ተባርካችኋል?

  • የአስራትን ሕግ ለሚከፍሉ ሠዎች ምን ዓይነት በረከቶች ይመጣሉ? (3 ኔፊ 24፥7–12 ይመልከቱ)። አንዳንዶቹን ከሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር Small and Simple Things” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2013 (እ.አ.አ) 17-20) መልእክት ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ። በተለይ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ በረከቶችን ተመልከቱ። እነዚህን በረከቶች በህይወታችሁ ያያችሁት እንዴት ነው?

“Jesus Teaches about the Widow’s Mite” (የወንጌል ቤተመፃህፍት) የሚለውን ቪዲዮ ልትመለከቱ ወይንም ማርቆስ 12:41–44 ልታነቡ ትችላላችሁ። ይህ ታሪክ ምን ያስተምራችኋል?

3 ኔፊ 25፥5-6

ኤሊያስ የእኔን ልብ ወደ አባቶቼ እንዲመልስ ጌታላከው።

በዘመናችን ልቦቻችን “ወደአባቶቻችን የሚመለሱት” በቤተመቅደስ እና የቤተስብ ታሪክ ሥራ አማካኝነት ነው። ለናንተ ይህ የሆነው እንዴት ነው? 3 ኔፊ 25:5–6 እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110:13–16 ስታነቡ ይህ ለምን የእግዚአብሔር እቅድ አስፈላጊ አካል እንደሆነ አሰላስሉ።

በተጨማሪም “ቤተሰቦች ለዘላለም አብረው ሊሆኑ ይችላሉ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 188 ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳብ ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መፅሄቶች እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

3 ኔፊ 23፥1፣5

ቅዱሳት መፃህፍትን በትጋት መመርመር እችላለሁ።

  • ማቴዎስ 14፥152 ውስጥ ያሉት የጌታ መመሪያዎች ቅዱሳት መፃህፍት ለእርሱ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ ያሳያል። ልጆቻችሁ ይህንን እንዲገነዘቡ ለመርዳት 3 ኔፊ 23:1፣ 5 ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ልታነቡና ሶስት ጊዜ የተደገመ አንድ ቃል እንዲሠሙ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። መመርመር ዝም ብሎ ከማንበብ የሚለየው እንዴት ነው?

  • ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ የምትወዱትን ቅዱስ ፅሁፍ ልትፅፉና ልትደብቁ ትችላላችሁ። ከዚያም በየተራ አንዳችሁ የሌላውን የተደበቀ ቅዱስ ፅሁፍ መፈለግ፣ አብራችሁ ማንበብ እንዲሁም እነዚህ ጥቅሶች ለምን ትርጉም ያላቸው እንደሆኑ መነጋገር ትችላላችሁ።

3 ኔፊ 24፥8–12

አስራትን መክፈል የሰማይን መስኮቶች ይከፍታል።

  • ልጆቻችሁ በ 3 ኔፊ 24:8–12 ውስጥ አሥራት ከከፈልኩኝ ጌታ …. የሚለውን ዓረፍተ ነገር የሚያሟሉበትን መንገዶች እንዲፈልጉ እርዷቸው። አሥራት በመክፈላችሁ ምክንያት የተባረካችሁበትን ተሞክሮ ለማካፈልም ትችላላችሁ። የሚጠቅም ከሆነ፣ የተወሰኑ ገንዘብ መጠኖችን መጻፍ እና ልጆችዎ ለእያንዳንዱ መጠን ምን ያህል አሥራት (10 በመቶ) መስጠት እንዳለባቸው እንዲያሰሉ መርዳትን አስቡ።

  • የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገፅ ጌታ የቤተክርስቲያኗን አባላት ለመባረክ አሥራትን ስለሚጠቀምበት አንዳንድ መንገዶች ልጆቻችሁ እንዲናገሩ መርዳት ይችላል። ምናልባት አሥራት እነርሱን የባረከበትን መንገዶች የሚያሳዩ ሥዕሎችን ሊስሉ( ወይም ብቤተ ክርስቲያን መፅሄቶች ውስጥ ፎቶዎችን ሊፈልጉ) ይችላሉ።

3 ኔፊ 25፥5-6

የሰማይ አባት ስለ ቅድመ ዓያቴ እንድማር ይፈልጋል።

  • ልጆቻችሁ ስለ ቅድመ ዓያቶቻቸው እንዲመረምሩ እና እንዲማሩ የምታነሳሷቸው እንዴት ነው? ልጆቻችሁ ሲያድጉ ለቅድመ ዓያቶቻቸው ሥርዓቶችን እንዲያከናውኑ ማበረታታት የምትችሉት እንዴት ነው? በኋለኛው ቀን መሆን ያለበትን ነገር ለማግኘት 3 ኔፊ 25:5–6 ውስጥ እንዲፈልጉ መርዳትን አስቡ። እነዚህን ጥቅሶች በምታነቡበት ጊዜ ትናንሽ ልጆች “ልብ” የሚለውን ቃል በሰሙ ቁጥር እጃቸውን ደረታቸው ላይ ማድረግ ይችላሉ። ይህ ትንቢት እንዴት እንደተፈፀም በትምህርት እና ቃልኪዳን 110:13–16 ውስጥ ልታነቡም ትችላላችሁ (በተጨማሪም የወንጌል የአርትመፅሐፍቁጥር 95 ይመልከቱ)። ልቦቻችሁ ወደ ቅድመ ዓያቶቻችሁ እንዴት እንደሚመለስ ለልጆቻችሁ ተናገሩ። ለምሳሌ ስለ ቅድመ ዓያቶቻችሁ የተማራችኋቸውን እና ለእነርሱ የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን ስታከናውኑ ስላጋጠሟችሁ ማናቸውም ተሞክሮዎች ለማካፈል ትችላላችሁ።

  • ልጆቻችሁ የቤተሰብ የዘር ሃረግ ግንድን በወላጆቻቸው እና በቅድመ ዓያቶቻቸው ሥሞች እንዲሞሉ እርዷቸው። ከቅድመ ዓያቶቻችሁ የአንዱን ምን ታሪኮችን ማካፈል ትችላላችሁ? የሚቻል ከሆነ ፎቶዎችን አሳዩ ። “Families Can Be Together Forever” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ ፣ 188) አብራችሁ ልትዘምሩ እንዲሁም ቤተሰቦች በሰማይ አባት እቅድ ውስጥ ለምን አስፈላጊ እንደሆኑ ከልጆቻችሁ ጋር ልትነጋገሩ ትችላላችሁ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ኢየሱስ የኔፋውያንን ታሪክ ከኔፊ ጋር እያነበበ።

Bring Forth the Record [መዝገቡን አምጡ]፣ በ ጋሪ ኤል. ካፕ.