ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 21–27፦ “እንደዚህ ያለ ደስተኛ ሊሆን የቻለ ህዝብ አልነበረም።” 3 ኔፊ 27–4 ኔፊ


“ጥቅምት 21–27፦ እንደዚህ ያለ ደስተኛ ሊሆን የቻለ ህዝብ አልነበረም።’ 3 ኔፊ 27–4 ኔፊ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023 (እ.አ.አ))

“ጥቅምት 21-27። 3 ኔፊ 27–4፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ህዝቡን ሲያስተምር

ጥቅምት 21–27፦ “እንደዚህ ያለ ደስተኛ ሊሆን የቻለ ህዝብ አልነበረም።”

3 ኔፊ 274 ኔፊ

የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ለማሰላሰል ከሚያስደስት ፍልስፍና በብዙ ይበልጣሉ። ዓላማቸው እንደ እርሱ እንድንሆን ማነሳሱት ነው። 4 ኔፊ መጽሐፍ የአዳኙ ወንጌል ሰዎችን እንዴት ሙሉ በሙሉ እንደሚለውጥ ያሳያል። የኢየሱስን አጭር አገልግሎት ተከትሎ በኔፋውያን እና በላማናውያን መካከል የነበረው የዘመናት ጠብ ፍጻሜውን አገኘ። በመለያየት እና በኩራት የታወቁ ሁለት ህዝቦች “በአንድነት የክርስቶስ ልጆች” ሆኑ (4 ኔፊ 1:17) እንዲሁም “ሁሉም ነገሮች [የ]ጋራ [ማድረግ]” ጀመሩ (4 ኔፊ 1:3)። “የግዚአብሄር ፍቅር…በሕዝቡ ልብ ውስጥ [ነበር]” ስለዚህም “በእግዚአብሔር እጅ ከተፈጠሩት ሰዎች መካከል እንደዚህ ያለ ደስተኛ ሊሆን የቻለ ህዝብ አልነበረም” (4 ኔፊ 1:15–16)። የአዳኙ ትምህርቶች ኔፋውያንን እና ላማናውያንን የለወጡት እንዲህ ነበር። እናንተንስ እየቀየሯችሁ ያሉት እንዴት ነው?

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

3 ኔፊ 27፥1–12

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በስሙ ትጠራለች።

የአዳኙ ደቀ መዛሙርት ቤተክርስቲያኗን በመላው ምድር ማቋቋም በጀመሩ ጊዜ ለአንዳንድ ሰዎች ከቁብ የማይቆጠር ሊመስል የሚችል ጥያቄ መጣ።—የቤተክርስቲያኑ ስም ምን መሆን አለበት? (3 ኔፊ 27:1–3) ይመልከቱ። አዳኙ በ3 ኔፊ 27:4–12 ውስጥ ከሰጠው መልስ ስለ ስሙ አስፈላጊነት ምን ትማራላችሁ?

አዳኙ የቤተክርስቲያኑን ስም ዛሬ በትምህርት እና ቃልኪዳኖች 115፥4 ገልጿል። በዚያ ስም ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ቃል አሰላስሉ። እነዚህ ቃላት ማን እንደሆንን፣ ምን እንደምናምን እና እንዴት እንዳለብን እንድናውቅ የሚረዱን እንዴት ነው?

በተጨማሪም የራስል ኤም.ኔልሰንን “ትክክለኛ የቤተክርስትያኗ ስም [The Correct Name of the Church]፣” ሊያሆና ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣87–89 ይመልከቱ።

3 ኔፊ 27፥10–22

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በስሙ ነው።

አዳኙ የእርሱ ቤተክርስቲያን “[በእርሱ] ወንጌል [መመሥረት]” እንዳለባት ከገለፀ በኋላ (3 ኔፊ 27:10)፣ ወንጌሉ ምን እንደሆነ አብራራ። በ3 ኔፊ 27:13–22 ውስጥ የተናገረውን እንዴት ታጠቃልሉታላችሁ? በዚህ ትርጓሜ መሰረት በእርሱ ወንጌል መመስረት ማለት ለቤተክርስቲያኗ እና ለእናንተ ምን ማለት ነው?

እየተማራችሁ ያላችሁትን መዝግቡ።3 ኔፊ 27:23–26 ውስጥ ለደቅ መዛሙርቱ ምን እንዳስተማራቸው አስተውሉ። መንፈሳዊ ተሞክሮዎችን መመዝገብ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በ 3 ኔፊ የአዳኙን አገልግሎት ስታጠኑ ምን ለመመዝገብ መነሳሳት ይሰማችኋል?

3 ኔፊ 28፥1–11

“የምትፈልጉት ምንድን ነው?”

ደቀ መዛሙርቱን እንደጠየቃቸው አዳኙ “ከእኔ የምትፈልጉት ምንድን ነው?” ብሎ ጠይቋችሁ ቢሆን ኖሮ ምን ትሉ ነበር? (3 ኔፊ 28:1)። 3 ኔፊ 28:1–11 በምታነቡበት ጊዜ ስለዚህ አስቡ። ለጠየቀው ጥያቄ ከሰጡት ምላሽ ስለ ደቀ መዛሙርቱ የልብ ፍላጎት ምን ተማራችሁ? የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስትኖሩ ፍላጎቶቻችሁ የተለወጡት እንዴት ነው?

መዝሙሮች አብዛኛውን ጊዜ የልብ ፍላጎቶችን ይገልፃሉ—“More Holiness Give Me” ጥሩ ምሳሌ ነው (መዝሙር፣ ቁ. 131)። ፍላጎቶቻችሁን የሚያንፀባርቅ መዝሙር መፈለግን አስቡ።

3 ኔፊ 29–30

መፅሐፈ ሞርሞን የእግዚአብሄር የኋለኛው ቀን ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ የሚያሳይ ምልክት ነው።

የሆነ ነገር ሊከሰት እንደሆነ የሚያሳውቋችሁን ምልክቶችን አስቡ። ለምሳሌ፣ ዝናብ እየመጣ እንደሆነ ወይንም ወቅቶች እየተቀያየሩ መሆናቸውን እንዴት ታውቃላችሁ 3 ኔፊ 29:1–3፣ መሰረት የእግዚአብሄር ህዝቡን የመሰብሰብ ሥራ “እንዲፈፅም እንደጀመረ” እንዴት ታውቃላችሁ? (በተጨማሪም 3 ኔፊ 21:1–7 ይመልከቱ)። በ3 ኔፊ 29:4–9፣ ውስጥ በዘመናችን ሰዎች የሚክዷቸውን ነገሮች ልታስተውሉም ትችላላችሁ። መፅሐፈ ሞርሞን በእነዚህ ነገሮች ላይ ያላችሁን እምነት የሚያጠነክረው እንዴት ነው?

4 ኔፊ 1፥1–18

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
የኢየሱስ የአኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ወደ አንድነት እና ደስታ ይመራሉ።

የአዳኙን ጉብኝት ተከትሎ በነበሩት አመታት ውስጥ መኖር ምን ይመስላል? 4 ኔፊ 1:1–18 በምታጠኑበት ጊዜ ህዝቡ የተቀበላቸውን በረከቶች መዘርዘርን አስቡ። ወደዚህ የተባረከ ሕይወት እንዲያመሩ በረዷቸው ምርጫዎች ላይ ምልክት ልታደርጉ ወይም ልታስተውሏቸውም ትችላላችሁ። ኢየሱስ የጽድቅ ምርጫ እንዲያደርጉ አነሳስቷቸው የነበረ ሊሆን የሚችል ምን ነገር አስተማራቸው? አንዳንድ ምሳሌዎች እነሆ፣ ነገር ግን ሌሎችንም ልታገኙ ትችላላችሁ፡ 3 ኔፊ 11:28–3012:8–9፣ 21–24፣ 40–4413:19–21፣ 28–3314:1218:22–25

ቤተሰባችሁ፣ አጥቢያችሁ ወይም ማህበረሰባችሁ በታላቅ አንድነት እና ደስታ እንዲኖር ምን ልታደርጉ እንደምትችሉ አሰላስሉ። ክፍፍልን ለማሸነፍ እና ሌሎች የእግዚአብጌር ልጆች “አንድ” እንዲሆኑ ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? ይህንን ግብ እንድታሳኩ የሚረዷችሁ የትኞቹ የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ናቸው።

በሚያሳዝን መልኩ በ4ኔፊ የተገለፀው የፅዮን ማህበረሰብ በመጨረሻ ክፋት ውስጥ ገብቷል። 4 ኔፊ 1:19–49ን ስታነቡ፣ ደስታቸው እና አንድነታቸው እንዲያከትም ያደረጉትን ዝንባሌዎች እና ባህርያት ፈልጉ። እነዚህ ዝንባሌዎች እና ባህርያት እንዲወገዱ ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

በተጨማሪም ሙሴ 7:18; ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “Sustainable Societies,” ሊያሆና፣ ህዳር 2020(እ.አ.አ)፣ 32–35፤ ሬይና አይ. አቡርቶ፣ “With One Accord,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 78–80፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “Belonging in the Church of Jesus Christ,” የወንጌል ላይብረሪ።.

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

3 ኔፊ 27፥3–8

እኔ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አካል ነኝ።

  • የኢየሱስን ቤተክርስቲያን ስም አስፈላጊነት ለማስተዋወቅ ከልጆቻችሁ ጋር ስለየራሳቸው ስሞች ተነጋገሩ። ስሞቻችን አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የነበራቸውን ጥያቄ እየፈለጋችሁ 3 ኔፊ 27፥3–8ን አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ መልሱን በ3 ኔፊ 27:5-8 ውስጥ እንዲፈልጉ እርዷቸው። የቤተክርስቲያኗ ሥም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • ልጆቻችሁ የሚካተቱባቸው እንደ ቤተሰብ ወይም የመጀመሪያ ክፍል ያሉ የተለያዩ ቡድኖችን እንዲያስቡ ልትረዱም ትችላላችሁ። ከእያንዳንዱ ቡድን አባልነታቸው ምን እንደሚወዱ ጠይቋቸው። ከዚያም “The Church of Jesus Christ” (የልጆች የመዝሙር መፅሃፍ፣ 77) አብራችሁ ልትዘምሩ እና የአዳኙ ቤተክርስቲያን አባል በመሆናችሁ ለምን አመስጋኝ እንደሆናችሁ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ።

3 ኔፊ 27፥13–16

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በወንጌሉ ነው።

  • አዳኙ ወንጌሉን በ3 ኔፊ 27 ውስጥ በአጭሩ አስቀምጧል። ወንጌል የሚለው ቃል ትርጉም “መልካም ዜና” ማለት እንደሆነ ለልጆቻችሁ ልታብራሩ ትችሉ ይሆናል። በ 3 ኔፊ 27:13–16 ውስጥ ምን መልካም ዜና እናገኛለን? የአዳኙ ቤተክርስቲያን በወንጌሉ ላይ እንደተመሰረተች ለማስተማር የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገፅ ተጠቀሙ።

3 ኔፊ 27፥30–31

ልጆቹ ወደ እርሱ ሲመለሱ የሰማይ አባት ደስ ይለዋል።

  • አንድ ሰው የሚደበቅበትን እና ሌሎች ሊያገኙት/ኟት የሚሞክሩበትን ጨዋታ መጫወትን አስቡ። ይህ፣ አንድ የጠፋ ሰው ሲገኝ የሚሰማንን ደስታ አስመልክቶ ወደሚደረግ ውይይት ሊያመራ ይችላል። 3 ኔፊ 27:30–31፣ ካነበባችሁ በኋላ “አንድም… እንዳይጠፋ” ወደ ሰማይ አባት መቅረብ እንችል ዘንድ እንዴት መረዳዳ እንደሚቻል ልትነጋገሩ ትችላላችሁ።

4 ኔፊ

ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ደስታን ያመጣልኛል።

  • ልጆቻችሁ በ4 ኔፊ ውስጥ ስለተገለጹት ሰዎች ደስታ እንዲያውቁ ለመርዳት፣ የደስተኛ ሰዎችን ምስሎች ልታሳዩዋቸው ትችላላችሁ። ከዚያም ቁጥር 2–3 እና 15–17 (ወይም “Chapter 48: Peace in America,” የመፅሃፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 136–37)፣ አብራችሁ በታነቡበት ጊዜ በታሪኩ ውስጥ አንድ ደስታን ሊያመጣ ወደሚችል ነገር ስትደርሱ ወደ ሥዕሎቹ ሊጠቁሙ ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁ በ4 ኔፊ 8-16 ውስጥ የተገለጹትን ልምዶች እንዲገነዘቡ ለመርዳት የእነዚህን ምዕራፎች የተወሰኑ ክፍሎች በጨለማ ክፍል ውስጥ እንደገና ለመተረክ ወይም ለማዳመጥ ትችላላችሁ። በልባችን የእግዚአብሄር ፍቅር ቢኖረን ሁኔታው ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ ትወና እንዲተውኑ ጋብዟቸው።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ከሶስት ኔፋውያን ደቀ መዛሙር ጋር ሲነጋገር

Christ with Three Nephite Disciples[ኢየሱስ ከሶስት ኔፋውያን ደቀ መዛሙርት ጋር ፣ በጋሪ አኤል. ካፕ

አትም