ሕዳር 11-17፦ “የአለማመን[ን] መጋረጃ [ቅደ]ዱት።” ኤተር 1–5፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ)
“ህዳር 11–17 (እ.አ.አ)። ኤተር 1–5፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])
ሕዳር 11-17፦ “የአለማመን[ን] መጋረጃ [ቅደ]ዱት።”
ኤተር 1–5
የእግዚአብሔር መንገዶች ከእኛ ከፍ የሚሉ መሆናቸው እና ሁልጊዜ ለፈቃዱ መገዛት ያለብን መሆኑ እውነት ቢሆንም በራሳችን እንድናስብ እና በራሳችን እንድንሠራም ያበረታታናል። ያ ያሬድ እና ወንድሙ የተማሩት አንድ ትምህርት ነው። ለምሳሌ፣ “ከምድሪቱ ሁሉ በላይ ወደ ተመረጠችው” አዲስ ምድር የመጓዝ ሃሳብ በያሬድ የጀመረ ይመስላል፣ ጌታም “ይህንንም አደርግልሃለሁ ምክንያቱም ለነዚህ ለረጅም ጊዜያት ወደ እኔ ስለ ጮህክ” በማለት የያሬድን ወንድም ጥያቄው ተቀበለ( ኤተር 1:38–43ይመልከቱ)። እንዲሁም የያሬድ ወንድም ወደ ተስፋ ምድራቸው በሚወስዳቸው ጀልባ ውስጥ ብርሃን አስፈልጎት በነበረ ጊዜ ጌታ እኛ ብዙ ጊዜ እርሱን የምንጠይቀውን ጥያቄ ጠየቀው፦ ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ? (ኤተር 2፥23)። ሀሳባችንን እና እቅዳችንን መስማት ይፈልጋል፤ ስለዚህም ያዳምጠናል ከዚያም ማረጋገጫ ይሰጠናል ወይም ሀሳባችንን እና እቅዳችንን እንዳናደርግ ይመክረናል። አንዳንድ ጊዜ ከምንፈልገው በረከቶች የሚለየን ብቸኛው ነገር የራሳችን “ያለማመን መጋረጃ” ነው እናም “[ያንን መጋረጃ መቅደድ]” (ኤተር 4:15) ከቻልን ጌታ ለእኛ ሊያደርግልን ፈቃደኛ በሆነው ነገር ልንደነቅ እንችላለን።
በተጨማሪም “The Lord Appears to the Brother of Jared” (ቪዲዮ)፣ በወንጌል ቤተመፃሕፍት ይመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ወደ ጌታ ስጮህ ርህራሄ ያሳየኛል።
ኤተር 1:33–43 ስለያሬድ ሶስት ፀሎቶች ይናገራል። ጌታ ለእያንዳንዱ ፀሎቶች ከሰጠው ምላሽ ምን ትማራላችሁ? በጸሎት ወደ እርሱ በጮሃችሁ ጊዜ የጌታ ርህራሄ የተሠማችሁ መቼ እንደነበር አስቡ። ይህን ተሞክሮ ለመመዝገብ እና ምስክርነታችሁን ለመስማት ለሚፈልግ ሰው ለማካፈል ትፈልጉ ይሆናል።
በተጨማሪም “Secret Prayer,” መዝሙር፣ ቁጥር. 144።
ለህይወቴ የሚሆን መገለጥን መቀበል እችላለሁ።
ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፣ “ራዕይን ለመቀበል መንፈሳዊ አቅማችሁን እንድታሳድጉ እማፀናችኋለሁ።… በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ለመደሰት እና የመንፈስን ድምጽ ይበልጥ በተደጋጋሚ እና ይበልጥ በጥራት ለመስማት አስፈላጊ የሆነውን መንፈሳዊ ስራ መስራትን ምረጡ (“ራእይ ለቤተክርስቲያን፣ ራእይ ለህይወታችን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 96)።
ኤተር 2፤ 3:1–6፤ 4:7–15 ስታነቡ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ስለተናገሩት “መንፈሳዊ ስራ” ምን ትማራላችሁ? የያሬድ ወንድም የነበሩትን ጥያቄዎች ወይም ሥጋቶች እና እነሱን በተመለከተ ያደረጋቸውን ነገሮች በአንድ ቀለም ጌታ እንዴት እንደረዳው እና ፈቃዱን እንዳሳወቀ ደግሞ በሌላ ቀለም ምልክት ማድረግ ትችላላችሁ።
በምታጠኑበት ጊዜ ልታሰላስሉ የምትችሉባቸው አንዳንድ ጥያቂዎች እነሆ፦
-
በኤተር 2:18–25 ውስጥ ጌታ የያሬድን ወንድም ጥያቄዎች ስለመለሰበት መንገድ ምን ያስደነቃችኋል? ?
-
ፀሎት እንዴት እንደሚቀርብ እየተማረ ያለን ሰው ለመርዳት ኤተር 3:1–5ን ልትጠቀሙ የምትችሉት እንዴት ነው?
-
ከጌታ ራዕይን ከመቀበል ሊያግዳችሁ የሚችለው ምንድን ነው? (ኤተር 4:8–10 ይመልከቱ)። ከእርሱ ራዕይን ይበልጥ በተደጋጋሚ መቀበል የምትችሉት እንዴት ነው? (ኤተር 4:7, 11–15 ይመልከቱ)።
-
በህይወታችሁ ያለውን “ያለማመን መጋረጃ [መቅደድ] ”ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? (ኤተር 4:15ን ይመልከቱ)።
ከያሬድ ወንድም ስለግል ራዕይ ሌላ ምን ነገር ትማራላችሁ?
ሽማግሌ ዴል ጂ. ረንላንድ፤ ስለ “A Framework for Personal Revelation፣” (ሊያሆና፣ ሕዳር 2022 (እ.አ.አ) 16-19 ይመልከቱ) አስተማሩ። የፎቶ ፍሬም መሳልን እና በእያንዳንዱ ጎን የማዕቀፉን አራት አካላት መፃፍን አስቡ። ይህ ማዕቀፍ “ራዕይን የመቀበል አቅማችሁንን ለማሳደግ” የሚረዳችሁ እንዴት ነው?
በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች “Personal Revelation፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ይመልከቱ።
በተግሣፁ አማካኝነት ጌታ ንስሐ እንድገባ እና ወደ እርሱ እንድመጣ ይጋብዘኛል።
እንደ ያሬድ ወንድም ያለ ታላቅ ነቢይም እንኳን ከጌታ ተግፃፅ አስፈልጎት ነበር። ስለ ጌታ ተግሳፅ ከኤተር 12:-15–6 ምን ትማራላችሁ? የጌታ ተግሳጽ እና የያሬድ ወንድም ምላሽ በኤተር 3:1–20 ውስጥ ላሉት ልምዶቹ እንዴት እንዲዘጋጅ ረድተውት እንደነበር አስቡ።
ጌታ የእኔን “ታላቅ ውሃ” እንዳቋርጥ ያዘጋጀኛል።
አንዳንድ ጊዜ “ታላቅ ውሃን” ማቋረጥ የእግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ፈቃድ ለመፈፀም ብቸኛው መንገድ ነው። በኤተር 2:16–25 ውስጥ ከህይወታችሁ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነገር ታያላችሁ? ጌታ ለፈተናዎቻችሁ ያዘጋጃችሁ እንዴት ነው? ወደፊት እንድታደርጉት ለሚፈልገው ነገር እንድትዘጋጁ አሁን ምን እንድታደርጉ እየጠየቃችሁ ነው?
በተጨማሪም ኤል. ቶድ በጅ፣ “ቀጣይ እና ጽኑ እምነት፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 47–49 ተመልከቱ።
ምስክሮች ስለ መፅሐፈ ሞርሞን እውነተኛነት ይመሰክራሉ።
በኤተር 5 ውስጥ ያለውን የሞሮኒ ትንቢት ስታነቡ ጌታ ብዙ የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮችን ስላዘጋጀበት አላማ አሰላስሉ። መፅሐፈ ሞርሞን የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እንድታምኑ ያነሳሷችሁ የትኞቹ ምስክሮች ናቸው? መፅሐፈ ሞርሞን “የእግዚአብሔርን እና የቃሉን ኃይል” ያሳያችሁ እንዴት ነው? (ኤተር 5፡4)
ልጆችን ለማስተማር የኒረዱ ሀሳቦች
የሰማይ አባት ጸሎቴን ይሰማል እንዲሁም ይመልሳል።
-
ልጆቻችሁ የማችሉት እናንተ የምትችሉት ቋንቋ ካለ በዚያ ቋንቋ አንዳንድ ቅላል ተዕዛዞችን ስጧቸው (ወይም የሌላ ቋንቋ ቅጂን አጫውቱ)። በኤተር 1:33–37ውስጥ የያሬድ ወንድም እርዳታ ለማግኘት የጸለየበትን ምክንያት ለማስረዳት ይህን መጠቀም ትችላላችሁ። ጌታ ስለዚህ ጸሎት ምን እንደተሰማው እንዲሁም እንዴት ምላሽ እንደሰጠ አፅንዖት ስጡ (በተጨማሪም “Chapter 50: The Jaredites Leave Babel,” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፤ 143–44 ይመልከቱ)።
-
እናንተ አኤተር 2:16–17ን በምታነቡበት ጊዜ ልጆቻችሁ ጀልባ እንደሚሰሩ ሊያስመስሉ ይችላሉ። ከዚያም እናንተ እና ልጆቻችሁ የያሬዳውያን ጀልባዎች ስለነበሩባቸው ችግሮች (ኤተር 2:19 ይመልከቱ) እንዲሁም ጌታ የያሬድን ወንድም ጸሎት ስለመለሰባቸው የተለያዩ መንገዶች ማንበብ ትችላላችሁ ( ኤተር 2:19–25፤ 3:1–6 ይመልከቱ)። በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ያሉ ምስሎች እና አክቲቪቲዎች እናንተ እና ልጆቻችሁ ታሪኩን እንድትናገሩ ሊረዷችሁ ይችላሉ። ከያሬድ ወንድም ስለፀሎት ምን ነገር እንማራለን? እርዳታ ለማግኘት የጸለያችሁበትን እንዲሁም የሰማይ አባት እናንተን የረዳበትን አንድ ተሞክሮ ማካፈልን አስቡ።
በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥሬአለሁ።
-
ልጆቻችሁ እያደጉ ሲሄዱ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለራሳቸው እና ስለ አካላቸው ብዙ የተሳሳቱ መልእክቶችን ያገኛሉ። በኤተር 3:6–16ውስጥ ስለ እነዚህ ርዕሶች እውነቶችን እንድታገኙ እንዲረዷችሁ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። በኤተር 3:13፣ 15 በተሰጠው ትምህርት ውስጥ ያለውን እውነት ለማጉላት፣ የአዳኙን ምስል አንድ ላይ መመልከት እና ልጆቻችሁ ወደ ተለያዩ የአካሉ ክፍሎች እንዲጠቁሙ መጋበዝ ትችላላችሁ። ከዚያም ወደራሳቸው ተመሳሳይ የአካላቸው ክፍል ሊያመለክቱ ይችላሉ። ከአካላችን ጋር የተያያዘ እንደ “The Lord Gave Me a Temple” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ -153) ያለ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ። እናንተ እና ልጆቻችሁ ስለአካሎቻችሁ ለምን አመስጋኝ እንደሆናችሁ ለመናገርም ትችላላችሁ።
ሶስት ምስክሮች ስለመፅሐፈ ሞርሞን መስክረዋል፡፡
-
ሦስቱ ምስክሮች የመፅሐፈ ሞርሞንን እውነተኝነት ለመመስረት እንደሚረዱ ሞሮኒ ተንብዮ ነበር። ስለምስክር ምንነት ለማስተማር ልጆቻችሁ ያዩትን ወይም ያጋጠማቸውን ሆኖም ሌሎች ያላዩትን ነገር እንዲገልጹ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ኤተር 5ን አንድ ላይ በምታነቡበት ጊዜ እግዚአብሄር በስራዎቹ ምስክሮችን ለምን እንደሚጠቅም ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። መፅሐፈ ሞርሞን እውነት መሆኑን እንዴት እንዳወቃችሁ እንዲሁም ምስክርነታችሁን ለሌሎች እንዴት ማካፈል እንደምትችሉ አንዳችሁ ለሌላችሁ ማካፈል ትችላላችሁ።