ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሕዳር 18–24፦ “ክፉ ነገርም ይወገድ ዘንድ።” ኤተር 6–11


“ሕዳር 18–24፦ “ክፉ ነገርም ይወገድ ዘንድ።” ኤተር 6-11፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

“ሕዳር 18–24። ኤተር 6-11፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

የያሬዳውያን ጀልባ በባህር ላይ

I Will Bring You Up Again out of the Depths[በድጋሚ ከባህሩ ውስጥ አወጣችኋለሁ፣ በጆናታን አርተር ክላርክ

ሕዳር 18–24፦ “ክፉ ነገርም ይወገድ ዘንድ።”

ኤተር 6–11

ያሬዳውያን ከተደመሰሱ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በኋላ ኔፋውያን የጥንት ሥልጣኔያቸውን ፍርስራሽ አገኙ። ከእነዚህ ፍርስራሾች ውስጥ “በንጹሕ የወርቅ” ሰሌዳዎች ላይ “በፅሁፍ የተሸፈኑ” ሚስጥራዊ መዝገቦች ይገኙበት እናም ኔፋውያን ለማንበብ ያላቸው “ፍላጎታቸው ከልክ በላይ ነበር” (ሞዛያ 8:928:12)። ዛሬ አጥሮ የተዘጋጀው ይህ መዝገብ አላችሁ እሱም የኤተር መፅሃፍ ይባላል። ኔፋውያን እሱን ባነበቡት ጊዜ ስለያሬዳውያን አሳዛኝ ውድቀት በማወቃቸው “በሀዘን ተሞልተው ነበር”። “ይሁን እንጂ ብዙ እውቀትን ሰጥቷቸዋል፣ በእርሱም ተደስተዋል” (ሞዛያ 28:12፣ 18)። እናንተም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አሳዛኝ ጊዜዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ። ነገር ግን በዚህ የእውቀት ሥጦታ ልትደሰቱም ትችላላችሁ። ሞሮኒ እንደፃፈው“ይህን እንድታነቡ በእግዚአብሔር ጥበብ ነው…ክፉ ነገርም ይወገድ ዘንድ፣እናም ሰይጣንም በሰው ልጆች ልብ ላይ ኃይል አያገኝም…” (ኤተር 8:26)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኢተር 6፥1–12

ጌታ በምድራዊ ጎዞዬ ይመራኛል።

ያሬዳውያን በውቅያኖስ ላይ ያደረጉትን ጉዞ ከእናንተ የህይወት ጉዞ ጋር ብታነጻጽሩ መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ። ለምሳሌ በያሬዳውያን ጀልባ ውስጥ እንደነበሩት ድንጋዮች መንገዳችሁን የሚያበራ ጌታ ምን ሰጥቷችኋል? ጀልባዎቹ ወይም “ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር [የ]ሚያመራው ነፋስ ምንን ይወክላሉ? (ኤተር 6፡8)። ከጉዞው በፊት፣ በጉዞው ወቅት እና ከጉዞው በኋላ ስለነበረው የያሬዳውያን ድርጊቶች ምን ትማራላችሁ? ጌታ ወደ ተስፋይቱ ምድር እየመራችሁ ያለው እንዴት እየመራህ ነው?

“ለጌታ የምስጋና መዝሙር ዘምሩ።” ያሬዳውያን ምስጋናቸውን እና ፍቅራቸውን በመዝሙር እና በውዳሲ ገልፀዋል (ኤተር 6:9 ይመልከቱ)። በቤት እና በቤተክርስቲያን ሙዚቃን እና ከልብ የመነጨ ምስክርነትን እግዚአብሔርን ለማወደስ ለመጠቀም እድሎችን ልትፈልጉ ወይም ልትፈጥሩ ትችላላችሁ። ለምሳሌ እንደ “Praise the Lord with Heart and Voice” (መዝሙር፣ ቁጥር 73) ያለውን የውዳሴ መዝሙር ኤተር 6:1–12ን በምታጠኑበት ጊዜ መዘመር ተገቢ ሊሆን ይችላል።

የያሬድ ቤተሰቦች በጀልባቸው ውስጥ

ህፃን በጀልባ ተሳፍሮ በኬንዳል ሬይ ጆንሰን

ኤተር 6:5–18፣ 309:28–3510:1–2

“በጌታ ፊት በትህትና መራመድ።”

ምንም እንኳን ኩራት እና ክፋት በያሬዳውያን ታሪክ ውስጥ በስፋት የሚታዩ ቢመስልም በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ የትህትና ምሳሌዎችም ይገኛሉ—በተለይ በኤተር 6:5–18, 309:28–35፤ እና 10:1–2። በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ማሰላሰላችሁ ከእነዚህ ምሳሌዎች እንድትማሩ ሊረዳችሁ ይችላል። ትህትናቸውን ያሳዩት እንዴት ነው? በውጤቱም እግዚአብሄር የባረካቸው እንዴት ነው? ትሁት እንድትሆኑ ከመገደዳችሁ በፊት በፍላጎታችሁ “በጌታ ፊት በትህትና ለመራመድ” (ኤተር 6:17) ምን ልታደርጉ እንደምትችሉ አስቡ (ሞዛያ 4:11–12አልማ 32:14–18 ይመልከቱ)።

ጌል ጂ.ረንለንድን፣ “Do Justly, Love Mercy, and Walk Humbly with God፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 109–12 ይመልከቱ።

ኤተር 7–11

የሴሚናሪ ምልክት
እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ መሪ መሆን እችላለሁ።

ኤተር ምዕራፍ 7–11 ቢያንስ 28 ትውልዶችን ይሸፍናል። ይህን ያህል ትንሽ በሆነ ቦታ ላይ መስጠት የሚቻለው ትንሽ ዝርዝር ቢሆንም እንኳን የፅድቅ እና የክፋት አመራርን ውጤቶች በተመለከተ አንድ የተለመደ መንገድ በፍጥነት ይከስታል። ከታች ስለተጠቀሱት ነገሥታት አዎንታዊ እና አሉታዊ ምሳሌዎቹ ስለአመራር ምን ትማራላችሁ?

ሽማግሌ ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ “The Greatest among You” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 78–81) መልዕክታቸው ስለ አመራር ጠቃሚ ምክር ለግሰዋል። የክርስቶስ መሰል የአመራር መርሆዎችን እና መንገዶችን እየፈለጋችሁ ይህንን ምክር ማጥናትን አስቡ—በተለይ የሚናገሯቸውን ታሪኮች። እነዚህን መርሆዎች ወይም መንገዶች በህይወታችሁ በመሪዎች ሲተገበሩ ያያችሁት መቼ ነው?

የተማራችሁትን በምታሰላስሉበት ጊዜ በቤታችሁ፣ በማህበረሰባችሁ፣ በቤተክርስቲያን ጥሪያችሁ እና በመሳሰሉት ውስጥ ሌሎችን ለመምራት ወይም በሌሎች ላይ ተፅዕኖ ለማሣረፍ ስላሏችሁ ዕድሎች አስቡ። የተለየ የአመራር የስራ ምደባ የተሰጣችሁ ባይሆንም የክርስቶስን የመሠለ የአመራር ባሕርያት ማዳበር የምትችሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም የወንጌል አርዕስቶች፣ “Serving in Church Callings,” ወንጌል ላይብረሪ “Principles of Leadership in the Church,” አጠቃላይ መመሪያ መፅሃፍ: በኋለኛው ቀን የኢየሱስ ቤተክርስቲያን ማገልገል፣ 4.2 (ChurchofJesusChrist.org)።

ኢተር 8፥7–26

ጌታ በጨለማ አይሰራም።

ሰዎች የክፋት ተግባራቸውን ሚስጥር ለማድረግ ሲያሴሩሚስጥራዊ ውህደት ይፈፅማሉ። በኤተር 8:7–18 ውስጥ ከተገለፀው ሚስጥራዊ ውህደት በተጨማሪ ሌሎች ምሳሌዎች በሄለማን 1:9–122:2–116:16–30ሙሴ 5:29–33 ውስጥ ይገኛሉ። እነዚህን ጥቅሶች ጌታ ስራውን እንዴት እንደሚሰራ ኔፊ ከገለፀባቸው ከ2 ኔፊ 26:22–24 ጋር ማነፃፀርን አስቡ። ሞሮኒ ሚስጥራዊ ውህደቶችን በተመለከተ ያደረገውን ነገር እንዲጽፍ የታዘዘው ለምን ይመስላችኋል?

ከኤተር መጽሐፍ ኤተር 8:26 ውስጥ የተገለጹትን በረከቶች እንድታገኙ የሚረዳችሁ ምን ነገር ተማራችሁ?

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኢተር 6፥1–12

በምፈራበት ጊዜ የሰማይ አባት እንደሚያጽናናኝ ማመን እችላለሁ።

  • ልጆች ሳይቀሩ እያንዳንዱ ሰው አስቸጋሪ ጊዜያት ይገጥመዋል። ምናልባት ልጆቻችሁ በአንዳንድ በጣም አስቸጋሪ እና አስፈሪ ቀናት ያሬዳውያን እንዴት በእግዚአብሔር ታምነው እንደነበረ የሚያሳዩ ቃላትን እና ሀረጎችን በኤተር 6፡1-12 ውስጥ እንዲፈልጉ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። በህይወታችሁ ባጋጠሟችሁ አስቸጋሪ ጊዜያት እግዚአብሔር ረድቷችሁ የነበረበትን አንዳንድ ተሞክሮዎች አንዳችሁ ለአንዳችሁ ማካፈልን አስቡ።

ኤተር 6:9፣ 12፣ 307:2710:2

ጌታ ያደረገውን ማስታወስ አመስጋኝነትን እና ሰላምን ያመጣል።

  • ያሬዳውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር በሰላም ከደረሱ በኋላ አመስጋኝ ከመሆናቸው የተነሳ “የደስታ እንባቸውን አፈሰሱ” (ኤተር 6:12)። ያሬዳውያን ምስጋናቸውን ለእግዚአብሔር እንዴት እንደገለጹ የሚያሳዩ ሐረጎችን ከኤተር 6:9፣ 12 ውስጥ እንዲፈልጉ ልጆቻችሁን በመርዳት እግዚአብሔር ለሚሰጣቸው በረከቶች አመስጋኝ እንዲሆኑ ልታነሳሷቸው ትችላላችሁ። ያሬዳውያን እንዳደረጉት ስለምስጋና የሚገልፅ እንደ “My Heavenly Father Loves Me” (የልጆች የመዝሙር መፅሃፍ 195) ያለ መዝሙር መዘመር ሊያስደስታቸው ይችላል። አመስጋኝ ስለሆኑባቸው አንዳንድ ነገሮች እንዲነግሯችሁ ልጆቻችሁን ጠይቋቸው።

  • ምናልባት ልጆቻችሁ ኤተር 6:307:27፤ እና 10:2 ሊያነቡ እና እነዚህ ፃድቅ ነገስታት ምን እንዳስታወሱሊፈልጉ ይችላሉ። ሕዝባቸውን በመሩበትን መንገድ ላይ ተፅዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው? እናንተ እና ልጆቻችሁ አምላክ ያደረገላችሁን ነገር ለራሳችሁ ማስታወስ ስለምትችሉበት መንገድ ልትወያዩ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ ምናልባት ስለሱ ሊፅፉ ወይም ሥዕል ሊስሉ ይችላሉ። ከእግዚአብሄር ሲመጡ ስላተዋሏቸው በረከቶች የመጻፍ ልምድ እንዲያዳብሩ ሃሳብ ልታቀርቡ ትችላላችሁ ( “O Remember, Remember” [ቪዲዮ]፣ ወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ)።

ኤተር 7፥24–27

የእግዚአብሄርን ነቢይ ስከተል እባረካለሁ።

  • ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ ነቢዩ እንድናደርጋቸው ያስተማሩንን አንዳንድ ነገሮች ማድረግ ያስደስታችሁ ይሆናል። ድርጊቶቹ ምን እንደሚወክሉ ወደምትገምቱበት ጨዋታ ልትለውጡትም ትችላላችሁ። ይህ ልጆቻችሁ ነቢዩን መከተል ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ለመወያየት ሊያዘጋጃቸው ይችላል። ከዚያም ኤተር 7:24–27ን ልታነቡና ሕዝቡ የእግዚአብሄርን ነቢይ ባከበሩ ጊዜ ምን እንደተከሰተ እወቁ። ዛሬ ነቢዩን በመከተላችን የምንባረከው እንዴት ነው?

ኤተር 9:28–3511:5–8

ጌታ ንስሐ ስገባ ይቅር ባይ ነው።

  • ተመሳሳይ መንገዶችን መፈለግ ጠቃሚ የቅዱሳት ፅሁፎች ጥናት ክህሎት ነው። የኤተር መፅሐፍ የጌታን ምህረት የሚያጎላ ተደጋጋሚ የተለመደ መንገድ ይዟል። ልጆቻችሁ ይህንን የተለመደ መንገድ እንዲያገኙ ለመርዳት በሁለቱ ዘገባዎች መካከል ያለውን ተመሳሳይነት እየፈለጉ ኤተር 9:28–35 እና ኤተር 11:5–8፣ እንዲያነቡ ጋብዟቸው። ከእነዚህ ታሪኮች ምን እንማራለን? ምናልባት በየወንጌል የአርት መፅሐፍ ውስጥ በቅዱሳት መፃሕፍት ውስጥ ያሉ ንሥሐ የገቡ እና ይቅር የተባሉ የሌሎች ሰዎችን ሥዕሎች ሊፈልጉ ይችላሉ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

የያሬዳውያን ጀልባዎች በባህር ላይ

Jaredite Barges [የያሬዳውያን ጀልባ፣ በጋሪ ኤርነስት ስሚዝ