ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሕዳር 25–ታሕሳስ 1፦“በእምነት ሁሉም ነገሮች ለመሟላት ይችላሉ።” ኤተር 12–15


“ሕዳር 25–ታሕሳስ 1፦“በእምነት ሁሉም ነገሮች ለመሟላት ይችላሉ።” ኤተር 12-15፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

“ህዳር 25–ታህሳስ 1 ኤተር 12-15፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

ኤተር ወደ ዋሻ ውስጥ እየገባ

Ether Hiding in the Cavity of a Rock [ኤተር በድንጋይ ዋሻ ውስጥ ተደብቆ፣ በጌሪ ኧርነስት ስሚዝ

ሕዳር 25–ታሕሳስ 1፦“በእምነት ሁሉም ነገሮች ለመሟላት ይችላሉ።”

ኤተር 12–15

ኤተር ለያሬዳውያን የተነበያቸው “ታላቅ እና አስገራሚ” ነገሮች ነበሩ (ኤተር 12:5)። እርሱ “ሰው ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ሁሉንም ነገሮች በእውነት ነግሮአቸዋል” (ኤተር 13:2)። እርሱ “የክርስቶስን ቀናት” እና አዲሲቷን ኢየሩሳሌም አስቀድሞ ተመልክቷል (ኤተር 13:4)። እንዲሁም “[ስ]ለተሻለ ዓለም፣ አዎን፣ በእግዚአብሄር ቀኝ እጅ በኩል [ስላለው] ስፍራ እንኳን” ተናግሯል (ኤተር 12:4)። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በዛሬው ጊዜ ያሉትን የአምላክ አገልጋዮች ትንቢቶች በማይቀበሉበት ተመሳሳይ ምክንያት ያሬዳውያን ቃሉን አልተቀበሉም —[ምክንያቱም] “ [ስላላዩዋቸው] አላመኑባቸውም” ነበር (ኤተር 12:5)። ልክ ኤተር ለማያምኑ ሰዎች ስለ “ታላቅ እና አስገራሚ” ነገሮች ትንቢት ለመናደር እምነት እንደጠየቀበት ሁሉ ስለማናያቸው ነገሮች የሚሰጡ ተስፋዎችን እና ማስጠንቀቂያዎችን አምኖ ለመቀበልም እምነት ይጠይቃል። ሞሮኒ “በመፃፍ ያለበትን ድክመት” ጌታ ወደ ጥንካሬ ሊውጥ እንደሚችል አምኖ ለምቀበል እምነት ጠይቆበታል (ኤተር 12:23–27 ይመልከቱ)። እንዲህ ዓይነቱ እምነት ነው“ፅኑ እና የማ[ንነቃነቅ] እን[ድንሆን] እናም ሁልጊዜም በርካታ መልካም ነገሮችን እን[ድንሰራ] እግዚአብሄርንም እንድ[ናከብር]” የሚያደርገን (ኤተር 12:4)። በእንደዚህ ዓይነት እምነት ነው “ሁሉም ነገሮች [የሚሟሉት]” (ኤተር 12:3)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኤተር 12

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለ እምነት ወደ ተዓምር ሊያመራ ይችላል።

በኤተር ዘመን እነደነበረው ሁሉ ዛሬም ሰዎች በእግዚአብሔር እና በኃይሉ ከማመናቸው በፊት ማስረጃ ለማየት መፈለጋቸው የተለመደ ነው። ከኤተር 12:5–6 ምን ትማራላችሁ?

ኤተር 12ን በምታነቡበት ጊዜ “እምነት” የሚለውን ቃለ በምታገኙበት በእያንዳንዱ ጊዜ ማስታወሻ ልትይዙ ትችላላችሁ። ቃሉን በምታገኙበት በእያንዳንዱ ጊዜ ምን እንደሚያስተምራችሁ አስቡ። እንደእነዚህ ያሉ ጥያቄዎች ሊረዱ ይችላሉ፦“እምነት” ምንድን ነው? እምነትን መለማመድ ማለት ምን ማለት ነው? በኢየሱስ ክርስቶስ የማመን ፍሬዎች ምንድን ናቸው? “እምነታችሁ እስከሚፈተን ድረስ” ቆይታችሁ ስላገኛችሁት ምስክርነት ሃሳባችሁን ልትመዘግቡም ትችላላችሁ (ኤተር 12:6)።

ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “ክርስቶስ ተነስቷል፤ በእርሱ ማመንም ተራራን ያነቃንቃል፣፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 101-4 ይመልከቱ።

ሌሎች እንዲያካፍሉ እንዲሁም እንዲያስተምሩ ፍቀዱላቸው። ሰዎች እየተማሩት ስላለው ነገር ለማካፈል እድሎች ሲያገኙ ወይም በመደበኛ ሁኔታ ሲያስተምሩ በተሻለ ሁኔታ ይማራሉ። በቤትም ሆነ በቤተክርስቲያን ወጣቶችን ጨምሮ ሌሎች የአንድን ትምህርት ክፍል እንዲያስተምሩ መፍቀድን አስቡ።

ኤተር 12፥1-9፣ 28፣ 32

ኢየሱስ ክርስቶስ “የላቀ ተስፋ ይሰጠኛል።”

ኤተር 12 ስለ እምነት ከሚሰጠው ጥልቅ ግንዛቤ በተጨማሪ ስለተስፋ ብዙ ይናገራል። እነዚህ ጥያቄዎች ጥናታችሁን እንዲመሩ ፍቀዱ።

  • ኤተር “ ለተሻለ ዓለም ተስፋ ያደረገበት” ምክንያቶች ምንድን ነበሩ? (ኤተር 12:2–5 ይመልከቱ)።

  • የመልህቅ ጥቅም ምንድን ነው? መልህቅ ለጀልባ እንደሚያደርገው ያለ ተስፋ ለነፍስህ ምን ተመሳሳይነት ነገር ያደርጋል? (ኤተር 12:4 ይመልከቱ)።

  • ምን ተስፋ እናድርግ? (ኤተር 12:4ሞሮኒ 7:41 ይመልከቱ)።

  • የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል “የላቀ ተስፋ” የሰጣችሁ እንዴት ነው? (ኤተር 12:32)

በተጨማሪም ሞሮኒ 7:40–41፤ ጄፍሪ አር. ሆላንድ “A Perfect Brightness of Hope፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 81-84 ይመልከቱ።

ኤተር 12:23–29

የሴሚናሪ ምልክት
ኢየሱስ ክርስቶስ ድክመትን ወደ ጥንካሬ መቀየር ይችላል።

የሞሮኒን ኃይለኛ ጽሑፎች በምናነብበት ጊዜ “በጽሑፉ ደካማነት” መጨነቁን እና ሰዎች በቃላቱ እንዳይሳለቁበት መፍራቱን መርሳት ቀላል ነው ( ኤተር 12:23–25)። በራሳችሁ ድክመቶች ተጨንቃችሁ የምታውቁ ከሆነ ስለሞሮኒ ፈተናዎች—እና ስለአዳኙ ምላሽ በኤተር 12:23–29 ውስጥ አንብቡ። ኢየሱስ ክርስቶስ ድክመታችሁን እንድታውቁ የረዳበትን እንዲሁም ምንም እንኳን ሙሉ በሙሉ ባያስወግደውም ጠንካራ እንድትሆኑ ያደረገበትን ጊዜ ልታስቡም ትችላላችሁ። በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ እየታገላችሁት ስላላችሁት ድካምም አስቡ። “ደካማ የሆኑትን ለእነርሱ ጠንካራ እንዲሆኑ አደርጋለሁ” የሚለውን ተስፋ ለመቀበል ምን ማድረግ ያስፈልጋችኋል?። (ኤተር 12፥27)።

ሌሎች እንዴት በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ አማካኝነትብርታት እንዳገኙ ለማየት በሚከተሉትት ምንባቦች ውስጥ መፈለግን አስቡ።

በተጨማሪም የወንጌል አርስቶች፣ “Grace,” ወንጌል ላይብረሪ፤ “The Lord Is My Light,” መዝሙር፣ ቁጥር 89።

ኤተር 13:13–2214–15

የጌታን ነቢያት አለመቀበል ወደ መንፈሳዊ አደጋ ይከተኛል።

የያሬዳውያን ንጉስ መሆን በታሪክ አደገኛ ሥልጣን ነበር። ብዙ “ኃያላን የሆኑ ሰዎች …ሊገድሉት ስለፈለጉ” ይህ በተለይ ለቆሪያንተመር እውነት ነበር(ኤተር 13:15–16)። በኤተር 13:15–22፣ ውስጥ ቆሪያንተመር እራሱን ለመከላከል ምን እንዳደረገ እና በምትኩ ነቢዩ ኤተር ምን እንዲያደርግ እንደመከረው አስተውሉ። ቀሪውን የኤተር መፅሃፍ በምታነቡበት ጊዜ ነቢያትን ያለመቀበል ውጤቶችን አሰላስሉ። “የጌታ መንፈስ ከእነርሱ ጋር መሆኑን [ሲያቆም]“ ሰዎች ምን ይሆናሉ? (ኤተር 15:19)። ከእነዚህ ዘገባዎች ጌታ ምን እንድትማሩ ሊፈልግ ይችላል? የእርሱን ነቢያት ለመከተል ምን እንደምታደርጉ አስቡ?

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ኢተር 12:6–22

እምነት በማላያቸው ነገሮች ማመን ነው።

  • “እምነት ተስፋ የምናደርጋቸው ነገሮች ነገር ግን የማናያቸው [ናቸው]” የሚለውን ከናንተ ጋር ደግመው እንዲሉ መርዳትን አስቡ (ኤተር 12:6)። የእምነት ምሳሌዎችን የሚያሳዩ ሥዕሎችን በኤተር 12:13–15፣ 19–21 መመልከት ያስደስታቸው ይሆናል (Gospel Art Book፣ ቁጥር 7885፣ እና የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገፅ ይመልከቱ) ልጆቻችሁ ሰለእያንዳንዱ ታሪክ እንዲያብራሩ ፍቀዱ። እነዚህን የእምነት ምሳሌዎች ለመወያየት እንዲረዳችሁ አንዳንድ ጥያቄዎች እነሆ፦

    • እነዚህ ሰዎች ምን ተስፋ አደረጉ?

    • እምነታቸው የተፈተነው በምን ነበር?

    • በእምነታቸው ምክንያትስ ምን ሆነ?

    የራሳችሁን እምነትን የመለማመድ ተሞክሮዎች ልታካፍሉም ትችላላችሁ፡፡

ኤተር 12፥4፣ 32

ተስፋ ለነፍሴ እንደ መልህቅ ነው፡፡

  • ኤተር 12፥4 ስለ ተስፋ ምን እንደሚያስተምር ለመረዳት እናንተ እና ልጆቻችሁ የጀልባ እና የመልህቅ ሥዕል ማየት ትችላላችሁ። ጀልባ መልህቅ የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? መልህቅ የሌለው ጀልባ ምን ይሆናል? ኤተር 12:4ን አንድ ላይ በምታነቡበት ጊዜ መልህቅ ጀልባን እንደሚረዳ ተስፋ እንዴት እንደሚረዳን ተነጋገሩ። ልጆቻችሁ ሌሎችን ስለተስፋ ማስተማር ይችሉ ዘንድ የጀልባ እና የመልህቅ ምስሎችን እንዲስሉ ጋብዟቸው።

  • ልጆቻችሁ ተስፋ ለሚለው ቃል ትርጓሜ የሚፈልጉ ከሆነ በቅዱሳን ጸሁፎች መመሪያ ውስጥ “ተስፋ” (ወንጌል ላይብረሪ) የሚለውን ቃል እንዲያገኙ እርዷቸው። በዚህ ትርጓሜ እና በኤተር 12:4፣ 32፣ መሰረት ምን ተስፋ እናድርግ? (በተጨማሪም ሞሮኒ 7:40–42 ይመልከቱ)። ልጆቻችሁ ከተስፋ ተቃራኒ ቃላት ጋር ለተስፋ ሌሎች ቃላትን እንዲያስቡ እርዷቸው። ተስፋ የሚሰጧችሁን አንዳንድ የወንጌል እውነታዎች አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታጋሩም ትችላላችሁ።

ኤተር 12:23–29

ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈሳዊ ጠንካራ እንድሆን ሊረዳኝ ይችላል።

  • ሞሮኒ ተሰምቶት እንደነበረው፣ አንዳንድ ጊዜ ልጆች ደካማ እንደሆኑ እንዲሰማቸው የሚያደርጉ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል። በኤተር 12:23–25፣ ውስጥ ሞሮኒ ለምን እንደዚህ እንደተሰማው እንዲፈልጉ እና ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ስሜቶች ተሰምቷቸው ያውቅ እንደሆነ ጠይቋቸው። ከዚያም ጌታ ሞሮኒን እንዴት እንደረዳው ለመፈለግ በቁጥር 26–27 ውስጥ እንዲያነቡ ጋብዟቸው።

  • ምናልባት ልጆቻችሁ ደካማ የሆነ ነገርን እና ጠንካራ የሆነ ነገርን ምስል ሊስሉ ይችላሉ። ከዚያም አዳኙ ድካማችንን እንዴት ወደ ጥንካሬ እንደሚለውጥ የሚያስተምሩ ከኤተር 12:23–29 ውስጥ የተወሰዱ አንዳንድ ቃላትን እና ሀረጎችን በሥዕላቸው ውስጥ ሊጨምሩ ይችላሉ። ልጆቻቸሁ ስላለባቸው አንድ ድካም እንዲያስቡ ከዚያም ጥንካሬ ለማግኘት የአዳኙን እርዳታ እንዲሹ አበረታቷቸው። አዳኙ አንድን ከባድ ነገር ለመስራት ጥንካሬ እንድታገኙ ስለረዳችሁ ጊዜ ያላችሁን ተሞክሮ ማካፈልም ትችላላችሁ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ኤተር በዋሻ መግቢያ ላይ ተንበርክኮ

Marvelous Were the Prophecies of Ether [የኤተር ትንቢቶች አስደናቂ ነበሩ፣ በዋልተር ሬን