ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 2፟–8፦“እነርሱን በትክክለኛው መንገድ ለማቆየት።” ሞሮኒ 1–6


“ታህሳስ 2፟–8፦‘እነርሱን በትክክለኛው መንገድ ለማቆየት።’ ሞሮኒ 1-6፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

“ታህሳስ 2–8። ሞሮኒ1–6 ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

አልማ በሞርሞን ውሀዎች ሰዎችን ሲያጠምቅ

ሚነርቫ ቴከርት (1888–1976 እ.አ.አ)፣ Alma Baptizes in the Waters of Mormon[አልማ በሞርሞን ውሀዎች ሲያጠምቅ፣ 1949–1951እ.አ.አ)፣ oil on masonite፣ 35 7/8 × 48 ኢንች። ብሪግም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የአርት ሙዚየም 1969 (እ.አ.አ)።

ታህሳስ 2፟–8፦“እነርሱን በትክክለኛው መንገድ ለማቆየት።”

ሞሮኒ 1–6

ሞሮኒ አባቱ የፃፈውን የኔፋውያንን መዝገብ ከጨረሰ እንዲሁም የያሬዳውያንን ሰዎች ታሪክ አሳጥሮ ከፃፈ በኋላ ታሪክ የመመዝገብ ስራው እንደተጠናቀቀ አስቦ ነበረ ( ሞሮኒ 1:1 ይመልከቱ)። ሊነገር በማይችል ደረጃ ስለተጠፉት ሁለት ሃገሮች ከዚህ በላይ ምን ሊባል ይችላል? ነገር ግን ሞሮኒ የእኛን ጊዜ አስቀድሞ አይቶ ነበረ (ሞርሞን 8:35 ይመልከቱ)፣ እንዲሁም “አንድ ቀን …ይጠቅ[ሙ] ዘንድ ከዚህ የበለጠ ጥቂት ነገሮችን ለመፃፍ” ተነሳስቶ ነበር (ሞሮኒ 1:4)። ከክህነት ሥርዓቶች እና ከአጠቃላይ የሃይማኖት ግራ መጋባት ጋር ክህደት እየተስፋፋ እየመጣ እንደነበረ አውቆ ነበር። ስለ ቅዱስ ቁርባን፣ ስለጥምቀት፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስለመስጠት እንዲሁም ከሌሎች አማኞች ጋር የመሰብሰብን በረከቶች አስመልክቶ ዝርዝር ማብራሪያ የሰጠው “[አንዳቸው ሌላውን] በትክክለኛው መንገድ [እንዲያቆዩ]፣ የእምነታቸው ደራሲ እና ፈፃሚ በሆነው በክርስቶስ … ላይ ብቻ [እንዲደገፉ]” ሊሆን ይችላል (ሞሮኒ 6:4)። እንደነዚህ ያሉ ውድ ግንዛቤዎች “ከዚህ የበለጠ [ይ]ፅፍ [ዘንድ]” ጌታ የሞሮኒን ህይወት ስላቆየልን አመስጋኝ እንድንሆን ምክንያት ይሆኑናል (ሞሮኒ 1:4)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሞሮኒ 1

በተቃውሞ ውስጥ ብሆንም ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል እችላለሁ።

ሞሮኒ 1 ስታነቡ ሞሮኒ ለጌታ እና ለጥሪው የነበረውን ታማኝነት በተመከከተ ምን ያነሳሳችኋል? አንድ ግለሰብ “ክርስቶስን ሊክድ” የሚችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ምን ናቸው? (ሞሮኒ 1፥2–3)። ፈተናዎች እና ተቃውሞዎች በሚያጋጥሟችሁ ጊዜም እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ መሆን የምትችሉት እንዴት እንደሆነ አሰላስሉ።

ሞሮኒ 2–6

የክህነት ሥርዓቶች ጌታ ባዘዘው መሰረት መከናወን አለባቸው።

እነዚህን ምዕራፎች እየጻፈ በነበረበትን ጊዜ ሞሮኒ ህይወቱን ለማዳን በመሸሽ ላይ ነበር። ሥርዓቶች እንዴት መከናወን እንዳለባቸው የሚናገሩ ዝርዝር አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ለመጻፍ ለምን አስፈለገው? ሞሮኒ 2–6ን ስታነቡ ይህንን አስቡ። እነዚህ ዝርዝሮች ለጌታ አስፈላጊ የሆኑት ለምን ይመስላችኋል? ጥናታችሁን ሊመሩላችሁ የሚችሉ አንዳንድ ጥያቄዎች እነሆ፦

ማረጋገጫ መስጠት (ሞሮኒ 26:4)።ማቴዎስ 14፥152 ውስጥ ያሉት የጌታ መመሪያዎች ስለማረጋገጫ አሰጣጥ ሥርዓት ምን ያስተምሩናል? “የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በላያቸው ላይ [የመስራትን] እናም [የማንጻትን]” ምንነትን እንዴት ታብራራላችሁ? (ሞሮኒ 6፥4)።

የክህነት ሹመት (ሞሮኒ 3)።በዚህ ምዕራፍ ውስጥ አንድን ሰው በክህነት ለመሾም እንዲዘጋጅ የሚረዳው ምን ነገር ታገኛላችሁ? አንድ ሰው ሥርዓትን ለማከናወን እንዲዘጋጅ የሚረዳው ምን ነገር ታገኛላችሁ?

ቅዱስ ቁርባን (ሞሮኒ4–56:6)።ቅዱስ ቁርባንን የሳምንታችሁ ጉልህ መንፈሳዊ ክንውን ለማድረግ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ጥምቀት ሞሮኒ 6፥1–3ለመጠመቅ ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶችን በማሟላት ለመቀጠል ምን እያደረጋችሁ ነው?

ወጣት ሴት በረከት ስትቀበል

ኢየሱስ ሥርዓቶች እንዴት መከናወን እንዳለባቸው አስተምሯል።

በተማራችሁት መሠረት ስለእነዚህ ሥርዓቶች የምታስቡበትን፣ በእነዚህ ሥርዓቶች ውስጥ የምትሳተፉበትን ወይም ሌሎችን ለእነዚህ ሥርዓቶች የምታዘጋጁበትን መንገድ የምትቀይሩት እንዴት ነው?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥20 ይመልከቱ።

ትወና እየተማራችሁያላችሁትን ነገር የማስታወስ አንዱ ትልቅ መንገድ ለሌሎች ማስረዳት ነው። ለምሳሌ፣ እንደዚህ ያሉ ሁኔታዎችን አስመስሎ መተወንን ሞክሩ፦አንድ ጓደኛችሁ ለመጠመቅ ብቁ ስለመሆኗ እርግጠኛ አይደለችም። እርሷን ለመርዳት ሞሮኒ 6 የምትጠቀሙት እንዴት ነው?

ሞሮኒ 4–5

ከቅዱስ ቁርባን መካፈል ወደአኢየሱስ ክርስቶስ እንድቀርብ ይረዳኛል።

የቅዱስ ቁርባን ጸሎቶችን ብዙ ጊዜ ሰምታችሁ ይሆን ይሆናል፣ ነገር ግን ስለ ቃላቱ ትርጉም ምን ያህል ደጋግማችሁ በትኩረት ታስባላችሁ? ምናልባት ሁለቱን የቅዱስ ቁርባን ጸሎቶች በቃላችህ ለመጻፍ መሞከር ትችላላችሁ። ከዚያም የፃፋችሁትን ከሞሮኒ 4:3 እና 5:2 ጋር አነፃፅሩ። ከዚህ በፊት ያላስተዋላችሁት እነዚህን ጸሎቶች የተመለከተ ምን ነገር አስተዋላችሁ?

በጥናታችሁ ውስጥ የቅዱስ ቁርባን መዝሙር ማካተትን አስቡ፣ ለምሳሌ “In Memory of the Crucified” (የልጆች መዝሙር፣ ቁጥር 190)።

ሞሮኒ 6፥4–9

የሴሚናሪ ምልክት
የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ ማዛሙርት አንዳቸው ለሌላው ነፍስ ያስባሉ።

ኢየሱስን መከተል የግል ምርጫ ነው ሆኖም አማኞች እኛን “በትክክለኛው መንገድ [በ]ማቆየት” ሊረዱ ይችላሉ (ሞሮኒ 6፥4–9)። በሞሮኒ ዘመን የነበሩ የቤተክርስቲያኗ አባላት አንዳቸው ሌላውን ለማበረታታት ምን አደረጉ? ሞሮኒ 6:4–9ን ስታነቡ፣ “ከክርስቶስ ቤተክርስቲያን ህዝቦች ጋር [በመቆጠር]” ስለሚመጡት በረከቶች አስቡ (ሞሮኒ 6:4)።

በአጥቢያችሁ ወይም በቅርንጫፋችሁ የሚሳተፉ ሠዎችን ልታስቡም ትችላላችሁ። የእናንተ የተለየ ፍቅር የሚያስፈልገው—ምናልባትም አዲስ ወይም በቅርቡ እንደገና የተመለሰ ሰው አለ? የቤተክርስቲያን ተሞክሯቸውን ይበልጥ ሞሮኒ እንደገለፀው ለማድረግ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው? ( የቃል ኪዳን መንገዴ ወይም በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ የሚገኙትን “አዳዲስ አባላትን ማጠናከር” የሚሉትን ቪዲዮዎች ይመልከቱ) በፕሬዚዳንት ዳልን ኤች.ኦክስ “Small and Simple Things” የተሰኘ መልዕክት (ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ) 24-25) ክፍል ውስጥ አንዳንድ መነሳሻዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ።

“ከእግዚአብሔር መልካም ቃል መመገብ” (ሞሮኒ 6:4) ማለት ምን ማለት እንደሆነ በምታሰላስሉበት ጊዜ አንድ ችግኝ ወይም አንድ ሕፃን ስለሚያስፈልገው ምግብ እና ያ ቸል ከተባለ ሊፈጠር ስለሚችለው ነገር ማሰብ ሊረዳ ይችላል። ሌሎችን በመንፈሳዊ “መመገብ” ስለምትችሉባቸው መንገዶች ሃሳብ ለማግኘት ሞሮኒ 6:4–9 ውስጥ ፈልጉ። ሌሎች ደቀ መዛሙርት አናንተን በመመገብ የረዱት እንዴት ነው?

“ከክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሕዝቦች መካከል ጋር [መቆጠር]” እና በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ውስጥ “ሁል ጊዜ በአንድነት መሰብሰብ” ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ለሁሉም ሰው ግልጽ አይደለም የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል በመሆናችሁ አመስጋኝ የሆናችሁበትን ምክንያት እንዴት ትገልፃላችሁ? (የፕሬዚዳንት ኦክስን “The Need for a Church” የተሰኘ መልዕክት ሌሎች ክፍሎች ይመልከቱ)።

ተጨማሪ ሃሳብ ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መፅሄቶች እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሞሮኒ 2–6

መንፈስ ቅዱስ የተቀደሰ ስጦታ ነው።

  • መንፈስ ቅዱስ ወይም መንፈስ በሞሮኒ 2–6 ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል። ምናልባት ልጆቻችሁ ስለእርሱ የሚናገር እያንዳንዱን ጥቅስ እንዲፈልጉ ልትጠይቋቸው፣ጥቅሶቹን ማንበብ እንዲሁም ስለመንፈስ ቅዱስ የተማሩትን መዘርዘር ትችላላችሁ። የመንፈሱ ተጸዕኖ በተሰማችሁ ጊዜ የነበራችሁን ልምድ አንዳችሁ ለአንዳችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ።

ሞሮኒ 4–5

ቅዱስ ቁርባንን በመውሰድ ኢየሱስ ክርስቶስን ሁል ጊዜ እንደማስታውስ አሳያለሁ።

  • የቅዱስ ቁርባን ጸሎቶችን ከልጆችዎ ጋር ማንበብ በቅዱስ ቁርባን ጊዜ የበለጠ ትርጉም ያለው ተሞክሮ ስለማግኘት ወደሚደረግ ውይይት ሊያመራ ይችላል። አንድ ጓደኛቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቅዱስ ቁርባን ስብሰባ እንደሚመጣ ያህል ማሰባቸው ሊረዳ ይችላል። ስለቅዱስ ቁርባን ምንነት እና ለምን ቅዱስ እንደሆነ ለጓደኛችን እንዴት እናስረዳለን? ልጆቻችሁ በማብራሪያቸው ላይ ከሞሮኒ 4 ወይም 5 እንዲጠቀሙ አበረታቷቸው። ትንንሽ ልጆች የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገፅ ወይም የወንጊል የአርት መፅሐፍቁ. 108 ሊጠቀሙ ይችላሉ።

  • እንደ “Reverently, Quietly” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 26 ይመልከቱ) ያለ ልጆቻችሁ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያስታውሱ የሚረዳ መዝሙር አብራችሁ መዘመርን አስቡ። እንዲሁም በቅዱስ ቁርባን ጊዜ ጥልቅ አክብሮት እያሳዩ መቀመጥን ልትለማመዱም ትችላላችሁ።

ሞሮኒ 6፥1-3

ለመጠመቅ መዘጋጀት እችላለሁ።

  • መጠመቅ የሚችለው ማን ነው? ልጆቻችሁ በሞሮኒ 6፧1-3 ውስጥ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሥ እንዲፈልጉ እርዷቸው። አንድ ሠው “የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ” አለው ማለት ምን ማለት ነው? (ሞሮኒ 6:2)። ይህ ለጥምቀት ለመዘጋጀትየሚረዳን እንዴት ነው? ለጥምቀታችሁ የተዘጋጃችሁት እንዴት እንደነበረ ለልጆቻችሁ መንገርን አስቡ።

ሞሮኒ 6:4–6፣ 9

ቅዱስ ቁርባንን ለመውሰድ እና እርስ በርሳችን ለመደጋገፍ ወደ ቤተከርስቲያን እንሄዳለን።

  • ልጆቻችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ለምን እንደምትወዱያውቃሉ? ሞሮኒ 6:4–6, 9ን ማንበብ ብቤተክርስቲያን ስለምንሰራቸው አንዳንድ ነገሮች በጋራ የመወያየት እድሎችን ሊሰጣቸሁ ይችላል። ምናልባት እነዚህን ነገሮች (ለምሳሌ እየፀለዩ፣ እያስተማሩ፣ እየዘመሩ እና ቅዱስ ቁርባንን እየወሰዱ) የሚያሳዩ የራሳቸውን ምሥሎች ሊስሉ ይችላሉ።

  • ሞሮኒ 6:ን በጋራ ካነበባችህ በኋላ እናንተ እና ልጆቻችሁ ምግብ ስለመመገብ የሚያሳዩ ሥዕሎችን ወይም ምሳሌዎችን መመልከትና ሰውነታችንን መመገብን “የእግዚአብሔርን መልካም ቃል ከመመገብ” ጋር ማወዳደር ትችላላችሁ። “Children Sharing the Gospel” የሚለውን ቪዲዮ (የወንጌል ቤተመፃሕፍት) ልትመለከቱ ትችላላችሁ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ሞሮኒ በዋሻ ውስጥ ተደብቆ

Moroni in the Cave[ሞሮኒ በዋሻ ውስጥ፣ በጆርጅ ኮኮ