ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ህዳር 4–10፦ “እናንተ እዚህ እንዳላችሁ አድርጌ እናገራችኋለሁ።” ሞርሞን 7–9


“ህዳር 4–10፦ ‘እናንተ እዚህ እንዳላችሁ አድርጌ እናገራችኋለሁ።’ ሞርሞን 7-9፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

“ህዳር 4–10 (እ.አ.አ)። ሞርሞን 7-9፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

ሞሮኒ በወርቅ ሰሌዳዎች ላይ እየፃፈ

Moroni Writing on Gold Plates[ሞሮኒ በወርቅ ሰሌዳዎች ላይ እየፃፈ፣ በዴል ኪልቦርን

ህዳር 4–10፦ “እናንተ እዚህ እንዳላችሁ አድርጌ እናገራችኋለሁ።”

ሞርሞን 7–9

ሞሮኒ በክፋት ዓለም ውስጥ ብቸኛ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያውቅ ነበር—በተለይ አባቱ በጦርነት ከሞተ እና ኔፋውያን ከተደመሰሱ በኋላ። “ብቻዬን ቀረሁ” ሲል ፅፏል። “ወዳጆችም ሆኑ የምሄድበት የለኝም” (ሞርሞን 8:3፣ 5)። ነገሮች ምንም ተስፋ የሌላቸው ይመስሉ ነበር፣ ነገር ግን ሞሮኒ በኢየሱስ ክርስቶስ እና “የጌታ ዘላለማዊ አላማዎች እንደሚቀጥሉ” በነበረው ምስክርነት ተስፋን አገኘ (ሞርሞን 8:22)። ሞሮኒ አንድ ቀን ብዙ ሰዎችን “ክርስቶስን ወደ ማወቅ” የሚያመጣው፣ በአሁኑ ጊዜ በትጋት እያጠናቀቀ ያለው ታሪክ ይኸውም መፅሐፈ ሞርሞን የእነዚያ ዘላለማዊ ዓላማዎች ዋና ክፍል እንደሚሆን ያውቅ ነበር (ሞርሞን 8:169:36)። ሞሮኒ በእነዚህ ቃል ኪዳኖች ላይ ያለው እምነት ለወደፊቱ የዚህ መጽሐፍ አንባቢዎች፣ “እናንተ እዚህ እንዳላችሁ አድርጌ እናገራችኋለሁ” እና “እናንተ የእኔ ቃል እንደሚኖራችሁ አውቃለሁ” እንዲል አስችሎታል (ሞርሞን 8:359:30)። አሁን ቃሉ አለን፤ እንዲሁም የጌታ ስራ እያደገ ነው፣ ይህ የሆነው በከፊልም ቢሆን ሞርሞን እና ሞሮኒ ብቻቸውን በነበሩበት ጊዜም እንኳን በአገልግሎታቸው ጸንተው ስለቆዩ ነው።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሞርሞን 7

“በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ” እንዲሁም “[የእርሱን] ወንጌል ያዙ።”

የሕዝቡን ታሪክ ካሳጠረ በኋላ ሞሮኒ የማሳረጊያ ንግግሩን በሞርሞን 7 ውስጥ ሰጥቷል። ይህንን መልዕክት የመረጠው ለምን ይመስላችኋል? “የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መያዝ” ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው? (ሞሮኒ 7፥8)።

በተጨማሪም፣ “በክርስቶስ አምናለሁ፤” መዝሙር፣ ቁጥር 134 ይመልከቱ።

ሞርሞን 7:8–108:12–169:31–37

መፅሐፈ ሞርሞን ትልቅ ዋጋ ያለው ነው።

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “አልማዝ ወይም ሩቢ ወይም መጽሐፈ ሞርሞን ተሰጥቷችሁ ቢሆን ኖሮ የትኛውን ትመርጡ ነበር? ሲሉ ጠይቀዋል። ለእናንተ ትልቅ ዋጋ ያለው የትኛው ነው? (“The Book of Mormon: What Would Your Life Be Like without It?,” ሊያሆና፣ ሕዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 61)።

ሞርሞን 7:8–108:12–22፤ እና በ9:31–37 ውስጥ መፅሐፈ ሞርሞን በእኛ ዘመን ጠቃሚ የሆነው ለምን እንደሆነ እንድትገነዘቡ የሚረዳችሁ ምን ታገኛላችሁ? ለእርሶ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? ተጨማሪ ግንዛቤዎችን በ 1 ኔፊ 13:38–412 ኔፊ 3:11–12፤ እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33:1642:12–13 ልታገኙ ትችላላችሁ።

በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉ የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂዎች

የመጽሐፈ ሞርሞን ነቢያት ፅሁፎች ለእኛም ይሆናሉ።

ሞርሞን 8፥1–11

ሌሎች በማያከብሩበት ጊዜም እንኳን ትዕዛዛትን አከብራለሁ።

አንዳንድ ጊዜ ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ ጥረት የምታደርጉት ብቻችሁን እንደሆነ ሊሰማችሁ ከሞሮኒ ምሳሌ ሊረዳችሁ የሚችል ምን መማር ትችላላችሁ? (ሞርሞን 8:1–11 ይመልከቱ)። ሞሮኒ እንዴት ታማኝ ሆኖ እንደቀጠለ ልትጠይቁት ብትችሉ ኖሮ ምን ይል ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ?

በተጨማሪም “All May Know the Truth: Moroni’s Promise ”(ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተመፃሕፍት ውስጥ ይመልከቱ።

ሞርሞን 8:26–419፥ 1–30

መፅሐፈ ሞርሞን የተፃፈው ለእኛ ዘመን ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ መፅሐፈ ሞርሞን በሚወጣበት ጊዜ (ሞርሞን 8:34–35 ይመልከቱ) ስለሚሆነው ነገር ለሞሮኒ አሳይቶታል። ይህም ለዘመናችን በድፍረት የተሞሉ ማስጠንቀቂያዎችን እንዲሰጥ አድርጎታል። ሞርሞን 8:26–41 እና 9:1–30 በምታነቡበት ጊዜ ቃሉ እንዴት ለእናንተም እንደሚሆን አሰላስሉ። ለምሳሌ፣ በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ሞሮኒ 24 ጥያቄዎችን ጠይቋል። በእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ ሞሮኒ የእኛን ዘመን እንዳየ የሚያሳይ ምን ማረጋገጫ ታያላችሁ? መጽሃፈ ሞርሞን ሞሮኒ አስቀድሞ የተመለከታቸውን ፈተናዎች በተመለከተ እንዴት ሊረዳ ይችላል?

መንፈሱን አድምጡ ከንባባችሁ ጋር የማይዛመዱ ቢመስሉም እንኳን ለሀሳቦቻችሁ እና ለስሜቶቻችሁ ትኩረት ስጡ። እነዚያ ግንዛቤዎች የሰማይ አባታችሁ እንድትማሩ የሚፈልጋቸው ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ሞሮኒ በሞርሞን 9:1–30 ውስጥ የጠየቃቸውን ጥያቄዎች ካሰላሰላችሁ በኋላ ምን ግንዛቤዎችን አገኛችሁ?

ሞርሞን 9፥1–25

የሴሚናሪ ምልክት
ኢየሱስ ክርስቶስ የተዓምራት አምላክ ነው።

ሞሮኒ በዘመናችን ላሉ በተዓምራት ለማያምኑ ሰዎች ኃይለኛ የሆነ መልዕክት በማስተላለፍ የአባቱን ጽሑፎች ደመደመ (ሞርሞን 8:269:1፣ 10–11 ይመልከቱ)። ዛሬ በተዓምራት ማመን አስፈላጊ እንደሆነ የሚሰማችሁ ለምንድን ነው? ሞርሞን 9:9–11፣ 15–27 እና ሞሮኒ 7:27–29 መርምሩ እንዲሁም እንደሚከተሉት ባሉ ጥያቄዎች ላይ አሰላስሉ፦

  • ከእነዚህ ጥቅሶች ስለአዳኙ ምን እማራለሁ?

  • ስለቀድሞ እና ስለአሁን ተዓምራት ምን እማራለሁ?

  • ኢየሱስ ክርስቶስ የተዓምራት አምላክ እንደሆነ የማመን ጥቅሞች ምን ምን ናቸው? ይህንን አምኖ ያለመቀበል ውጤቶች ምን ምን ናቸው?

  • አዳኙ በህይወቴ ውስጥ ምን ትልቅ እና ትንሽ ተዓምራት ሰርቷል እነዚህ ተዓምራት ስለእርሱምን ያስተምሯችኋል?

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም.ኔልሰን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል “አዳኛችን እጅግ ታላቅ ስራውን አሁን አሁን እና ተመልሶ በሚመጣበት መካከል ያከናውናል እግዚአብሔር አብ እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማዊነት እና በክብር ይህችን ቤተክርስቲያን እንደሚመሩ ተዓምራዊ ምልክቶችን እንመለከታለን (“ራእይ ለቤተክርስቲያን፣ ራእይ ለህይወታችን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 96)። ከእነዚህ ተዓምራት መካከል አንዳንዶቹ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ይሰማችኋል? አዳኙ እንዲያሟላቸው ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

የሳሞአ፣ የቶንጋ፣ የፊጂ እና የታሂቲ ቅዱሳን ፕሬዚዳንት እና እህት ኔልሰን መጥተው በነበረበት ጊዜ ከነበራቸው ተሞክሮ ስለ እምነት እና ስለተዓምራት ምን ትማራላችሁ? (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Christ Is Risen; Faith in Him Will Move Mountains,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021(እ.አ.አ)፣ 101–4)

በተጨማሪም ሮናልድ ኤ. ራስባንድ “Behold!፣ I Am a God of Miracles,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 109–12፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “ተአምራት፣” ወንጌል ቤተመፃሕፍት።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሞርሞን 7፥8–10

መፅሐፈ ሞርሞን እና መፅሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራሉ።

  • ሞሮኒ እንዳደረገው፣ በመጽሐፍ ቅዱስ እና በመፅሐፈ ሞርሞን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጉላት፣ እንደዚህ አይነት ጨዋታ ከልጆቻችሁ ጋር መጫወት ትችላላችሁ፦የመፅሐፍ ቅዱስን ቅጂ ከፍ አድርጋችሁ በምትይዙበት ግዜ “ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን” እንዲሉ ጠይቋቸው እንዲሁም የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂን ከፍ አድርጋችሁ በምትይዙበት ጊዜ ደግሞ “ሌላኛው ምስክርነት” እንዲሉ ጠይቋቸው። መፅሐፈ ሞርሞንም መፅሐፍ ቅዱስም የሚመሰክሩላቸው እንደ የኢየሱስ ውልደት፣ ሞት፣ እና ትንሳኤ ያሉ ብዙ ሁነቶችን ልትመርጡም ትችላላችሁ (ለምሳሌ፣ በወንጌል የአርት መፅሐፍ)።

  • ልጆቻችሁ ስምንተኛውን የእምነት አንቀጽ እንዲማሩ ለመርዳት እያንዳንዱን ቃል በተለያየ ቁራጭ ወረቀት ላይ ልትፅፉ ትችላላችሁ። ቃላቶቹን በትክክለኛው ቅደም ተከተል ስታስቀምጡ እና ይህንን ብዙ ጊዜ ስትደጋግሙ ልጆቻችሁ አብረዋችሁ እንዲሠሩ ጋብዟቸው።

ሞርሞን 8፥1–7

ብቻዬን እንደሆንኩኝ በሚሰማኝ ጊዜም እንኳን ትዕዛዛትን ማክበር እችላለሁ።

  • የሞሮኒ ምሳሌ ልጆቻችሁ ብቻቸውን እንደሆኑ በሚሰማቸው ጊዜም እንኳን ትዕዛዛትን እንዲያከብሩ ሊያነሳሳቸው ይችላል። ሞርሞን 8:1–7ን ከእነርሱ ጋር ስታነቡ ሞሮኒን ቢሆኑ ኖሮ እንዴት ይሰማቸው እንደነበረ ሊያካፍሉ ይችላሉ። በቁጥር 1፣ 3፣ እና 4፣ ሞሮኒ ምን እንዲሰራ ታዞ ነበር? እንዴትስ ታዘዘ? ይበልጥ እንደሞሮኒ ልትሆኑ የምትችሉት እንዴት ነው?

  • ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ ማንም ሰው በማይመለከትበት ጊዜ ትክክል የሆነውን ስህተት ከሆነው መምረጥ ስለሚገደዱባቸው ሁኔታዎች ማውራት ትችላላችሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ይአለን እምነት በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ስንሆን የሚረዳን እንዴት ነው? እንደ “Stand for the Right” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 159) ዓይነት መዝሙር ይህን ውይይት ለማጠናከር ሊረዳ ይችላል።

ሞርሞን 8:24–269:7–26

ኢየሱስ ክርስቶስ “የተዓምራት አምላክ ነው።”

  • ተዓምር እግዚአብሔር ኃይሉን ለማሳየት እና ህይወታችንን ለመባረክ የሚያደርገው ነገር እንደሆነ ለልጆቻችሁ ለማስረዳት ትፈልጉ ይሆናል። ከዚያም ከሞርሞን 9:11–13፣ 17 አንዳንድ የእግዚአብሔርን ተዓምራት የሚገልጹ ሃረጎችን ልታነቡ ትችላላችሁ፤ እንዲሁም ልጆቻችሁ ሌሎች ተዓምራትን ማሰብ ይችላሉ (በGospel Art Book፣ ውስጥ ያሉ እንደ ቁጥር 264041፣ እና 83 ሊረዱ ይችላሉ)። እግዚአብሄር በሕይወያችሁ ስላደረገው ተዓምር ተነጋገሩ።

  • አንድን የምግብ አሰራር ሂደት ለልጆቻችሁ አሳዩዋቸው እና አንድ አስፈላጊ ግብዓት ሳታስገቡ ብትቀሩ ምን እንደሚፈጠር ተነጋገሩ። ከእግዚአብሄር ወደሚመጡ ተዓምራት ሊመሯችሁ የሚችሉ “ግብዓቶችን” ለማግኘት ሞርሞን 8:24 እና 9:20–21 አብራችሁ አንብቡ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ሞሮኒ የኔፋውያንን ውድመት እየተመለከተ

ሞሮኒ የኔፋውያንን ውድመት እየተመለከተ፣ በጆሴፍ ብሪኪ