ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 28–ግንቦት 4 (እ.አ.አ)፦ “ቤተክርስቲያኔን የሚያስተዳድር ህግ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41–44


“ሚያዝያ 28–ግንቦት 4 (እ.አ.አ)፦‘ቤተክርስቲያኔን የሚያስተዳድር ህግ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41–44፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41–44፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ክርስቶስ

ሚያዝያ 28–ግንቦት 4 (እ.አ.አ)፦ “ቤተክርስቲያኔን የሚያስተዳድር ህግ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41–44

ቤተክርስቲያኗ በ1830 እና 1831 (እ.አ.አ) በፍጥነት አደገች፣ በተለይም በከርትላንድ ኦሃዮ አዳዲስ አባላት በብዛት እየመጡ ነበር። ይህ እድገት ለቅዱሳኑ የሚያስደስት እና የሚያበረታታ ነበር፣ ነገር ግን አንዳንድ ፈተናዎችንም ይዞ መጥቷል። በፍጥነት እያደገ ያለውን የአማኞች ቡድን እንዴት አንድ ታደርጋላችሁ? በተለይ ከቀድሞ እምነታቸው ትምህርትን እና ልምዶችን ይዘው ቢመጡ ምን ታደርጋላችሁ? ለምሳሌ ጆሴፍ ስሚዝ በከርትላንድ በየካቲት 1831 (እ.አ.አ) ሲደርስ፣ አባላቶቹ በቅን ልቦና በአዲስ ኪዳን ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ያደርጉት እንደነበረው አይነት ሃብታቸውን በጋራ መጠቀም ጀምረው አገኛቸው (የሐዋርያት ስራ 4፥32–37 ተመልከቱ)። ጌታ በዚህ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አንዳንድ አስፈላጊ ማስተካከያዎችን እና ማብራሪያዎችን ሰጥቷል። ይህን ያደረገው በአብዛኛው በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42 ውስጥ በተመዘገበው “ቤተክርስቲያኔን የሚያስተዳድር ህግ” ብሎ በጠራው (ቁጥር 59) ራዕይ አማካኝነት ነው። በዚህ ራዕይ ውስጥ፣ በኋለኛው ቀናት የጌታን ቤተክርስቲያን ለመመስረት መሰረታዊ የሆኑትን እውነቶች እንማራለን። እንዲሁም፣ ብዙ የምንማረው ነገር እንዳለ እንማራለን፦ “ብትጠይቁ፣” አለ ጌታ፣ “በራዕይ ላይ ራዕይን፣ በእውቀት ላይ እውቀትን ትቀበላላችሁ” (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥61)።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥114–19 ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41

“ህጌን ተቀብሎ የሚያደርገው፣ እርሱ ደቀ መዝሙሬ ነው።”

በ1831 (እ.አ.አ) መጀመሪያ ላይ፣ ቅዱሳን ወደ ኦሃዮ መሠባሠብ ጀምረው ነበር። እግዚአብሔር በዚያ እገልጻለሁ ብሎ ቃል ገብቶላቸው የነበረውን ህግ ለመቀበል ጓጉተው ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥32 ተመልከቱ)። ነገር ግን ጌታ በመጀመሪያ ደቀ መዛሙርቱ ህጉን ለመቀበል እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው አስተማረ። በትምህርትና ቃል ኪዳኖች 41፥1–6 ውስጥ ቅዱሳኑ የእግዚአብሔርን ህግጋት ለመቀበል የረዷቸውን ምን መርሆዎች ታገኛላችሁ? እነዚህ መርሆዎች ከእርሱ መመሪያዎችን እንድትቀበሉ ሊረዷችሁ የሚችሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም “A Bishop unto the Church [ለቤተክርስቲያኗ ኤጲስ ቆጶስ]፣” ራዕይ በአገባብ፣ 77–83 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42

ጌታ ስለሚወደኝ ትዕዛዛትን ሰጥቶኛል።

ቅዱሳን፣ በትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥1–72 ውስጥ የሚገኘውን ራዕይ ነቢዩ ከተቀበላቸው በጣም ጠቃሚ ራእዮች አንዱ አድርገው ይመለከቱታል። ከታተሙት የመጀመሪያዎቹ ራዕዮች አንዱ ነበር። ቅዱሳን ለብዙ አመታት “ህጉ” ብለው ይጠሩት ነበር። ክፍሉ ሁሉንም የጌታ ትዕዛዛት ወይም ህጎች አጠቃሎ የያዘ ባይሆንም፣ እነዚህ መርሆች እንደ አዲስ ዳግም ለተመለሰችው ቤተክርስቲያን አስፈላጊ የነበሩት ለምን እንደሆነ ማሰላሰል አስፈላጊ ነው። እነዚህን ማወቁ ለእኛ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

በአንጻራዊነት፣ ክፍል 42 ረጅም ስለሆነ፣ በሚከተለው መልኩ በትንሽ በትንሹ በመከፋፈል ማጥናትን ልታስቡ ትችላላችሁ። በእያንዳንዱ ውስጥ የተሰጡትን የመርሆዎች ትምህርት ለዩ፣ ከዚያም እነዚህ ህጎች እንዴት ጌታ ለህዝቡ ያለውን ፍቅር የሚያሳዩ ምልክቶች እንደሆኑ አስቡ።

እግዚአብሔር ህግጋትን እና ትዕዛዛትን የሚሰጠን ለምንድን ነው? ትዕዛዛቱን በማወቃችሁ እና በመከተላችሁ የተባረካችሁት በምን መንገዶች ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥30–42

“ድሆችን [አስታውሱ]።”

በክፍል 42 ውስጥ በራዕይ እንደተሰጠ ህግ አካል፣ ቅዱሳኑ እንደቀደምት የክርስቶስ ተከታዮች “ሁሉም ነገር በጋራ” (የሐዋርያት ሥራ 2፥444 ኔፊ 1፥3) እየኖራቸው “ማንም ድሃ ሳይኖር” (ሙሴ 7፥18) ለመኖር እንደሚችሉ አስተማራቸው። ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥30–42 ቅዱሳኑ የመቀደስን ህግ ስለኖሩበት መንገድ ምን ትማራላችሁ? (መቀደስ ማለት አንድን ነገር ለአንድ የተቀደሰ ዓላማ መለየት ማለት ነው።)

ምንም እንኳን ዛሬ “ሁሉም ነገር በጋራ” ባይኖረንም፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን አሁንም በቤተመቅደስ የመቀደስን ህግ ለመኖር ቃል ኪዳን ይገባሉ። የተቸገሩ ሰዎችን ለመባረክ እግዚአብሔር የሰጣችሁን እንዴት ማካፈል ትችላላችሁ? እንደ “Because I Have Been Given Much [ብዙ ስለተሰጠኝ]” (መዝሙር፣ ቁጥር 219) አይነት መዝሙር ሃሳቦችን ሊሰጣችሁ ይችላል።

በተጨማሪም፣ ሼረን ዩባንክ፣ “I Pray He’ll Use Us [እርሱ እንዲጠቀመን እጸልያለሁ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2021 (እ.አ.አ)፣ 53–56፤ “The Law [ህጉ]፣”በራዕይ በአገባብ፣ 93–95 ተመልከቱ።

ክርስቶስ እና ሀብታሙ ወጣት ገዢ

ክርስቶስና ሀብታሙ ወጣት ገዢ፣ በሄንሪች ሆፍማን

ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥61፣ 65–6843፥1–16

የሴሚናሪ ምልክት
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኑን እና እኔን ለመምራት ራዕይን ይሰጣል።

ቤተክርስቲያኗ በራዕይ እንደምትመራ ለማወቅ ከጓጓ አዲስ የቤተክርስቲያን አባል ጋር እየተነጋገራችሁ እንደሆነ አስቡ። ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 43፥1–16ን በመጠቀም ለእርሱ ወይም ለእርሷ ጌታ ቤተክርስቲያኑን በነቢዩ አማካኝነት የሚመራበትን መንገድ ማብራራት የምትችሉት እንዴት ነው? ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥61፣ 65–68ን በመጠቀም የግል ራዕይን ስለመቀበል ማስተማር የምትችሉት እንዴት ነው?

በመንፈሱ አማካኝነት ከጌታ የተቀበላችኋቸው አንዳንድ “ሰላማዊ የሆኑ ነገሮች” እና ደስታንና የሚያመጡ ነገሮች ምንድን ናቸው?

የቤተክርስቲያኗ መሪዎች የጌታን ድምጽ እንዴት እንደሰሙ ለማወቅ፣ በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ባለው “እርሱን ሥሙት” ስብስብ ውስጥ ካሉት ቪዲዮዎች አንዱን ልትመለከቱ ትችላላችሁ። ጌታ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደሚነጋገር የሚገልፅ የራሳችሁን ቪዲዮ መሥራትን አስቡ።

በተጨማሪም የራስል ኤም. ኔልሰንን፣ “ራዕይ ለቤተክርስቲያኗ እና ራዕይ ለህይወታችን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 93–96፤ “All Things Must Be Done in Order [ሁሉም ነገሮች በስርዓት … መከናወን አለባቸው]፣” ራዕይ በአገባብ፣ 50–53 ተመልከቱ።

ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮችን ተጠቀሙ። ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ወይም የእይታ መርጃዎች የምታስተምሯቸው ሰዎች የወንጌልን እውነት በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ እና ረዘም ላለ ጊዜ እንዲያስታውሱ ይረዳቸዋል። ለምሳሌ፣ “በራዕይ ላይ ራዕይን፣ በእውቀት ላይ እውቀትን” (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 42፥61) ስለመቀበል ለማስተማር አንድ በአንድ የሚገጣጠምን የመገጣጠም ጨዋታን መጠቀም ትችላላችሁ።

የልጆች ክፍል ምልክት 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41፥5

ደቀ መዝሙር ማለት የእግዚአብሔርን ህግ ተቀብሎ የሚታዘዝ ሠው ማለት ነው።

  • ልጆቻችሁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲያውቁ ለመርዳት፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 41፡5 ን በወረቀት ላይ በመፃፍ ደቀመዝሙር የሚለው ቃል የሚፃፍበትን ቦታ ባዶውን ለመተው ትችላላችሁ። ከዚያም እነርሱ የጎደለውን ቃል ቁጥር 5 ውስጥ ሊፈልጉ ይችላሉ። በዚህ ቁጥር ላይ በሠፈረው መሠረት፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ማለት ምን ማለት ነው? የተሻል የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን እንዴት እየሞከርን ነን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥2

ጌታን ስታዘዘው ደሥተኛ እሆናለሁ።

  • ልጆቻችሁ በጥሞና ማዳመጥን እና መመሪያዎችን መከተልን የሚጠይቅ ጨዋታ መጫወት ያስደስታቸው ይሆናል። ይህንን ጨዋታ፣ ጌታን “[ማዳመጥ እና መስማት እንዲሁም መታዘዝ[” ምን ማለት እንደሆነ ለመነጋገር ልትጠቀሙበትም ትችላላችሁ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፡2)። ምን መመሪያዎች ሰጥቶናል? ህግጋቱን እና ትዕዛዛቱን በመከተላችን የተባረክነው እንዴት ነው?

  • የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገፅ ከልጆቻችሁ ጋር ማከናወን ትችላላችሁ። እንደ “I Want to Live the Gospel [በወንጌል ለመኖር እፈልጋለሁ]” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 148) አይነት ስለ እግዚአብሔር ህግጋት የሚያወሳ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ። የእግዚአብሔርን ህግጋት መታዘዝ እንዴት ደስታ እንዳመጣላችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ ማካፈልን አስቡ።

    የመጀመሪያ ክፍል የትምህርት ክፍል

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥38

ሌሎችን በማገለግልበት ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስን እያገለገልኩኝ ነው።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥38ን በአንድነት ካነበባችሁ በኋላ፣ ልጆቻችሁ ሌሎችን በማገልገል ኢየሱስ ክርስቶስን ማገልገል የሚችሉበትን መንገድ እንዲያስቡ እርዷቸው። እነርሱም “Pass It On [ከአንድ ወደሌላ አሳልፋችሁ ስጡ]” (ChurchofJesusChrist.org) በሚለው ቪዲዮ ውስጥ አንዳንድ ሃሳቦችን ማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም አዳኙ ሌሎችን ሲረዳ፣ የታመሙትን ሲፈውስ ወይም ለልጆች ደግ ሲሆን የሚያሳዩ ምስሎችን መመልከትም ይችላሉ (የወንጌል የአርት መፅሐፍቁጥር 4247) ተመልከቱ።

    2:3
    Jesus Christ (at the pools of Bethesda) lifting a blanket under which a crippled man lies. Christ is looking compassionately at the man and extending His hand toward him. Other people are gathered around the pools and around Christ.
  • የአሥራት እና የሌሎች የፆም በኩራት መመዝገቢያ ወረቀቶችን ለልጆቻችሁ ልታሳዩዋቸውም ትችላላችሁ፤ ከዚያም፣ ያለንን በመስጠት ሌሎችን ለመባረክ እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል ተወያዩ (በተጨማሪም “Tithing and Donations Online [አስራት እና በኩራት በበይነመረብ]” ተመልከቱ)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 43፥1–7

ነቢዩ ብቻ ለመላው ቤተክርስቲያኗ ራዕይን ሊቀበል ይችላል።

  • አንድ ሰው በምስክርነት ስብሰባ ላይ ተነሥቶ ለመላው ቤተክርስቲያን ራዕይ እንደተቀበለ (ለምሳሌ ካሮት መብላት እንደሌለብን ወይም እጃችንን ከውሃ ይልቅ በወተት መታጠብ እንዳለብን የሚገልፅ ራዕይ) ለአጥቢያው እንደተናገረ እንዲያስቡ ልጆቻችሁን ጋብዟቸው። ነቢዩ ከሚናገረው ይልቅ እርሱን መስማት እንዳለብን ይላል። ያንን ምን ትክክል አያደርገውም? ከዚያም፣ ጌታ ለቤተክርስቲያኑ እንዴት ትዕዛዛትን እንደሚሰጥ ለማወቅ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 43፥1–7ን አብራችሁ ልታጠኑ ትችላላችሁ።

  • በተጨማሪም በህይወት ያለ ነቢይን ምስል ማሳየት እና ልጆቻችሁን በቅርቡ ያስተማረውን ነገር እንዲያካፍሉ መጋበዝ ትችላላችሁ። እርዳታ ከፈለጉ፣ ከቅርብ ጊዜ የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክት የተወሰደ ቪዲዮን በማየት ወይም አንድ ምንባብ አካፍሏቸው። ዛሬ በህይወት ያለ ነቢይ ማግኘት በረከት የሆነው ለምን ይመስላችኋል?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ጆሴፍ ስሚዝ እያስተማረ

ጆሴፍ ስሚዝ እየሰበከ፣ በሳም ሎውሎር

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ