ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ግንቦት 5–11፦ “ቃል የገባሁላችሁ … [ይፈጸማሉ]”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45


“ግንቦት 5–11፦ ‘ቃል የገባሁላችሁ … [ይፈጸማሉ]’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ቤተሰብ በቤተመቅደስ

ግንቦትት 5–11፦ “ቃል የገባሁላችሁ … [ይፈጸማሉ]”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45

ክፍል 45 ውስጥ ያለው ራዕይ የመጣው፣ በክፍል መግቢያው መሠረት “ለቅዱሣኑ ደስታ” ነው። እናም በዚህ ራዕይ ውስጥ ብዙ ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ። በዚህ ውስጥ፣ አዳኙ አብን ስለእኛ እንደሚለምንልን የደግነት ተስፋውን ሰጥቷል (ቁጥር 3–5ን ተመልከቱ) “[በፊቱ] መንገድን [እንደ]ሚያዘጋጅ[ለት] መልዕክተኛ” በመላው አለም ስለተሰራጨው የዘለዓለም ቃል ኪዳኑ ተናግሯል (ቁጥር 9)። ስለእርሱ ታላቅ ዳግም ምፅዓቱም ተንብዩዋል። አዳኙ እነዚህን ሁሉ ያደረገው፣ በከፊልም ከመምጣቱ በፊት ሊፈጸሙ በሚገባቸው አደጋዎች ምክንያት፣ እነዚህ አስጨናቂ ጊዜያት መሆናቸውን በማወቅም ነው(ቁጥር 34ን ተመልከቱ)። ሆኖም ያ አደጋ፣ ያ ጨለማ የተስፋን ብርሃን የማጥፋት አቅም አይኖረውም። ጌታ፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ … በጨለማም የማበራ ብርሐን ነኝ” ሲል ተናግሯል(ቁጥር 7)። ለመሥጠት ከሚፈልገው ከማንኛውም ምክር እና ማስጠንቀቂያ እንዲሁም እውነት ጋር፣ ይህንን ራዕይ በደስታ ለመቀበል ብችኛ ምክንያት ነው።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥1–5

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ዘንድ አማላጃችን ነው።

በእግዚአብሔር ፊት ብቃት እንደሚያንሰን ወይም ብቁ እንዳልሆንን ሲሰማን፣ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥1–5 ውስጥ ካሉት የአዳኙ ቃላት ማረጋገጫ ማግኘት እንችላለን። እነዚህን ጥቅሶች ስትፈትሹ፣ እንደእነዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን አስቡ፦

  • በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ለእናንተ በተለይ ትርጉም እንዳላቸው የሚሰማችሁ የትኛዎቹ ቃላት ወይም ሐረጎች ናቸው?

  • አማላጅ ማለት አንድን ሰው ወይም ምክንያት በይፋ የሚደግፍ ወይም ስለተገቢነቱ የሚመከር ሰው ነው። በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን የሚያደርግላችሁ እንዴት ነው? ይህን እንዲያደርግ ብቁ ያደረገው ምንድን ነው?

  • አዳኙ ለአብ ከተናገራቸው ቃላት ምን ያስደንቃችኋል?(ቁጥሮች 4–5)።

ሽማግሌ ዴል ጂ. ረንለንድ ዛሬ ምረጡ” (ሊያሆና፣ ህዳር. 2018 (እ.አ.አ)፣ 104–5) በተሠኘው መልዕክት ውስጥ ስለአማላጃችን ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማሩትን ልታጠኑም ትችላላችሁ። በሽማግሌ ረንለድ መሠረት፣ የአዳኙ ዓላማ ከሉሲፈር ዓላማ ጋር የሚነጻጸረው እንዴት ነው?

የሚከተሉት ምንባቦች አዳኙ ያለውን የአማላጅነት ሚና ግንዛቤያችሁን ሊጨምሩ ይችላሉ። እነሱን ስታጠኑ፣ ለሌሎች ልታካፍሏቸው የምትችሏቸውን ሀረጎች ወይም እውነቶች መጻፍን አስቡ፦ 2 ኔፊ 2፥8–9ሞዛያ 15፥7–9ሞሮኒ 7፥27–28ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥562፥1። እነዚህ ሃረጎች ለእናንተ ትርጉም ያላቸው ለምንድን ነው?

በተጨማሪም “I Stand All Amazed፣” መዝሙር፣ ቁጥር 193፤ Topics and Questions፣ “Atonement of Jesus Christ፣” ወንጌል ላይብረሪ፤ “The Mediator” (ቪድዮ)፣ ወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥9–10

ወንጌል የአገሮች መሥፈርት ነው።

በጥንት ጊዜ፣ መሥፈርት ጦርነት ሲኬድ የሚያዝ ወታደሮችን ለማሰባሰብ እና ለማዋሃድ የሚያገለግል ሰንደቅ ዓላማ ነበር። መስፈርት በተጨማሪም ሌሎች ነገሮች የሚለኩበት ማነጻጸሪያ ምሳሌ ወይም ደንብ ነው። ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 45፥9–10ን ስታነቡ፣ ከጌታ ጋር የገባችኋቸው ቃል ኪዳኖች ለእናንተ እንዴት መሥፈርት እንደሆኑላችሁ አሰላስሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥11–75

ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ይመለሳል።

የጌታ ዳግም ምፅዓት “ታላቁ” እና “የሚያስፈራው” ተብሎ ተገልጿል (ሚልክያስ 4፥5)። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45 ውስጥ፣ ሁለቱም መግለጫዎች የሚስማሙ ይመስላሉ። ይህ ራዕይ የጌታን መምጣት የሚመለከቱ ጥንቃቄ የታከለባቸው ማስጠንቀቂያዎችን እና ብሩህ ተስፋዎችን ያካትታል። ቁጥር 11–75ን ስታጠኑ፣ ክርስቶስን በመፍራት ሣይሆን በእርሱ በማመን ለዳግም ምፅዓቱ እንዴት መዘጋጀት እንደምትችሉ አስቡ። የምታገኙትን እንደዚህ ባለ ሠንጠረዥ መዝግቡ፦

ትንቢት ወይም ተስፋ

ምን ማድረግ እችላለሁ

ትንቢት ወይም ተስፋ

በጨለማ ለተቀመጡትም ብርሃን (ወንጌል) ይመጣል (ቁጥር 28)

ምን ማድረግ እችላለሁ

ብርሃኑን ተቀበሉ—እንዲሁም አጋሩት (ቁጥር 29)።

ትንቢት ወይም ተስፋ

ምን ማድረግ እችላለሁ

ትንቢት ወይም ተስፋ

ምን ማድረግ እችላለሁ

ትንቢት ወይም ተስፋ

ምን ማድረግ እችላለሁ

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “Men’s Hearts Shall Fail Them” (ወንጌል ላይብረሪ) በሚለው ቪዲዮ ላይ አስፈሪ ሁኔታዎችን በሰላም መጋፈጥ የሚያስችለንን ምን ምክር ሰጥተዋል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥31–32፣ 56–57

“በተቀደሰ ስፍራዎች ላይ [መቆም]” እችላለሁ እናም አልነቃነቅም።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥31–32፣ 56–57 ውስጥ ለጌታ ዳግም ምፅዓት ስለመዘጋጀት ምን ትማራላችሁ? የእናንተ “የተቀደሱ ስፍራዎች“ ምን ምን ናቸው? “አለመነቃነቅ“ ማለት ምን ማለት ነው? ያላችሁበትን ሥፍራ የተቀደሰ ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው?

ጌታ በአሥሩ ደናግላን ምሳሌ ውስጥ ያለውን ዘይት ከእውነትና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በማነጻጸር እንደተናገረ አስተውሉ። ያንን በአዕምሯችሁ ይዛችሁ በማቴዎስ 25፥1–13 ውስጥ ያለውን ምሣሌ ማንበብን አስቡ። ምን ግንዛቤዎችን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “ብታውቁኝ ኖሮ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 102–5 ተመልከቱ።

ምስል
አምስት ልባም ደናግላን

የአስሩ ደናግላን ምሳሌ በዳን በር

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥11–15፣ 66–71

ፅዮን ለእግዚአብሔር ቅዱሳን የደህንነት ስፍራ ናት ።

በጆሴፍ ስሚዝ ዘመን የነበሩ ቅዱሳን፣ አዲሲቷን ኢየሩሳሌም፣ ፅዮንን ለመገንባት ጓጉተው ነበር (ኤተር 13፥2–9ሙሴ 7፥18፣ 62–64ን ተመልከቱ)። ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥11–15፣ 66–71 ስለ ፅዮን ምን ትማራላችሁ—በሔኖክ ዘመን ስለነበረችው ስለጥንቷ ከተማ እና ስለኋለኛው ቀን ከተማ? በዛሬው ጊዜ ጽዮንን የመመሥረት ትዕዛዝ የሚያመለክተው በምንኖርበት ቦታ የእግዚአብሔርን መንግሥት መመሥረትን ነው። በምትኖሩበት ቦታ ፅዮንን በመገንባት ለማገዝ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥3–5

ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ፊት የእኔ አማላጅ ነው።

  • ልጆቻችሁ፣ አማላጅ ማለት ሌላ ሰውን የሚደግፍ ግለሠብ መሆኑን እንዲገነዘቡ መርዳት ትፈልጉ ይሆናል። ከዚያም እነርሱ ሊያውቋቸው ስለሚችሏቸው አማላጅ የመሆን ምሳሌዎች (ለጓደኛ እንደመቆም) ልትናገሩ ትችላላችሁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥3–5ን በአንድነት ስታነቡ፣ ልጆቻችሁ አማላጃችን ማን እንደሆነ እና እንዴት እንደሚረዳን እንዲፈልጉ እርዷቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥32

“በተቀደሱ ሥፍራዎች [መቆም]” እችላለሁ።

  • በክፍሉ ዙሪያ፣ የቤት፣ የቤተክርስቲያን ህንፃ እና ቤተመቅደስ ምሥሎችን ማስቀመጥ አስደሳች ሊሆን ይችላል። ከዚያም፣ ለልጆቻችሁ እነዚህን ቦታዎች የሚገልጹ ፍንጮችን መስጠትና እናንተ ከገለፃችሁት ምሥል አጠገብ እንዲቆሙ መጋበዝ ትችላላችሁ። የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥32ን የመጀመሪያ መስመር በምታነቡበት ጊዜ ሳይነቃነቁ እንዲቆሙ ጠይቋቸው። እግዚአብሔር የሚሰጠን አንዳንድ የተቀደሱ ስፍራዎች ምን ምን ናቸው? ልጆቻችሁ፣ “በተቀደሱ ሥፍራዎች ላይ መቆም፣ እናም አለመነቃነቅ” ማለት፣ የፈለገው ነገር ቢሆን ሁልጊዜ ትክክለኛውን ነገር መምረጥ እንደሆነ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። ቤታችንን የበለጠ የተቀደሰ ስፍራ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥9

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የዓለም መስፈርት ነው።

  • በጥንት ጊዜ መስፈርት ጦርነት ሲኬድ የሚያዝ ባንዲራ ወይም ሰንደቅ ዓላማ እንደነበር ለልጆቻችሁ ልታብራሩ ትችላላችሁ። ወታደሮች የት መሰብሰብ እንዳለባቸው እና ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲያውቁ ይረዳቸው ነበር። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥9ን በአንድነት አንብቡና ወንጌል እንደ መስፈርት ስለሆነባቸው መንገዶችተወያዩ። ልጆቻችሁ ስለአዳኙ ያላቸውን ስሜት የሚገልጹ ምስሎችን ወይም ቃላትን በማካተት የራሳቸውን መስፈርት ወይም ባንዲራ በማዘጋጀት ሊደሰቱ ይችሉ ይሆናል።

ምስል
መሥፈርትን ከፍ አድርጎ መያዝ

ወንጌል እንደ መስፈርት ወይም እንደ ባንዲራ ወይም እንደ ሰንደቅ አላማ ነው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥44–45

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና ይመጣል።

  • ከዳግም ምፅዓቱ በፊት የሚከሰተው ጥፋት ልጆችን ሊያስፈራቸው ይችላል። እነርሱን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መጠቆም በእምነት እንዲጠባበቁ ይረዳቸዋል! እንደ አያት ወይም ጓደኛ ያለ ልዩ የሆነ ሰው ለጉብኝት እየመጣ በሚሆንበት ጊዜ እንዴት ሊሰማቸው እንደሚችል እንዲያስቡ መጋበዝን አስቡ። ለጉብኝቱ የሚዘጋጁት እንዴት ነው? ከዚያም የአዳኙን ምሥል ልታሳዩና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥44–45ን ልታነቡ ትችላላችሁ። ስለአዳኙ መምጣት እንዴት እንደሚሰማችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።

  • ልጆቻችሁ ስለአዳኙ ዳግም ምፅዓት ጉጉት እንዲሰማቸው ለመርዳት፣ አንዳንድ ብሩህ ተስፋዎችን ከክፍል 45 ውስጥ (ለምሳሌ፣ ቁጥር 44–45፣ 51–52፣ 55፣ 58–59፣ 66–71ን ተመልከቱ) በትንሽ ወረቀት ላይ ልትፅፉ ትችላላችሁ። ወረቀቶቹን ለልጆቻችሁ ስጧቸው፣ ከዚያም ጥቅሶቹን በምታነቡበት ጊዜ በእጃቸው የያዙት የተስፋ ቃል ከተጠቀሰ እጃቸውን እንዲያወጡ ጠይቋቸው። እነዚህ ተስፋዎች ምን ማለት እንደሆኑ ተወያዩ። ከልጆቻችሁ ጋር ስለአዳኙ ዳግም ምፅዓት የሚያወሳ እንደ “When He Comes Again [እንደገና ሲመጣ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 82–83) ያለ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ።

ልጆቻችሁ መንፈሱን እንዲያውቁ እርዷቸው። ልጆቻችሁን በምታስተምሩበት ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ ሲሰማችሁ ንገሯቸው። ከእርሱ የሚመጣ ተጽዕኖን እንዴት እንደምታውቁ ተናገሩ። ለምሳሌ፣ ስለአዳኙ የሚያወሳ መዝሙር በምትዘምሩበት ጊዜ ሰላም ወይም ደስታ ሊሰማችሁ ይችላል።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

አትም