ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ግንቦት 12–18፦ “የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በፅኑ ፈልጉ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46–48


“ግንቦት 12–18፦ ‘የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በፅኑ ፈልጉ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46-48፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46-48፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

በወንዝ አጠገብ መገናኘት

የካምፕ ስብሰባ በወርዚንግተን ዊትሬጅ

ግንቦት 12–18፦ “የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በፅኑ ፈልጉ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46–48

ፓርሊ ፒ. ፕራት፣ ኦሊቨር ካውድሪ፣ ዚባ ፒተርሰን እና ፒተር ዊትመር፣ ዳግማዊ ከከርትላንድ በመውጣት ወንጌልን መስበካቸውን በቀጠሉበት ጊዜ፣ ከመቶ የሚበልጡ ቅንዓት የነበራቸው ነገር ግን ልምድ ወይም አቅጣጫ ያልነበራቸው አዳዲስ የቤተክርስቲያኗን አባላት ትተው ሄደው ነበር። ምንም አይነት የማስተማሪያ መመሪያ መፅሀፎች አልነበሯቸውም፣ ምንም የመሪዎች ስልጠናዎች አልነበረም፣ ምንም የአጠቃላይ ጉባኤ ስርጭትም አልነበረም—በእርግጥ፣ ይዘዋቸው የሚንቀሳቀሱት በቂ የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂዎች እንኳን አልነበሯቸውም። አብዛኛዎቹ እነዚህ አማኞች ዳግም ወደተመለሰው ወንጌል የተሳቡት በተለይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተገለፁት ቃል በተገቡት አስደናቂ የመንፈስ መገለጦች ተሥፋዎች ተስበው ነበር ( ለምሳሌ1 ቆሮንቶስ 12፥1–11ን ተመልከቱ)። ነገር ግን ብዙዎች እውነተኛዎቹ የመንፈሱ መገለጫዎች የትኞቹ እንደሆኑ መለየት አስቸጋሪ ሆኖ አግኝተውት ነበር። የነበረውን ግራ መጋባት ተመልክቶ ጆሴፍ ስሚዝ እርዳታ ለማግኘት ጸለየ። የጌታ ምላሽ፣ ብዙውን ጊዜ ሰዎች የመንፈስን ነገር በማይቀበሉበት ወይም ችላ በሚሉበት በዛሬው ጊዜም በእኩል ደረጃ ጠቃሚ ነው። መንፈሳዊ መገለጫዎች እውን እንደሆኑ አረጋግጧል። በተጨማሪም፣ “ለሚወዱ[ት] እና ትእዛዛ[ቱ]ን ለሚጠብቁ፣ እናም ይህን ለማድረግ ፈቃድ ላላቸው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥9) ከአፍቃሪ የሰማይ አባት የተሰጡ ስጦታዎች እንደሆኑም አብራርቷል።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥1–7

አዳኙ በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማምለክ የሚፈልጉትን ሁሉ ይቀበላል።

ጓደኞቻችሁ እና በአቅራቢያችሁ የሚገኙ ሰዎች በአጥቢያዎቻችሁ በሚደረጉ የአምልኮ አገልግሎቶች ላይ መልካም አቀባበል እንደተደረገላቸው እንደሚሰማቸው ታውቃላችሁ? የቤተክርስቲያን መሰብሰቢያ ቦታዎቻችሁ ሰዎች ተመለልሰው የሚመጡባቸው ቦታዎች እንዲሆኑ ምን እያደረጋችሁ ነው? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥1–7 (በተጨማሪም 2 ኔፊ 26፥24–283 ኔፊ 18፥22–23ን ተመልከቱ) ውስጥ ያለውን የጌታ ምክር እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ።

እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ወይም በሌላ የቡድን ስብሰባ ላይ የተሣተፋችሁበትን ጊዜ ልታስቡ ትችላላችሁ። ሠዎች መልካም አቀባበል እንደተደረገላችሁ እንዲሰማቸሁ ለመርዳት ምን አድርገዋል?

በተጨማሪም ሞሮኒ 6፥5–9፤ “’Tis Sweet to Sing the Matchless Love፣” መዝሙር፣ ቁጥር. 177፤ “Welcome” (ቪዲዮ)፣ ወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

1:5

Welcome | Comeuntochrist.org

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥7–33

የሴሚናሪ ምልክት
የሰማይ አባት ሌሎችን እንድባርክ መንፈሥ ሥጦታዎችን ይሠጠኛል።

ቀደምት ቅዱሳን በመንፈስ ስጦታዎች ያምኑ ነበር፣ ነገር ግን እነርሱን ስለመለየት እና ስለአላማቸው ለመረዳት የተወሰነ እርዳታ አስፈልጓቸው ነበር። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥7–33 ውስጥ ስለመንፈስ ስጦታዎች ስታጠኑ፣ “ለምን” አላማ “እንደተሰጧችሁ“ (ቁጥር 8) አስቡ። የእነዚህ ሥጦታዎች ሠጪ ስለሆነው ስለእግዚአብሔር ምን ትማራላችሁ?

ሰዎች እነዚህን ወይም ሌሎች የመንፈሥ ስጦታዎችን ሲጠቀሙ ያያችኋቸውን ምሳሌዎች ማሰብ ትችላላችሁ? “ለእግዚአብሔር ልጆች ጥቅም” (ቁጥር 26) የዋሉት እንዴት ነበር? እንደእነዚህ ባሉ የቅዱሳት መፃህፍት ጥቅሶች ውስጥ የተለያዩ የመንፈሥ ስጦታዎች ምሳሌዎችን መለየት ትችላላችሁ፦ 1 ነገሥት 3፥5–15ዳንኤል 2፥26–30ሥራ 3፥1–8ሔለማን 5፥17–19ሞርሞን 1፥1–5ኤተር 3፥1–15ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥10–12ሙሴ 7፥13

ስለመንፈሥ ስጦታችሁ የምታደርጓቸው ጥናቶች እግዚአብሔር ምን ሥጦታ እንደሰጣችሁ ወደ ማሰላሰል ሊመራችሁ ይችላል። እነዚህን ሥጦታዎች የእርሱን ልጆች ለመባረክ መጠቀም የምትችሉት እንዴት ነው? የፓትርያርክ በረከት ተቀብላችሁ ከሆነ ምናልባት የተሰጧችሁን ሥጦታዎች ለይቶላችሁ ይሆናል። የሽማግሌ ጆን ሲ. ፒንግሪ፣ ዳግማዊ መልዕክት የሆነውን “I Have a Work for Thee”ን ማንበብ፣ ላላሰባችኋቸው ሥጦታዎች አእምሯችሁን ሊከፍትላችሁም ይችላል (ሊያሆና፣ ህዳር. 2017 (እ.አ.አ)፣ 32–35)።

የመንፈሥ ሥጦታዎችን እንዴት ማዳበር እንደሚቻል ለማወቅ ከፈለጋችሁ፣ የሽማግሌ ሁዋን ፓብሎ ቪለር መልእክት በሆነው “መንፈሳዊ ጡንቻዎቻችንን መጠቀም” በሚለው ፅሁፍ መጀመሪያ ላይ ያለው ንፅፅር ሊረዳችሁ ይችላል (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 95)። የመንፈሥ ሥጦታዎቻችሁን ለማዳበር ምን “ልምምዶች” ሊረዷችሁ ይችላሉ?

በተጨማሪም Topics and Questions፣ “Holy Ghost፣” ወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 47

ጌታ፣ የእርሱ ቤተክርስቲያን ታሪኳን መዝግባ አንድትይዝ ይሻል።

ጆን ዊትመር የቤተክርስቲያኗን ታሪክ መዝግቦ እንዲይዝ የተሠጠው ጥሪ፣ በእግዚአብሔር ህዝቦች መካከል የነበረውን የታሪክ መዝጋቢዎች ረጅም ባህል አስቀጥሏል። ታሪክን መመዝገብ ለጌታ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? ክፍል 47ን እና በ2 ኔፊ 29፥11–12ሙሴ 6፥5አብርሐም 1፥28፣ 31ውስጥ ያሉትን ተመሳሳይ መመሪያዎች ስታነቡ ይህንን አሰላስሉ። ጌታ ስለ ህይወታችሁ ምን እንድትመዘግቡ የሚፈልግ ይመስላችኋል?

በFamilySearch ላይ የህይወታችሁን እና የቅድመ ዓያቶቻችሁን ህይወት ትዝታዎች እና ተሞክሮዎች መመዝገብ ትችላላችሁ(FamilySearch.orgን ተመልከቱ)።

ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “O Remember፣ Remember፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2007 (እ.አ.አ)፣ 66–69 ተመልከቱ።

ጆን ዊትመር

ጆን ዊትመር

ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 47

ጥሪዬን በምፈፅምበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሊመራኝ ይችላል።

ምናልባት፣ ጆን ዊትመር የተሠጠው ጥሪ ከእግዚአብሔር እንደሆነ ማረጋገጫ በፈለገበት ጊዜ ከተሰማው ጋር ልታዛምዱ ትችላላችሁ። እርሱ የሚሰጣቸውን ጥሪዎች ለመፈጸም መተማመንን ለማነሳሳት ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 47ውስጥ ለጆን ዊትመር—እንዲሁም ለእናንተ ምን ተናገረ?

የአስተማሪ ሚና። ማስተማር መረጃ ከመሥጠት በላይ ነው። የክፍል አባላት ሊማሩ የሚችሉበትን እና በራሳቸው እውነቶችን የሚያገኙበትን እንዲሁም የተማሩትን አንዳቸው ለሌላቸው የሚያካፍሉበት አካባቢ መፍጠርን ያካትታል (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 26ን ተመልከቱ)።

የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥2–6

ሌሎች በቤተክርስቲያን መልካም አቀባበል እንደተደረገላቸው እንዲሠማቸው መርዳት እችላለሁ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥5ን ከልጆቻችሁ ጋር ካነበባችሁ በኋላ፣ ሰዎች ወደ እርሱ ቤተክርስቲያን ሲመጡ አዳኙ ምን እንዲሰማቸው እንደሚፈልግ ተናገሩ። ልጆቻችሁ፣ አንድን ሠው ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተክርስቲያን እንዳዩት እንዲያስቡ ጋብዟቸው። ይህ ሰው መልካም አቀባበል እንደተደረገለት እንዲሰማው የሚረዱ መንገዶችን እንዲለማመዱ እርዷቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥7–26

የሰማይ አባት ሌሎችን እንድባርክ መንፈሳዊ ሥጦታዎችን ይሠጠኛል።

  • ልጆቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥13–26 ውስጥ ስለተገለጹት የመንፈሥ ሥጦታዎች እንዲያውቁ ለመርዳት፣ ይህንን ሃሳብ ግምት ውስጥ አስገቡ። ሥጦታዎቹን በቁርጥራጭ ወረቀቶች ላይ መጻፍ እና በክፍሉ ዙሪያ መደበቅ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ እያንዳንዱን ወረቀት ሲያገኙ፣ ሥጦታው በክፍል 46 ውስጥ በየትኛው ቦታ እንደተገለፀ እንዲፈልጉ እርዷቸው። እያንዳንዱ ስጦታ ሌሎችን ለመባረክ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ከእነርሱ ጋር ተነጋገሩ (“በምዕራፍ 20፦ የመንፈስ ሥጦታዎች፣” በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 77–80 ውስጥ የሚገኘው መግለጫ ሊረዳ ይችላል)።

    2:19

    Chapter 20: Gifts of the Spirit: 8•March 1831

  • የሰማይ አባት እንደሰጣቸው የሚሰማችሁን ስጦታዎች ለልጆቻችሁ ንገሯቸው፣ እንዲሁም አንዳቸው በሌላቸው ውሥጥ ስለሚያዩዋቸው ሥጦታዎች እንዲናገሩ አድርጉ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥8–9፣ 26 እንደሚገልፁት፣ የሰማይ አባት የመንፈሥ ሥጦታዎችን የሚሰጠን ለምንድን ነው? ችሎታዎቻችንን ሌሎችን ለመርዳት መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 47፥1፣ 3

ታሪኬን መመዝገብ እችላለሁ።

  • ጌታ፣ ጆን ዊትመር ምን እንዲያደርግ ይፈልግ እንደነበረ ልጆቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 47፥1፣3 ውስጥ እንዲፈልጉ አድርጉ። ከቅዱሣት መፃህፍት ውስጥ የምትወዷቸውን ታሪኮች አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉም ትችላላችሁ። ስለእነዚህን ታሪኮች የምናውቀው አንድ ሰው ስለመዘገባቸው እንደሆነ ግለፁ።

  • ልጆቻችሁ የግል ታሪካቸውን እንዲመዘግቡ እንዴት ማነሳሳት እንደምትችሉ አስቡ። ከግል ማስታወሻ ደብተራችሁ የተወሰነ ፅሁፍ ወይም ከአንድ ቅድመ አያታችሁ አንድ ታሪክ ማጋራት ትችላላችሁ (FamilySearch.org ወይም የ Memories appን ተመልከቱ)። “በዚህ ሳምንት የልጅ ልጆቻችሁ እንዲያውቋቸው የምትፈልጓቸው ምን ነገሮች ተከናውነዋል?” ወይም “በዚህ ሳምንት በህይወታችሁ ውስጥ የጌታን እጅ ያያችሁት እንዴት ነው?” የሚሉ የተወሰኑ በማስታወሻ ደብተር የሚጻፉ ጥያቄዎችን ማቅረብ ትችሉ ይሆናል። ትናንሽ ልጆች ልምዶቻቸውን የሚያንጸባርቁ ሥዕሎችን መሳል ይችላሉ፣ ወይም ደግሞ ታሪኮቻቸውን ሲናገሩ ልትቀርጿቸው ትችላላችሁ። “መደበኛ ታሪክን” መመዝገብ ምን በረከቶችን ያስገኛል? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 47፥1)።

አንዲት ልጅ በማስታወሻ ደብተሯ ላይ እየፃፈች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 48፥2–3

የተሠጠኝን በማካፈል ሌሎችን መርዳት እችላለሁ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 48፥2–3ን ከልጆቻችሁ ጋር ስታነቡ፣ ሠዎች ከምስራቅ ወደ ኦሃዮ እየመጡ እንደነበር እና የመኖሪያ ቦታ እንዳልነበራቸው ማስረዳት ሊኖርባችሁ ይችላል። መርዳት ይችሉ ዘንድ ጌታ ቅዱሳኑን ምን እንዲያደርጉ ጠየቃቸው? ልጆቻችሁ እግዚአብሔር የሠጣቸውን ለሌሎች ማካፈል የሚችሏቸውን ነገሮች እንዲያስቡ እርዷቸው። “‘Give፣’ Said the Little Stream፣” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 236) የሚለውን መዝሙር ከእነርሱ ጋር ልትዘምሩም ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

የቤተክርስቲያን አባላት ሰላምታ ሲለዋወጡ

አዳኙን ለማምለክ የሚፈልጉ ሁሉ በእርሱ ቅዱሳን ስብሰባ ላይ ልናያቸው እንወዳለን።

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ