ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የዳግም መመለስ ድምጾች፦ ወደ ኦሀዮ መሠባሠብ


“የዳግም መመለስ ድምጾች፦ወደ ኦሃዮ መሠባሠብ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ወደ ኦሃዮ መሠባሠብ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

የዳግም መመለስ ድምጾች ምልክት

የዳግም መመለስ ድምጾች

ወደ ኦሃዮ መሠባሠብ

ከርትላንድ በ1830 (እ.አ.አ) አመታት ውስጥ

የከርትላንድ መንደር በኦል ራውንድስ

ፊቢ ካርተር

Picture of Phoebe Carter Woodruff, wife of Wilford Woodruff, circa 1840.

ፊቢ ካርተር በ1830 (እ.አ.አ) አመታት አካባቢ ውስጥ ወደ ኦሃዮ ከተሠባሠቡት ብዙ ቅዱሳን መካከል ነበረች። ወላጆቿ ቤተክርስቲያኗን ባይቀላቀሉም፣ እርሷ ግን ዕድሜዋ በሃያዎቹ አጋማሽ ላይ በነበረበት ወቅት በደቡብ ምስራቅ አሜሪካ ቤተክርስቲያኗን ተቀላቀለች። በኋላም ወደ ኦሃዮ ሄዳ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ለመቀላቀል ስለደረገችው ውሳኔ ጽፋለች፦

“ጓደኞቼ ልክ እንደእኔ በወሰድኩት እርምጃ ተደነቁ፣ ነገር ግን አንዳች ነገር ከውስጤ ይገፋፋኝ ነበር። ቤቴን ትቼ ለመሄድ በመወሰኔ እናቴ ላይ የደረሰው ሃዘን ከምቋቋመው በላይ ነበር፤ እናም በውስጤ በነበረው መንፈስ ሃይል ባይሆን ኖሮ በስተመጨረሻው እሸነፍ ነበር። እናቴ እንዲህ ወደ ጨካኙ አለም ብቻዬን ስሄድ ከምትመለከት ይልቅ ስቀበር ብታየኝ እንደምትመርጥ ነገረችኝ።

“‘[ፊቢ]፣’ አለችኝ በሚያስደንቅ ሁኔታ፣ ‘የሞርሞን እምነት ሃሰት ሆኖ ካገኘሽው ወደ እኔ ትመለሻለሽ?’

“እኔም እንዲህ በማለት መለስኩላት ‘አዎ እማዬ፣ እመለሳለሁ።’ … መልሴ ለጭንቀቷ እፎይታ ቢሠጣትም መለያየታችን ግን ብዙ ሃዘንን አስከተለ። መሄጃዬ ሲደርስ ለመሰናበት ድፍረት አገኛለሁ ብዬ እራሴን አላመንኩትም፤ ስለዚህም ለሁሉም ስንብቴን በጽሁፍ አሠፈርኩኝና ጠረጴዛዬ ላይ አስቀምጬላቸው ደረጃው ቁልቁል እሮጬ ወረድኩና ጋሪው ላይ ተሳፈርኩኝ። እንዲህ ነበር፣ ውድ የልጅነት ቤቴን ትቼ ከእግዚአብሔር ቅዱሳን ጋር ህይወቴን ለማቀላቀል የሄድኩት።”

ከእነዚያ የስንብት ደብዳቤዎቿ ባንዱ ፊቢ እንዲህ ብላ ፅፋለች፦

“ውድ ወላጆቼ፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ ባላውቅም አሁን የወላጆቼን ቤት ትቼ ለጊዜው ልሄድ ነው—ነገር ግን ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ላገኘሁት ደግነት የአመስጋኝ ስሜቶች ሣላቀርብ አይደለም—ነገር ግን አምላክ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን ይህን ያዛል። ሁሉንም ነገር ለአምላክ ፍቃድ አሳልፈን እንስጥ እንዲሁም ከሁሉም ነገር አስበልጠን እግዚአብሔርን ከወደድነው ለበጎ እንደሚሆንልን በማመን፣ እስካሁን በአንድ ላይ ደስ በሚል ሁኔታዎች ውስጥ እንድንኖር ስለተፈቀደልን አመስጋኝ እንሁን። የሁሉንም ፍጡራን ልባዊ ጸሎት ወደሚሰማው እና ለእኛ መልካም የሆነውን ወደሚሰጠን ወደ አንድ እግዚአብሔር መጸለይ እንደምንችል እንወቅ። …

“እማዬ፣ የእኔ ወደ ምዕራብ መሄድ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ አምናለሁ እንዲሁም ፍቃዱ ይህ እንደሆነ ለረጅም ጊዜ አምን ነበር። አሁን መንገዱ ተከፍቷል … ፤ ይህን ያደረገው ለሁሉም በቂ የሆነው የጌታ መንፈስ እንደሆነ አምናለሁ። አቤቱ፣ እባካችሁ ስለልጃችሁ አትጨነቁ፤ እኔን ጌታ ያጽናናኛልና። ጌታ እንደሚጠብቀኝ እንዲሁም መልካም የሆነውን እንደሚሰጠኝ አምናለሁ። … የምሄደውም ጌታዬ ስለ ጠራኝ ነው—ሀላፊነቴንም ግልጽ አድርጓል።”

ማስታወሻዎች

  1. ኤድዋርድ ደብሊው. ቱሊጅ The Women of Mormondom [የሞርሞንነት ሴቶች] [1877 (እ.አ.አ)]፣ 412።

  2. ፊቢ ካርተር ለወላጆቿ የፃፈችው ደብዳቤ፣ ቀን የለውም፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻሕፍት፣ ሶልት ሌክ ሲቲ፤ ስርአተ ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል። ፊቢ ቤተክርስቲያኗን በ1834 (እ.አ.አ) ተቀላቀለች፣ በ1835 (እ.አ.አ) ወደ ኦሃዮ ተጓዘች፣ እንዲሁም በ1837 (እ.አ.አ) ውልፈርድ ውድረፍን አገባች።