ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መጋቢት 31–ሚያዝያ 6 (እ.አ.አ)፦ “ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቦቹን ይሰበስባል”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29


“መጋቢት 31–ሚያዝያ 6 (እ.አ.አ)፦ ‘ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቦቹን ይሰበስባል’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29”ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) 2025 (እ.አ.አ)

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ በአማኞች ተከቦ

መጋቢት 31–ሚያዝያ 6 (እ.አ.አ)፦ “ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቦቹን ይሰበስባል”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29

ምንም እንኳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በ1830 (እ.አ.አ) የተቋቋመች ብትሆንም፣ ብዙ የወንጌል እውነቶች ገና አልተገለጡም ነበር፣ እንዲሁም ብዙ ቀደምት የቤተክርስቲያኗ አባላት ጥያቄዎች ነበሯቸው። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ስለእስራኤል መሰባሰብና ስለፅዮን መገንባት ትንቢቶችን አንብበው ነበር (3 ኔፊ 21ን ተመልከቱ)። ያ የሚሆነው እንዴት ነው? ሀይረም ፔጅ ተቀበልኳቸው ያላቸው ራዕዮች በጉዳዩ መላ ምቶችን አስነስቷል ይህም የአባላቱን ጉጉት ይበልጥ ጨምሮታል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28)። ሌሎችም ሰዎች ስለአዳም እና ሔዋን ውድቀት እና ስለ ዘለአለማዊ ሞት አሰቡ። ጌታ እነዚህን ጥያቄዎች በ1830 (እ.አ.አ) ተቀብሎ ነበር፤ ዛሬም የእኛን ጥያቄዎች ይቀበላል። ለቅዱሳኑ እንዲህ ብሏቸዋል፣ “እንደ ትእዛዜ በጸሎት አንድ ሆናችሁ በእምነት የምትጠይቁትን ማንኛውንም ነገር ትቀበላላችሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥6)። በእርግጥም በአስተምህሮቱ ራእይ ሙሉ የሆነው ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29 እንደሚያሳየው፣ እርሱ አንዳንድ ጊዜ መልስ የሚሰጠው እኛ በመጀመሪያ ከጠየቅነው በላይ የበለጠ እውነትና እውቀትን በመጨመር ነው።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29

የሰማይ አባት ለልጆቹ ደህንነትእቅድ አለው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29 እግዚአብሔር ለእናንተ ስላለው እቅድ ብዙ እውነቶችን ያስተምራል። ስታነቡም፣ ስለሚከተሉት ስለእያንዳንዱ የእቅዱ ክፍሎች የምትማሯቸውን እውነቶች ፈልጉ፦

ምን ግንዛቤዎችን አገኛችሁ? የሚጠቅሟችሁ ከሆነ፣ በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ካሉት ምስሎች ጋር በተዘጋጀው ቦታ ላይ ልትጽፏቸው ትችላላችሁ። እነዚያ እውነቶች በህይወታችሁ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩት እንዴት ነው?

በተጨማሪም፣ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “የደህንነት ዕቅድ፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

ምስል
ወደ እኔ ኑ

ዝርዝሩ ከወደ እኔ ኑ፣ በጀነዲ ፔጅ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥1–28

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
ኢየሱስ ክርስቶስ ከዳግም ምፅዓቱ በፊት ህዝቦቹን በመሠብሰብ እንድረዳ ይጋብዘኛል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ስለህዝቦቹ መሰባሰብ የተናገረው “ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምሰበስብ” አድርጎ ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥2)። ይህ ንፅፅር ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ያስተምሯችኋል? በዚህ መዘርዝር ውስጥ ያሉትን የዶሮ እና የጫጩቶች ሥዕላዊ ማብራሪያ ስታጠኑ ምን ተጨማሪ ሀሳቦችን ወይም ግንዛቤዎችን አገኛችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰበስባችሁ እና ሲጠብቃችሁ ምን እንደተሰማችሁ አስቡ።

ትምህርትና ቃል ኪዳኖችን 29፥1–11ን ስታነቡ፣ስለሚከተሉት ግንዛቤዎችን ፈልጉ።

  • ማን እንደሚሰበሰብ።

  • ወደ ክርስቶስ “መሠብሠብ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ።

  • ወደ እርሱ የምንሰበስበው ለምን እንደሆነ።

ሌሎችን ሰዎች ወደ ክርስቶስ ለምን እንደምትሠበስቡ አሰላስሉ። ለመርዳት ትችሉ ዘንድ ምን ለማድረግ መነሳሳት ይሰማችኋል?

“A Witness of God [የእግዚአብሔር ምስክር]” (ወንጌል ላይብረሪ) የሚለውን ቪዲዮ በምትመለከቱበት ጊዜ ወይም ስለመሠብሠብ የሚናገሩ እንደ“Israel, Israel, God Is Calling [እስራኤል፣ እስራኤል፣ እግዚአብሔር እየጠራሽ ነው]” (መዝሙር፣ ቁ. 7) ያሉ መዝሙሮችን በምታነቡበት ወይም በምታዳምጡበት ጊዜ የራሳችሁን ተመሳሳይ ጥያቄዎች መጠየቅ ትችላላችሁ። ጌታ ስለመሠብሠብ ሥራው ምን ሊያስተምራችሁ እየሞከረ እንደሆነ ይሰማችኋል?

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፦ “አሁን ግን መሰብሰቡ የሚከናወነው በእያንዳንዱ አገር ውስጥ ነው። ጌታ ለቅዱሳኑ የትወለዱበትን እና ዜግነታቸውን በሰጣቸው በእያንዳንዱ ግዛት ጽዮን እንደምትመሰረት ተናግሯል” (“The Gathering of Scattered Israel [የተበተነችው እስራኤል መሰብሰብ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2006 (እ.አ.አ)፣ 81)። በዚህ መንገድ መሰብሰብ ለአዳኙ ዳግም ምፅዓት “በሁሉም ነገር እንድንዘጋጅ” የሚረዳን እንዴት ነው? (ቁጥር 8፣ በተጨማሪም ቁጥር 14–28ን ተመልከቱ)።

በተጨማሪም ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እና ዌንዲ ደብልዩ. ኔልሰን፣ “Hope of Israel [የእስራኤል ተስፋ]” [worldwide youth devotional፣ ሰኔ 3፣ 2018 (እ.አ.አ)]፣ ወንጌል ላይብረሪ፤ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “The Doctrine of Belonging [አባል የመሆን ትምህርት]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022(እ.አ.አ)፣ 53–56፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “Gathering of Israel [የስራኤል መሰብሰብ]፣” ወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥31–35

“ሁሉም ነገሮች ለእኔ መንፈሳዊ ናቸው።”

ትምህርትና ቃል ኪዳኖችን 29፥31–35ን ስታጠኑ፣ “ሁሉም ት ትዕዛዛት መንፈሳዊ የሆኑት በምን መልኩ ነው?” ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። ጥቂት ትዕዛዛትን ልትዘረዝሩና ከእያንዳንዳቸው ጋር የተያያዙትን መንፈሳዊ እውነቶች ግምት ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ። For the Strength of Youth፥ A Guide for Making Choices [ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ መከለስ ሊረዳ ይችላል—ከብዙ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ጀርባ ያሉትን አንዳንድ ዘለአለማዊ እውነቶች ያስተምራል።

“ሁሉም ነገሮች … መንፈሳዊ [መሆናቸውን]” ማወቃችሁ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በምትመለከቱበት መንገድ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው? በሌሎች የህይወታችሁ ዘርፎች ውስጥም መንፈሳዊ ትርጉምን ወይም ዓላማን መፈለግን አስቡ።

በተጨማሪም 2 ኔፊ 9፥39 ተመልከቱ።

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አተኩሩ። “እያንዳንዱን የወንጌል ርዕስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የማስተማር እና የመማር እድል [ነው] (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 6)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29 ስታነቡ ስለባሕርዩ፣ ስለሚናዎቹ እና ስለምሣሌነቱ ምን ትማራላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥36–50

ኢየሱስ ክርስቶስ ከውድቀት አድኖናል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ለምን እንደሚያስፈልገን ለማብራራት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥36–50ን መጠቀም የምትችሉት እንዴት ነው?

የአዳምና የሔዋን ውድቀት ሞትን እና ኃጢአትን ወደ ዓለም አመጣ፤ ሆኖም በክርስቶስ በኩል ቤዛውን እና ደስታ የምናገኝበትን መንገድም አዘጋጅቷል። ያንን ሃሳብ በአዕምሯችሁ በመያዝ ቁጥር 39–43ን አንብቡ እንዲሁም ደስታን የሚያመጡላችሁን ቃላት እና ሐረጋት አስተውሉ። በሙሴ 5፥10–12 ውስጥ አዳም እና ሔዋን ስለውድቀት ከተናገሩት ያስደነቃችሁ ምንድን ነው?

በተጨማሪም “Why We Need a Savior [አዳኝ ለምን ያስፈገናል]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29

የሰማይ አባት ለልጆቹ ደህንነት እቅድ አለው።

  • የሰማይ አባት ለእኛ ስላለው ዕቅድ ውይይት ለመጀመር፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ ለጉዞ ወይም አንድን ተግባር ለመፈፀም ዕቅድ ስላወጣችሁበት ጊዜ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። እንዲሁም በላዩ ላይ የሚከናወኑ ተግባራት የተፃፉበት የቀን መቁጠሪያ ወይም አንድን ነገር ለመስራት የሚያገለግሉ መመሪያዎችን የያዘ የዕቅዶች ምሳሌዎችን ማጋራት ትችላላችሁ። ዕቅዶች አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? ከዚያም የሰማይ አባት ምን ማከናወን እንደሚፈልግ እና እቅዱ እንዴት እንድንፈፅመው እንደሚረዳን መነጋገር ትችላላችሁ።

  • ልጆቻችሁ ስለሰማይ አባት እቅድ የተለያዩ ክፍሎች የሚያስተምሩ ጥቅሶችን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29 ውስጥ እንዲያገኙ ለመርዳት በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ያሉትን ምስሎች መጠቀም ትችላላችሁ። ምስሎቹን ቆርጣችሁ በማውጣት ልጆቻችሁ በትክክለኛው ቅደም ተከተል እንዲያስቀምጧቸው ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። የሰማይ አባት ለእኛ እቅድ እንዳለው በማወቃችን አመስጋኝ የምንሆነው ለምንድን ነው? ስለእርሱ ማወቃችን በእለት ተዕለት ኑሯችን ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥1–2፣ 7–8

ኢየሱስ ክርስቶስ ከዳግም ምፅዓቱ በፊት ህዝቦቹን ይሰበስባል።

  • ዶሮ ጫጩቶቿን ስትሰበስብ የሚያሳየው ሥዕላዊ መግለጫ ወይም “ጫጩቶች እና ዶሮዎች” ChurchofJesusChrist.org የሚለው ቪዲዮ ልጆቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥1–2 ውስጥ ያለውን ምሣሌ በአዕምሯቸው እንዲመለከቱ ይረዳቸዋል። ከዚያም፣ እነዚህን ጥቅሶች አብራችሁ ማንበብ እና ዶሮ ጫጩቶቿን የምትጠብቅበት መንገድ እና አዳኙ ለእኛ ሊያደርግልን ከሚችለው ነገር ጋር እንዴት እንደሚመሳሰል እርስ በርሳችሁ መነጋገር ትችላላችሁ።

    ምስል
    በክንፎቿ ስር ጫጩቶች የሰበሰበች እናት ዶሮ

    I Would Gather Thee [እሰበስባችኋለሁ]፣ በሊዝ ሌመን ስዊንድል

  • አዳኙ ህዝቡን እንዲሰበስብ ይረዱ ዘንድ ልጆቻችሁን ምን ሊያነሳሳቸው ይችላል? ምናልባት የእርሱን ቤተክርስቲያን በመቀላቀል ወደ እርሱ “የተሰበሰበን” ሰው ተሞክሮ መስማት ይፈልጉ ይሆናል። ለምሳሌ፣ ቤተሰባችሁን ስለቤተክርስቲያኗ ያስተዋወቃችሁ ማን ነው? ወደ እርሱ እንድንሰበሰብ የቀረበልንን ጥሪ በመቀበላችን እንዴት ተባርከናል? ሌሎች ወደ እርሱ እንዲሰበሰቡ እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን? (“ከፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ወደ ልጆ የተላከ መልዕክት” [ቪዲዮ]፣ ChurchofJesusChrist.org.ተመልከቱ)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥11

ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ይመጣል።

  • የአዳኙን ዳግም ምፅዓት የሚያሳይ (እንደ የወንጌል የአርት መፅሐፍ፣ቁ. 66) ምሥል ወይም ስለእርሱ የሚያወሳ (እንደ “When He Comes Again [ርሱ እንደገና ሲመጣ]፣የልጆች የመዝሙር መፅሃፍ፣ 82–83) መዝሙር እናንተ እና ልጆቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥11 ላይ እንድትወያዩ ሊረዳ ይችላል። ልጆቻችሁ በሥዕሉ ወይም በመዝሙሩ ውስጥ ካለው ነገር ጋር የሚዛመዱ ሐረጎችን በቅዱሳት መፃህፍት ውስጥ እንዲያስተውሉ እርዷቸው። ስለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር መምጣት ምን እንደሚሰማችሁ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።

ምስል
The resurrected Jesus Christ (wearing white robes with a magenta sash) standing above a large gathering of clouds. Christ has His arms partially extended. The wounds in the hands of Christ are visible. Numerous angels (each blowing a trumpet) are gathered on both sides of Christ. A desert landscape is visible below the clouds. The painting depicts the Second coming of Christ. (Acts 1:11)

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

አትም