“ሚያዚያ14–20 (እ.አ.አ)፦ ‘እኔ ህያውም ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ’፦ ፋሲካ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]
“ፋሲካ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
“ሚያዚያ14–20 (እ.አ.አ)፦ “እኔ ህያውም ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ”
ፋሲካ
ሚያዝያ 3 ቀን 1836 (እ.አ.አ) የፋሲካ ሰንበት ነበር። ቅዱስ ቁርባንን አዲስ በተመረቀው በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ለቅዱሳን ካሳለፉ በኋላ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ ከመጋረጃው በስተጀርባ ጸጥ ያለ ስፍራን መርጠው ለጸሎት ተንበረከኩ። በኋላም በሁሉም ስፍራ ክርስቲያኖች የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤ እያሰቡ ባለበት በዚህ በተቀደሰ ቀን፣ ከሞት የተነሳው አዳኝ እራሱ በቤተመቅደሱ ተገልጾ “እኔ ህያውም ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ” ሲል ተናገረ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥4)።
ኢየሱስ ክርስቶስ “ህያው ነው” ማለት ምን ማለት ነው? ከመቃብር ተነስቶ በገሊላ ለነበሩት ደቀ መዝሙሮቹ ተገለጸ ማለት ብቻ አይደለም። ዛሬም በህይወት አለ ማለት ነው። ዛሬም በነቢያት በኩል ይናገራል። ዛሬም የእርሱን ቤተክርቲያን ይመራል። ዛሬም የታመሙ ነፍሳትን ያድናል እንዲሁም የተሰበሩ ልቦችን ይጠግናል። እኛም የጆሴፍ ስሚዝን ጠንካራ የምስክርነት ቃላት፦ “ስለ እርሱ ከተሰጡት ብዙ ምስክሮች በኋላ፣ ይህም … ስለ እርሱ የምንሰጠው ምስክርነት፦ እርሱ ህያው … ነው!” በማለት ማስተጋባት እንችላለን። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥22)። በእነዚህ ራዕዮች ውስጥ ድምፁን ልንሰማ፣ በህይወታችን ውስጥ እጆቹ እንዳሉ ልንመሰክር እንችላለን እንዲሁም “‘አዳኜ ህያው እንደሆነ አውቃለው!’” የሚለው ይህ አረፍተ ነገር የሚሰጠው ደስታ ሊሰማን ይችላል። (መዝሙሮች፣ ቁ. 136)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው ነው።
አብዛኞቻችን ኢየሱስ ክርስቶስን ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳየው አላየነውም።። ነገር ግን እንደ እርሱ፣ አዳኙ ህያው እንደሆነ፣ ስኬቶቻችንን እና የምንቸገርባቸውን ነገሮች እንደሚያውቅ እንዲሁም በችግር ጊዜ እንደሚረዳን ልናውቅ እንችላለን። ከታች ባሉት ጥያቄዎች ላይ ስታሰላስሉ እና አብረዋቸው ያሉትን ፅሁፎች ስታጠኑ ስለህያው ክርስቶስ ያላችሁን የራሳችሁን ምስክርነት አስቡ።
-
ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው? የምናመልከው ለምንድን ነው? (“ህያው ክርስቶስ፦ የሐዋሪያት ምስክርነት)።
-
መንፈስ ስለ ጆሴፍ ስሚዝ እና አዳኙን ያዩ ሌሎች ሰዎች ስለነበሯቸው ተሞክሮዎች ምን ያስተምረኛል? ምስክርነታቸው የሚያጠነክረኝ እንዴት ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥11–14፤ 20–24፤ 110፥1–10፤ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 17 ተመልከቱ)።
-
ስለ አዳኙ ተልእኮ እና አምላክነት ከራሱ ቃላት ምን እማራለሁ? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥5፤ 38፥7 ተመልከቱ)።
-
ዛሬ አዳኙ ሊረዳኝ የሚችለው እንዴት ነው? (ኢሳይያስ 53፥3–5፤ ዕብራውያን 2፥17–18፤ ሞዛያ 3፥7፤ አልማ 7፥11–13፤ 36፥3፤ ኤተር 12፥27፤ ሙሴ 5፥10–12 ተመልከቱ)።
“My Spiritual Goal [መንፈሳዊ ግቤ]” በሚለው ቪዲዮ ውስጥ አንዲት ወጣት “ህያው ክርስቶስን” (ወንጌል ላይብረሪ) የሚለውን ምስክርነት ለማስታወስ ወስናለች። ስለእርሷ ተሞክሮ ምን ያስደንቃችኋል? “በህያው ክርስቶስ” ውስጥ ያሉትን እውነቶች በልባችሁ እና በአዕምሯችሁ ለመቀበል ምን ለማድረግ መነሳሳት ይሰማችኋል?
ዛሬ አዳኙ እንዴት እንደሚባርከን የበለጠ ለማወቅ፣ “I Know That My Redeemer Lives [አዳኜ እንደሚኖር አውቃለሁ]” (መዝሙር፣ ቁ. 136) የሚለውን መዝሙር ማጥናት፣ ማዳመጥ ወይም መዘመር ትችላላችሁ። በዚህ መዝሙር ውስጥ ያሉ፣ በትምሕርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥34፤ 84፥77፤ 98፥18፤ 138፥23 ውስጥም የተሰጡ ትምህርቶች እውነቶችን መፈለግ የሚያነሳሳ ሊሆን ይችላል።
በተጨማሪም ርዕሶች እና ጥያቄዎች “ኢየሱስ ክርስቶስ፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።
በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በትንሳኤ እነሳለሁ።
ጆሴፍ ስሚዝ፣ አባቱን እና ሁለት ወንድሞቹን ጨምሮ የሚወዱትን ሰው በማጣት የሚያመጣውን ሃዘን ያውቃል። ጆሴፍ እና ኤማ፣ እያንዳንዳቸው ከሁለት አመት በታች የሆኑ ስድስት ልጆችን ቀብረዋል። ጆሴፍ እና ኤማ እግዚአብሔር ከሰጣቸው ራዕዮች ዘለዓለማዊ እይታን አግኝተዋል።
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥26–27፤ 42፥45–46፤ 63፥49፤ 88፥14–17፣ 27–31፤ 93፥33–34 ውስጥ ስለሞት እና ስለእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ዕቅድ የሚገልፁ እውነቶችን ፈልጉ። እነዚህ እውነቶች ስለሞት ያላችሁን አስተሳሰብ የሚነኩት እንዴት ነው? በአኗኗራችሁስ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?
በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 15፤ Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፦ ጆሴፍ ስሚዝ] (2007 [እ.አ.አ])፣ 174–76 Easter.ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኔ “ፍጹም የኃጢያት ክፍያን” አከናውኗል።
በፋሲካ ወቅት በአዳኙ ላይ ለማተኮር የሚረዳ አንደኛው መንገድ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ያሉትን ስለኃጢያት ክፍያው የሚገልፁ ራዕዮች ማጥናት ነው። አንዳንዶቹ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–13፤ 19፥16–19፤ 45፥3–5፤ 76፥69–70 ውስጥ ይገኛሉ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የምታገኟቸውን እውነቶች ዝርዝር ማዘጋጀት ትችላላችሁ። ጥናታችሁን ጥልቅ ለማድረግ፣ ከሉቃስ 22፥39–44፤ 1 ዮሐንስ 1፥7፤ 2 ኔፊ 2፥6–9፤ ሞዛያ 3፥5–13፣ 17–18፤ ሞሮኒ 10፥32–33 በመፈለግ በዝርዝራችሁ ውስጥ መጨመር ትችላላችሁ።
ጥናታችሁን ሊመሩላችሁ የሚችሉ አንዳንድ ጥያቄዎች እነሆ፦
-
የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምንድን ነው?
-
ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ ለመሰቃየት እና ለመሞት የመረጠው ለምንድን ነው?
-
የእርሱን መስዋዕትነት በረከት ለመቀበል ማድረግ ያለብኝ ምንድን ነው?
-
እነዚህን ጥቅሶች ካነበብኩኝ በኋላ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ስሜት አለኝ?
በተጨማሪም የቅዱሳት መፃህፍት መመሪያ፣ “የኃጢያት ክፍያ፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ “The Savior Suffers in Gethsemane [አዳኝ በጌቴሴማኒ ተሰቃየ]” (ቪዲዮ)፣ በየወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በትንሳኤ እነሳለሁ።
-
ልጆቻችሁን ስለ ትንሣኤ ለማስተማር፣ የአዳኙን ሞት እና ትንሳኤ የሚያሳዩ ምስሎችን በማሳየት መጀመር ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ስለእነዚህ ክስተቶች የሚያውቁትን እንዲያካፍሉ ፍቀዱላቸው። “Did Jesus Really Live Again? [ኢየሱስ በእውነት ህያው ነውን?]፣” የሚለውን መዝሙር ልትዘምሩም ትችላላችሁ። የልጆች መዝሙር መፅሀፍ 64)።
-
ልጆቻችሁ ስንሞት ምን እንደሚፈጠር (መንፈሳችን እና አካላችን እንደሚለያዩ) እና በትንሣኤ ከሞት ስንነሳም (መንፈሳችን እና አካላችን አንድ እንደሚሆኑ፣ እንዲሁም አካላችን ፍጹም እና የማይሞት እንደሚሆን) እንዲገነዘቡ የሚረዳ የተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ትምህርትን አስቡ። ለምሳሌ፣ ከእጅ መብራት ውስጥ ባትሪ ድንጋዩን ወይም ከስኪርቢቶ ውስጥ የቀለም መያዣውን ስናወጣው ምን ይሆናል? ወደ ቦታቸው ሲመለሱስ ምን ይሆናል? (አልማ 11፥43–45 ተመልከቱ።)
-
ልጆቻችሁ የሞተን አንድ ሰው ያውቃሉ? ስለእነዚህ ግለሠቦች የተወሰነ እንዲያካፍሉ ፍቀዱላቸው፤ ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥17 ን በአንድነት አንብቡ። የምንወዳቸው ሰዎች ከሞት እንደሚነሱ እና እንደገና አካል እንደሚኖራቸው ማወቅ ምን ሥሜት እንደሚፈጥር እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።
-
ትልልቅ ልጆች ካሏችሁ፣ በሚቀጥሉት ምንባቦች ውስጥ የፋሲካን መልእክት የሚይዙ ሀረጎችን እንዲፈልጉ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥49፤ 88፥14–17፣ 27፤ 138፥11፣ 14–17። Because He Lives [ህያው ስለሆነም]” (የወንጌል ላይብረሪ) በሚለው ቪዲዮም እንዲሁ ማድረግ ትችላላችሁ። ይህን መልዕክት ለሌሎች ሰዎች ማካፈል የምንችለው እንዴት ነው?
ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ኢየሱስ ክርስቶስን አየው።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለሌሎች ስለተገለጠባቸው ሦስት የተለያዩ ጊዜያት በጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥14–17፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥11–24፤ 110፥1–10 ውስጥ ለማንበብ ትፈልጉ ይሆናል። ልጆቻችሁ የእነዚህን ክስተቶች ምስሎች በዚህ ሣምንት የአክቲቪቲ ገፅ ውስጥ ማየት ይችላሉ። ከእነዚህ ከእያንዳንዱ ተሞክሮዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንማራለን? ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች ከሞት የተነሳውን አዳኝ እንዳዩ ማወቅ በረከት የሆነው ለምንድን ነው?
በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት፣ ለኃጢአቴ ይቅርታን አገኛለሁ።
-
ጆሴፍ ስሚዝ በክርስቶስ በኩል ስለሚገኘው ይቅርታ የተማረው እውነት፣ ልጆቻችሁ ስህተታቸው እና ኃጢአታቸው ይቅር እንደሚባልላቸው ተስፋ ሊሰጣቸው ይችላል። ልጆቻችሁ እንደዚህ አይነት ርዕስ ያለው ሠንጠረዥ እንዲያዘጋጁ መጋበዝን አስቡ፦ አዳኙ ለእኔ ያደረገውን እና ይቅርታውን ለማግኘት ማድረግ ያለብኝ ነገር። ልጆቻችሁ፣ በእነዚህ ርዕሶች ስር ሊገቡ የሚችሉትን ነገሮች ለማግኘት በሚከተሉት ምንባቦች ውስጥ እንዲፈልጉ እርዷቸው፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–13፤ 19፥16–19፤ 45፥3–5፤ 58፥42–43። አዳኙ ስላደረገላችሁ ነገር የሚሰማችሁን ደስታ እና ምስጋና አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።
-
እንዲሁም “The Shiny Bicycle [የሚያንጸባርቀው ቢስክሌት]” (የወንጌል ላይብረሪ) የሚለውን ቪዲዮ ከልጆቻችሁ ጋር ልታዩና ንስሀ ስትገቡ የአዳኙ ይቅርታ የተሰማችሁን ጊዜ ተሞክሮዎች ልታካፍሉ ትችላላችሁ።