ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሚያዚያ 21–27 (እ.አ.አ)፦ “አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37–40


“ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 21–27፦ ‘አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37–40፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37–40፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ቅዱሳን ለመጓዝ ሲዘጋጁ

ዝርዝር ከቅዱሳን ወደ ከርትላንድ ሲጓዙ፣ በሳም ላውሎር

ሚያዝያ 21–27 (እ.አ.አ)፦ “አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37–40

ቤተክርስቲያኗ፣ ለቀደምት ቅዱሳን፣ እሁድ ስብከት ከሚሰሙባት ሥፍራ በላይ ነበረች። ራዕዮቹ ምክንያትመንግሥትፅዮን፣ እና በተደጋጋሚ፣ ሥራ የመሣሠሉ ቃላትን ተጠቅመዋል። ምናልባትም፣ ብዙዎቹን ቀደምት አባላት ወደ ቤተክርስቲያን እንዲሳቡ ያደረጋቸው በከፊል ያ ሊሆን ይችላል። ትምህርቱን የወደዱትን ያህል፣ ብዙዎቹ በህይወታቸው የሚሠጡለትን ነገርም ጭምር ይፈልጉ ነበር። ይህም ቢሆን፣ ጌታ በ1830 (እ.አ.አ) ወደ ኦሃዮ እንዲሠባሠቡ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ ማክበር ቀላል አልነበረም። ለብዙዎች የተደላደለ ቤትን ትቶ ወደማይታወቅ ጠረፍ መጓዝ ማለት ነበር (“በዳግም የመመለስ ድምጾች፦ ወደ ኦሀዮ መሰብሰብ” ተመልከቱ)። ዛሬ እኛ እነዚያ ቅዱሳን በእምነት አይናቸው ብቻ ሊያዩት የሚችሉትን በግልጽ ማየት እንችላለን፦ ጌታ ታላቅ በረከቶች በኦሃዮ አሰናድቶላቸው ነበር።

በኦሃዮ መሰብሰብ አስፈላጊ መሆኑ ካለዘ ብዙ ጊዜ አልፏል፣ ነገር ግን ዛሬም ቅዱሳን “ፅዮንን [በማምጣት]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39፥13) ተመሳሳይ አላማ ህብረትን ይፈጥራሉ። ልክ እንደእነዚያ ቀደምት ቅዱሳን፣ እኛም “ለአለም መጨነቅን” እድንተው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 40፥2) እና “የማታውቀውን ታላቅ በረከት ትቀበላለህ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39፥10) የሚለውን የጌታን ቃል ኪዳን እንድናምን ተጋብዘናል።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥109–11ን ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37–38

እግዚአብሔር ሊባርከን ያሠባሥበናል።

በፋየት፣ ኒው ዮርክ ውስጥ የነበሩ የቤተክርስቲያኗ አባላት በ1831 (እ.አ.አ) ክረምት ወደ ኦሃዮ (ከ250 ማይል ርቀት በላይ) ለመጓዝ አስቸጋሪ መስዋዕቶችን መክፈል ነበረባቸው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37፥3–4 ውስጥ ስለጌታ ትዕዛዝ ስታነቡ፣ ጌታ እንድትከፍሉ ስለጠየቃችሁ መስዋዕትነት ልታስቡ ትችላላችሁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥1–33ን ስታጠኑ፣ ምክሩን እንድትከተሉ እምነት የሚሰጧችሁን የአዳኙን እውነቶች ፈልጉ። ከቁጥር 11–33 ውስጥ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች በመሰባሰብ ስለሚመጡ በረከቶች ምን ትማራላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥22

“ድምጼን ስሙና ተከተሉኝ።”

ኢየሱስ ክርስቶስን “ህግ ሰጪ[ያችሁ]” ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? የእርሱን ትዕዛዝ መከተል “ነጻ ህዝብ” የሚያደርጋችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም 2 ኔፊ 2፥26–27 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥30

ከተዘጋጀሁ፣ ፍርሐት አይኖረኝም።

ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥30 ውስጥ የገለፀውን “ከተዘጋጃችሁ ፍርሀት አይኖራችሁም” የሚለውን መርህ በራሳችሁ ህይወት ያያችሁት መቼ ነበር? እናንተ ቁጥር 38ን ስታነቡ፣ የወደፊቱን በድፍረት መጋፈጥ እንዲችሉ ጌታ ቅዱሳኑን እንዴት እንደሚያዘጋጃቸው አስተውሉ። በዚያን ጊዜ ፍርሃት እንዳይኖራችሁ ለአስቸጋሪ ሁኔታዎች እንድትዘጋጁ የሚፈልገው እንዴት ነው?

በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “We Will Prove Them Herewith [ዚህ እንፈትናቸዋለን]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 8–11 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥24–27

የሴሚናሪ ምልክት
እግዚአብሔር “አንድ [እንድንሆን]” ይፈልጋል።

በኦሃዮ የተሠባሠቡ ቅዱሳን ከተለያዩ ሁኔታዎች የመጡ ነበሩ። በአጥቢያችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁኔታም ተመሳሳይ ይሆናል። ሆኖም ጌታ፣ ህዝቦቹ “አንድ [እንዲሆኑ]” ያዛል (ቁጥር 27)። እንዲህ ዓይነት አንድነት ልናረጋግጥ የምንችለው እንዴት ነው? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥24–27ን ስታነቡ ምን ምን ሃሳቦች ወደ አዕምሯችሁ መጡ? የእግዚአብሔር ህዝብ ለመሆን አንድ መሆን የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

እነዚህን ጥቅሶች ማንበብ፣ ለምሳሌ፣ ከቤተሰብ አባላት፣ ከአጥቢያ አባላት እና ከቡድን ወይም ከክፍል አባላት ጋር ስለሚኖራችሁ ግንኙነቶች እንድታስቡ ሊያነሳሳችሁም ይችላል። በክርስቶስ አንድ ከመሆን የሚያግዳችሁ ምንድን ነው? አዳኙ [አንድ እንድትሆኑ] የሚረዳችሁ እንዴት ነው? “A Friend to All [ለሁሉም ጓደኛ]” ወይም “Love in Our Hearts [ፍቅር በልባችን]” (የወንጌል ላይብረሪ) የመሣሠሉ ቪዲዮዎች እነዚህን ጥያቄዎች እንድትመልሱ ሊረዷችሁ ይችላሉ። በዴል ጂ. ረንለንድ፣ “የክርስቶስ ሰላም ጠላትነትን ያስወግዳል፣” (ሊያሆና፣ ህዳር. 2021 (እ.አ.አ)፣ 83–85) መልዕክት ውስጥ ሃሳቦችን ልታገኙም ትችላላችሁ።

4:0

A Friend to All

3:14

Love in Our Hearts

እነዚህ ቡድኖች ይበልጥ አንድ እንዲሆኑ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው? ለምሳሌ፣ ለቡድናችሁ፣ ለክፍላችሁ ወይም ለቤተሰባችሁ አባላት ደግነት የተሞላበት ማስታወሻ መላክን ወይም የፅሑፍ መልዕክት መላክን አስቡ። እነማንን ለማግኘት መነሳሳት ይሰማችኋል?

ኤፌሶን 2፥14፣ 18–222 ኔፊ 26፥24–28 ውስጥ ስለው የአዳኙ ምሳሌ የሚያነሳሳችሁ ምንድን ነው?

በተጨማሪም ክውንተን ኤል. ኩክ፣ “Hearts Knit in Righteousness and Unity [ልቦች በጻድቅነት እና አንድነት ተሳስሮ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 18–21፤ “Love One Another [እርስ በራስ ተዋደዱ]፣” መዝሙር፣ ቁ. 308፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “Belonging in the Church of Jesus Christ [በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መቀላቀል]፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ወጣት ወንዶች በአፍሪካ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥3939–40

የሰማይ አባት የዘለዓለም ሃብት ሊሰጠኝ ይፈልጋል።

በእናንተ አስተያየት፣ “በምድር ሀብት” እና “በዘለዓለም ሀብት” መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥39)። ለዘለዓለም ሃብት ዋጋ እንድትሠጡ ምን ልምዶች አስተምረዋችኋል?

ቁጥር 39–40 ውስጥ (በክፍል አርዕስቶች ውስጥ ያሉትን ታሪካዊ አመጣጥ ጨምሮ) ስለጄምስ ኮቬል ስታነቡ ይህንን በአዕምሯችሁ ያዙ። የእርሱ ተሞክሮ እናንተን እንዴት እንደሚመለከት አስቡ። ለምሳሌ “[ልባችሁ በእግዚአብሔር] ፊት መልካም” የነበረበትን ጊዜ አስቡ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 40፥1)። በታማኝነታችሁ ምክንያት የተባረካችሁት እንዴት ነበር? እንዲሁም ምን ዓይነት “ለአለም መጨነቅ” እንደሚገጥሟችሁ አስቡ። እነዚህ እንዴት የእግዚአብሔርን ቃል “በደስታ” ከመቀበል ሊያግዷችሁ ይችላሉ? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39፥940፥2። በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ የበለጠ ያለማቋረጥ ለእግዚአብሔር ታዛዥ እንድትሆኑ የሚያነሳሳችሁን ምን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ማቴዎስ 13፥3–23 ተመልከቱ።

ቅዱሳት መጻህፍትን በህይወታችሁ ካሉት ሁኔታዎች ጋር አመሳስሉ። “ተማሪዎች [የቅዱሳት መፃህፍት] አግባብነት እንዲመለከቱ የምትረዱበት አንደኛው መንገድ ‘ይሄ አሁን ባጋጠማችሁ ነገር ላይ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?’ ‘ይህንን ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?’ ‘ይህ በህይወታችሁ ውስጥ ምን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል?’ የመሰሉ አይነት ጥያቄዎችን በመጠየቅ ነው።” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 23) ስለ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39–40 በዚህ አክቲቪቲ ውስጥ ያሉት ጥያቄዎች እነዚህን ራዕዮች በህይወታችን ውስጥ ተግባራዊ እንድናደርግ የሚረዱን የሌሎች ጥያቄዎች ምሳሌዎች ናቸው።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37፤ 38፥31–33

እግዚአብሔር ሊባርከን ያሰባስበናል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥24–27

እግዚአብሔር “አንድ እንድንሆን” ይፈልጋል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥24–25ን ከልጆቻችሁ ጋር ስታነቡ፣ ወንድምህን ወይም እህትህን እንደራስህ ተመልከት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተነጋገሩ (ማቴዎስ 7፥12)። “ወንድምህን” የሚለውን አንዳቸው የሌላቸውን ስም በመተካት ጥቅሱን እንዲደግሙ እርዷቸው።

  • ልጆቻችሁን “አንድ መሆን” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥27) ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማስተማር፣ 1 ቁጥርን በትልቁ እንዲስሉና በቤተሰባችሁ ወይም በክፍላችሁ ባለ በእያንዳንዱ ሰው ሥም እና ሥዕሎች ወይም ፎቶዎች ማስጌጥ ትችላላችሁ። ከ1 አጠገብ የበለጠ አንድ ለመሆን የሚረዷችሁን የምትፈጽሟቸውን ነገሮች መጻፍ ትችላላችሁ።

  • ነገሮች እንዴት ሊዋሃዱ ወይም አንድ ለመሆን ሊጣመሩ እንደሚችሉ የሚያሳይ ለምሳሌ ተሰፍተው አንድ ብርድ ልብስ ሊሆኑ የሚችሉ የጨርቅ ቁርጥራጮች ወይም አንድ ዳቦ ለመጋገር የሚያስፈልጉ ንጥረ ነገሮች የመሣሰሉ የተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮችን ማካፈልን አስቡ። እነዚህ ምሳሌዎች እንደ አምላክ ህዝብ አንድ ስለመሆን ምን ያስተምሩናል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥30

ከተዘጋጀሁ፣ ፍርሐት አይኖረኝም።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥17 አብራችሁ ስታነቡ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ ዝግጅትን ይጠይቅ ስለነበረ አንድ የቅርብ ጊዜ ተሞክሮ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ከዚያም የሰማይ አባት እንድንዘጋጅባቸው ስለሚፈልጋቸው ነገሮች ልጆቻችሁን ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። መዘጋጀታችሁ እንዳትፈሩ የረዳበትን አንድ ተሞክሮ ለልጆቻችሁ አካፍሉ። “Men’s Hearts Shall Fail Them [የሰዎች ልብ ይወድቅባቸዋል]” (የወንጌል ላይብረሪ) የሚለውን ቪዲዮ በአንድነት ልትመለከቱም ትችላላችሁ።

3:24

Men's Hearts Shall Fail Them

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39፥6፣ 23

ማረጋገጫ ሲሰጠኝ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀበልኩ።

  • ማረጋገጫ እየተቀበለ ያለ ግለሠብን ምሥል ማሳየትን አስቡ። ልጆቻችሁ በሥዕሉ ላይ ምን እየተከናወነ እንደሆነ እንዲገልጹ ጠይቋቸው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39፥6፣ 23 (ወይም እንደ “መንፈስ ቅዱስ፣” የልጆች የመዝሙር መፅሀፍ፣ 105 ባሉ መዝሙሮች ውስጥ)፣ መንፈስ ቅዱስ የሚሉትን ቃላት በሚሰሙበት ጊዜ ወደ ሥዕሉ እንዲያመለክቱ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንዴት እንደባረካችሁ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።

ወጣት ሴት ልጅ ማረጋገጫ እየተቀበለች

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።