ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 7–13 (እ.አ.አ)፦ “ድምጻችሁን … ከፍ [አድርጉ] …ወንጌሌን … [አውጁ]”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30–36


“ሚያዝያ 7–13 (እ.አ.አ)፦ “ድምጻችሁን … ከፍ [አድርጉ] …ወንጌሌን … [አውጁ]”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30–36፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30–36፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ቀደምት ሚስዮናውያን

ሚያዝያ 7–13 (እ.አ.አ)፦ “ድምጻችሁን … ከፍ [አድርጉ] …ወንጌሌን … [አውጁ]”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30–36

ፓርሊ ፒ. ፕራት ጥሪ ደርሶት “ወደ ምድረበዳ” ሄዶ ወንጌልን እንዲሰብክ ሲጠየቅ ገና የአንድ ወር ገደማ የቤተክርስቲያን አባል ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 32፥2)። ቶማስ ቢ. ማርሽ “የተልዕኮህ ሰዓት መጥቷልና” ተብሎ ሲነገረው፣ በዚያ ጊዜ ላነሰ ጊዜ ነበር አባል የነበረው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 31፥3)። ኦርሰን ፕራት፣ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ፣ እናም ሌሎችም ብዙዎች እንደዚሁ የአገልግሎት ጥሪያቸውን ሲቀበሉ ገና የተጠመቁ አባላት ነበሩ። ምናልባት ከዚህ ሂደት ዛሬ ለእኛ የሚሆን ትምህርት አለ፦ ዳግም የተመለሰውን ወንጌል በጥምቀት ለመቀበል በቂ እውቀት ካላችሁ፣ ለሌሎች ለማካፈልም በቂ እውቀት አላችሁ። በእርግጥ ሁላችንም የወንጌል እውቀታችንን ሁልጊዜ ለማሳደግ እንፈልጋለን፣ ነገር ግን እግዚአብሔር “ያልተማሩት” የእርሱን ወንጌል እንዲሰብኩ ለመጥራት አመንትቶ አያውቅም (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 35፥13)። በእርግጥም፣ እርሱ ሁላችንንም “ወንጌሌን ለማወጅ [አንደበታችሁን ክፈቱ]” በማለት ሁላችንንም ይጋብዘናል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30፥5)። እናም ይህንንም ከሁሉ በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ የምናደርገው በራሳችን ጥበብና ተሞክሮ ሳይሆን ነገር ግን “[በመንፈስ] ኃይል” ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 35፥13).

በተጨማሪም “The Faith and Fall of Thomas Marsh [የቶማስ ማርሽ እምነት እና ወድቀት]፣” “Ezra Thayer፥ From Skeptic to Believer [እዝራ ታየር፥ ከተጠራጣሪነት ወደ አማኝነት]፣” “Orson Pratt’s Call to Serve [የኦርሰን ፕራት አገልግሎት ጥሪ]፣” ራዕይ በአገባብ፣ 54–69 ውስጥ ተመልከቱ።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30–36

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር እንድሆን ተጠርቻለሁ።

እንደ ሚስዮናዎ መደበኛ ጥሪ ኖራችሁም አልኖራችሁም “በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገር፣ [በሁሉም] ቦታዎች” የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር (ሞዛያ 18፥9) መሆን ትችላላችሁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30–36ን ስታጠኑ፣ ወንጌልን ለማካፈል ስላሏችሁ እድሎች የምትማሯቸውን መዝግቡ። ወንጌሉን በምታካፍሉበት ጊዜ ጌታ እናንተን የሚጠይቃችሁን ነገሮች ዝርዝር እና ጌታ ቃል የገባቸውን ነገሮች ዝርዝር ልታዘጋጁ ትችላላችሁ (ለምሳሌ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30፥831፥3–532፥1535፥13–15፣ 24 ተመልከቱ)። በተጨማሪም ወንጌልን ለማካፈል የሚረዷችሁን መርሆዎች ልትፈልጉ ትችላላችሁ። “የታላቅ ደስታ የምስራችንም [ለማወጅ]” የሚያነሳሳችሁ ምን ታገኛላችሁ? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 31፥3)።

ሽማግሌ ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን ወንጌልን ማወጅ “ከልጅነት ጀምሮ እያንዳንዳችን በተማርነው ቀላል በሆኑ እና በቀላሉ ለመረዳት በሚያስችሉ መርሆች፦ ፍቅር፣ ማካፈል እና መጋበዝ በኩል ሊሳካ ይችላል” ሲሉ አስተምረዋል (“ለመውደድ፣ ለማካፈል፣ ለመጋበዝ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 85)። ስለምታውቋቸው ሰዎች፣ ስለጓደኞቻችሁ እና ስለቤተሰባችሁ እያሰባችሁ መልዕክቱን ማጥናትን አስቡ። “ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል [የምትወዱትን]” ማካፈል ስለምትችሉበት መንገድ ምን ሃሳቦች መጡላችሁ? “እንዲመጡና እንዲያዩ”፣ “እንዲመጡና እንዲያገለግሉ” እንዲሁም “እንዲመጡና የዚያ አካል እንዲሆኑ” ልትጋብዟቸው የምትችሉት በምን ዓይነት መንገዶች ነው? “I’ll Go Where You Want Me to Go [እንድሄድ ወደምትፈልገኝ እሄዳለሁ]” (መዝሙር፣ ቁ. 270) ወይም ከዚህ ጋር የሚመሳሰል መዝሙር ስትዘምሩ ወይም ስታዳምጡ ራሳችሁን “ወንጌሉን ለማካፈል ጌታ ምን እንድል እና እንድሆን ይፈልጋል?” ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ማርኮስ ኤ. አይዱካይተስ፣ “Lift Up Your Heart and Rejoice [ብህን አንሳ እናም ተደሰት]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 40–43፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “Inviting All to Receive the Gospel of Jesus Christ [ሁሉንምም የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን እንዲቀበሉ ጋብዙ]፣” “Ministering as the Savior Does [አዳኝ እንደሚያደርገው ማገልገል]፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ “Inviting All to Come unto Christ: Sharing the Gospel [ሁሉም ወደክርስቶስ እንዲመጡ ጋብዙ፦ ወንጌልን መካፈል]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት ተመልከቱ።

ምስል
እህት ሚስዮናውያን የሴቶች ስብስብን ሲያስተምሩ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 31፥1–2፣ 5–6፣ 9፣ 13

ጌታ ከቤተሰቦቼ ጋር ባለኝ ግንኙነት ሊረዳኝ ይችላል።

በ1830 (እ.አ.አ) አካባቢ የነበሩ ቤተሰቦች አሁን ካሉ ቤተሰቦች ጋር ብዙ ተመሳሳይ ችግሮች ነበሩባቸው። ጌታ ለቶማስ ቢ. ማርሽ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 31 (በተለይ ቁጥር 1–2፣ 5–6፣ 9፣13 ተመልከቱ) ውስጥ ስለቤተሰቡ ምን አይነት መመሪያ እና ቃል ኪዳን ሰጠው? የእርሱ ቃል በቤተሰባችሁ ግንኙነት እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?

ስለ ቶማስ ማርሽ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቅዱሳን፣ 1፥79–80119–20ን ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 32–3335

ጌታ እንድሰራ ለሚፈልገው ስራ ያዘጋጀኛል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 32–3335 ውስጥ ጌታ እንድትሰሩት ለሚፈልገው ስራ እንዴት እያዘጋጃችሁ እንደሆነ እንድታውቁ ሊረዳችሁ ይችላል። ለምሳሌ፣ “የዳግም መመለስ ድምፆች፦ ቀደምት ተቀያሪዎች” ውስጥ በፓርሊ ፒ. ፕራት እና ስድኒ ሪግደን መካከል ስለነበረው ግንኙነት ልታነቡ ትችላላችሁ። ይህ ግንኙነት የእግዚአብሔርን ልጆች የባረከው እንዴት ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 35 ተመልከቱ)።

ሌላ ምሳሌ እነሆ፦ ዕዝራ ታየር ከመጠመቁ ጥቂት ቀደም ብሎ ራዕይ እንዳየ በመጻፍ እንዲህ ብሏል፣ “አንድ ሰው መጣና ጥቅልል ወረቀት አመጣልኝ እና ሠጠኝ፣ ጥሩምባም ሰጠኝና [ተጫወተው] አለኝ። በህይወቴ ምንም [ተጫውቼ] እንደማላውቅ ነገርኩት፡፡ [ልትጫወተው] ትችላለህ፣ ሞክረው አለኝ። … እስካሁን ከሰማሁት እጅግ የሚያምር ድምጽ አሰማ” (“Revelation, October 1830–B, Revelation Book 1 [ራዕይ፣ ጥቅምት 1830 (እ.አ.አ)–ለ፣ ራዕይ መፅሐፍ 1]፣” historical introduction [ታሪካዊ መግቢያ]፣ josephsmithpapers.org)፡፡ በኋላም፣ አሁን ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33 ውስጥ የተመዘገበውን ራዕይ ጆሴፍ ስሚዝ ለዕዝራ ታየር እና ለኖርዝሮፕ ስዊት ሲቀበል፣ ዕዝራ ራዕዩን በራሱ ራዕይ ያየው ጥቅል ወረቀት እንደሆነ ተረጎመው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33፥1–13 ውስጥ ለሠጠው ተልዕኮ ጌታ እንዴት እያዘጋጀው ነበር?

በእነዚህ ቀደምት የቤተክርስቲያን አባላት ህይወት ውስጥ የጌታ እጅ እንደነበረ ምን ማስረጃ ታያላችሁ? ወደ ክርስቶስ እንድትመጡ እንዲረዳችሁ ጌታ በህይወታችሁ ያስቀመጠው ማንን ነው? በታማኝነታችሁ፣ በፍቅራችሁ ወይም በምታቀርቡት ግብዣ ሌሎችን እንድትባርኩ እያዘጋጃችሁ ያለው እንዴት ነው?

በተጨማሪም “A Mission to the Lamanites [ተልዕኮ ወደ ላማናውያን]፣ ” ራዕይ በአገባብ፣ 45–49 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33፥12–18

ህይወቴን በአዳኙ ወንጌል ላይ ከገነባሁ አልወድቅም።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33 የተጻፈው ኖርዝሮፕ ስዊት እና እዝራ ታየር ለተባሉ ሁለት አዲስ የተቀየሩ አባላት ነበር። ኖርዝሮፕ ይህ ራዕይ ከተሰጠ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ቤተክርስቲያኗን ለቆ ሄደ። እዝራም ለተወሰነ ጊዜ ታማኝ ሆኖ አገለገለ፣ ነገር ግን እርሱም በመጨረሻም ተሰናከለ። በዚህ ክፍል ውስጥ ስለእነርሱ ማንበብ ህይወታችሁ ምን ያህል በወንጌሉ “አለት ላይ” (ቁጥር 13) ጠንካራ ሆናችሁ እንደተገነባችሁ እንድታስቡ ሊያነሳሳችሁ ይችላል። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የትኞቹ እውነታዎች በአዳኙ እንደታመናችሁ እንድትቀጥሉ ይረዷችኋል?

በተጨማሪም ሔለማን 5፥12ን ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የጥናት ምልክት

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30፥1–2

ከምድር ነገሮች ይልቅ በእግዚአብሔር ነገር ላይ የበለጠ ማተኮር አለብኝ።

  • ልጆቻችሁ የሁሉም የቤተሰብ አባላቶቻቸውን ስም እንደመፃፍ እና የሚወዱትን መዝሙር በአዕምሯቸው እንደመያዝ ያሉ ሁለት ተግባራትን በአንድ ጊዜ ለመስራት መሞከር የሚያስደስታቸው ሊሆን ይችላል። ሁለት ነገሮችን በአንዴ መሥራት አስቸጋሪ የሆነው ለምንድን ነው? ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30፥1–2ን አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። ኢየሱስ ክርስቶስን እና ወንጌሉን ከማስታወስ ትኩረታችንን ሊከፋፍሉ የሚችሉ አንዳንድ “ምድ[ራዊ] ነገሮች” ምን ምን ናቸው። ትኩረታችንን በእርሱ ላይ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33፥2–3፣ 6–10

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማካፈል እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33፥8–10ን እንዲገነዘቡ ለማድረግ አፋቸውን ዘግተው አንድ ሐረግ እንዲናገሩና ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ ከዚያም እናንተ ወይም ሌሎች ልጆቻችሁ ምን እየተናገሩ እንደሆነ በግምት ሞክሩ ። ቁጥር 8–10 አንብቡና “አፋችሁን ክፈቱ” የሚለው ሃረግ ሲደገም አፋቸውን እንዲከፍቱ ጠይቋቸው። የሰማይ አባት አፋችንን እንድንከፍት እና ወንጌልን ለሌሎች እንድናካፍል የሚፈልገው ለምንድነው? ስለ አዳኙ ወይም ስለ ወንጌሉ ለቤተሰባችን እና ለጓደኞቻችን ምን ልንነግራቸው እንችላለን? እንደ “We’ll Bring the World His Truth [እውነቱን ለአለም እናመጣለን]፣” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 172) ያሉ ወንጌልን ስለማካፈል የሚያወሡ መዝሙሮችን ልትዘምሩም ትችላላችሁ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 30–34 ውስጥ ካሉት መርሆዎች ወይም ቃል ኪዳኖች ጋር የተያያዙ ያሏችሁን ተሞክሮዎች ማካፈልን አስቡ። አዳኙን ስታገለግሉት ስለ እርሱ እና ስለ ስራው ምን ተማራችሁ ወይም ምን ተሰማችሁ?

ምስል
ልጆች ተሰብስበው መጽሔት ሲመለከቱ

ወንጌሉን የማስተማሪያ ብዙ መንገዶች አሉ።

ቃል ስለተገቡ በረከቶች መስክሩ። ልጆች አንድን የወንጌል መርህ እንዲኖሩ ስትጋብዙ፣ እግዚአብሔር ያንን መርህ ለሚኖሩ ሰዎች የገባውን ቃል ኪዳን ልታካፍሉ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ አፋችንን በመክፈት ወንጌልን ስናካፍል ስለሚሰጠን በረከቶች ምስክርነታችሁን መስጠት ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33፥12–13

ህይወቴን በኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ላይ መገንባት እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁ የቤታቸውን ወይም የቤተክርስቲያንን ህንፃ መሠረት እንዲያዩ ወደ ውጭ ልትወስዷቸውና እንዲገልጹት ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ህንፃ ጠንካራና ፅኑ መሠረት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33፥12–13ን ከእነርሱ ጋር ልታነቡና ጌታ ህይወታችንን በወንጌሉ ላይ እንድንገነባ የሚፈልገው ለምን እንደሆነ ያሏችሁን ስሜቶች አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። “ዓለት” ወንጌሉን ለመግለፅ ጥሩ ቃል የሆነው ለምንድን ነው? ህይወታችንን በወንጌሉ ዓለት ላይ መገንባት የምንችለው እንዴት ነው? (በተጨማሪም ማቴዎስ 7፥24–29 ተመልከቱ)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

አትም