ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መጋቢት 24–30 (እ.አ.አ)፦ “ሁሉም ነገሮች በስርዓት … መከናወን አለባቸው”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27–28


“መጋቢት 24–30 (እ.አ.አ)፦ ‘ሁሉም ነገሮች በስርዓት … መከናወን አለባቸው’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች27–28፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27–28፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
የጆሴፍ ስሚዝ ሃውልት

መጋቢት 24–30 (እ.አ.አ)፦ “ሁሉም ነገሮች በስርዓት … መከናወን አለባቸው”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27–28

ዳግም መመለሱ እየተገለጠ መሄዱን በቀጠለበት ወቅት ራዕይ ለቅዱሳኑ በአንፃራዊነት አዲስ ነገር ነበር። ቀደምት የቤተክርስቲያኗ አባላት ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለቤተክርስቲያኗ ራዕይን መቀበል እንደሚችል ያውቁ ነበር። ይሁንና ሌሎችስ ይችሉ ነበር? ከወርቅ ሰሌዳዎቹ ስምንት ምስክሮች አንዱ የሆነው ሀይረም ፔጅ ለቤተክርስቲያኗ ራዕይ ተቀብያለሁ ብሎ ባመነ ጊዜ እንደዚህ አይነት ጥያቄዎች አንገብጋቢ እየሆኑ መጡ። ብዙ ታማኝ ቅዱሳን ይህ ከእግዚአብሔር የመጣ ራዕይ እንደሆነ አመኑ። ጌታ፣ በእርሱ ቤተክርስቲያን “ሁሉም ነገሮች በስርዓት … መከናወን አለባቸው” ብሎ በማስተማር ምላሽ ሰጠ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥13)። ይህም ማለት ለመላ ቤተክርስቲያኗ “ትእዛዛትን እና ራዕዮችን እንዲቀበል የሚሾመው” አንድ ሰው ብቻ ነው ማለት ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥2)። ቢሆንም፣ ሌሎችም ለሚመለከታቸው የጌታ ስራ ክፍል ራዕይን ሊቀበሉ ይችላሉ። በእርግጥም፣ ለኦሊቨር ካውድሪ ከጌታ የተሰጡት ቃላት ለሁላችንም እንደማስታወሻ ናቸው፥ “የምታከናውነው ነገር ይሰጥሀል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥15)።

በተጨማሪም “ሁሉም ነገሮች በስርአት ይከናወኑ፣” ራዕይ በአገባብ፣ 50–53ን ተመልከቱ።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥1–4

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
ቅዱስ ቁርባንን የምወስደው ኢየሱስ ክርስቶስን ለማስታወስ ነው።

ሳሊ ናይት እና ኤማ ስሚዝ በሰኔ 1830 (እ.አ.አ) ነበር የተጠመቁት፣ ነገር ግን ማረጋገጫ የመቀበል ሥርዓታቸው በህገ ወጦች ሥብሥብ ተስተጓጎለ። ከሁለት ወራት በኋላ፣ ሳሊ እና ባለቤቷ ንዌል ኤማን እና ጆሴፍን ሊጎበኙ መጡ፣ ስለዚህም ማረጋገጫቸውን በዚያን ጊዜ እንደሚቀበሉና ቡድኑም ቅዱስ ቁርባኑን አንድ ላይ በመሆን እንደሚቋደስ ተወሰነ። ለቅዱስ ቁርባን የሚሆን ወይን ለማምጣት በመሄድ ላይ ሳለ፣ አንድ መልአክ ጆሴፍን አስቆመው።

መልዓኩ ስለቅዱስ ቁርባን ምን እንዳስተማረው ለማግኘት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥1–4 አንብቡ። አዳኙ፣ ቅዱስ ቁርባንን በምን አይነት መልኩ መቋደስ እንዳለባችሁ እነዚህ ጥቅሶች ምን ይጠቁማሉ? “ሙሉ ዓይናችሁን ወደ እርሱ ክብር” አድርጋችሁ ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? ሉቃስ 22፥19–20 እና 3 ኔፊ 18፥1–11ን ስታነቡ፣ ይህንን አሰላስሉ እንዲሁም ስለቅዱስ ቁርባን ሌሎች ግንዛቤዎችን ፈልጉ። (በተጨማሪም “The Last Supper [የመጨረሻው እራት]፣” “Jesus Christ Blesses Bread in Remembrance of Him [ኢየሱስ ዳቦውን እርሱን ለማስታወስ ባረከው]፣” እና “Jesus Christ Blesses Wine in Remembrance of Him [ኢየሱስ ወይኑን እርሱን ለማስታወስ ባረከው]፣” ቪዲዮዎችን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ)።

ቅዱስ ቁርባንን የአምልኮ ልምድ ማድረግ ስለሚቻልበት መንገድ ለመማር፣ የዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን መልዕክት የሆነውን “ከሰማይ የወረደ ህያው እንጀራ፣” (ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 36–39ን) ማጥናትን አስቡ። ሽማግሌ ክሪስቶፈርሰን በቅዱስ ቁርባን አማካኝነት ከአዳኙ ጋር የላቁ ግንኙነት እንዳላችሁ እንዲሰማችሁ ሊረዳችሁ የሚችል ምን አስተማሩ? ከአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ምልክት ለመካፈል እና እነሱን በጥልቅ አክብሮት ወይም አላማ ለመያዝ ትችሉ ዘንድ በተሻለ ሁኔታ ለመዘጋጀት ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ።

እንደ “As Now We Take the Sacrament [ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል]” (መዝሙር፣ ቁ. 169) ያሉ የቅዱስ ቁርባን መዝሙሮችን መዘመርን፣ ማዳመጥን ወይም ማንበብን እንዲሁም በዚህ የተቀደሰ ሥርዓት ስለመሳተፍ ያላችሁን ሥሜት መመዝገብን አስቡ።

ሙዚቃን ተጠቀሙ። ቅዱስ መዝሙር የወንጌልን እውነቶች ይመሰክር ዘንድ መንፈስን ይጋብዛል። እነዚህን እውነቶች ሊታወስ በሚችል መንገድ እንድትገነዘቡ እና እንዲሰማችሁ ሊረዳችሁ ይችላል። በተጨማሪ፣ ሙዚቃም መማርን የበለጠ አሳታፊ ለማድረግ ይረዳል።

በተጨማሪም፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 7959፥9–13፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “ቅዱስ ቁርባን፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ “Obtaining and Retaining a Remission of Sins through Ordinances [በስርዓቶች በኩል ምህረትን ማግኘት እና መጠበቅ]፣” በ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “Always Retain a Remission of Your Sins [ሁልጊዜ የኃቲያት ስርየትን ጠብቁ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 60–62 ተመልከቱ።

ምስል
የተቆረሰ ዳቦ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥5–14

ጌታ የእርሱን ስራ እንዲሰሩ ለአገልጋዮቹ የክህነት ቁልፍን ይሰጣል።

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለተጠቀሱት ነቢያት ምን ታውቃላችሁ? ስለእነርሱ መረጃ ለማግኘት በየቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ ውስጥ መፈተሽ ትችላላችሁ። እነርሱ በያዙት ቁልፍ ለእናንተ ምን አይነት በረከቶች ተከፍተውላችኋል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥15–18

የእግዚአብሔር የጦር እቃ ልብስ ክፉን እንድቋቋም ይረዳኛል።

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፦ “እራሳችንን በመንፈሳዊነት ለማስታጠቅ ልናደርግ የምንችለው አንድ ትልቅና አስደናቂ ነገር የለም። እውነተኛ መንፈሳዊ ኃይል ከክፉ ነገር ሁሉ በሚጠብቁትና በሚከላከሉት በመንፈሳዊ ምሽግ ገመዶች አንድ ላይ በተገመዱ ብዛት ያላቸው ትናንሽ ተግባራት ውስጥ ይገኛል” (“በጌታ ጠንክሩ፣” ኤንዛይን፣ ሐምሌ 2004 (እ.አ.አ)፣ 8)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥15–18 ስለ እግዚአብሔር የጦር እቃ ልብስ ስትማሩ፣ ከዚህ በታች እንዳለው አይነት ሠንጠረዥ መስራት ትችላላችሁ። እያንዳንዱን የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ ልብስ ለመልበስ ምን እያደረጋችሁ ናችሁ?

የጦር እቃ ልብስ ክፍል

የተሸፈነው የሰውነት ክፍል

ይህ የሰውነት አካል ምን እንደሚወክል

የጦር እቃ ልብስ ክፍል

የጽድቅ ጥሩር

የተሸፈነው የሰውነት ክፍል

ልብ

ይህ የሰውነት አካል ምን እንደሚወክል

የእኔ ፍላጎት እና ዝንባሌ

የጦር እቃ ልብስ ክፍል

የደህንነት የራስ ቁር

የተሸፈነው የሰውነት ክፍል

ጭንቅላት ወይም አዕምሮ

ይህ የሰውነት አካል ምን እንደሚወክል

የጦር እቃ ልብስ ክፍል

የተሸፈነው የሰውነት ክፍል

ይህ የሰውነት አካል ምን እንደሚወክል

የጦር እቃ ልብስ ክፍል

የተሸፈነው የሰውነት ክፍል

ይህ የሰውነት አካል ምን እንደሚወክል

እንዲሁም “ኤፌሶን 6፥11–18፣” ሆርሄ ኤፍ. ዘባዮስ፣ “Building a Life Resistant to the Adversary [ጠላትን ለመቋቋም የሚችል ህይወትን መገንባት]፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2022(እ.አ.አ)፣ 50–52።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28

ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን በህይወት ባለ ነቢይ አማካኝነት ይመራል።

ማንም ሰው ለመላው ቤተክርስቲያን ትእዛዛትን እና ራእይ መቀበል የሚችል ቢሆን ኖሮ ምን ሊከሰት ይችል እንደነበር አስቡት። ሀይረም ፔጅ እንደዚያ አይነት ራዕይ ተቀብያለሁ ብሎ ሲናገር ብዙ የቤተክርስቲያኗ አባላት ግራ ተጋብተው ነበር። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28 ውስጥ፣ ጌታ በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለው ራዕይ የመቀበል ቅደም ተከተል ገለጿል። በዚህ ክፍል ውስጥ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት ስላለው ግልጽ የሆነ ሃላፊነት ምን ትማራላችሁ? እግዚአብሔር እናንተን ስለሚመራበት መንገድ ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ዴል ጂ ረንላንድ፣ “A Framework for Personal Revelation [ለግል መገለጥ ማዕቀፍ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 16–19 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥8–9

ወደ ላማናውያን ሊደረግ የታሠበው ተልዕኮ አስፈላጊ የነበረው ለምንድን ነው?

አንደኛው የመሐፈ ሞርሞን አላማ “ላማናውያን ወደ አባቶቻቸው እውቀት ይመጡ ዘንድ፣ እናም የጌታን የተስፋ ቃል ያውቁ ዘንድ” ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥20)። ይህ ደግሞ ጌታ ለተለያዩ የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢያት ከገባው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው (ለምሳሌ 1 ኔፊ 13፥34–41ኢኖስ 1፥11–18ሔለማን 15፥12–13 ተመልከቱ)። ቀደምት የቤተክርስቲያኗ አባላት የአሜሪካ ህንዶች የመፅሐፈ ሞርሞን ህዝቦች እንደሆኑ ይቆጥሯቸው ነበር። (ዛሬ፣ ቤተክርስቲያኗ ኦፊሴላዊ አቋም ላማናዊያን “ከአሜሪካን ህንዶች የዘር ሃረግ መሃከል” እንደሆኑ ነው [የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ]።)

ኦሊቨር ካውድሪ በአቅራቢያው ወደነበሩት የአሜሪካ ህንዶች ጎሳ ስለነበረው ተልዕኮ ተጨማሪ ለማንበብ “ተልዕኮ ወደ ላማናውያንን ” (ራዕይ በአገባብ፣ 45–49) ተመልከቱ። ይህ ተልዕኮ ስለጌታ እና ስለስራው ምን ያስተምራችኋል?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥1–2

ቅዱስ ቁርባን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳስታውስ ይረዳኛል።

  • ኢየሱስ ለቅዱስ ቁርባን ወይን ተጠቅሞ ሳለ እኛ ለምን ውሃ እንጠቀማለን በማለት ልጆች ሊያስቡ ይችላሉ (ሉቃስ 22፥19–20 እና 3 ኔፊ 18፥1–11 ተመልከቱ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥1–2ን በአንድነት ልታነቡ እና “ሙሉ ዓይ[ን]ን ወደ እርሱ ክብ[ር]” (ቁጥር 2) ማድረገ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተወያዩ። ቅዱስ ቁርባንን በምንካፈልበት ወቅት ትኩረታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ለማድረግ ምን ማድረግ እንችላለን?

  • ምናልባት ስለአዳኙ የሚገልፁ ሥዕሎች፣ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች ወይም የመዝሙር ግጥሞች እንዲኖሩ ማድረግ ልጆቻችሁ ቅዱስ ቁርባንን በሚወስዱበት ወቅት እሱን እንዲያስታውሱ ሊረዳቸው ይችላል። እነርሱም እነዚህን ሥዕሎች፣ ጥቅሶች እና ግጥሞች የያዘ ትንሽ መፅሐፍ ማዘጋጀት ያስደስታቸው ይሆናል። የራሳቸውን ሥዕል ሊስሉ ወይም በጓደኛ መፅሄት ውስጥ ጥቂት ሥዕሎችን ሊፈልጉ ይችላሉ።

ምስል
ኢየሱስ ዳቦ እየቆረሰ

ዝርዝሩ ከየመጨረሻው እራት፣ በሳይመን ዲዊ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥15–18

የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ ይከላከለኛል።

  • ወይም በኤፌሶን መዘርዝር ውስጥ ባለው የአክቲቪቲ ገፅ ላይ ያለን የጦር እቃ ለልጆቻችሁ ለማሳየት ትችላላችሁ፣ ይህም በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) ውስጥ ይገኛል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥15–18ን ስታነቡ የጦር እቃ ክፍሎችን እንዲያገኙ እርዷቸው። የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ “ክፉውን ቀን ለመቃወም” (ቁጥር 15) ሊረዳችሁ የሚችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥2፣ 6–7

ነቢዩ ለቤተክርስቲያኗ ራዕይን ይቀበላል፤ እኔ ለህይወቴ የሚሆን ራዕይን መቀበል እችላለሁ።

  • ብዙ ልጆች ካሏችሁ፣ “መሪውን ተከተሉ” የሚባለውን ጨዋታ እንዲጫወቱ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ፤ ሆኖም ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ልጆች በአንዴ መሪ እንዲሆኑ ጠይቋቸው። ከአንድ በላይ መሪ ሲኖር ምን ይፈጠራል? ከዚያም ስለሃይረም ፔጅ መማር ትችላላችሁ (“Chapter 14: The Prophet and Revelations for the Church [ምዕራፍ 14፦ ነቢዩ እና ለቤተክርስቲያኗ የሚሰጡ ራዕዮች]” (በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 56–57፣ ውስጥ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን ከወንጌል ላይብረሪ) ወይም ከDoctrine and Covenants 28 የክፍል መግቢያ ተመልከቱ)። የሰማይ አባት፣ ለቀደምት የቤተክርስቲያን አባላት ግራ መጋባት እርማት የሰጠው እንዴት ነበር? ዛሬ ቤተክርስቲያኗን የሚመራው እንዴት ነው? (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 28፥2 ተመልከቱ)። አሁን ያለው ነቢይ በእኛ ዘመን ቤተክርስቲያኑን እንዲመራ በጌታ እንደተጠራ ምስክርነታችሁን ሥጡ።

  • ለቤተክርስቲያን የሚሆን ራዕይ የሚሰጠው ሁል ጊዜ በነቢዩ በኩል ቢሆንም፣ ሁላችንም በመንፈስ ቅዱስ መመራት እንችላለን። ልጆቻችሁ ከሚከተሉት የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች የተወሰኑትን እንዲፈልጉ እና መንፈስ ቅዱስ እኛን የሚመራባቸውን መንገዶች ዝርዝር እንዲያዘጋጁ ልትረዷቸው ትችላላችሁ፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥1 4፣ 15ዮሐንስ 14፥26ሞሮኒ 8፥2610፥4–5። በመንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደተመራችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

አትም