“መጋቢት10–16 (እ.አ.አ)፣ ‘የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መነሳት’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20–22፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]
“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20–22፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
መጋቢት10–16 (እ.አ.አ)፦ “የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መነሳት”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20–22
የኢየሱስ ክርስቶስ መፅሐፈ ሞርሞንን የማምጣት ሥራ ተጠናቆ ነበር። ሆኖም ዳግም የመመለስ ሥራው ገና መጀመሩ ነበር። አስተምህሮን እና የክህነት ስልጣንን ዳግም ከመመለስ በተጨማሪ፣ ጌታ፣ በቀደሙት ራዕዮቹ መደበኛ ድርጅቱን—የእርሱን ቤተክርስቲያን—ዳግም ለመመለስ እንደሚፈልግ ግልጽ አድርጎ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥53፤ 18፥5ን ተመልከቱ)። ሚያዝያ 6 ቀን 1830 (እ.አ.አ)፣ ከ40 በላይ የሚሆኑ አማኞች በፈየት፣ ኒው ዮርክ በሚገኘው የዊትመር ቤተሰብ የእንጨት ቤት ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ስትመሰረት ምስክር ለመሆን ተሰብስበው ነበር።
አንዳንድ ሰዎች የተደራጀ ቤተክርስቲያን ለምን ያስፈልገናል በማለት ያስባሉ? በከፊልም ቢሆን መልሱ በ1830 (እ.አ.አ) ከተደረገው የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ስብሰባ ጋር ተያይዞ በተሰጠው ራዕይ ውስጥ ሊገኝ ይችላል። እውነተኛዋ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በኋለኛዎቹ ቀናት “ተስማሚ በሚሆን ሁኔታ ተደራጅታ [የተመሰረተች]” ባትሆን ኖሮ ሊፈጸሙ ስለማይችሉ በረከቶች ይገልፃሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥1)።
በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥84–86፤ “[Build Up My Church] ቤተክርስቲያኔን ገንቡ፣” ራዕይ በአገባብ፣ 29–32ን ውስጥ ተመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን ዳግም መልሷል።
የተደራጀ ቤተክርስቲያን የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? ምናልባት ከሁሉም የተሻለው መልስ “ኢየሱስ ክርስቶስ ስላቋቋመ” የሚል ይሆናል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20–21ን ስታጠኑ፣ በጥንትጊዜ ባቋቋማት ቤተክርስቲያን እና ዛሬ ዳግም በመለሳት ቤተክርስቲያን መካከል ተመሳሳይነትን ልታዩ ትችላላችሁ። በጥንት ጊዜ ስለነበረችው የአዳኙ ቤተክርስቲያን ለማወቅ የሚከተሉትን ጥቅሶች ተጠቀሙ ማቴዎስ 16፥15–19፤ ዮሐንስ 7፥16–17፤ ኤፌሶን 2፥19–22፤ 3 ኔፊ 11፥23–26፤ ሞሮኒ 4–5። ዳግም ስለተመለሠችው ቤተክርስቲያን ለማወቅ የሚከተሉትን ጥቅሶች ተጠቀሙ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥17–25፣ 60፣ 72–79፤ 21፥1–2። የምታገኙትንም ይህን በመሠለ ሠንጠረዥ ልትመዘግቡ ትችላላችሁ፦
ትምህርት |
ሥርዓቶች |
የክህነት ስልጣን |
ነቢያት | |
---|---|---|---|---|
የክርስቶስ የጥንት ቤተክርስቲያን | ትምህርት | ሥርዓቶች | የክህነት ስልጣን | ነቢያት |
የክርስቶስ ዳግም የተመለሰች ቤተክርስቲያን | ትምህርት | ሥርዓቶች | የክህነት ስልጣን | ነቢያት |
ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን ለምን እንዳቋቋመ እና ዳግም እንደመለሰ ከዚህ አክቲቪቲ ምን ትማራላችሁ?
በተጨማሪም ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “The Need for a Church [የቤተክርስቲያኗ አስፈላጊነት]፣” ኢንዛይን፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 24–26 ተመልከቱ።
ትምህር እና ቃል ኪዳኖች 20፥37፣ 75–79፤ 22
ቅዱስ ሥርዓቶች አዳኙን እንድመስል ይረዱኛል።
ቤተክርስቲያኗ በተቋቋመች ወቅት ጌታ፣ ጥምቀትና ቅዱስ ቁርባንን ጨምሮ፣ ስለቅዱስ ሥርአቶች ቅዱሳኑን አስተማረ። ስለእነዚህ ሥርዓቶች ስታነቡ፣ በመንፈሣዊ እና በሥሜታዊ እንዴት ወደ አዳኙ እንደቀረባችሁ እንዲሰማችሁ እንደሚረዷችሁ አሰላስሉ? ለምሳሌ፣ እነዚህ ሥርዓቶች “[ኢየሱስ ክርስቶስን] እስከመጨረሻ ድረስ [የ]ማገልገል ፈቃ[ዳችሁን]” እንድትጠብቁ የሚረዷችሁ እንዴት ነው? (ቁጥር 37)። እንዲሁም የቅዱስ ቁርባን ጸሎቶችን ማንበብና (ቁጥር 77፣ 79) ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሰማችኋቸው አድርጋችሁ ማሰብ ትችላላችሁ። ምን ግንዛቤዎች ታገኛላችሁ?
በተጨማሪም ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን “Why the Covenant Path [ለምን የቃል ኪድን መንገድ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 116–19ን ተመልከቱ።
የክህነት አገልግሎቶች የቤተክርስቲያን አባላትን እና ቤተሰቦቻቸውን ይባርካሉ።
ክህነትን በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ዳግም መመለስ ለአዳኙ ለምን አስፈላጊ እንደነበረ አስባችሁ ታውቃላችሁን? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥38–60 ውስጥ የክህነት ተሸካሚዎች እንዲያደርጉ የጠየቃቸውን ማንበብ የተወሰነ ግንዛቤ ይሰጣችኋል። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በተገለፀው ሥራ ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተን እና ቤተሰባችሁን የባረካችሁ እንዴት ነው?
በክህነት ከተሾሙት በተጨማሪ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለማገልገል የተለዩ ሴቶችም በስራው በሚሳተፉበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ስልጣን ይጠቀማሉ። እንዴት እንደሆነ ለማየት፣ የፕሬዚዳንት ዳለን ኤች. ኦክስ መልዕክት የሆነውን “የክህነት ቁልፎች እና ስልጣን” ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 49–52 ተመልከቱ።
በተጨማሪም፣ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “የጆሴፍ ስሚዝ ትምህርቶች ስለ ክህነት፣ ቤተመቅደስ እና ሴቶች፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።
በነቢያቱ በኩል የሚመጣን የእግዚአብሔር ቃል መታዘዜ መለኮታዊ ጥበቃ ያስገኝልኛል።
ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 21፥4–9 የጌታን ነቢይ ለመከተል ግብዣዎችን ያቀርባል እንዲሁም ይህንን ለሚያደርጉት ሃይለኛ ተስፋዎችን ይዟል። የሚከተሉት ሃሳቦች በጥቅሶቹ ላይ እንድታሰላስሉ ሊረዷችሁ ይችላሉ፦
-
ቁጥር 4–5 ውስጥ አዳኙ በህይወት ባለው ነቢዩ ቃል አማካኝነት እንድታደርጉ የሚፈልጋቸውን ነገሮች የሚገልጹት ቃላት የትኞቹ ናቸው? ይህንን ለማድረግ “ትዕግስት እና እምነት” አስፈላጊ የሆኑት ለምን ይመስላችኋል?
-
አዳኙ የእርሱን ነብይ በመከተል ስለሚመጡት በረከቶች ለመግለጽ ቁጥር 6 ላይ በተጠቀማቸው ሥዕላዊ መግለጫዎች ላይ አሰላስሉ። “የሲዖል ደጆች” ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? ጌታ ከላያችሁ ላይ “የጭለማን ኃይል … [የሚገፈው]” እንዴት ነው? “ለእናንተ ጥቅም … ሰማያት እንዲንቀጠቀጡ” ማለት ምን ማለት ነው?
-
በወቅቱ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት አማካኝነት ምን እንድታደርጉ እየጠየቃችሁ ነው? ምክሩን በተከተላችሁ ጊዜ ጌታ በህይወታችሁ ቃሉን የፈፀመው እንዴት ነው?
ከሚከተሉት የሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን መልዕክት ክፍሎች የምታገኟቸውን ተጨማሪ ግንዛቤዎች ዘርዝሩ፣ “The Prophet of God [የእግዚአብሔር ነቢይ]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 24–27)፦
-
ነቢዩን የምንከተልበት ምክንያት፦
-
በማማው ላይ ጠባቂ፦
-
እትደነቁ፥
በተጨማሪም “Watchman on the Tower [በማማው ላይ ጠባቂ]” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “ነቢያት፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ “We Listen to a Prophet’s Voice [የነቢዩን ድምጽ እንሰማለን]፣” መዝሙር፣ ቁ. 22 ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዳግም ተመልሳለች
-
የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፣ ምዕራፍ 9 የክፍል ርዕስ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች ውስጥ ወይንም “Organization of the Church [የቤተክርስትያኗ መደራጀት]” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪዲዮ ልጆቻችሁ ቤተክርስቲያኗ በተቋቋመች በዚያን ቀን ምን እንደተከሰተ እንዲገነዘቡ ለመርዳት መጠቀምን አስቡ።
2:37 -
ምናልባት ልጆቻችሁ የኢየሱስ ክርስቶስን፣ እያገለገለ ያለ ሠውን፣ የጥምቀትን እና የቅዱስ ቁርባን ሥዕሎችን ከክፍል 20 (ቁጥር 21–23፣ 47፣ 72–74፣ 75–79 ተመልከቱ) ቁጥሮች ጋር ማዛመድ ይችላሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን ዳግም በመመለሱ ምክንያት ስላገኘናቸው በረከቶች ለመወያየት እነዚህን ሥዕሎች እና ጥቅሶች ተጠቀሙ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37፣ 41፣ 71–74
ስጠመቅ እና ማረጋገጫ ስቀበል ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ቃል ገብቻለሁ።
-
ልጆቻችሁ አንድ ልጅ ሲጠመቅ እና ማረጋገጫ ሲቀበል የሚያሳይ ሥዕል በመመልከት ሊደሰቱ ይችላሉ። ይህ መረጃ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥41፣ 71–74 ውስጥ ካሉት መመሪያዎች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ መዘርዘር ይችላሉ? በትምህርትና ቃል ኪዳኖች 20፥37 ውስጥ መጠመቅ ስለሚፈልጉ ሰዎች ምን እንማራለን? “When I Am Baptized [ስጠመቅ]” የሚለውን መዝሙር በአንድነት ልትዘምሩም ትችላላችሁ (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 103) ወይም “The Baptism of Jesus [የክርስቶስ ጥምቀት]” (ወንጌል ላይብረሪ) የሚለውን ቪዲዮ ልትመለከቱ ትችላላችሁ።
-
ልጆቻችሁ የተጠመቁ እና ማረጋገጫ የተቀበሉ ከሆኑ ስለተሞክሯቸው ጠይቋቸው። ሊያጋሯቸው የሚችሏቸው ፎቶዎች አሏቸው? ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ምን እያደረጉ እንደሆነ እና እንዴት እየባረካቸው እንደሆነ አነጋግሯቸው።
የኢየሱስን ስም በራሴ ላይ መውሰድ እና ሁልጊዜ እርሱን ማስታወስ እችላለሁ።
-
ልጆቻችሁ “ፈቃደኞች” የሚለውን ቃል በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37 (ስለጥምቀት) እና በ ቁጥር 77 (የቅዱስ ቁርባን ፀሎት) ውስጥ ሊፈልጉ ይችላሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ለማድረግ ፈቃደኞች እንድንሆን ይፈልጋል? ምናልባት ልጆቻችሁ በላዩ ላይ ስም የተለጠፈበት ነገር (የብራንድ ስም ወይም የሠው ስም) ሊመለከቱ ይችላሉ። ሥሙ ስለተለጠፈበት ነገር ምን ይነግረናል? የኢየሱስ ክርስቶስን ሥም በላያችን መውሰድ ማለት ምን ማለት ነው?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77ን አንድ ላይ ማንበብ እና እንደቅዱስ ቁርባን አካል የምንገባቸውን ቃል ኪዳኖች እንዲለዩ ልጆቻችሁን መጠየቅ ትችላላችሁ። ምናልባት አዳኙን “ሁልጊዜ ለማስታወስ” ስለሚያደርጉት ነገር ተራ በተራ ሊተውኑ እና አንዳቸው የሌላኛውን ድርጊት ትርጉም መገመት ይችላሉ። በቁጥር 77 መሰረት፣ አዳኙን ሁል ጊዜ በማስታወሳችን የተባረክነው እንዴት ነው?
ኢየሱስ ነቢዩን ስከተል ይባርከኛል።
-
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፥4–6 ውስጥ ያሉትን ግብዣዎች እና ቃል ኪዳኖች ካገኙ በኋላ፣ ልጆቻችሁ የወቅቱን ነቢይ ሥዕል ሊመለከቱ እና ስለእርሱ ስለተማሩት ወይም ስለሰሙት አንድ ነገር ሊያጋሩ ይችላሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢዩን በመከተላችሁ ምክንያት እናንተን የባረከበትን መንገዶች አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።