ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መጋቢት 17–23 (እ.አ.አ)፦ “የተሻሉ ነገሮችን ትሺያለሽ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23–26


“የካቲት 17–23 (እ.አ.አ)፦‘የተሻሉ ነገሮችን [እሹ]’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23–26፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ኤማ ስሚዝ

መጋቢት 17–23 (እ.አ.አ)፦ “የተሻሉ ነገሮችን ትሺያለሽ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 23–26

ለብዙ ሰዎች መጠመቅ ጥልቅ አክብሮት ያለው እና ሰላማዊ ተሞክሮ ነው። የኤማ ስሚዝ እና የሌሎች ጥምቀት ግን በህዝቡ ላይ በሚያፌዙ፣ ህዝቡን በሚያስፈራሩ እና በግድ እንዲሰደዱ በሚያደርጉ ህገ ወጦች ስብስብ የተረበሸ ነበር። ከዚያም በኋላ ጆሴፍ ለአዳዲስ አባላቱ ማረጋገጫ ሊሰጥ ሲል፣ ህብረተሰቡን በማስተማር አበሳጭተሃል በሚል ምክንያት ለእስር ተዳረገ። በዚህ ሁሉ ተቃውሞ ውስጥ፣ ኤማ ትክክለኛውን ነገር እየሰራች ስለመሆኗ ማረጋገጫ ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው? ሁላችንም የምናገኘው ከዚያው ተመሳሳይ ምንጭ ነው—ይኸውም ከጌታ በሚመጣ ራዕይ ውስጥ ነው። እርሱም ከኤማ ጋር “[ስለ]ተሻሉ ነገሮች [ዓለም]”—ስለመንግሥቱ—እና በዚያ ስለሚኖራት ቦታ ተነጋገረ። “ል[ቧ]ን [እንድታቀና] እናም [እንድትደሰት]”፣ እና “ከገባ[ቸው] ቃል ኪዳን ጋርም [እንድትጣበቅ]” ነገራት። እናም እነዚህ ማበረታቻ ቃላት እና ምክሮች “ለሁሉም የሆነው … [የእርሱ] ድምፅ ነው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥9–10፣ 13፣ 16)።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥89–9094–97ን ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24

አዳኙ “[ከስቃዬ] ከፍ” ሊያደርገኝ ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24 ውስጥ ያለው ራዕይ የተሰጠው ጆሴፍ ስሚዝን እና ኦሊቨር ካውድሪን በፈተና ወቅት “ለማጠንከር፣ ለማበረታታት፣ እና ለማስተማር” ነበር (የክፍል ርዕስ፤ በተጨማሪም ቅዱሳን1፥94–96 ተመልከቱ)። እነርሱን የሚያጠነክሩ እና የሚያበረታቱ እንደሆኑ የምታስቧቸውን ቃላት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24 ውስጥ ፈልጉ።

አስቸጋሪ ጊዜያት ሲገጥማችሁ አዳኙ እናንተን ስለሚረዳባቸው መንገዶች የሚከተሉት የቅዱሳት መፃሕፍት ጥቅሶች ምን ይጠቁማሉ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥1–3

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥8

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥7–8

ኢሳይያስ 40፥28–31

ሞዛያ 24፥14–15

ኢየሱስ አንድን ሰው ሲፈውስ

ዝርዝር ከበልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፣ በጄ.ከርክ ሪቻርድስ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ የምጫወተው አስፈላጊ ሚና አለኝ?

ኤማ ስሚዝ፣ ዳግም መመለሡ በባለቤቷ በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ሲከናወን ስትመለከት፣ ሚናዋ ምን ሊሆን እንደሚችል አስባ ሊሆን ይችላል። ጌታ የሰጠውን ምላሽ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25 ውስጥ ተመልከቱ። በዚህ ክፍል ውስጥ የእርሱ የሚመስላችሁን “[ለእናንተ የሆነ] ድምጽ” ታገኛላችሁን? ቁጥር 16

በተጨማሪም “የተመረጠች ሴት” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ፤ “አንቺ የተመረጥሽ ሴት ነሽ፣” ራዕይ በአገባብ፣ 33–39 ውስጥ፤ ጆይ ዲ. ጆንስ፣ “ልዩ የሆነ አጠራር፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 15–18 ተመልከቱ።

2:3

"An Elect Lady"

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥5፣ 14

“በትህትና መንፈስ ቀጥዪ።”

“የትህትና መንፈስ” የሚለው ሃረግ ለእናንተ ምን ማለት ነው? በክፍል 25 ውስጥ ትሁት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለመገንዘብ የሚረዱ ምን ቃላት እና ሃረጎች ታገኛላችሁ? የሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር መልዕክት፣ “የዋህ እና ትሑት ልብ፣”ሊረዳችሁም ይችላል (ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 30–33።። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ለእናንተ የትህትና ምሳሌ ነው? (ማቴዎስ 11፥28–30 ተመልከቱ)። በህይወታችሁ ውስጥ ያሉ በትህትና መንፈስ ልታደርጓቸው የምትችሏቸውን ነገሮች አስቡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥10፣ 13

የሴሚናሪ ምልክት
“የዚህን አለም ነገሮች ወደጎን ትተያቸዋለሽ እናም የተሻሉ ነገሮችን ትሺያለሽ።”

ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥10 ውስጥ የሰጠውን ምክር ስታሰላስሉ እርሱ “[እንድትተዋቸው]” የሚፈልጋቸውን “የዓለም ነገሮች” ዝርዝር ማዘጋጀት ሊረዳ ይችላል። ከዚያም እንድትሹ የሚፈልገውን “የተሻሉ [የዓለም] ነገሮች” ዝርዝር ልታዘጋጁ ትችላላችሁ። ከመጀመሪያው ዝርዝር ውስጥ የምትተዉትን ቢያንስ አንድ ነገር እንዲሁም ከሁለተኛው ዝርዝር ውስጥ ደግሞ የምትሹትን አንድ ነገር ልትመርጡ ትችላላችሁ።

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “ብዙ የዚህ ዓለም ነገሮችን [ስለ]ማስወገድ” ምክር እና ተስፋ ሰጥተዋል። ይህንንም የፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን መልዕክት በሆነውን “መንፈሳዊ ሀብቶች፣” (ሊያሆና፣ ህዳር –79 በገጽ 77) ላይ ፈልጉት። የእርሳቸውን ምክር የምትከተሉት እንዴት ነው?

ቁጥር 13ን ስታነቡ፣​ከሰማያዊ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የገባችኋቸውን ቃል ኪዳኖች አስቡ። ከእነዚህ ቃል ኪዳኖች ጋር “መጣበቅ” ማለት ምን ማለት ነው? ቃል ኪዳኖቻችሁ “ዚህን አለም ነገሮች ወደጎን [እንድትተዉ] እናም የተሻሉ ነገሮችን [እንድትሹ]” የሚረዷችሁ እንዴት ነው?

“በዚህ ዓለም ነገሮች” እና “በተሻሉ” መካከል ያለውን ልዩነት እንድትገነዘቡ የሚረዷችሁ ሌሎች የቅዱሳት መፃሕፍት ጥቅሶች እነሆ፦ ማቴዎስ 6፥19፣ 2125–34ሉቃስ 10፥39–422 ኔፊ 9፥51

በተጨማሪም፣ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “መስዋዕት፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

ማካፈልን ጋብዙ። ሌሎች “የዚህን ዓለምን ነገሮች [መተው]” እንዴት እንደሚችሉ እያስተማራችሁ ከሆነ ይህን ምክር ለመከተል እያደርጉ ያሉትን ነገር እንዲያካፍሉ የምትጋብዙባቸውን መንገዶች አስቡ። አንዳችን የሌላችንን ግንዛቤ እና ተሞክሮ በመስማት ታላቅ ጥንካሬ እና ድፍረት ማግኘት እንችላለን።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥11–12

ጌታ በእኔ“ከልብ የሆነ ዝማሬ” ይደሰታል።

ስለሰማይ አባት ወይም ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያሏችሁን ስሜቶች የሚገልጹ አንዳንድ መዝሙሮች—“ከልብ የሆ[ኑ] ዝማሬ[ዎች]” የትኞቹ ናቸው? ከእነዚህ ጥቂቶቹን መዘመርን ወይም ማዳመጥን አስቡ። እነዚህን መዝሙሮች ለእናንተ ልዩ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው?

እነዚህ መዝሙሮች እንዴት እንደ ጸሎት እንደሆኑ ልታስቡም ትችላላችሁ። ቅዱስ መዝሙርን እና ጸሎትን ምን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ? ቅዱስ መዝሙሮቻችሁ “በረከትን በራሳ[ችሁ] ላይ በማድረግ [የተመለሰላችሁ]” እንዴት ነው?

በተጨማሪም “Oh፣ What Songs of the Heart [አቤቱ፣ ምን የልብመዝሙር ነው]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 286 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 26፥2

“ሁሉም ነገሮች በቤተክርስቲያን በጋራ ስምምነት … ይከናወኑ።”

በዚህ ጥቅስ ውስጥ “በጋራ ስምምነት” የሚለው ሐረግ ጥሪን ወይም የክህነት ሹመት የሚቀበልን ሰው እንደምንደግፍ እና ድጋፍ እንደምንሰጥ ለማሳየት እጆቻችንን የማውጣትን ተግባርን ያመለክታል። አንድን ሰው መደገፍ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለአንድ የቤተክርስቲያን ስብሰባ ጎብኚ እንዴት ማስረዳት ይቻላል? “The Power of Sustaining Faith [የመደገፍ እምነት ሀይል]” ከተሰኘው የፕሬዚዳንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ መልዕክት ውስጥ ምን መልሶችን ልታገኙ ትችላላችሁ? (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 58–60)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥1፣ 8

አዳኝ “[ከስቃዬ] ከፍ” ሊያደርገኝ ይችላል።

  • ጆሴፍ ስሚዝ እና ቀደምት ቅዱሳን ስላጋጠሟቸው አንዳንድ መከራዎች ወይም ፈተናዎች ለማወቅ “Chapter 11: Joseph Smith and His Family [ምዕራፍ 11፦ ጆሴፍ ስሚዝ እና ቤተሰቡ]፣” በበትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 46–47፣ ወይም የሱን ተዛማጅ ቪዲዮ በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ልትከልሱ ትችላላችሁ። ከዚያም እናንተ እና ልጆቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥1፣ 8 ውስጥ ጆሴፍ ስለደረሰበት መከራ ጌታ ምን እንዳለውለማግኘት ትችላላችሁ። አስቸጋሪ ጊዜያት በሚገጥሟችሁ ጌታ እንዴት እንደሚረዳችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ ማካፈልም ትችላላችሁ።

    1:52

    Chapter 11: More People Join the Church: April–June 1830

  • “በመከራ[ችን] መታገሥ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ እናንተና ልጆቻችሁ “Continue in Patience [በትዕግስት ቀጡ]” (የወንጌል ላይብረሪ) በሚለው ቪዲዮ ውስጥ ያለውን ሙከራ እንደገና ማከናወን ትችላላችሁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 24፥8 ስለታጋሽነት ምን ያስተምራል? ጌታ በመከራችን ጊዜ “[ከእኛ] ጋር” እንድንደሆነ የሚያሳውቀን እንዴት ነው?

    2:41

    Continue in Patience

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥11–12

ኢየሱስ “ከልብ የሆነ ዝማሬን” ይወዳል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥12ን ካነበባችሁ በኋላ የምትወዱትን መዝሙር ወይም የቤተክርስቲያን መዝሙር—“ከልብ የሆነ ዝማሬ” አንዳችሁ ለሌላችሁ ልትነግሩ እንዲሁም አብራችሁ ልትዘምሯቸው ትችላላችሁ። እነዚህን መዝሙሮች ለምን እንደምትወዱ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ። እነዚህን መዝሙሮች ስንዘምር ጌታ የሚደሰተው ለምንድን ነው? እነዚህ መዝሙሮች “ለ[እርሱ] እንደጸሎት” የሚሆኑት እንዴት ነው ?

ቤተሰብ በፒያኖ እየዘመሩ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥13፣ 15

ከሰማይ አባት ጋር የገባኋቸው ቃል ኪዳኖች ደስታ ያመጡልኛል።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ኤማ ቅዱሳት መጻህፍትን እያጠናች

የኤማ መዝሙሮች፣ በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

የመጀመሪያ ክፍል የአክቲቪቲ ገጽ