ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የዳግም መመለስ ድምጾች፦ ኤማ ሄል ስሚዝ


“የዳግም መመለስ ድምጾች፦ ኤማ ሄል ስሚዝ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ኤማ ሄል ስሚዝ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
የዳግም መመለስ ድምጾች ምልክት

የዳግም መመለስ ድምጾች

ኤማ ሄል ስሚዝ

ምስል
A painted portrait by Lee Greene Richards of Emma Hale Smith in a black dress and a white shawl.

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25 ተመዝግበው የሚገኙት የጌታ ቃላት ስለእርሷ ያለውን ስሜት እና ለስራው ልታደርገው ስለምትችለው አስተዋጽኦ ይገልጻሉ። ነገር ግን ኤማ ምን ዓይነት ሰው ነበረች? ሰለስብዕናዋ፣ ስለግንኙነቶቿ፣ ስለጥንካሬዋ ምን እናውቃለን? ስለዚህች “የተመረጠች ሴት” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥3) የምናውቅበት አንደኛው መንገድ በግል ያውቋት የነበሩትን ሰዎች ቃላት በማንበብ ነው።

ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ የእርሷ ባለቤት

ምስል
One drawing in pencil, charcoal and ink on paper. A left profile, head/shoulders portrait of Joseph Smith; drawn basically in charcoal, highlighted with white paint and black ink. titled at bottom "Jospeh Smith the Prophet." Signed at left shoulder "Drawn from the most authentic sources by Dan Weggeland" A drawn border surrounds it. No date apparent.

“በዚያ ምሽት፣ የእኔን ውድ ኤማ፣ የእኔን ሚስት፣ እንዲሁም የልጅነት ሚስቴን፣ የልቤን ምርጫ፣ በእጄ ስይዝ ሊነገር በማይችል ደስታ እንዲሁም ውስጤን ተጉዞ በሞላ ደስታ ተጥለቅልቄ ነበር። እንድንጓዝባቸው የተጠራንባቸውንና ብዙ ድርጊቶች የተከናወኑባቸውን ቦታዎች ለአፍታ ዞር ብዪ ሳስብ ቦታዎቹ የሚያመነጯቸው የተለዩ የአዕምሮዬ ሥሜቶች ብዙ ነበሩ፡፡ ድካሞቹ፣ ልፋቶቹ፣ ሃዘኖቹ፣ ስቃዮቹ፣ እና አልፎ አልፎ ይመጡ የነበሩት ደስታዎች እና መጽናኛዎች መንገዳችንን የተደላደለ አድርገውልናል እንዲሁም መጨረሻችንን ያማረ አድርገውታል። አቤቱ! ለጊዜው አእምሮዬን እንዴት የተለያዩ ሃሳቦች ሞሉት። አፍቃሪዋ ኤማ በሰባተኛው ችግር ውስጥም፣ ሳትበገር፣ ጠንክራ፣ ሳታወላውል፣ ሳትለወጥ፣ አሁንም እዚህ አለች።”

ሉሲ ማክ ስሚዝ፣ የባሏ እናት

“ያኔ እርሷ ወጣት ነበረች፣ እንዲሁም በተፈጥሮዋ ሥኬትን ለማምጣት ቁርጠኛ ስትሆን፣ ልቧ በሙሉ በጌታ ስራ ላይ ነበር፣ እንዲሁም ስለቤተክርስቲያኗ እና ስለእውነት ዓላማ ካልሆነ በስተቀር ስለሌላ ነገር ፍላጎት አልነበራትም። እጇ ውስጥ የገባውን ማንኛውንም ነገር የምትሰራው በሙሉ ሃይሏ ነበር እንዲሁም ‘ከሌላው ሰው በበለጠ እጠቀማለው ወይ?’ የሚልን ራስ ወዳድ ጥያቄ አትጠይቅም ነበር። ሽማግሌዎች ለመስበክ ከተላኩ፣ የራሷን ጉዳዮች እንዳሉ በመተው፣ ለጉዟቸው የሚያሰፈልጓቸውን ልብሶች እንዲለብሱ ለመርዳት አገልግሎቷን በፈቃደኝነት በመስጠት የመጀመሪያዋ ነበረች።”

ጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ፣ አማቷ

በወቅቱ የቤተክርስቲያኗ ፓትሪያሪክ ሆነው ሲያገለግሉ በነበሩት በጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ የተሰጠ የኤማ የፓትሪያሪክ በረከት፦

“ኤማ፣ ምራቴ፣ በታማኝነትሽና እውነትሽ በጌታ የተባረክሽ ነሽ፣ ከባለቤትሽ ጋር ትባረኪያለሽ፣ ለእርሱ በሚመጣው ክብርም ትደሰቻለሽ፤ የአጋርሽን መውደም በሚፈልጉ ሰዎች ክፋት የተነሳ ነፍስሽ ታውካለች፣ ለእርሱ ደህንነትም ነፍስሽ በሙሉ በጸሎት ተስባለች፤ ተደሰቺ ጌታሽ እግዚአብሔር ልመናሽን ሰምቶሻልና።

“ስለ አባትሽ ቤት ልበ ደንዳናነት በጣም አዝነሻል፣ ደህንነታቸውንም ናፍቀሻል። ጌታ ጩኸትሽን ይሰማል፣ በፍርዱም የተወሰኑት ስህተታቸውን እንዲገነዘቡና ለኃጢያታቸው ንስሃን እንዲገቡ ያደርጋል፤ ነገር ግን የሚድኑት በመከራ ነው። ብዙ ዘመናትን ትኖሪያለሽ፤ አዎን፣ እስከምትረኪ ድረስ ጌታ ያኖርሻል፣ አዳኛሽን ታያለሽና። በጌታ ስራም ልብሽ ደስ ይለዋል፣ እንዲሁም ማንም ደስታሽን ካንቺ አወስድም።

“መልዓኩ የኔፋውያንን መዝገብ እንዲጠብቅ በሰጠው ጊዜ ከልጄ ጋር አብረሽ እንድትሄጂ ስለፈቀደልሽ ሁልጊዜም የአምላክሽን ታላቅ ትህትና ታስታውሻለሽ። ጌታ ሶስት ልጆችሽን ስለወሰደ ብዙ ሃዘን ገጥሞሻል፣ የእኔ ልጅ ስም ይባረክ ዘንድ ልጆችን ለማሳደግ ያለሽን ንጹህ ፍላጎት ስለሚያውቅ አንቺ በዚህ አትወቀሽም። እናም እነሆ፣ አሁን እንዲህ እልሻለሁ፣ ጌታም እንዲህ ይላል፣ ብታምኚ በዚህ ነገር ገና ትባረኪያለሽ እናም ለነፍስሽ ሃሴትና እርካታ እንዲሁም ለባልንጀሮችሽ ደስታ ይሆን ዘንድ ሌሎች ልጆችን ትወልጃለሽ።

“በማስተዋልም ትባረኪያለሽ፣ እናም የጾታ አጋሮችሽን የማስተማር ሃይል ታገኛለሽ። ቤተሰብሽን ጽድቅን፣ ትንንሾችሽንም የህይወትን መንገድ አስተምሪ፣ እናም ቅዱሳት መላዕክት ይጠብቁሻል፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ትድኛለሽ፤ ይህም ይሁን። አሜን።”

ምስል
ኤማ ስሚዝ እና ልጆች

ኤማ ስሚዝ ከልጆቿ ጋር። የመሳቅ ጊዜ፣ በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

አትም