“የካቲት 24–መጋቢት 2 (እ.አ.አ)፦ ‘የነፍስ ዋጋ … ታላቅ ነው’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]
“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
የካቲትት 24–መጋቢት 2 (እ.አ.አ)፦ “የነፍስ ዋጋ … ታላቅ ነው”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18
የአንድን ሰው ዋጋ ለመለካት መሞከር የሚቻልባቸው ብዛት ያላቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ። ተሰጥኦ፣ ትምህርት፣ ሀብት እና አካላዊ ቁመና እርስ በርስ በምንገማገምበት እንዲሁም ራሳችንን በምንገመግምበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። ሆኖም፣ በእግዚአብሔር ዓይን የእኛ ዋጋ በጣም የማያሻማ ጉዳይ ነው፤ ይኸውም በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18 ውስጥ “የነፍስ ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ እንደሆነ አስታውስ” (ቁጥር 10) በማለት በግልፅ እንደተቀመጠው ነው። ይህ ቀላል እውነት እግዚአብሔር ምን እንደሚያደርግ እና ለምን እንደሚያደርግ አብዛኛውን ነገር ያብራራል። የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን በዘመናችን እንዲመሰርቱ ጆሴፍ ስሚዝን እና ኦሊቨር ካውደሪን ለምን አዘዛቸው? (ቁጥር 1–5 ተመልከቱ) ምክንያቱም የነፍስ ዋጋ ታላቅ ስለሆነ ነው። “በሁሉም ሥፍራ ሁሉም ሰዎች ንስሐ እንዲገቡ [የሚያዛቸው]” እና ንስሐን እንዲሰብኩ ሐዋርያትን የላከው ለምንድን ነው? (ቁጥር 9)። ምክንያቱም የነፍስ ዋጋ ታላቅ ስለሆነ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ “የሥጋ ሞትን የሞተው” እና “የሰዎችን ሁሉ ህመም የተሠቃየው” ለምንድን ነው? (ቁጥር 11)። ምክንያቱም የነፍስ ዋጋ ታላቅ ስለሆነ ነው። ከእነዚህ ነፍሳት ውስጥ አንዱ እንኳን የአዳኙን ስጦታ ለመቀበል ቢመርጥ ይደሰታል፣ ምክንያቱም “ንስሃ በሚገባ ነፍስ ያለው ደስታ ታላቅ [ስለሆነ]” (ቁጥር 13)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
“ቤተክርስቲያኔን [ገንቡ]።”
በቁጥር 18 ውስጥ፣ ኦሊቨር ካውደሪ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን መሰረት በመመስረት ይረዳ ዘንድ ጌታ መመሪያ ሰጠው። በተለይ በቁጥር 1–5 ውስጥ እርሱ ስለሰጠው ምክር ምን ታስተውላላችሁ? በክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት “ስትገነቡ” ይህ ምክር ለእናንተ እንዴት እንደሚሠራ ልታስቡ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፦
-
ስለጌታ “ለማወቅ የምትሹት” የነበረው ምንድን ነው? (ቁጥር 1)።
-
“በተፃፉት ላይ እንድትደገፉ” ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው? (ቁጥር 3)። እነዚህ ነገሮች እውነት እንደሆኑ መንፈሱ “የገለጠላችሁ” እንዴት ነው? (ቁጥር 2፤ በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥22–24ን ተመልከቱ)።
-
ህይወታችሁን “በ[አዳኙ] ወንጌል እና [በአለቱ] መሠረት” ላይ እንዴት መገንባት ትችላላችሁ? (ቁጥር 5)
“የነፍስ ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ [ነው]”
የአንድን ነገር ዋጋ የምንወስነው እንዴት ነው? ለምሳሌ፣ በገበያ ላይ አንድ ነገር ከሌላው የበለጠ ውድ የሚሆነው ለምንድን ነው? በዚህ ሳምንት ቁጥር 18 በተለይም ቁጥር 10–13ን ስታነቡ፣ ብዙውን ጊዜ ሰዎች ዋጋን የሚወስኑበትን መንገድ በእግዚያብሔር ዓይን የነፍስን ዋጋ ውድ ከሚያደርገው ነገር ጋር ልታነፃፅሩ ትችላላችሁ። “ነፍስ”፣ “ነፍሳት”፣ እና “ሰዎች” በሚሉት ቦታዎች የራሳችሁን ስም ተክታችሁ ማንበብን አስቡ። እነዚህ ጥቅሶች የእርሱን ወይም የእርሷን ዋጋ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባን/የምታስገባን ሰው እንዴት ሊረዱ ይችላሉ?
ስለነፍስ ዋጋ የሚያስተምሩ የተወሰኑ ሌሎች ጥቅሶች እነሆ፦ ሉቃስ 15፥1–10፤ ዮሐንስ 3፥16–17፤ 2 ኔፊ 26፥24–28፣ ሙሴ 1፥39። በእነዚህ ምንባቦች ላይ በመመስረት እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን ስሜት እንዴት በአጭሩ ትገልፁታላችሁ? በፕሬዚዳንት ዲየተር ኤፍ.ኡክዶርፍ መልዕክት “You Matter to Him [ለእርሱ ዋጋ አላችሁ]” (ሊያሆና፣ ህዳር 2011 (እ.አ.አ)፣ 19–22) ውስጥ እናንተ እግዚአብሔር ምን ዋጋ እንዳላችሁ እንድታውቁ የሚረዷችሁን ቃላት እና ሀረጎች ልትፈልጉ ትችላላችሁ።
እግዚአብሔር ለእርሱ ትልቅ ዋጋ እንዳላችሁ የሚያሳያችሁ እንዴት ነው? ይህ ስለራሳችሁ እና ስለ ሌሎች በሚሰማችሁ ስሜት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?
እንዲሁም ጆይ ዲ. ጆንስ፣ Value beyond Measure [ከመጠን በላይ ዋጋ ያለው]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 13–15፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “Children of God [የእግዚአብሔር ልጆች]፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።
ንስሃ ስገባ ጌታ ይደሰታል።
እንደ ንስሃ ግቡ እና ንስሃ ያሉ ቃላት በመላው በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18 ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ጥቅም ላይ እንደዋሉ አስተውሉ። ጥቅም ላይ በዋሉባቸው በእያንዳንዱ ጊዜ ከእነዚህ ቃላት ምን እንደምትማሩ አስቡ። በተለይ ደግሞ ቁጥሮች 11–16ን ግምት ውስጥ አስገቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለንስሃ ያላችሁን አስተሳሰብ—ስለራሳችሁ ንሰሃ መግባትና ሌሎች ወደ ንስሃ እንዲገቡ እና እንዲሻሻሉ ለማድረግ ያለባችሁን ሃላፊነትስ እንዴት ይነኩታል? የምትማሩትን የመመዝገብ አንድ መንገድ እነሆ፦ “ንስሐ መግባት ማለት ” የሚለውን ዓረፍተ ነገር የምታሟሉባቸውን የተለያዩ መንገዶች ዘርዝሩ።
በተጨማሪም አልማ 36፥18–21፤ የቅዱሳት መፃሕፍት መመሪያ “ንስሃ መግባት፣” ወንጌል ላይብረሪ፤ ዴል ጂ. ረንለንድ፣ “Repentance: A Joyful Choice [ንስሀ መግባት፦ አስደሳች ምርጫ]፣” ሊያሆና ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 121–24ን ተመልከቱ።
ሌሎችን ወደክርስቶስ እንዲመጡ በመርዳት ደስታ ይገኛል።
ቁጥር 31፥14–16ን ስታነቡ “ንሥሃን እንድትጮሁ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ደስታን ለምን እንደሚያመጣ አሰላስሉ። ሌሎች ወደ አዳኝ እንዲመጡ እና ይቅርታን እንዲያገኙ ለመርዳት ያገኛችኋቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ናቸው? ሌሎች ሰዎች ይህንን ለእናንተ እንዴት ያደረጉላችኋል?
በተጨማሪም ክሬግ ሲ ክርስቲያንሰን፤ “There Can Be Nothing So Exquisite and Sweet as Was My Joy [እንደ ደስታዬ በጣም የሚያምር እና ጣፋጭ ነገር ሊኖር አይችልም]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 45–47 ተመልከቱ።
በቅዱሳት መፃሕፍት ውስጥ የጌታን ድምጽ እሰማለሁ።
አንድ ሰው የጌታ ድምጽ ምን አይነት ነው ብሎ ቢጠይቃችሁ ምን ብላችሁ ትመልሳላችሁ? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥34–36ን ስታነቡ ይህንን ጥያቄ አስቡ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን ስታነቡ ስለ ጌታ ድምጽ ምን ተማራችሁ? ድምጹን በበለጠ ጥራት ለመስማት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
በተጨማሪም “As I Search the Holy Scriptures [ቅዱሳት መጻህፍትን ስፈትሽ]፣” መዝሙር፣ ቁ. 277 ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ዋጋ አለን።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–13ን ስታነቡ አንዳችሁ የሌላችሁን ስም “ነፍስ”፣ “ነፍሳት”፣ እና “ሰዎች” በሚለው መተካትን አስቡ። ከዚያም እነዚህ ጥቅሶች የሰማይ አባት ስለእያንዳንዳችን እንዴት እንደሚሰማው እኛን ስለሚረዱበት መንገዶች ልትነጋገሩ ትችላላችሁ።
-
ሰዎች ውድ እንደሆኑ ስለሚያስቧቸው ነገሮች ልጆቻችሁን ልትጠይቋቸውም ትችላላችሁ። ወይም ለእናንተ ዋጋ ያለውን ነገር ልታሳዩአቸውም ትችላላችሁ። ለእኛ ጠቃሚ የሆኑትን ነገሮች የምንይዛቸው እንዴት ነው? ከዚያም ተራ በተራ በመስታወት እንዲመለከቱ ፍቀዱላቸው። ይህንን ሲያደርጉ፣ ሁሉንም ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆኑና ታላቅ ዋጋ እንዳላቸው ንገሯቸው። “የነፍ[ሳቸው] ዋጋ [በእኛ] ፊት ታላቅ [እንደሆነ]” ለሌሎች ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–13 ስታነቡ፣ ሁሉም ሰዎች ለሰማይ አባት ትልቅ ዋጋ እንዳላቸው አፅንዖት ለመስጠት፣ ልጆቻችሁ በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ያለውን ምሥል መመልከት ይችላሉ። እንደ “Every Star Is Different [እያንዳንዶ ኮኮብ ልዩ ነው]” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 142–43) ዓይነት መዝሙር ይህን ነጥብ ለማጠናከር ሊረዳ ይችላል።
ወንጌልን ማካፈል ደስታን ያመጣል።
-
ልጆቻችሁ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲያካፍሉ ለማነሳሳት፣ ከጓደኞቻችሁ ወይም ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ልታካፍሉ ፈልጋችሁ የነበረውን ነገር ስታገኙ ስለነበራችሁ ተሞክሮ እርስ በርሳችሁ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ልታካፍሉ የፈለጋችሁት ለምን ነበር፣ እንዲሁም ማካፈሉስ ምን እንዲሰማችሁ አደረገ? ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥13፣ 16ን ልታነቡ ትችላላችሁ። ለጌታ ደስታን የሚያመጣው ምንድን ነው? ጌታ ደስታ የሚያመጣልን ምን ነው ብሏል? እናንተ እና ልጆቻችሁ የአዳኙን ወንጌል ደስታ በማካፈል ስላገኛችሁት ስለማንኛውም ተሞክሮ ልትናገሩም ትችላላችሁ።
-
እንደ “አሁን ሚሲዮናዊ ለመሆን እፈልጋለሁ” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 168) ያሉ ወንጌልን ስለማካፈል የተዘመሩ መዝሙሮች ልጆቻችሁ ወንጌልን ማካፈል ስለሚችሉባቸው መንገዶች እንዲያስቡ ሊረዳቸው ይችላል።
በቅዱሳት መፃህፍት ውስጥ የጌታን ድምጽ መስማት እችላለሁ።
-
ልጆቻችሁ የቤተሰብ አባላትን፣ የጓደኞችን ወይም የቤተክርስቲያን መሪዎችን የመሰሉ ሰዎችን ድምጽ የመለየት ሙከራ የሚያደርጉበት ጨዋታ በመጫወት ሊዝናኑ ይችላሉ። አንዳችን የሌላችንን ድምፅ መለየት የምንችለው እንዴት ነው? የጌታን ድምጽ የምንለየው እንዴት ነው? በዚህ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥34–36 በጋራ ማንበብ ትችላላችሁ። የጌታን ድምጽ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እንዴት እንደሰማችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ ማካፈልም ትችላላችሁ።