ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መጋቢት 3–9 (እ.አ.አ)፦ “ከእኔ ተማሩ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19


“መጋቢት 3–9 (እ.አ.አ)፦ ‘ከእኔ ተማሩ’ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ በአንድ ዛፍ አጠገብ ባለ መንገድ ላይ እየሄደ

ዝርዝር ከየጌቴሴማኒ መንገድ፣” በስቲቭ ማክጊንቲ

መጋቢት 3–9 (እ.አ.አ)፦ “ከእኔ ተማሩ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19

ማርቲን እና ሉሲ ሃሪስ በፓልማይራ፣ ኒው ዮርክ ውስጥ ድንቅ የሆነ እርሻዎች ለማግኘት አመታትን ፈጀባቸው። ነገር ግን በ1829 (እ.አ.አ)፣ መፅሐፈ ሞርሞን ለመታተም የሚችለው ማርቲን መሬቱን በብድር አስይዞ ለማተሚያ ቤቱ ከከፈለ ብቻ መሆኑ ግልጽ ሆነ። ማርቲን የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክርነት ቢኖረውም ሉሲ ግን አልነበራትም። ማርቲን መሬቱን በብድር በማስያዙ ቢገፋበትና መፅሐፈ ሞርሞን በደንብ ባይሸጥ መሬቱን ያጣል፣ ትዳሩን አደጋ ላይ ይጥላል እንዲሁም በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ስም ያበላሻል። ምንም እንኳን የእኛ ሁኔታ ማርቲን ከነበረበት ሁኔታ የተለየ ቢሆንም፣ በአንድ ወይንም በሌላ ጊዜ፣ ልክ እንደ እርሱ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለእኔ ያለው ዋጋ ምን ያህል ነው? ከሚል ከባድ ጥያቄ ጋር እንጋፈጣለን። የእግዚአብሔርን መንግስት በመገንባት ለመርዳት ምን መስዋዕነት ለመክፈል ፍቃደኛ ነኝ? በመጨረሻም ማርቲን ሃሪስ የመጀመሪያዎቹ 5 ሺህ የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂዎች ይታተሙ ዘንድ መሬቱን በብድር ለማስያዝ ወሰነ። ሆኖም፣ ይህ መስዋዕትነትም ሆነ ልንከፍለው የምንችለው ማንኛውም መስዋዕትነት ንስሃ የገቡትን ለማዳን ደሙ ከእያንዳንዱ የሠውነቱ ቀዳዳ የፈሠሠው “የሁሉም ታላቅ የሆነው”፣ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥18) ኢየሱስ ክርስቶስ ከከፈለው መስዋዕትነት ጋር ሲነፃፀር ትንሽ ነው።

ሰለመፅሐፈ ሞርሞን ህትመት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቅዱሳን፣ 1፥76–84ን ተመልከቱ።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥1–12

“እኔ እግዚአብሔር መጨረሻ የለኝምና።”

ጆሴፍ ስሚዝ በክፍል 19 ውስጥ የተገለፀው ራዕይ “ለማርቲን ሃሪስ … ዘለዓለማዊ በሆነው … የተሰጠ ትዕዛዝ” (የክፍል ርዕስ) እንደሆነ አብራርቷል። ቁጥር 1–12 ውስጥ ጌታ ስለዘለዓለማዊ ተፈጥሮው አፅናዖት የሰጠባቸውን ቦታዎች ፈልጉ። ማርቲን፣ ስለጌታ እነዚህን እያንዳንዱን ነገሮች ማወቁ ጠቃሚ የነበረው ለምን ይመስላችኋል? ይህንን ማወቃችሁ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ክርስቶስ “አልፋና ኦሜጋ” ተብሎ የሚጠራው ለምን ይመስላችኋል? (ቁጥር 1)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥15–20

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቃየው ንስሃ መግባት እና ወደ እርሱ መምጣት እንድችል ነው።

አዲስ ኪዳን፣ የአዳኙን የጌተሰማኔ ስቃይ በዓይናቸው በተመለከቱት ሰዎች እይታ አንጻር ይገልፃል። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥15–20 ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ስቃዩ ከራሱ እይታ አንፃር ተናግሯል። ይህን የተቀደሰ የግል ታሪክ ስታነቡ፣ አዳኙ ስቃዩን እንዴት እንደገለፀ ፈልጉ። እያንዳንዱ ቃል ወይም ሃረግ ምን እንደሚያስተምራችሁ አስቡ። ጌታ ለመሰቃየት ፈቃደኛ የነበረው ለምንድን ነው? በዮሀንስ 15፥13ሞዛያ 3፥7አልማ 7፥11–12ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–13 ውስጥ ተጨማሪ ማግኘት ትችላላችሁ።

የአዳኙን ስቃይ በምታጠኑበት ጊዜ የሚኖራችሁ ስሜት እንደእነዚህ የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ሊያስነሳ ይችላል፦ አዳኙ ለኃጥያቴ ለምን መሰቃየት አስፈለገው? የእርሱን ሙሉ የመስዋዕትነት በረከት ለመቀበል ለምን ንስሐ መግባት አለብኝ? በዮልሲስ ሶሬስ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ፦ የነፍሳችን ተንከባካቢ [Jesus Christ: The Caregiver of Our Soul]፣” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ) 82–84) ውስጥ ስለእነዚህ እና ስለሌሎች ጥያቄዎች ግንዛቤዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ። ስታጠኑ ምን ሃሳቦች ወደ አዕምሮአችሁ መጡ። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ለእናንተ ስለከፈለው መስዋዕትነት የሚሰማችሁን ስሜት መመዝገብን አስቡ።

የጥናታችሁ እና የአምልኳችሁ አካል በማድረግ፣ አዳኙ ስለእናንተ ስለደረሰበት መከራ ያላችሁን ምሥጋና የሚገልጽ ልታዳምጡት ወይም ልትዘምሩት የምትችሉትን መዝሙር ልትፈልጉ ትችላላችሁ። “I Stand All Amazed [በድንቀት ቆሜ አለሁ]” የሚለው መዝሙር (መዝሙር፣ ቁጥር 193)፣ ጥሩ ምሳሌ ነው።

የተሰማችሁን ሥሜት እና ጥናታችሁን ተከትሎ የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንድታደርጉ እንደሚፈልጉ ይሰማችኋል?

በተጨማሪም “Jesus Christ Will Help You [ኢየሱስ ክርስቶስ ይረዳችኋል]፣” በለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ (2022)፣ 6–9፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “Atonement of Jesus Christ [የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ]፣” “Repentance [ንስሀ መግባት]”፣ ወንጌል ላይብረሪ፤ ዲ.ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “The Divine Gift of Repentance [ንስሀ የመግባት መለኮታዊ ስጦታ]፣” lሊያሆና፣ ህዳር 2011፣ 38–41፤ “Jesus Suffers in Gethsemane [ኢየሱስ በጌትሰመኔ ተሰቃየ]” (ቪዲዮ)፣ ወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥23

ሰላም የሚመጣው ከኢየሱስ ክርስቶስ በመማርና እርሱን በመከተል ነው።

“ከእኔ ተማሩ” የሚለውን የአዳኙን ግብዣ አስቡ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19 ውስጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ትማራላችሁ? እነዚህ የአዳኙ እውነታዎች ሰላምን ማግኘት እንድትችሉ እንዴት እንደረዷችሁ ሃሳባችሁን መዝግቡ ከዚያም አሰላስሉ። “[በመንፈሱ] በትህትና [መጓዝ]” ማለት ለእናንተ ትርጉም አለው?

በተጨማሪም ሄንሪ ቢ. አይሪንግ፣ Finding Personal Peace [የግል ሰላምን ማግኘት]፣ “ሊያሆና፣” ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 29–31፤ “Peace in Christ [ሰላም በክርስቶስ]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥26–41

የእግዚአብሔር በረከቶች ከምድር ሁሉ ሃብት ይበልጣሉ።

መፅሐፈ ሞርሞን በፓልማይራ በደንብ አልተሸጠም። በዚህም የተነሳ ማርቲን ሃሪስ ብዙውን የእርሻውን ክፍል ሸጦ የአሳታሚውን እዳ መክፈል ነበረበት (“The Contributions of Martin Harris [የማርቲን ሃሪስ አስተዋጽዖ]፣” ራዕያት በአገባብ፣ 7–8ን ተመልከቱ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥26–41ን ስታነቡ ስለ ማርቲን አስተዋፅዖ እና በእርሱ ምክንያት ስለተቀበላችኋቸው በረከቶች አሰላስሉ። በተጨማሪም ጌታ ምን መስዋዕት እንድታደርጉ እንደጠየቃችሁም ማሰብ ትችላላችሁ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ መስዋዕትነቶችን “በደስታ” እና “ልብን ለደሥታ በማነሳሳት” እንድትከፍሉ የሚያበረታታችሁን ምን ታገኛላችሁ? (በተጨማሪም ቁጥር 15–20ን ተመልከቱ)።

ምስል
በፓልማይራ የሚገኝ እርሻ ሥዕል

ዝርዝር ከማርቲን ሀሪስ እርሻ በአል ራውንድስ

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥16–19

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ ተሰቃየ።

  • ከልጆቻችሁ ጋር በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥16–19 ወይም በ“Chapter 51: Jesus Suffers in the Garden of Gethsemane [ምዕራፍ 51፦ ኢየሱስ በጌትሰመኔ የኣትክልት ስፍራ ውስጥ ተሰቃየ]፣” (በአዲስ ኪዳን ታሪኮች፣ 129–32፣ ወይም ዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ያለውን አብራችሁ በማንበብ ጥልቅ አክብሮት እና ምስጋና እንዲሰማቸው ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ እንደተገነዘቡ ለማረጋገጥ እና ሥሜታቸውን እንዲገልፁ ለመፍቀድ ለአፍታ ቆም ማድረግን አስቡ። ለምሳሌ፣ በቁጥር 16 ውስጥ ስለ እኛ የተሰቃየባቸው “እነዚህ ነገሮች” ምንድን ናቸው (ሞዛያ 3፥7አልማ 7፥11–12 ተመልከቱ)። ስሥቃዩን በተመለከተ ካደረገው ገለፃ ምን እንማራለን? ስላደረገልን ነገር ያለንን ምስጋና እንዴት ለማሳየት እንችላለን?

ልጆች ከቅዱሳት መጻህፍት እንዲማሩ አግዙ። አንዳንድ ልጆች ቅዱሳት መፃህፍትን በማንበብ ይቸገራሉ። በአንድ ጥቅስ ወይም ሐረግ ላይ ማተኮር ሊረዳቸው ይችል ይሆናል።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ በመዝሙር ወይም በ ልጆች የመዝሙር መፅሐፍ ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰማችሁን ሥሜት የሚገልፁ መዝሙሮችን ልትመለከቱ ትችላላችሁ (በእነዚህ መፃህፍት ውስጥ የሚገኙትን የርዕስ ማውጫዎች ተመልከቱ)።

ምስል
ኢየሱስ በጌትሴማኔ ሲጸልይ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥18–19፣ 24

አስቸጋሪ በነበረበት ጊዜም እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማያዊ አባት ታዛዥ ሆኗል።

  • ለኃጢያታችን መሰቃየት ከባድ ነበር፣ ሆኖም ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱን ለመታዘዝ እንዲሁም ለእርሱ እና ለእኛ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ሲል ያንን ለማድረግ ፈቃደኛ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ በጌቴሴማኒ ሥቃይ ሲቀበል የሚያሳይን አንድ ሥዕል (በዚህ መዘርዝር እንዳለው አይነት) አብራችሁ ልትመለከቱና ልጆቻችሁ በሥዕሉ ላይ እየሆነ ስላለው ነገር የሚያውቁትን እንዲነግሯችሁ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ለኃጢአታችን መሰቃየት ማንም ሰው ካደረገው ሁሉ ከባዱ ነገር እንደሆነ ሆኖም ኢየሱስ አባቱን እና እኛን ስለወደደ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደታዘዘ አጽንዖት ለመስጠት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥18–19፣ 24ን አብራችሁ ልታነቡ እና ትችላላችሁ (በተጨማሪም ሞዛያ 3፥7 ተመልከቱ)። ምን አስቸጋሪ ነገሮችን የሰማይ አባት እንድናደርግ ይጠይቀናል? እርሱን ለመታዘዝ ድፍረት ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥23

“ከእኔ ተማር፣ እናም ቃላቴን አድምጥ።”

  • ልጆቻችሁ በትምህርትና ቃል ኪዳኖች 19፥23 ውስጥ ከሚገኙ ሀረጎች ጋር አብረው የሚሄዱ ቀላል ተግባራትን እንዲያስቡ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ድርጊቶቹን በሚያከናውኑበት ጊዜ ጥቅሶቹን ለበርካታ ጊዜያት አንብቡ። ከክርስቶስ ልንማርባቸው እና ቃሉን ልናዳምጥ የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥38

የእግዚአብሔር በረከቶች ከምድር ሁሉ ሃብት ይበልጣሉ።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ የመፅሐፈ ሞርሞንን አንድ ቅጂ ተራ በተራ በእጃችሁ ልትይዙ እና ስለእሱ የምትወዱትን ልታካፍሉ ትችላላችሁ። መፅሐፈ ሞርሞን ይታተም ዘንድ ማርቲን ሃሪስ የከፈለውን መስዋዕትነት በአጭሩ ተናገሩ (የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች33 ተመልከቱ)። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥38 ውስጥ ምን ማርቲን ታማኝ እና ታዛዥ እንዲሆን ሊረዳው የሚችለውን ጌታ ነገረው? ልጆቻችሁ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ወይም ስራው እንዲከናወን ለመርዳት ሊከፍሉ የሚችሉትን አንድ መስዋዕትነት እንዲያስቡ እርዷቸው።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ በጌቴሴማኔ ሥዕል

ክርስቶስ በጌቴሴማኔ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በሀርማን ክሌመንትዝ

ምስል
የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ

አትም