ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የዳግም መመለስ ድምጾች፦ የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮች


“የዳግም መመለስ ድምጾች፦የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

የዳግም መመለስ ድምጾች ምልክት

የዳግም መመለስ ድምጾች

የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮች

መልዓኩ ሞሮኒ፣ በፌየት፣ ኒው ዮርክ በሚገኘው የዊትመር ቤተሰብ ቤት አቅራቢያ ባለው ጫካ ውስጥ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ለኦሊቨር ካውድሪ፣ ለዴቪድ ዊትመር እና ለማርቲን ሃሪስ አሳያቸው። በዚያ ወቅት የጆሴፍ ወላጆች የዊትመርን ቤተሰብ ለመጠየቅ ሄደው ነበር። የጆሴፍ እናት፣ ሉሲ ማክ ስሚዝ፣ ይህ ተአምራዊ ተሞክሮ በምስክሮቹ ላይ የነበረውን ተጽዕኖ እንዲህ ገልፃለች፦

“በሶስት እና አራት ሰዓት መካከል ነበር። ወይዘሮ ዊትመር እና አቶ ስሚዝ እንዲሁም እኔ በአንድ መኝታ ቤት ውስጥ ተቀምጠን ነበር። እኔ ከአልጋው ጎን ተቀምጬ ነበር። ጆሴፍ ወደ ውስጥ ገባና እራሱን አጠገቤ በነበረው አልጋ ላይ ወረወረ። ‘አባዬ! እማዬ!’ አለ። ‘ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ አታውቁም። ጌታ ሰሌዳዎቹን ከእኔ በተጨማሪ ሌሎች ሶስት ሰዎች እንዲያዩዋቸው አደረገ፣ መልዓክንም አይተዋል እናም ስለተናገርኩት ነገር እውነትነት መመስከር አለባቸው። እየዞርኩኝ ሰዎችን እንደማላጭበርበር እነርሱ ራሳቸው አውቀዋል። እናም ልቋቋመው ከምችለው በላይ በጣም ከባድ ሸክም እንደተገላገልኩኝ ለራሴ እየተሰማኝ ይገኛል። ነገር ግን አሁን እነርሱም የተወሰነውን ይሸከማሉ፣ ስለዚህም በዚህ አለም ላይ በችግሮቼ ያለረዳት ብቻዬን አለመሆኔን ማወቄ ነፍሴን ያስደስታታል።’ ከዚያም ማርቲን ሃሪስ ወደ ውስጥ ገባ። በደስታ የተጥለቀለቀ ይመስላል። ከዚያም እርሱ ስላየውና ስለሰማው መሰከረ፣ ሌሎቹም፣ ኦሊቨርና ዴቪድም እንዲሁ አደረጉ። ምስክርነታቸው በመፅሐፈ ሞርሞን ላይ ከሰፈረው ጋር በይዘቱ አንድ ነበር። …

“ማርቲን ሃሪስ በተለይ ስሜቱን በቃላት መግለፅ የተሳነው ይመስል ነበር። እርሱም እንዲህም አለ፣ ‘አሁን መዝገቦቹን አስመልክቶ የሰማሁት ሁሉ በእርግጠኝነት እውነት እንደሆነ የመሰከረልኝን ከሰማይ የመጣ መልዓክ አይቻለሁ፣ በእርግጥም አይኖቼ አይተውታል። ሰሌዳዎቹንም አይቻቸዋለሁ፤ በእጄም ዳስሻቸዋለሁ እናም ይህንን በተመለከተም ለመላው አለም መመስከር እችላለሁ። ነገር ግን ቃላት የማይገልጹት፣ ማንም በቃላት ማብራራት የማይችለውን የራሴን ምስክርነትን አግኝቻለሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔርን ራሱን ዝቅ አድርጎ እኔን፣ ያውም እኔን፣ ለሰው ልጆች ታላቅ ስራውና እቅዱ ምስክር ስላደረገኝ ከልቤ በትህትና እባርከዋለሁ።’ ኦሊቨርና ዴቪድም ስለደግነቱና ስለምህረቱ ለእግዚአብሔር መለኮታዊ ምስጋናን በማድረግ ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉ። በሚቀጥለው ቀን ደስተኛ ቡድን በመሆን ወደ ቤታችን [ወደ ፓልማይራ፣ ኒው ዮርክ] ተመለስን።”

ኦሊቨር ካውድሪ፣ ዴቪድ ዊትመር፣ እና ማርቲን ሃሪስ

ኦሊቨር ካውድሪ፣ ዴቪድ ዊትመር፣ እና ማርቲን ሃሪስ

ስምንቱ ምስክሮች ከተሞክሯቸው ሲመለሱ ሉሲ ማክ ስሚዝም በስፍራው ነበሩ።

A painting depicting Lucy Mack Smith, mother of Joseph Smith.

“እነዚህ ምስክሮች ወደቤት ከተመለሱ በኋላ፣ መልዓኩ በድጋሚ ለጆሴፍ ተገለጠ፣ በዚህ ወቅትም ጆሴፍ ሰሌዳዎቹን በእጁ አስረከበው። በዛን ምሽት ስብሰባን አደረግን፣ በዚሁም ሁሉም ምስክሮች ምስክርነታቸውን ከላይ በተገለጸው መልኩ ሰጡ፤ መላ ቤተሰባችን፣ እንዲሁም ምንም እንኳን 14 አመቱ ቢሆንም ዶን ካርሎስ [ስሚዝ] እንኳን ሳይቀር ስለኋለኛው ቀን የዘመን ፍጻሜ፣ ይህም በሙላት እንደመጣ፣ ምስክርነት ሰጡ።”

የጆሴፍ ስሚዝ እና የስምንቱ ምስክሮች ቅርፅ

የጆሴፍ ስሚዝ እና የስምንቱ ምስክሮች ቅርፅ

ከሶስቱ ምስክሮች እና ከስምንቱ ምስክሮች በተጨማሪ የዴቪድ ዊትመር እናት የሆነችውሜሪ ዊትመርም የወርቅ ሰሌዳዎች ምስክር በመሆን ተባርካለች። ጆሴፍ፣ ኤማ፣ እና ኦሊቨር በቤቷ ይኖሩ በነበረበት ጊዜ ለከፈለችው መስዋዕትነት እውቅና ለመስጠት መልአኩ ሞሮኒ እነኚህን አሳያት። ሞሮኒ “አንቺ ታማኝ እና በሥራሽም ታታሪ ነበርሽ” ሲል ነገራት። “ስለዚህ እምነትሽ ይጠነክር ዘንድ ምስክርነት ልትቀበዪ ይገባሻል።”