ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥር 27–የካቲት 2 (እ.አ.አ)፦ “ስራዬ ወደፊት ይቀጥላል”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3–5


“ጥር 27–የካቲት 2 (እ.አ.አ)፦ “ስራዬ ወደፊት ይቀጥላል”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3–5፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3–5፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ሠራተኛ በሜዳ ላይ

ጥር 27–የካቲት 2 (እ.አ.አ)፦ “ስራዬ ወደፊት ይቀጥላል”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3–5

ጆሴፍ ስሚዝ የጌታ ነቢይ በነበረባቸው የመጀመሪያዎቹ ጥቂት አመታት እንዲሰራው ስለተጠራበት “ድንቅ ስራ” ሁሉንም ነገር ገና አያውቅም ነበር። ነገር ግን የቀድሞ ተሞክሮው ያስተማረው አንድ ነገር ቢኖር የእግዚአብሔርን ስራ ለመስራት አይኖቹ “ወደ እግዚአብሔር ክብር” ብቻ መሆን እንዳለባቸው ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4፥1፣ 5)። ለምሳሌ፣ ከእርሱ ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ምክር ጌታ ቢሰጠው እንኳን የጌታን ምክር መከተል ያስፈልገው ነበር። ምንም እንኳን “ብዙ ራዕይ ቢቀበል፣ እናም ብዙ ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት ሀይል ቢኖረውም፣” የእርሱ ፍላጎት ከእግዚአብሔር ፍላጎት የበለጠ አስፈላጊ እንደሆነ ከተሰማው ለእርሱ “ውድቀት” ያመጣበታል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥4)። ነገር ግን ጆሴፍ ልክ የእግዚአብሔርን ስራ እንደመስራት አስፈላጊ የሆነ ሌላ ነገርን ተማረ፦ “እግዚአብሔር መሃሪ ነው፣” እናም ጆሴፍ ከልቡ ንስሃ ከገባ እርሱ “[አሁንም የተመረጠ]” ነበር (ቀጥር 10)። ከሁሉም በላይ፣ የእግዚአብሔር ስራ የማዳን ስራ ነው። እናም ያም ስራ “ሊከሸፍ … አይችልም”(ቀጥር 1)።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥1–16

የሴሚናሪ ምልክት
በእግዚአብሔር መታመን እችላለሁ።

በጆሴፍ ስሚዝ አገልግሎት መጀመሪያ አካባቢ ጥሩ ጓደኞችን—በተለይም እንደ ማርቲን ሃሪስ አይነት የተከበረ፣ ሃብታም፣ የጆሴፍን ስራዎች ለመደገፍ ታላላቅ መስዋዕቶችን የሚያደርግ ሰው ማግኘት በጣም ከባድ ነበር። ስለዚህም፣ ማርቲን የመፅሐፈ ሞርሞንን ትርጉም የእጅ ፅሁፍ የመጀመሪያ 116 ገጾች ለሚስቱ ለማሳየት ፈቃድ በጠየቀ ጊዜ፣ ምንም እንኳን ጌታ እንደዚያ እንዳያደርግ አስጠንቅቆት የነበረ ቢሆንም፣ ጆሴፍ ስሚዝ የማርቲንን ፍላጎት ለማክበር ፈለገ። በሚያሳዝን ሁኔታም፣ ጽሁፎቹ በማርቲን ይዞታ እያሉ ጠፉ፣ በዚህም የተነሳ ጌታ ጆሴፍን እና ማርቲንን በሃይለኛ ሁኔታ ገሰጻቸው (ቅዱሳን1፥51–53ን ተመልከቱ)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥1–15ን ስታነቡ፣ ከእነርሱ ተሞክሮ ጌታ ምን እንድትማሩ እንደሚፈልግ አሰላስሉ። ለምሳሌ፣ ስለሚከተሉት ነገሮች ምን ትማራላችሁ፦

  • ስለእግዚአብሔር ሥራ? (ቁጥር 1–3፣ 16 ተመልከቱ)።

  • በእግዚአብሔር ከመታመን ይልቅ ሰውን ስለመፍራት? (ቁጥር 4–8ን መልከቱ)።

  • ታማኝ ሆኖ በመዝለቅ ስለሚገኙ በረከቶች? (ቁጥር 8ን ተመልከቱ)።

  • ጌታ ጆሴፍን ስላስተካከለበት እና ስላበረታታበት መንገድ? (ቁጥር 9–16 ን ተመልከቱ)

ሽማግሌ ሊን ጂ. ሮቢንስ፣ Which Way Do You Face? [ወደየት ትመለከታላችሁ?] በተሰኘው መልዕክታቸው ውስጥ እግዚአብሔርን ስለፈሩ እንዲሁም ለሌሎች ግፊት እጅ ስለሠጡ ሠዎች የሚናገሩ ብዙ የቅዱሳት መፃህፍት ምሳሌዎችን አቅርበዋል (ሊያሆና፣ ህዳር 2014 (እ.አ.አ)፣ 9–11)። እርሳቸው የጠቆሟቸውን በቅዱሳት መፃህፍት የሚገኙትን ምሳሌዎች ማንበብን አስቡ። ከእነዚህ ምሳሌዎች ምን ትማራላችሁ? የተለየ ነገር እንድታደርጉ ግፊት በገጠማችሁ ጊዜ በጌታ የታመናችሁበት ምን ተሞክሮ አላችሁ? የድርጊቶቻችሁ ውጤቶች ምንድን ነበሩ?

በተጨማሪም ዴል ጂ. ረንለንድ “A Framework for Personal Revelation [የግል ራዕይ ንድፍ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 16–19፤ “The Contributions of Martin Harris [የማርቲን ሀሪስ አስተዋጽዖ]፣” በRevelations in Context [ራዕዮች በዐውደ-ጽሑፉ] [2016 (እ.አ.አ)]፣ 1–9፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “Seeking Truth and Avoiding Deception [እውነትን እሹ እናም መታለልን አስወግዱ]፣” ወንጌል ላይብረሪ፤ “How Gentle God’s Commands [ገር ነው የእግዚአብሔር ትእዛዝ]፣” መዝሙር፣ ቁ. 125 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4

እግዚአብሔርን በፍጹም ልቤ በፍጹም ነፍሴ በፍጹም አሳቤ ማገልገል እችላለሁ።

ክፍል 4 ብዙውን ጊዜ በሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን ላይ ይተገበራል። ነገር ግን ልብ መባል ያለበት አስደናቂ ነገር ቢኖር፣ ይህ ራዕይ በቅድሚያ ተሰጥቶ የነበረው ምንም እንኳን በሚስዮን ለማገልገል ባይጠራም “እግዚአብሔርን ለማግልግል ፈቃድ” ለነበረው ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ ነበር (ቁጥር 3)።

ይህንን ክፍል የማንበቢያ አንዱ መንገድ ቢኖር፣ ልክ በጌታ ስራ ለመርዳት የሚፈልግ የተሰጠ የአንድ ሰው የስራ ዝርዝር እንደሆነ አድርጎ በማሰብ ነው። ጌታ የሚፈልገው ምንድን ነው? ምን ጥቅሞችን ሰጥቶናል?

ከዚህ ራዕይ ጌታን ስለማገልገል ምን ትማራላችሁ?

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እስራኤልን የመሰብሰብ ስራ “ዛሬ በአለም ውስጥ ከሚገኙት በላይ ታላቁ ፈተና፣ ታላቁ ምክንያት፣ እና ታላቁ ስራ ” ነው ብለው ጠርተውታል (“Hope of Israel [የእስራኤል ተስፋ]” [አለም ዓቀፍ የወጣቶች የሃይማኖት ትምህርት፣ ሰኔ 3፣ 2018 (እ.አ.አ)]፣ ወንጌል ላይብረሪ)። በንግግራቸው ውስጥ በእርሱ ሥራ እንድትሳተፉ የሚያነሳሳችሁን ምን ታገኛላችሁ?

ሚስዮናውያን አገልግሎት በመሥጠት ላይ እያሉ አንዲትን ሴት እያነጋገሯት

እግዚአብሔርን ለማገልገል ፍላጎት ያለው ሁሉ ወደ ስራው ተጠርቷል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5

በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፣ የመፅሐፈ ሞርሞንን ምስክርነት ማግኘት እችላለሁ።

መጋቢት 1829 (እ.አ.አ) የማርቲን ሃሪስ ባለቤት ሉሲ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ሰዎችን ከወርቅ ሰሌዳዎች ላይ እየተረጎምኩ ነው በማለት እያጭበረበረ ነው ብላ ከሰሰች (ቅዱሳን1፥56–58ን ተመልከቱ)። ስለዚህም ማርቲን የወርቅ ሰሌዳዎቹ እውነት ስለመሆናቸው የሚያሳይ ተጨማሪ መረጃ እንዲያቀርብ ጆሴፍን ጠየቀው። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5 ለማርቲን ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተሰጠ ራእይ ነው። ከዚህ ክፍል ስለሚከተሉት ነገሮች ምን ትማራላችሁ፦

  • የወርቅ ሰሌዳዎቹ ለዓለም እንዲታዩ ቢደረጉ ኖሮ ሊከሰት ይችል ስለነበረው ነገር ጌታ ምን ብሎ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥7 ተመልከቱ)። እንደዚያ የሆነው ለምን ይመስላችኋል?

  • በጌታ ስራ ላይ ምስክሮች ስላላቸው ድርሻ (ቁጥር 11–15፤ በተጨማሪም 2 ቆሮንቶስ 13፥1ን ተመልከቱ)።

  • የራሳችሁን የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክርነት እንዴት ማግኘት እንደምትችሉ (ቁጥር 16፣ 24፤ በተጨማሪም ሞሮኒ 10፥3–5ን ተመልከቱ)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥1–10

ኢየሱስ ክርስቶስ ቃሉን በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ይሰጠናል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥1–10 ጆሴፍ ስሚዝ በእኛ ዘመን እና በህይወታችሁ ስላለው ሚና ምን ያስተምራችኋል? (በተጨማሪም 2 ኔፊ 3፥6–24ን ተመልከቱ።)

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥5–105፥21–22

ሌሎች የተሳሳተ ነገር እንዳደርግ ለመግፋፋት ሲሞክሩ ተክክለኛውን ነገር መምረጥ እችላለሁ።

  • በሰማይ አባት እንዴት መታመን እንደሚቻል ለመማር የሚደረግን ውይይት ለመጀመር፣ የጠፉትን የእጅ ጽሑፍ ገጾች ታሪክ መከለስ ትፈልጉ ይሆናል (የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች18–21 ተመልከቱ)። ከዚያም ትክክል እንዳልሆነ የሚያውቁትን ነገር ለማድረግ የሚፈተኑበትን ጊዜ የሚያሳዩ ሁኔታዎችን ከልጆቻችሁ ጋር መተወን ትችላላችሁ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥5–85፥21–22 ውስጥ እነዚህ ሁኔታዎች በሚያጋጥሟቸው ጊዜ የሚረዷቸው ምን ቃላት እና ሃረጎች ታገኛላችሁ?

    4:39

    Martin Harris Helps Joseph: Learning to trust the Lord

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4

ጌታ በሥራው ላይ እንድረዳ ይጋብዘኛል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4 ውስጥ ያሉ እያንዳንዱ ቁጥሮች ልጆቻችሁ እግዚአብሔርን ስለማገልገል እንዲማሩ ሊረዱ የሚችሉ ውድ እውነቶችን ይዘዋል። እነዚህን እውነቶች ለማግኘት ሊረዷቸው የሚችሉ አንዳንድ ሀሳቦች እነሆ፦

    • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4፥1ን አብራችሁ ልታነቡና የእግዚአብሔርን “ድንቅ” የኋለኛው ቀን ሥራ የሚያሳዩ ሥዕሎችን ማሳየት ትችላላችሁ።

    • ልጆቻችሁ “በፍጹም ልባችሁ፤ ኃይላችሁ፣ አዕምሮአችሁ፣ እና ብርታታችሁ እንድታገለግሉት” የሚለውን ሐረግ የሚያሳዩ ድርጊቶችን ሊያስቡ ወይም ሥዕሎችን ሊስሉ ይችላሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4፥2)።

    • በእርሻ ውስጥ ለመስራት የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን አንድ ላይ ሆናችሁ መመልከት ትችላላችሁ። እነዚህ መሳሪያዎች የሚረዱን እንዴት ነው? ከዚያም ልጆቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4፥5–6 ውስጥ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት እንደመሳሪያ የሆኑ ነገሮችን መፈለግ ይችላሉ።

    • ትልልቅ ልጆች ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4ን በራሳቸው ሊፈትሹና እግዚአብሔርን ስለማገልገል የተማሯቸውን ነገሮች ዝርዝር ሊያዘጋጁ ይችላሉ።

    • እንደ “I Want to Be a Missionary Now [አሁን ሚስዮን ለመሆን እፈልጋለሁ]” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 168) አይነት ስለሚስዮን አገልግሎት የሚያወሳ መዝሙር አብራችሁ መዘመር ትችላላችሁ።

ትንሽ ልጅ ዛፍ በመትከል እያገዘ

ሌሎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን ሥራ መርዳት እችላለሁ።

አክቲቪቲዎች አካል ጉዳተኞችን እንዲሳትፉ እንዲያስችል ማስተካከያዎችን አድርጉ። በአክቲቪቲዎች ላይ የሚደረጉ ትናንሽ ማስተካከያዎች ሁሉም ሰው የመማር አጋጣሚ እንደሚያገኝ ሊያረጋግጡ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ አንድ አክቲቪቲ ፎቶ ማሳየትን ቢያመለክት፣ የማየት እክል ያላቸውን ሰዎች ለማካተት መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥1–7፣ 11፣ 16፣ 23–24

መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ምስክር መሆን እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁን ስለምስክሮች ለማስተማር ጓደኛቸው አንዲት ድመት በሁለት እግሮቿ ስትራመድ እንዳዩ እንደነገራቸው እንዲያስቡ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ያንን ያምኑታል? ሌላ ጓደኛም የዚህን ተመሳሳይ ነገር ቢናገርስ? “ስለ ምስክር” ምንነት እንዲሁም ምስክሮች አስፈላጊ የሆኑት ለምን እንደሆነ ተነጋገሩ። ከዚያም ልጆቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥1–3፣ 7, 11 ውስጥ እንደሚከተሉት ላሉ ጥያቄዎች መልስ እንዲፈልጉ ልትረዷቸው ትችላላችሁ፦

    • ማርቲን ሃሪስ ለማወቅ የፈለገው ምን ነበር?

    • ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ለማን ማሳየት ይችል ነበር?

    • ሰሌዳዎቹን ማየት አንድን ሰው መፅሐፈ ሞርሞን እውነት መሆኑን ላያሳምን የሚችለው ለምንድን ነው?

    • የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮች ለመሆን ምን ልናደርግ እንችላለን? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥16ሞሮኒ 10፥3–5)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ጆሴፍ ስሚዝ እና ወላጆቹ በጭንቀት ተውጠው የሚያሳይ ምሥል

አስጨናቂው የ116 ገጾች ክብደት፣ በክዋኒ ፖቪ ዊንደር

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ