ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥር 20–26 (እ.አ.አ)፦ “የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2፦ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–65


“ጥር 20–26 (እ.አ.አ)፦‘የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2፤ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–65፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2፤ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–65፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ጆሴፍ ስሚዝ ከመልዓኩ ሞሮኒ ራዕይ እየተቀበለ

ዝርዝር ከHe Called Me by Name [በስሜ ጠራኝ]፣ በማይክል ማልም

ጥር 20–26 (እ.አ.አ)፦ “የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–65

እግዚአብሔር አብ እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በጥሻ ውስጥ ለጆሴፍ ስሚዝ ከተገለጡለት ሶስት አመት ሆኖት ነበር፤ እንዲሁም ጆሴፍ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምንም አይነት ተጨማሪ ራዕይን አልተቀበለም። ጌታ በእርሱ አዝኖ እንደሆነ ማሰብ ጀመረ። ልክ እንደሁላችንም ስህተትን ሰርቶ ነበር፣ እናም በእነርሱ ምክንያት ጥፋተኝነት ተሰምቶት ነበር። ቢሆንም እግዚአብሔር አሁንም እርሱ እንዲሰራው የሚሠጠው ስራ ነበረው። እንዲሁም ጆሴፍ እንዲሰራው የተጠራበት ስራ እግዚአብሔር እኛን ከሚጠይቀው ጋር የተገናኘ ነው። ጆሴፍ መፅሐፈ ሞርሞንን እውን ያደርጋል፤ እኛ ደግሞ የዚህን መልዕክት እንድናካፍል ተጋብዘናል። ጆሴፍ የልጆችን ልብ ወደ አባቶች ለመመለስ የሚያስችሉትን የክህነት ቁልፎች ይቀበላል፤ እኛ አሁን በቤተመቅደስ ለቅድመ ዓያቶቻችን ሥርዓቶችን መቀበል እንችላለን። ጆሴፍ በቅርቡ ስለሚፈጸሙ ትንቢቶች ተነግሮታል፤ እነዚህ ትንቢቶች ይፈፀሙ ዘንድ ለመርዳት ተጠርተናል። በእግዚአብሔር ስራ ላይ ስንሳተፍ፣ ልክ ነቢዩ እንዳጋጠመው፣ ነቀፋ እና ስደትም እንኳን ሊደርስብን እንደሚችል ልንጠብቅ እንችላለን። ሆኖም፣ ጌታ ልክ ጆሴፍን እንዳደረገው፣ በእርሱ እጅ መሳሪያ እንደሚያደርገን እምነት ሊኖረንም ይችላል።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣1፥20–48ን ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–33

የሴሚናሪ ምልክት
እግዚአብሔር እኔ እንድሰራው የሚፈልገው ስራ አለው።

እግዚአብሔር፣ ጆሴፍ ስሚዝ እንዲሠራው የሚፈልገው ሥራ እንደነበረው ማመን አንድ ነገር ነው—ህይወቱን ወደ ኋላ መለስ ብለን ማየት እና ምን እንዳከናወነ በግልጽ ማየት እንችላለን። ሆኖም፣ እናንተም እንድትሰሩት እግዚአብሔር የሚፈልገው ስራ እንዳለው አስባችሁ ታውቃላችሁን? የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–33ን ስታነቡ፣ ያ ስራ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቡ። ይህም ለአዳኙ ወንጌል ዳግም መመለስ አስተዋጽዖ የሚያደርገው እንዴት ነው?

ሽማግሌ ጋሪ ኢ. ስቲቨንሰን እንዳስተማሩት፦ “ወደ ክርስቶስ ስንመጣ እና ሌሎችንም እንደዚሁ እንዲያደርጉ ስንረዳቸው፣ በእግዚአብሔር የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግ ስራ ላይ ተሳተፍን ማለት ነው፣ ይህም በተመደበልን መለኮታዊ ሀላፊነቶች ላይ ትኩረት ያደርጋል። … እነዚህ ኃላፊነቶች ቀላል፣ የሚያነሳሱ፣ የሚያነቃቁ እና ሊተገበሩ የሚችሉ ናቸው። ቀጥሎም ቀርበዋል፦

  • በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር

  • እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መንከባከብ

  • ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ

  • ቤተሰቦችን ለዘለዓለም ማጣመር” (“Simply Beautiful—Beautifully Simple [በቀላሉ የሚያምር—በሚያምር ሁኔታ ቀላል]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 47)።

በእነዚህ በእያንዳንዱ በመለኮት በታዘዙ ኃላፊነቶች ውስጥ በመሳተፍ አግኝታችኋቸው ስለነበሩት ልምዶች አስቡ። አዳኙ ቀጥሎ እንድታደርጉ የሚፈልገው ምንድን ነው? ለእነዚህ ለእያንዳንዱ ኃላፊነቶች የርዕስ እና ጥያቄዎች ገፅ አለ (“በእግዚአብሔር የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ውስጥ ያለን ሚና” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ)። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንዲረዷችሁ እነዚህን ገፆች መፈተሽ ትችላላችሁ።

አንዳንድ ጊዜ፣ በሠራችኋቸው ሥህተቶች ምክንያት ጌታ እነንተን ለመጠቀም እንደማይችል ሊሰማችሁ ይችላል። በጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥28–29 ውስጥ ከጆሴፍ ስሚዝ ተሞክሮ ምን ትማራላችሁ? “[በእግዚአብሔር] ፊት ያላችሁን አቋም” እንዴት ልታውቁ ትችላላችሁ?

ትርጉም ያለው ውይይትን የሚያበረታቱ ጥያቄዎችን ጠይቁ። ከአንድ በላይ ትክክለኛ መልስ ያላቸው ጥያቄዎች፣ ተማሪዎች ከራሳቸው ሀሳቦች፣ ስሜቶች እና ተሞክሮዎች በመነሳት ምላሽ እንዲሰጡ ይጋብዛሉ። በዚህ መዘርዝር ውስጥ ያሉት ጥያቄዎች የዚህ ምሳሌዎች ናቸው።

በተጨማሪም “Youth Responsibility in the Work of Salvation [በደህንነት ስራ የወጣቶች ሀላፊነቶች]” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org፤ “የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግ ሥራ፣” አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ1.2 ተመልከቱ።

3:15

Youth Responsibility in the Work of Salvation

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥34–47

ወንጌሉን ዳግም በመመለስ አዳኙ የጥንት ትንቢቶች ፍፃሜያቸውን እንዲያገኙ አድርጓል።

ለጆሴፍ ስሚዝ በተገለጠ ጊዜ፣ እንደ ኢሳይያስ 11የሐዋርያት ሥራ 3፥22–23፤ እና ኢዮኤል 2፥28–32 ያሉ በርከት ያሉ ትንቢቶችን ሞሮኒ ከብሉይ ኪዳን እና ከአዲስ ኪዳን ላይ ጠቅሷል። የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥34–47ን ስታነቡ፣ ጆሴፍ እነዚህን ትንቢቶች ሊያውቃቸው ያስፈልግ የነበረው ለምን እንደሆነ አስቡ። እናንተስ እነዚህን ልታውቋቸው የሚያስፈልጋችሁ ለምንድን ነው?

እንዲሁም፣ ሽማግሌ ዴቪድ ኤ.ቤድናር ስለሞሮኒ የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ጉብኝት ያስተማሩትን በ“With the Power of God in Great Glory [የእግዚአብሔርን ኃይል በታላቅ ክብር]” (ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 28) ውስጥም ማንበብ ትችላላችሁ።

13:16

With the Power of God in Great Glory

በተጨማሪም “An Angel from on High [መልዓክ ከከፍተኛው ቦታ]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 13 ተመልከቱ።

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥48–60

እግዚአብሔር በመንግሥቱ ውስጥ እንድሠራ ያዘጋጀኛል።

ጆሴፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ ሰሌዳዎቹን በተመለከተ ጊዜ ገና 17 ዓመቱ ነበር። ይሁን እንጂ አራት ዓመታት እስኪያልፉ ድረስ፣ እርሱ እንዲንከባከባቸው አልተሰጡትም ነበር። በዚያን ወቅት በጆሴፍ ስሚዝ ህይወት ውስጥ ምን እንደተፈጠረ እየፈለጋችሁ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥48–60ን አንብቡ። እነዚህ ክስተቶች እግዚአብሔር እርሱ እንዲሰራው ለተጠራበት ስራ እንዴት ያዘጋጁት ይመስላችኋል? እግዚአብሔርን እና ሌሎችን እንድታገለግሉ ያዘጋጇችሁ ምን ተሞክሮዎች ነበሯችሁ? በአሁኑ ወቅት፣ ለወደፊት አገልግሎት እንድትዘጋጁ ሊረዷችሁ የሚችሉ ምን ተሞክሮዎችን እያገኛችሁ ናችሁ።

በኒው ዮርክ ማንችስተር አቅራቢያ የሚገኘው የኩሞራ ኮረብታ ሥዕል

የኩሞራ ኮረብታ፣ በኦል ራውንድስ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2

ኤሊያስ የእኔን ልብ ወደ አባቶቼ እንዲመልስ ጌታ ላከው።

በዚህ ክፍል ውስጥ የሚገኙት “ተክል”፣ “ልብ” እና “መመለስ” የሚሉት ቃላት ስለኤሊያስ ተልዕኮ እና በዳግም ስለመለሳቸው የክህነት ቁል በረከቶች ምን ያስተምሯችኋል? ልባችሁ ወደ ቅድመ ዓያቶቻችሁ ሲመለስ በምን አይነት መልኩ ተሰምቷችኋል? እንደዚህ አይነት ስሜቶች በተደጋጋሚ እንዲሰሟችሁ የሚያስችሏችሁን መንገዶች አስቡባቸው። ቅድመ ዓያቶቻችሁን መፈለግ እና ለእነርሱ በቤተመቅደስ ሥርዓቶችን መፈፀም አንዱ መንገድ ነው (FamilySearch.org ተመልከቱ)። ምን ሌሎች ነገሮችን ማሰብ ትችላላችሁ?

እንዲሁም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፡13–16፤ ጌሪት ደብሊው. ጎንግ፣ “Happy and Forever [ደስተኛ እና ለዘለአለም]፣” ሊያሆና ህዳር፣ 2022 (እ.አ.አ)፣ 83–86 ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥28–29።

ንስሐ መግባት እና ይቅርታን ማግኘት እችላለሁ።

  • አንዳንድ ጊዜ እኛም እንደ ጆሴፍ ስሚዝ “በድክመ[ታችን] እና ፍፁም ስላልሆንን እንደተኮነንን” ይሰማናል። እናንተ እና ልጆቻችሁ እንደዚያ በሚሰማችሁ ጊዜ ጆሴፍ ምን እንዳደረገ እየፈለጋችሁ ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥28–29ን በአንድነት ልታጠኑ ትችላላችሁ። ሥህተቶችን በምንሰራበት ጊዜ ሊረዳን ከሚችለው ከእርሱ ምሳሌ ምን እንማራለን? ጆሴፍ ፍፁም ባይሆንም እንኳን በእግዚአብሔር የተጠራ መሆኑን ማወቁ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–54

የሰማይ አባት ሥራውን እንዲሰራለት ጆሴፍ ስሚዝን ጠራው።

  • ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–54 ወይም በ“Chapter 3: The Angel Moroni and the Gold Plates [ምዕራፍ 3፦ መልዓኩ ሞሮኒ እና የወርቅ ሰሌዳዎች]፣” (Doctrine and Covenants Stories [በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]13–17፣ ወይም በዚህ ተዛማጅ ቪዲዮ በወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ ያለውን የሞሮኒ ጉብኝት ዘገባ ስትናገሩ ልጆቻችሁ እንደ ጆሴፍ ስሚዝ በመምሰል ሊደሰቱ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ፀሎት እንደሚያደርጉ ሁሉ እጆቻቸውን እንዲያገናኙ ወይንም የከሞራ ኮረብታን እንደሚወጡ ወይም የሚመሳሰሉትን እንደሚያደርጉ ሊያስመስሉ ይችላሉ። ከዚያም እግዚአብሔር፣ ጆሴፍ ስሚዝ ምን እንዲያደርግ እንደጠራው እና በውጤቱም እኛ እንዴት እንደተባረክን እንዲናገሩ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን በመተርጎሙ ምክንያት የተባረክነው እንዴት ነው? የእርሱ ሥራ ወደ ሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንቀርብ የረዳን እንዴት ነው።

    2:29

    The Angel Moroni Visits Joseph Smith: Learning about a sacred book

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2

የሰማይ አባት ቤተሰቦች በቤተመቅደስ እንዲታተሙ ይፈልጋል።

  • ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ አንዳንድ የቤተሰባችሁን ፎቶዎች፣ ከተቻለ በቤተመቅደስ የተነሳችሁትን ፎቶ (ወይም የወንጌል የአርት መፅሐፍቁ. 120) መመልከት ሊያስደስታችሁ ይችላል። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2ን ልታነቡና ቤተመቅደሶች ለምን እንደሚያስፈልጉን እንዲሁም የሰማይ አባት ቤተሰቦች ለዘለዓለም በአንድነት እንዲኖሩ የሚፈልገው ለምን እንደሆነ ያሏችሁን ሃሳቦች አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። “ቤተሰቦች ለዘለአለም አብረው ሊሆኑ ይችላሉ፣” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 188) ማንበብን አስቡ። ከቤተሰባችን ጋር ለዘለዓለም መሆን እንድንችል ይህ መዝሙር ምን ማድረግ እንዳለብን ይላል?

Young Couple Going to the Temple, English
የፓልማይራ ኒውዮርክ ቤተመቅደስ

የፓልማይራ ኒውዮርክ ቤተመቅደስ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2

ስለ ቅድመ ዓያቶቼ መማር ደስታ ሊያመጣልኝ ይችላል።

  • ልጆች በቤተሰብ ታሪክ ሊደሰቱና ከቤተሰብ ታሪክ የሚገኝ ደስታ ሊሰማቸው ይችላል። እነርሱን ለመርዳት የቅድመ ዓያቶቻችሁን ታሪኮች ወይም ፎቶዎች ልታካፍሏቸው ትችላላችሁ። ቅድመ ዓያቶቻችሁ ልጆች በነበሩበት ጊዜ ህይወት ምን ይመስል እንደነበረ ከልጆቻችሁ ጋር ተነጋገሩ። በተጨማሪም ልጆቻችሁ በFamilySearch.org/discovery ውስጥ በሚገኙት የተወሰኑ የቤተሰብ ታሪክ አክቲቪቲዎች ሊዝናኑም ይችላሉ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

መልዓኩ ሞሮኒ የወርቅ ሰሌዳዎቹ የት እንደተደበቁ ለጆሴፍ ስሚዝ እያሳየ

ጆሴፍ ሰሌዳዎችን ተቀበለ በጌሪ ኢ. ስሚዝ

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ