አጠቃላይ ጉባኤ
ደስተኛ እና ለዘላለም
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ፈደስተኛ እና ለዘላለም

እውነት፣ የሚፀና ደስታ እና ዘላለምነት ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር የእግዚአብሔር የደስታ ዕቅድ ትርጉም ነው።

ጓደኞች ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ በእስከመጨረሻ ድረስ ደስታ ማመን ወይም መፈለግ ታስታውሳላችሁን?

ከዛ ሕይወት ተከሰተ። እኛ “አደግን።” ግንኙነቶች ይወሳሰባሉ። ይህ ዓለም በጫጫታ፣ በመጨናነቅ፣ በግፊት፣ በማስመሰል እና በማጭበርበር የተሞላ ነው። ነገር ግን በእኛ “ጥልቅ ልብ” 1 ውስጥ የሆነ ቦታ፣ በሆነ አጋጣሚ ደስተኛ እና ለዘላለም እውን እና የሚቻል እንደሆነ እንናምናለን ወይም ለማመን እንፈልጋለን።

“ደስተኛ እና ለዘላለም” የተረቶች ምናባዊ ነገሮች አይደሉም። እውነት፣ የሚፀና ደስታ እና ዘላለምነት ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር የእግዚአብሔር የደስታ ዕቅድ ትርጉም ነው። የእርሱ በፍቅር የተዘጋጀው መንገድ የዘላለም ጉዞአችንን ደስተኛ እና ዘላለማዊ ያደርጋል።

የምናከብርበት እና የምናመሰግንበት ብዙ ነገሮች አሉን። ነገር ግን፣ ማናችንም ወይም ማንኛውም ቤተሰብ ፍፁም አይደለም። ግንኙነቶቻችን ፍቅርን፣ ማህበራዊነትን እና ግለሰባዊነትን ያካትታሉ፣ ነገር ግን ብዙ ጊዜም ግጭትን፣ ጉዳትን አንድ አንዴ ደግሞ ከፍተኛ ህመምን ያካትታሉ።

“ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።”2 በኢየሱስ ክርስቶስ መኖር አለመሞትን ማለትም እርሱ ለእኛ የሰጠውን የአካለዊ ትንሳኤ ስጦታን ያካትታል። በእምነት እና በመታዘዝ ስንኖር፣ በክርስቶስ መኖር ከእግዚአብሔር እና ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር የዘላለም ሕይወት ደስታን ሊያካትት ይችላል።

በሚገርም ሁኔታ፣ የጌታ ነብይ ወደ አዳኛችን እያስጠጋን ነው፣ በብዙ ቦታዎች እየቀረበን በመጣው የቅዱስ ቤተመቅደስ ስነስርዓቶች እና ቃልኪዳኖችን ጨምሮ። ለግዜ እና ለዘላለም እርስ በእርስ እና ከቤተሰባችን ጋር አዲስ መንፈሳዊ መረዳትን፣ ፍቅርን፣ ንስሃን እና ይቅርታን ለማግኘት ከፍተኛ እድል እና ስጦታ አለን።

በተሰጠኝ ፍቃድ በጓደኞች የተነገሩ ኢየሱስ ክርስቶስ ከትውልድ ወደ ትውልድ የቀጠለን ግጭት በመፈወስ እንዴት ቤተሰቦችን አንድ እንዳደረገ የሚገልጹ ሁለት የተቀደሱ ባልተለመደ ሁኔታ በመንፈሳዊ ቀጥተኛ የሆኑ ልምዶችን አካፍላለሁ።3 “ማለቂያ የሌለው እና ዘላለማዊ” የሆነው 4 “ከሞት ገመድ የጠነከረ[ው]” 5 የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ላለፈው ነገር ሰላምን እና ለወደፊታችን ደግሞ ተስፋን በመስጠት ሊረዳን ይችላል።

ጓደኛዬ እና ባለቤቷ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ሲቀላቀሉ፣ የቤተሰብ ግንኙነቶች “ሞት እስኪለየን” መሆን እንደሌለባቸው በደስታ ተማሩ። በጌታ ቤት ውስጥ ቤተሰቦች ለዘላለም አንድ ይሆናሉ (ይታተማሉ)።

ነገር ግን ጓደኛዬ ከአባቷ ጋር መታተም አልፈለገችም ነበር። “ለእናቴ መልካም ባል አልነበረም። ለልጆቹም መልካም አባት አልነበረም” ብላ አለች። “አባቴ መጠበቅ አለበት። የቤተመቅደስ ስራውን ለመስራት እና ለዘላለም ከእሱ ጋር አብሮ ለመታተም ምንም ፍላጎት የለኝም።

ለአንድ ዓመት ፆመች፣ ጸለየች፣ ስለ አባቷ ከጌታ ጋር ብዙ አወራች። በመጨረሻ፣ ዝግጁ ሆነች። የአባቷ የቤተመቅደስ ስራ ተጠናቀቀ። ከዛ በኋላ፣ እንዲህ አለች፣ “በእንቅልፌ አባቴ ነጭ ልብስ ለብሶ ለእኔ በህልሜ ተገለጠ። ተቀይሮ ነበር። እንዲህ አለ፣ ‘ተመልከቱኝ። ንፁ ነኝ። ስራውን በቤተመቅደስ ውስጥ ለእኔ ስለሰራሽልኝ አመሰግናለው።’” አባቷ እንደዚ በማለት ጨመረ፣ “ተነሺ እና ወደ ቤተመቅደስ ተመልሰሽ ሂጂ፣ ወንድምሽ ለመጠመቅ እየጠበቀ ነው።”

ጓደኛዬ እንደዚ አለች፣ “ቅደመ አያቶቼ እና ያለፉት ሰዎች ስራቸው እንዲሰራ በጉጉት እየጠበቁ ነው።”

“ለእኔ” አለች “ቤተመቅደስ የፈውስ፣ የመማሪያ እና የኢየሱስ ክርስቶስን የሃጢያት ክፍያ የምገነዘብበት ቦታ ነው።”

ሁለተኛው ልምድ። ሌላ ጓደኛ ስለ ቤተሰቡ ታሪክ በታታሪነት አጠና። የወንድ ቅድመ አያቱን ለማወቅ ፈለገ።

አንድ ጠዋት ጓደኛዬ የሰውዬውን የመንፈስ መገኘት በክፍል ውስጥ ተሰማኝ አለ። ሰውዬው በቤተሰብ ውስጥ ለመታወቅ እና ለመገኘት ፈለገ። ሰውዬው ላጠፋው ነገር አሁን ንስሃ ለገባው ሃዘን ተሰማው። ጓደኛዬ የቅድመ አያቴ ነው ብሎ ካሰበው ሰው ጋር ሰውዬው ምንም ዓይነት የዲኤንኤ ግንኙነት እንደሌለው ለጓደኛዬ እንዲገነዘብ አደረገ። “በሌላ አባባል፣” አለ ጓደኛዬ “የእኛ ቤተሰብ የቅድመ አያታችን ነው ብሎ የመዘገቡት ሰው የእኔ ቅድም አያት እንዳልሆነ አረጋገጥኩኝ።”

የእሱ የቤተሰብ ግንኙነት እንዲህ ገለፀ ብሎ አለ ጓደኛዬ፣ “ነፃነት፣ ሰላም ይሰማኛል። ቤተሰቤ እነማን እንደሆኑ ማወቁ ሁሉን ልዩነት ያመጣል።” ጓደኛዬ እንዲህ አለ፣ “የተጣመመ ቅርንጫፍ መጥፎ ዛፍ ነው ማለት አይደለም። ወደዚህ ምድር የምንመጣበት መንገድ ከዚህ ለቀን ስንሄድ ማንነታችን ጋር አይበልጥም።”

የግል ፈውስ እና ሰላም ቅዱስ መጽሐፎች እና ቅዱስ ልምዶች በመንፈስ ዓለም ያሉትን ጨምሮ አምስት የወንጌል መርሆዎችን ያሳያሉ።

አንደኛ፦ በእግዚአብሔር የቤዛነት እና የደስታ ዕቅድ ውስጥ ማዕከላዊ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሃጢያት ክፍያው አማካኝነት ነፍሳችንን እና አካላችንን ለማዋሃድ “በድጋሚ ላይለያዩ የደስታ ሙሉነትን እንቀበል ዘንድ” ቃል ገብቷል። 6

ሁለተኛ፦ የክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ—ቃል በቃል ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ መሆን ተብሎም ይገለጻል— እምነትን ስንለማመድ እና በንስሃ ፍሬን ስናፈራ ይመጣል።7 ልክ አንደ ሟችነት አለሟችነትም እንደዛው ነው። የቤተመቅደስ ስነ ስርዓቶች በራሳቸው እኛን ወይም በመንፈስ ዓለም ውስጥ ያሉትን አይቀይሩም። ነገር ግን እነዚህ መለኮታዊ ስነ ስርዓቶች የሚያነፁ ከእርሱ እና ከእርስ በእርስ ጋር ስምምነትን የሚያመጡ ቃልኪዳኖችን ከጌታ ጋር እንድንገባ ያስችላሉ።

የኢየሱስ ክርስቶስን ፀጋ እና ይቅርታ ሲሰማን ደስታችን ሙሉ ይሆናል። እናም የፀጋውን እና የይቅርባይነቱን ተአምር አንዳችን ላንዳችን ስንሰጥ፣ የምንቀበለው ምህረት እና የምንሰጠው ምህረት ሕይወት ኢፍትሃዊ የምታደርገውን ፍትሃዊ ማድረግ ይችላል።8

ሶስተኛ፦ እግዚአብሔር በደንብ ያውቀናል እንዲሁም ይወደናል። “እግዚአብሔር አይዘበትበትም” 9 አትሳቱ። በፍፁም ምህረት እና ፍትህ እርሱ በእጆቹ ያቅፈናል።

በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በራዕይ ወንድሙ አልቪንን በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ድኖ አየ። የማዳን የጥምቀት ስርዓት ከመቀበሉ በፊት አልቪን ሞቶ ስለነበረ ነብዩ ጆሴፍ ተደነቀ።10 በሚያፅናና መልኩ፦ “እንደ ስራችን እንደ የልባችን መሻት [የሚፈርድብን]” ለምን እንደሆነ ጌታ ገለፀ።11 ነፍሳችን የእኛን ስራዎች እና ፍላጎቶች መዝገብ ትይዛለች።

ደግነቱ በህይወት ያሉት እና “ንስሀ የገቡ ሙታንም የእግዚአብሔር ቤት ስርዓቶችን በማክበር” እና በክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ 12 አማካኝነት እንደሚድኑ እናውቃለን። በሃጢያት እና በመተላለፍ ውስጥ ያሉ ሰዎች በመንፈስ ዓለም ውስጥ ንስሃ ለመግባት እድል አላቸው።13

በተቃራኒው፣ ክፋትን የሚመርጡ፣ በማወቅ ንስሃን የሚያዘገዩ ወይም ሆነ ብለው ለቀላል ንስሃ ትዕዛዛትን የሚጥሱ ሰዎች በእግዚአብሔር እና “የጥፋተኝነት ስሜታቸው ትውስታ” ይፈረድባቸዋል።14 በማወቅ ቅዳሜ ሃጢያት ሰርተን ከዛ ደግሞ እሁድ ቅዱስ ቁርባንን በመውሰድ ይቅርታ ለማግኘት መጠበቅ አንችልም። መንፈስን መከተል ማለት የሚስዮን ህጎችን ወይም ትዕዛዛትን መታዘዝ አይደለም ለምትሉ ሚስዮኖች ወይም ሌሎች ሰዎች፣ እባካችሁን የሚስዮን ህጎችን ወይም ትዕዛዛትን መከተል መንፈስን እንደሚጋብዝ አስታውሱ። ማንኛችንም ንስሃ መግባትን ማቆየት የለብንም። የንስሃ መግባት በረከቶች ንስሃ መግባት ስንጀምር ይጀምራል።

አራተኛ፦ ሌሎች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ግን ማድረግ የማይችሉትን ለሌሎች መዳን የቤተመቅደስ ስነ ስርዓቶችን ስንሰጥ የበለጠ እንደ እርሱ እንድንሆን ጌታ መለኮታዊ እድልን ይሰጠናል። “በጽዮን ተራራ ላይ አዳኞች” ስንሆን የበለጠ ሙሉ እና ፍፁም እንሆናለን።15 16 ሌሎችን ስናገለግል፣ የቃልኪዳን መንፈስ ቅዱስ ስነ ስርዓቶችን ያጸድቃል እናም ሰጪውን እና ተቀባዩን ያንፃል። ሰጪ እና ተቀባይ ለአብርሃም፣ ይስሃቅ እና ያዕቆብ ቃል የተገቡትን በረከቶች በሂደት እንዲቀበሉ የሚለውጡ ቃልኪዳኖችን ማድረግ ይችላሉ።

በመጨረሻም አምስተኛ፦ ወርቃማው ህግ 17 እንደሚያስተምረው፣ በንስሃ እና በይቅርታ መቀደስ እራሳችን የምንፈልገውን እና የምንሻውን ለሌሎች እንድንሰጥ ይጋብዘናል።

አንድ አንድ ጊዜ ሌላ ሰውን ይቅር የማለት ፍቃደኝነታችን እነሱን እና እኛን ንስሃ መግባት እና ይቅር መባል እንደምንችል እንድናምን ያስችለናል። አንድ አንድ ጊዜ ንስሃ የመግባት ፍቃደኝነት እና ይቅርታ የማድረግ ችሎታ በተለያየ ጊዜ ይመጣሉ። አዳኛችን ከእግዚአብሔር ጋር አማላጃችን ነው፣ ነገር ግን ወደ እርሱ ስንመጣ ወደራሳችን እና ወደ እርስ በእርሳችን ሊያመጣን ይረዳል። በተለይ ጉዳት እና ህመም ጥልቅ ሲሆን፣ ግንኙነታችንን መጠገን እና ልባችንን መፈወስ ከባድ ይሆናል፣ ምናልባት ለእኛ ለብቻችን የማይቻል ይሆናል። ነገር ግን ሰማይ መቼ መያዝ እና መቼ መልቀቅ እንዳለብን እንድናውቅ እኛ ካለን በላይ ጥንካሬን እና ጥበብን ይሰጠናል።

ብቻችን እንዳልሆንን ስንገነዘብ ብዙም ብቻችን አንሆንም። አዳኛችን ሁሌም ይረዳል።18 በአዳኛችን እርዳታ፣ ኩራታችንን፣ ህመማችንን፣ ሃጢያታችንን ለእግዚአብሔር መስጠት እንችላለን። ይሁን እንጂ፣ እንደጀመርን ሊሰማን ይችል ይሆናል፣ ግንኙነቶቻችንን ሙሉ እንዲያደርግ ስናምነው የበለጠ ሙሉ እንሆናለን።

በፍፁም ሁኔታ ማየት እና መረዳት የሚችለው ጌታ የሚፈልገውን ሰው ይቅር ይላል፣ እኛ ፍፁም ያልሆነው ደግሞ ሁሉንም ይቅር ማለት አለብን። ወደ አዳኛችን ስንመጣ፣ እራሳችን ላይ ብዙም አናተኩርም። ትንሽ በመፍረድ ብዙ ይቅር እንላለን። የእርሱን ጥቅም፣ ምህረት እና ፀጋ ስናምን ከክርክር፣ ከንዴት፣ ከጥቃት፣ ከመተው፣ ከኢፍታዊነት እና በሟች ዓለም ውስጥ አንዳንዴም በስጋዊ አካል ላይ ከሚመጡ ከአካል እና ከአዕምሮ ችግሮች ነፃ ያወጣናል። ደስተኛ እና ዘላለማዊ ማለት እያንዳንዱ ግንኙነት ደስተኛ እና ዘላለማዊ ይሆናል ማለት አይደለም። ነገር ግን ሰይጣን የሚታሰርበት አንድ ሺህ ዓመት 20 አስፈላጊውን ጊዜ ሊሰጠን ይችላል እና ለዘላለም ስንዘጋጅ ለመውደድ፣ ለመረዳት እና መፍትሄ ለማግኘት አስገራሚ መንገዶችን እናገኛለን።

እርስ በእርስ ውስጥ የሰማይን ማህበራዊነት እናገኛለን።21 የእግዚአብሔር ስራ እና ክብር ደስታን እና ዘላለማዊነትን ማሳካትን ያካትታል።22 የዘላለም ሕይወት እና በዘላለም ሕይወት ከፍ መደረግ እግዚአብሔርን እና ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ነው እናም በአምላካዊ ኃይል አማካኝነት ያሉበት ቦታ እኛም እንገኛለን።23

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር እና ተወዳጁ ልጅ ህያው ናቸው። ሰላምን፣ ደስታን እና ፈውስን ለእያንዳንዱ ዘር እና ቋንቋ ይሰጣሉ። የጌታ ነብይ መንገዱን እየመሩ ናቸው። የኋለኛው ቀን ራዕይ ይቀጥላል። ልባችንን ክርስቶስ በሰጠው ርህራሄ፣ እውነት እና ምህረት ጋር በማዋሃድ በተቀደሰ ቤቱ ውስጥ ወደ አዳኛችን እንቅረብ እና ወደ እግዚአብሔር እና እርስ በእርስ ማለትም ለአጭር ጊዜ እና እስከመጨረሻ ያቅርበን፣ ደስተኛ እና ዘላለማዊ ያድርገን። በኢየሱስ ክርስቶስ ይቻላል፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እውነት ነው። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።

አትም