አጠቃላይ ጉባኤ
አንተን ያውቁ ዘንድ
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:49

አንተን ያውቁ ዘንድ

(ዮሐንስ 17፥3)

ልባዊ ምኞቴ ኢየሱስን በብዙ ስሞቹ እንድታውቁት እና እንደ እርሱ እንድትሆኑ ነው።

ከጥቂት አመታት በፊት፣ በአገራችን በአሪዞና በሚገኝ አጥቢያ ውስጥ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ወቅት ሕይወትን የሚቀይር ተሞክሮ አግኝቼ ነበር። የቅዱስ ቁርባን ጸሎት “[የኢየሱስ ክርስቶስን] ስም [በራሳችን ላይ] ለመውሰድ፣” ፍቃደኛ መሆናችንን እንደሚጠቁመው1 ኢየሱስ ብዙ ስሞች እንዳሉት መንፈስ ቅዱስ አስታወሰኝ። ከዚያም ይህ ጥያቄ ወደ ልቤ መጣ፦ “በዚህ ሳምንት ከኢየሱስ ስሞች የትኛውን በራሴ ላይ ልውሰድ?

ሦስት ስሞች ወደ አእምሮዬ መጡ፣ እኔም ጻፍኳቸው። እነዚያ ሦስቱ ስሞች እያንዳንዳቸው ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ ማዳበር የምፈልጋቸውን የክርስቶስን መሰል ባሕርያት ይዘዋል። በቀጠለው ሳምንት፣ በእነዚያ ሶስት ስሞች ላይ አተኩሬ ተዛማጅ ባህሪያቸውን ለመቀበል ሞከርኩ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ “በዚህ ሳምንት ከኢየሱስ ስሞች መካከል የትኛውን በላዬ ላይ ልወስድ?” የሚለውን ጥያቄ እንደ የግል አምልኮዬ ክፍል መጠየቁን ቀጠልኩ። ያንን ጥያቄ መመለሴ እና ተዛማጅ የሆኑትን የክርስቶስ ባህሪያት ለማዳበር መጣሬ ሕይወቴን ባርኮታል።

በታላቁ የምልጃ ጸሎቱ፣ ኢየሱስ ይህን አስፈላጊ እውነት፣ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላከኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ህይወት ናት ሲል ገልጿል።2 ዛሬ ኢየሱስ ክርስቶስን በብዙ ስሞቹ በማወቅ የሚገኙትን በረከቶች እና ሃይል ላካፍላችሁ እወዳለሁ።

አንድን ሰው ለመተዋወቅ የምንችልበት አንዱ ቀላል መንገድ ስሙን በማወቅ ነው። “በማንኛውም ቋንቋ የአንድ ሰው ስም ለዚያ ሰው በጣም ጣፋጭ እና በጣም አስፈላጊ ድምጽ ነው” ይባላል።3 አንድን ሰው በተሳሳተ ስም ጠርታችሁ ወይም ስሙን ረስታችሁ ታውቃላችሁ? እኔና ባለቤቴ አሌክሲስ አንዳንድ ጊዜ ከልጆቻችን አንዷን “ሎላ” ብለን ጠርተን እናውቃለን። እንደ አለመታደል ሆኖ እንደገመታችሁት ሎላ የእኛ ውሻ ነው! ለበጎም ይሁን ለመጥፎ፣ የአንድን ሰው ስም መርሳት ምናልባት ያንን ሰው በደንብ የማታውቁት መሆኑን ለዚያ ሰው ያስተላልፍለታል።

ኢየሱስ ሰዎችን በስማቸው ያውቃቸውና ይጠራቸው ነበር። ጌታ ለጥንቷ እስራኤል፣ “አትፍራ፤ ተቤዥቼሃለሁና፣ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ” ብሏል።4 በፋሲካ ጠዋት፣ ኢየሱስ በስሟ ሲጠራት ማርያም ከሞት ስለተነሳው ክርስቶስ የሰጠችው ምስክርነት ጠንክሮ ነበር።5 እንደዚሁም፣ ላቀረበው የእምነት ጸሎት ምላሽ ሲሰጠው እግዚአብሔር ጆሴፍ ስሚዝን በስም ጠርቶታል።.6

በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ኢየሱስ ተፈጥሮአቸውን፣ ብቃታቸውን እና አቅማቸውን የሚያመለክቱ አዳዲስ ስሞችን ለደቀ መዛሙርቱ ሰጥቷቸዋል። ይሖዋ ለያዕቆብ እስራኤል የሚል አዲስ ስም ሰጠው፤ ትርጉሙም “በእግዚአብሔር ፊት ድል የሚነሣ” ወይም “እግዚአብሄር ያሸንፍ” ማለት ነው።”7 ኢየሱስ ለያዕቆብና ለዮሐንስ ቦአኔርጌስ የሚል ስም ሰጣቸው፤ ትርጉሙም “የነጎድጓድ ልጆች.” ማለት ነው።8 ኢየሱስ የወደፊት መሪነቱን በመመልከት ለስምዖን ኬፋ ወይም ጴጥሮስ የሚለውን ስም ሰጠው ይህም ማለት ዓለት ማለት ነው።.9

ኢየሱስ እያንዳንዳችንን በስም እንደሚያውቀን፣ እኛም ኢየሱስን በደንብ የምናውቅበት አንዱ መንገድ ብዙ ስሞቹን በማወቅ ነው። እስራኤል እና ጴጥሮስ እንደሚሉት ስሞች፣ ብዙዎቹ የኢየሱስ ስሞች የእሱን ተልዕኮ፣ ዓላማ እና ባህሪ እንድንረዳ የሚረዱን የማዕረግ ስሞች ናቸው። የኢየሱስን ብዙ ስሞች ስናውቅ፣ መለኮታዊ ተልእኮውን እና ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ባህሪውን የበለጠ እንረዳለን። ብዙ ስሞቹን ማወቃችን ይበልጥ እርሱን እንድንመስልም ያነሳሳናል—ለሕይወታችን ደስታ እና ዓላማ የሚያመጡ የክርስቶስን መሰል ባህሪያት እንድናዳብር ያነሳሳናል።

ከጥቂት አመታት በፊት፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም.ኔልሰን በወንጌል አርዕስቶች መመሪያ ውስጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገሩትን ሁሉንም ቅዱሳት መጻሕፍት አጠኑ።10 ከዚያም ወጣት ጎልማሶች እነዚህን ተመሳሳይ ጥቅሶች እንዲያጠኑ ጋበዙ። 11የኢየሱስን ብዙ ስሞች በተመለከተ፣ ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፣ “እያንዳንዳቸው የተለያዩ ማዕረጎች እና ስሞች ለእናንተ ለግላችሁ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት በጸሎት እና በብርቱ በመሻት ኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን ሁሉንም ነገር አጥኑ።”

የፕሬዘዳንት ኔልሰንን ግብዣ ተከትሎ፣ የራሴን የኢየሱስን ብዙ ስሞች ዝርዝር ማዘጋጀት ጀመርኩ። የእኔ የግል ዝርዝር አሁን ከ300 በላይ ስሞች አሉት፣ እና እርግጠኛ ነኝ ገና ያላገኘኋቸው ብዙ ተጨማሪ ስሞች አሉ።

ለእርሱ ብቻ የተቀመጡ አንዳንድ የኢየሱስ ስሞች ሲኖሩ12 እያንዳንዳችንን የሚመለከቱ አምስት ስሞችን እና ማዕረጎችን ማካፈል እፈልጋለሁ። ኢየሱስን በብዙ ስሞቹ እያወቃችሁት ስትሄዱ የራሳችሁን ዝርዝር እንድታዘጋጁ እጋብዛችኋለሁ። ይህን ስታደርጉ እንደኢየሱስ የቃል ኪዳን ደቀ መዝሙርትነታችሁ በራሳችሁ ላይ ለመውሰድ የምትፈልጓቸው ሌሎች ስሞች ከተዛማጅ የክርስቶስ መሰል ባሕርያትጋር ታገኛላችሁ። 13

በመጀመሪያ፣ ኢየሱስ መልካም እረኛ ነው።.14 ስለዚህም ኢየሱስ በጎቹን ያውቃል።15 “የራሱን በጎች በስም ይጠራል፣”16 እንደ እግዚአብሔር በግ ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ሰጠ.17 በተመሳሳይም፣ ኢየሱስ ጥሩ እረኞች እንድንሆን ይፈልጋል፣ በተለይም በቤተሰባችን ውስጥ እና እንደ አገልጋይ ወንድሞች እና እህቶች። ለኢየሱስ ያለንን ፍቅር የምናሳይበት አንዱ መንገድ በጎቹን በመመገብ ነው።18 በመቅበዝበዝ ላይ ያሉትን፣ የጠፉትን በጎች ለማግኘት መልካም እረኞች ወደ ምድረ በዳ ይሄዳሉ ከዚያም ጥበቃ ወደሚያገኙበት ቦታ እስኪመለሱ ድረስ ከእነርሱ ጋር ይቆያሉ።.19 እንደ መልካም እረኞች እንዲሁም የአከባቢ ሁኔታዎች በሚፈቅዱት መጠን ሰዎችን ብዙውን ጊዜ በቤታቸው በማገልገል ለማሳለፍ መሻት አለብን። በአገልግሎታችን ውስጥ የጽሑፍ መልእክት እና ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸው የግል ግንኙነትን ለማሻሻል እንጂ ለመተካት መሆን የለበትም።20

ሁለተኛ፣ ኢየሱስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ነው።.21 ለመሰቀል ጥቂት ሰዓታት እንደቀረው በማወቁ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፣ “በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፥ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ አለምን አሸንፌዋለሁ።”22 ዛሬ፣ ዓለማችን በተደጋጋሚ ዋልታረገጥ እየሆነች እና እየተከፋፈለች በመሆኗ፣ መስበክ እንዲሁም አዎንታዊ አመለካከትን፣ ብሩህ ተስፋን እና ተስፋ ማድረግን እንድንለማመድ በጣም ያስፈልገናል። በቀደሙት ዘመናት ምንም አይነት ፈተናዎች የነበሩብን ቢሆንም፣ አይዟችሁ ሲል ኢየሱስ ያቀረበልንን ግብዣ እንድንፈጽም በማስቻል እምነት ሁልጊዜ በተስፋ ወደተሞላው ወደ መጪው ጊዜ ይጠቁማል።23 .24 ወንጌልን በደስታ መኖር ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ደቀ መዛሙርት እንድንሆን ይረዳናል።.

ከኢየሱስ የማዕረግ ስሞች ሌላው እሱ ትናንትና፣ ዛሬ እስከዘላለምም ያው ነው የሚለው ነው25 ወጥነት የክርስቶስ ዓይነት ባሕርይ ነው። ኢየሱስ ሁልጊዜ የአባቱን ፈቃድ ያደርግ ነበር,፣26 እንዲሁም እጁ እኛን ለማዳን፣ ለመርዳት እና ለመፈወስ ያለማቋረጥ የተዘረጋ ነው።.27 ወንጌልን በመኖር የበለጠ ወጥ ስንሆን፣ የበለጠ እንደኢየሱስ እንሆናለን።.28 ምንም እንኳን ሰዎች በእያንዳንዱ የትምህርት ነፋስ ወደ ፊት እና ወደ ኋላ እየተወረወሩ ሲሄዱ ዓለም በታዋቂነት ፔንዱለም ውስጥ ትልቅ ዥዋዥዌ ቢያጋጥማትም፣29 ወጥ የሆነ የወንጌል ኑሮ በሕይወት ማዕበል ውስጥ ጽኑ እና የማንንቀሳቀስ እንድንሆን ይረዳናል።30 እንዲሁም “ለጌታ ጊዜ ስጡ” የሚለውን የፕሬዚዳንት ኔልሰንን ግብዣ በመቀበል ወጥነትን ማሳየት እንችላለን 31 ታላቅ መንፈሳዊ ጥንካሬ32 “ቅዱስ ባህርያትን እና የጽድቅ ልምዶችን” እንደ ማዳበር33 የዕለት ተዕለት ጸሎት፣ ንስሐ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንደማድረግ እና ለሌሎች አገልግሎት እንደመስጠት ባሉ ትናንሽ እና ቀላል ነገሮች ይመጣል።

አራተኛ፣ ኢየሱስ የእስራኤል ቅዱስ.ነው34 የኢየሱስ ሕይወት የቅድስና ምሳሌ ነበር። ኢየሱስን ስንከተል እስራኤል ቅዱስ መሆን እንችላለን።35 በእያንዳንዱ መግቢያ አናትላይ “ቅድስና ለጌታ” የሚል ጽሁፍ የተቀረጸበትን ቤተመቅደስ አዘውትረን ስንጎበኝ በቅድስና እናድጋለን። በቤተመቅደስ ውስጥ በምናመልክበት ጊዜ ሁሉ ቤታችንን የቅድስና ቦታ ለማድረግ የበለጠ ኃይል ተሰጥቶን እንሄዳለን።36 በአሁኑ ጊዜ ወደ ቅዱስ ቤተመቅደስ የመግባት ፈቃድ የሌላችሁ፣ ከኤጲስ ቆጶሳችሁ ጋር እንድትገናኙ እና ወደዚያ ቅዱስ ቦታ ለመግባት ወይም ለመመለስ እራሳችሁን እንድታዘጋጁ እጋብዛችኋለሁ። በቤተመቅደስ ውስጥ የምናሳልፈው ጊዜ በህይወታችን ውስጥ ቅድስናን ይጨምራል

አንዱ የመጨረሻ የኢየሱስ ስም እርሱ ታማኝ እና እውነተኛ ነው የሚለው ነው።37 ኢየሱስ ታማኝ እና ሁል ጊዜም እውነተኛ እንደነበረ ሁሉ፣ ልባዊ ፍላጎቱ እነዚህን ባህሪያት በህይወታችን ውስጥ እንድናሳይ ነው። እምነታችን ሲዳከም፣ ጴጥሮስ በገሊላ ማዕበል ውስጥ መስጠም በጀመረ ጊዜ እንዳለው፣ “ጌታ ሆይ፣ አድነኝ” ብለን ወደ ኢየሱስ መጮህ እንችላለን።38 በዚያ ቀን፣ ኢየሱስ እየሰመጠ የነበረውን ደቀ መዝሙር ለማዳን ወረደ። ለኔም እንዲሁ አድርጓልና፣ ለአንተም እንዲሁ ያደርጋል። በኢየሱስ ተስፋ አትቁረጡ—እሱ በእናንተ ተስፋ አይቆርጥም!

ታማኝ እና እውነተኛ ስንሆን፣ “በእኔ ኑሩ” የሚለውን የኢየሱስን ጥሪ እንከተላለን፤ ይኸውም “ከእኔ ጋር ቆዩ” ማለትም ሊሆን ይችላል።”39 ጥያቄዎች ሲያጋጥሙን፣ በእምነታችን ምክንያት መሳለቂያ ስንሆን፣ በአለም ታላላቅ እና ሰፋፊ ህንፃዎች ውስጥ ባሉ ሰዎች የንቀት ጣቶች ሲቀሰሩብን፣ በታማኝነታችን እንጸናለን እንዲሁም እውነተኞች እንሆናለን። በእነዚህ ጊዜያት፣ የኢየሱስን ልመና እናስታውሳለን፣ “ባሰባችሁት ነገር ሁሉ ወደ እኔ ተመልከቱ፤ አትጠራጠሩ፤ አትፍሩ።“40 ይህን ስናደርግ፣ ለዘላለም ከእርሱ ጋር ለመቆየት የሚያስፈልገንን እምነት፣ ተስፋ እና ጥንካሬ ይሰጠናል። 41

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ ኢየሱስ እንድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች ያለው ብቸኛው ስም ስለሆነ እንድናውቀው ይፈልጋል። ኢየሱስ መንገድ፣ እውነት እና ሕይወት ነው —በእርሱ ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ ሊመለስ አይችልም።43 ኢየሱስ ብቸኛው መንገድ ነው! በዚህ ምክንያት፣ ኢየሱስም “ወደ እኔ ኑ፣”44 “ተከተሉኝ፣”45 “ከእኔ ጋር ተራመዱ፣”46 እንዲሁም “ከእኔ ተማሩ” በማለት የሚጠይቀው።47

በሙሉ ልቤ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለ፣ እንደሚወዳችሁ እና በስም እንደሚያውቃችሁ እመሰክራለሁ። የእግዚአብሔር ልጅ ነው።48 የአብ አንድያ ልጅ።49 እርሱ ዓለታችን፣ መሸሸጊያችን፣ መጠጊያችን እና አዳኛችን ነው።50 እርሱ በጨለማ የሚያበራ ብርሃን ነው።51 እርሱ አዳኛችን 52 እና ቤዛችን53ነው። እርሱ ትንሣኤና ሕይወት ነው።.54 ልባዊ ምኞቴ ኢየሱስን በብዙ ስሞቹ እንድታውቁት እና መለኮታዊ ባህርያቱን በሕይወታችሁ በማሳየት እርሱን እንድትመስሉ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77

  2. ዮሃንስ 17:3; አጽንዖት ተጨምሯል. ይህን ጸሎት በተመለከተ፣ ፕሬዘደንት ዴቪድ ኦ. ማኬይ እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፦ “ይህ ጽሑፍ የተወሰደው ከጌታ ጸሎት በስተቀር በዚህ አለም ውስጥ ከተደረጉት እጅግ በጣም ጥሩ ጸሎቶች አንዱ ይመስለኛል። ይህ ክርስቶስ በተከዳበት ምሽት ወደ ጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ከመግባቱ በፊት ያቀረበው ጸሎት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም ጠቃሚ ያልሆነ ምዕራፍ እንደሌለ አውቃለሁ” (በኮንፈረንስ ሪፖርት፣ ጥቅምት 1967(እ.አ.አ)፣ 5)።

  3. ዴል ካርኒጌ, How to Win Friends and Influence People፣በድጋሚ የታተመ (1981)(እ.አ.አ)፣83

  4. ኢሳይያስ 43፡1፣ አጽንዖት ታክሏል.

  5. ዮሀንስ 20፥16ይመልከቱ።

  6. የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥17.ይመልከቱ

  7. የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት “እስራኤል።”

  8. ማርቆስ 3:17

  9. ሉቃስ 6:14; ሃንስ 1:42.ይመልከቱ

  10. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “I Studied More Than 2,200 Scriptures about the Savior in Six Weeks: Here Is a Little of What I Learned፣” Inspiration (blog)፣ የካ. 28, 2017(እ.አ.አ)፣ ChurchofJesusChrist.org. ይህንን ልምድ ተከትሎ፣ ፕሬዚዳንት ኔልሰን “እኔ ሌላ ሰው ነኝ!” አሉ። (“የኢየሱስ ክርስቶስን ሀይል ወደ ህይወታችን መሳብ፣” ሊያሆና፣፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 39)።

  11. ራሰል ኤም. ኔልሰንን “Prophets, Leadership, and Divine Law” (worldwide devotional for young adults, ጥር 8፣ 2017(እ.አ.አ))፣ broadcasts.ChurchofJesusChrist.org.

  12. ለምሳሌ፣ ኢየሱስ መሲሕ፣ ክርስቶስ፣ ታላቁ ይሖዋ፣ የሙታን በኩር እና የአምላክ አንድያ ልጅ ነው።

  13. ፕሬዚዳንት ኔልሰን ኢየሱስን የሚመለከቱ ጥቅሶችን ከአርዕስት ማውጫው እንድታጠኑ ካደረጉት ግብዣ በተጨማሪ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “የክርስቶስ ስሞች፣” በሚለው ስር ያለውን በማየት ስለኢየሱስ ብዙ ስሞች ማጥናትም ትችላላችሁ። እንዲሁም የሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድን Witness for His Names (2019) (እ.አ.አ) የሚለውን መጽሐፍ እና “ከስሞች ሁሉ በላይ ስም” (ብሪገም ያንግ ዩኒቨርሲቲ–ሃዋይ ፣ ኦክቶበር 20፣ 2020(እ.አ.አ) በሚል ርዕስ በሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራስባንድ ያደረጉትን የአምልኮ ንግግር speeches.byuh.edu.ማጥናት ልትፈልጉም ትችላላችሁ።

  14. ዮሐንስ 10:11.ተመልከት።

  15. ዮሀንስ 10፥14ይመልከቱ።

  16. ዮሀንስ 10፥3

  17. ዮሐንስ 10:11–15; 1 ኔፊ 11:31–33.ተመልከት።

  18. ዮሀንስ21:15–17.ተመልከት።

  19. በተለይ የጆሴፍ ስሚዝን የ ሉቃስ 15:4ትርጉም ወድጄዋለሁ፣ እንዲህ ይነበባል፣ “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን ትቶ እስኪያገኘው ድረስ የጠፋውን ተከትሎ ወደ ምድረ በዳ የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው? , ?” (በ ሉቃስ 15:4፣ የግርጌ ማስታወሻ ፣ ትኩረት ተጨምሮበታል).

  20. ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዳስተዋሉት፡ “ሁሉም ሰው ጽሑፍ [ለማገልገል] በቂ እንደሆነ ያስባል። እቤት ውስጥ መሆን እና ሰዎችን በአይን ማየት የሚያስፈልጋችሁ አጋጣሚዎች አሉ፤ ምክንያቱም በሌላ በምንም መንገድ የማታገኟቸውን ግንዛቤዎች እና መነሳሻዎችን በቤት ውስጥ ትቀበላላችሁ። (“An Evening with Elder David A. Bednar” [broadcast for religious educators]፣ የካቲት 7፣ 2020 (እ.አ.አ)]፣ broadcasts.ChurchofJesusChrist.org).

  21. ዕብራውያን 9:11.ተመልከት።

  22. ዮሀንስ 16፥33

  23. ጄፍሪ አር ሆላንድን፣ “‘Remember Lot’s Wife’: Faith Is for the Future” (ብሪገም ያንግ ዩኒቨርሲቲ ፣ ጥር 13፣ 2009 (እ.አ.አ), speeches.byu.edu. ይመልከቱ። እምነት ሁል ጊዜ የሚያመለክተው ወደፊት ነው። እምነት ሁል ጊዜ ከበረከቶች እና እውነት እና ከሚሆኑ ክስተቶች ጋር የተያያዘ ነው። ገና በሕይወታችን ውስጥ ውጤታማ ይሁኑ ።

  24. ማቴዎስ 9:2; ማርቆስ 6:50; ዮሀንስ 16:33; 3 ኔፊ1:13; ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 61:36.ተመልከቱ።

  25. Hebrews 13:8; የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትንም ተመልከት, “የክርስቶስ, ስሞች.”ተመልከቱ።

  26. ዮሀንስ 8፥29ይመልከቱ።

  27. አልማ5:33አልማ 19:363 ኔፊ 9:14.ይመልከቱ።

  28. ለምሳሌ፣ ዴቪድ ኤ. ቤድናር, “More Diligent and Concerned at Home፣” ሊያሆና፣ ሕዳር 2009(እ.አ.አ)፣ 20፦ “በግል ህይወታችን ውስጥ ለታላቅ ስራ መሰረት ስንጥል ወጥነት ቁልፍ መርህ ነው … መሆን እና የበለጠ ወጥ መሆን አለብን።

  29. ኤፌሶን 4፥14ይመልከቱ።

  30. ሞዛያ 5፥15ይመልከቱ።

  31. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለጌታ ጊዜ ስጥ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 120።

  32. አልማ 37፥6ይመልከቱ።

  33. ይህ ፕሬዘደንት ዳሊን ኤች ኦክስ በአገልግሎቱ ውስጥ ብዙ ጊዜ የደገሙት ሀረግ ነው። ለምሳሌ “YSA Face to Face with Elder Oaks and Elder Ballard” (ዓለም አቀፍ ያላገቡ ወጣት አዋቂዎች ስርጭት፣ ህዳር 19፣ 2017(እ.አ.አ), ChurchofJesusChrist.org.

  34. 2 ኔፊ 9:18–19, 41.ይመልከቱ።

  35. እህት ዌንዲ ኔልሰን በቅርቡ ለወጣቶች ባደረገው ዓለም አቀፍ የአምልኮ ሥርዓት ሕይወትን ሊለውጥ፣ በራስ መተማመንን ይጨምራል እና ጭንቀትን ይቀንሳል፣ ያነሳሳል፣ ምስጋናን ይጨምራል እና ጭንቀትን ይቀንሳል፣ ፈተናን ለመቋቋም ይረዳል፣ እና ደስታን፣ መፅናኛን፣ ፍቅርን እና ሰላምን ያመጣል ያለችውን ጥያቄ አቀረበች። ይህ ጥያቄ “አንድ ቅዱስ ወጣት ምን ያደርጋል?” የሚል ነበር። ከዚያም ይህንን ጥያቄ በየቀኑ በአንድ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብቻ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ተግባራዊ ማድረግን አበረታታች። “One Question That Can Change Your Life” (worldwide devotional for young adults, ግንቦት 15, 2022(እ.አ.አ))፣ broadcasts.ChurchofJesusChrist.org.ይመልከቱ።

  36. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109:12–13, 22.ይመልከቱ።

  37. ራእይ 19:11.ይመልከቱ።

  38. ማቴዎስ 14:30

  39. ዮሀንስ 15፥4። የግሪክ ቃል ለ ይኖራል ማለት μείνατε (ሚነት ወይም ማኖት), መቆየት ወይም መቅረት ማለት ነው።

  40. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 6፥36

  41. ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ በአንድ ወቅት በስፓኒሽ “በእኔ ኑሩ” የሚለው የእንግሊዝኛ ሐረግ “permaneced en mi” ተብሎ ተተርጉሟል። ቀጠለ፡ “የዚህ ስሜት እንግዲህ ‘ቆይ—ነገር ግን ቆይ ለዘላለም።’ … ለእናንተና አናንተን መከተል ስላለባቸው ትውልዶች ሁሉ ስትሉ በቋሚነት ኑ፥ እኛም እርስ በርሳችን እንረዳዳለን እስከ መጨረሻም እንበርታ” Abide in Me፣” (“ሊያሆና፣ ግንቦት 2004(እ.አ.አ)፣ 32)።

  42. 2 ኔፊ 31:21.ይመልከቱ።

  43. ዮሃንስ 14:6.ይመልከቱ።

  44. ማቲዮስ 11:28; 3 ኔፊ 9:14, 22.

  45. ማቲዮስ 16:24; ሉቃስ 18:22; ዮሃንስ 21:19; በተጨማሪም 2 ኔፊ 31:10ይመልከቱ።

  46. ራዕይ 3፥4ሙሰ 6:34

  47. ማቲዮስ11:29; ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19:23.

  48. 3 ኔፊ 9፥15፣ ይመልከቱ።

  49. ዮሃንስ1:14; አልማ 5:48.ይመልከቱ።

  50. 2 ሳሙኤል 22:2–3.ይመልከቱ።

  51. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች6:21.ይመልከቱ።

  52. ሉቃስ 2፥11ይመልከቱ።

  53. ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 18:11–13.ይመልከቱ።

  54. ዮሀንስ 11፥25ይመልከቱ።