አጠቃላይ ጉባኤ
በቤተመቅደስ ላይ ማተኮር
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


7:19

በቤተመቅደስ ላይ ማተኮር

በቤተመቅደስ ውስጥ የበለጠ ጊዜ ስታሳልፉ ሌላ ነገር በማይችልበት መልኩ ሕይወታችሁን እንደሚባርክ ቃል ገባለው።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ በእነዚህ አምስት ታላቅ የአጠቃላይ ጉባኤ ስብሰባዎች ወቅት፣ የሰማያትን መከፈት በድጋሜ ተለማምደናል! ስሜታችሁን እንደመዘገባችሁ እና እንድትከተሉት እጸልያለው። እግዚአብሔር አብ እና የተወደደው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊረዱዋችሁ ዝግጁ ናቸው። የእነርሱን እርዳታ የመሻት ጥረታችሁን እንድትጨምሩ አበረታታችኋለው።

በቅርቡ እህት ኔልሰን እና እኔ አዲሱን የ መጽሐፈ ሞርሞን ቪድዮዎች ክፍል 4ን ለማየት እድሉ አግኝተን ነበር።1 በእነሱ መነሳሳትን አገኘን! አዳኙ ወደ ኔፋውያን ሲገለፅ የሚያሳየውን ትዕይንት አጭር ቅንጭብ ላሳያችሁ።

አዳኙ ለሰዎቹ በቤተመቅደስ ለመገለፅ መምረጡ አስፈላጊ ነው። የእርሱ ቤት ነው። በእርሱ ኃይል የተሞላ ነው። ጌታ አሁን ለእኛ እያደረገ ያለውን ነገር እይታ በፍፁም አንሳት። ቤተመቅደሶቹን የበለጠ እያቀረባቸው ነው ያለው። ቤተመቅደሶችን የምንገነባበትን ሂደት እያፈጠነ ነው። እስራኤልን የመሰብሰብ እርዳታ ችሎታችንን እየጨመረ ነው። እንዲሁም እያንዳንዳችን በመንፈስ የጠራን እንድንሆን እያቀለለ ነው። በቤተመቅደስ ውስጥ የበለጠ ጊዜ ስታሳልፉ ሌላ ነገር በማይችልበት መልኩ ሕይወታችሁን እንደሚባርክ ቃል ገባለው።

በአሁኑ ወቅት 168 በስራ ላይ ያሉ ቤተመቅደሶች፣ 53 በግንባታ ላይ ያሉ እንዲሁም 54 በቅድመ ግንባታ ደረጃ ላይ ያሉ ቤተመቅደሶች አሉን።2 በሚከተሉት ቦታዎች አዲስ ቤተመቅደስን ለመገንባት ያለንን ዕቅድ ለማስተዋወቅ ደስተኛ ነኝ፦ ቡሳና ኮሪያ፤ ናጋ ፊሊፒንስ፤ ሳንቲያጎ ፊሊፒንስ፤ ኤኬት ናይጄሪያ፤ ቺክላዮ ፔሩ፤ ቦኖስ አይረስ የከተማ ማዕከል አርጀንቲና፤ ሎንድሪና ብራዚል፤ ሪበርራው ፕሬቶ ብራዚል፤ ወወትኔንጎ ጉአቲማላ፤ ጃክሰንቪል ፍሎሪዳ፤ ግራንድ ራፒድስ ሚሽገን፤ ፕሮስፐር ቴክሳስ፤ ሎን ማውንቴን ነቫዳ እና ተኮማ ዋሺንግተን።

ወደሚገኝ ቤተመቅደስ የጉዞ ሰዓትን በጣም ከባድ የሚያደርጉ በተመረጡ ትልቅ የሜትሮፖሊታን አካባቢዎች ቡዙ ቤተመቅደሶችን ለመገንባት እንዲሁም ዕያቀድን ነው። ስለሆነም፣ በሜክሲኮ ሲቲ አካባቢ በኮርናቫካ፣ ፐቹካ፣ ቶሉካ፣ እና ቱላ ውስጥ አዲስ ቤተመቅደሶች የሚገነቡበት አራት ተጨማሪ ቦታዎችን ሳስተዋውቅ ደስታ ይሰማኛል።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ ከዚህ ቀደም ባላደረጋችሁት መንገዶች ቤተመቅደስ ላይ አተኩሩ። ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በየቀኑ እንድትቀርቡ እባርካችኋለው። እወዳችኋለሁ። እንደገና እስክንገናኝ ድረስ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆን ዘንድ የምጸልየው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. እነዚህ አዲስ ቪድዮዎች በብዙ ቋንቋዎች በወንጌል ቤተመጻህፍት እና ቻናሎች ላይ ይገኛሉ። ከዛሬ ጀምሮ ከጉባኤው በኋላ በየሳምንቱ ምዕራፎች ይለቀቃሉ።

  2. እንደ ጥቅምት1፣ 2022 (እ.አ.አ) ሰራት ቤተመቅደሶች እታደሱ ነው (ሴንት ጆርጅ ዩታ፣ ማንታይ ዩታ፣ ሴልት ሌክ እና ኮለምበስ ኦሃዮ) እና ሶስት ደግሞ ቡራኬን እየጠበቁ ነው (ሃሚልተን ኒው ዚላንድ፣ ኪቶ ኢኳዶር እና ቤለም ብራዚል)።