አጠቃላይ ጉባኤ
ዘላቂ ደቀ መዛሙርትነት
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:23

ዘላቂ ደቀ መዛሙርትነት

የእምነታችንን እሳት የሚደግፉ እና የሚያቀጣጥሉ ቅዱሳን ልማዶችን እና የጽድቅ ስራዎችን ስናዳብር፣ መንፈሳዊ መተማመን እና ሰላም ማግኘት እንደምንችል አውቃለሁ።

በዚህ ባለፈው የበጋ ወቅት፣ በመላው አለም የሚገኙ ከ200 ሺህ በላይ ወጣቶቻችን በመቶዎች በሚቆጠሩ አንድ ሳምንት በሚፈጁ የለወጣቶች ጥንካሬ ወይም የFSY ጉባኤዎች በአንድ ላይ በመሳተፍ በእምነት አድገው ነበር። በወረርሽኙ ምክንያት ከነበረው መገለል በመውጣት፣ በዚያ መሳተፍም እንኳ ለብዙዎች በጌታ የማመን ድርጊት ነበር። ብዙዎቹ ወጣት ተሳታፊዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ጥልቅ መለወጥ ማደግን የተከተሉ ይመስላሉ። በሳምንቱ መጨረሻ፣ “እንዴት ነበር?” ብዬ ለመጠየቅ ወደድኩ።

አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ይላሉ፡- “ደህና፣ ሰኞ ላይ እናቴ እንድመጣ ይህን እንዳደርግ ስላደረገችኝ በጣም ተናድጄ ነበር። እና ማንንም አላውቅም ነበር። እንዲሁም ለእኔ ነው ብዬ አላሰብኩም ነበር። እናም ምንም ጓደኞች አይኖሩኝም። … ግን አሁን አርብ ነው፣ እና እዚህ መቆየት እፈልጋለሁ። በህይወቴ ውስጥ መንፈስ እንዲሰማኝ እፈልጋለሁ። እንደዚህ መኖር እፈልጋለሁ።”

እያንዳንዳቸው ስለተሰማቸው እና በእድገት ወደ ላይ ስለሚወስዳቸው የግልጽነት እና የመንፈሳዊ ስጦታዎች ጊዜያት የሚናገሩት የራሳቸው ታሪክ አላቸው። እኔም በዚህ የበጋ ወቅት የለወጣቶች ጥንካሬ ፕሮግራም (ኤፍ.ኤስ.ዋይ) የእግዚአብሔር መንፈስ በእሱ ጥበቃ ስር በነበሩበት የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በእርሱ ለመተማመን ድፍረት ለነበራቸው ለእነዚህ ለብዙ ወጣቶች የግል ልብ የፅድቅ ፍላጎት ምላሽ ሲሰጥ በማየቴ ተለውጫለሁ።

በባህር ላይ በደማቅ ሁኔታ እንደተቀዘፉ የብረት መርከቦች፣ እኛም የምንኖረው አስደናቂ እምነቶቻችንን በጥሞና መጠበቅ ባለብን፣ አለበለዚያም ሊፋቁ፣ ከዚያም ሊበላሹ እና ሊወድቁ በሚችሉበት መንፈሳዊ ጎጂ በሆነ አካባቢ ነው።

የእምነቶቻችንን እሳት ለመጠበቅ ምን አይነት ነገሮችን ማድረግ እንችላለን?

እንደ የለወጣቶች ጥካሬ ጉባኤ፣ ካምፖች፣ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች እና የሚስዮን አገልግሎቶች አይነት ልምዶች በእድገት እና በመንፈሳዊ ግኝቶች ወደ አንጻራዊ ሰላም ቦታዎች በመውሰድ ምስክርነቶቻችንን ለማጠናከር ይረዳሉ። ነገር ግን ወደ ኋላ ከመንሸራተት ይልቅ እዚያ በመቆየት “በክርስቶስ [ባለን] ፅኑነት ለመቀጠል” (2 ኔፊ 31፥20) ምን ማድረግ አለብን? ደጋግመን እንደመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን በየእለቱ እንደማጥናት እና በቅንነት እንደማገልገል ያሉ በመጀመሪያ ደረጃ ወደዚያ ያደረሱንን ነገሮች ማድረግን መቀጠል አለብን።

ለአንዳንዶቻችን፣ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ለመገኘት እንኳን በጌታ የመታመን ልምምድን ሊጠይቅ ይችላል። ነገር ግን እዚያ ከደረስን፣ የጌታ ቅዱስ ቁርባን የፈውስ ተፅዕኖ፣ የወንጌል መርሆች መሰጠት እና የቤተክርስቲያን ማህበረሰብ እንክብካቤ ከፍተኛ ቦታ ላይ ወዳለው ቤታችን ሊልከን ይችላል።

በአካል የመሰብሰብ ሃይል ከየት ይመጣል?

በለወጣቶች ጥንካሬ ጉባኤ ላይ፣ ወደ 200 ሺህ እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ ወጣቶቻችን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሆነው በስሙ የመሰብሰብን ቀመር በመጠቀም ( ማቴዎስ 18፥20ተመልከት) በወንጌል እና በቅዱሳት መጻህፍት በመሳተፍ፣ በጋራ በመዘመር፣ በጋራ በመጸለይ፣ እና በአዳኝ ሰላምን በማግኘት አዳኝን የበለጠ ወደማወቅ መጥተዋል። ይህ መንፈሳዊ መነቃቃትን ለመቀበል ኃይለኛ ማዘዣ ነው።

ይህ ብዙ ቦታዎችን የሚሸፍን የወንድሞችና የእህቶች ቡድን፣ በተደበላለቀው አለም ጩኸት መካከል፣ አሁንም “በጌታ መታመን” (ምሳሌ 3፥5፤ የ2022 (እ.አ.አ.) የወጣቶች ጭብጥ) ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ወደ ቤታቸው ሄደዋል። ቅዱሳት መጻህፍት በሰፊው በተገለጡበት ጸጥ ባለ የማሰላሰያ ቦታ ውስጥ “እርሱን መስማት” (ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥17) አንድ ነገር ነው። ነገር ግን እርሱን ለመስማት” መጣር በሚያስፈልግበት፣ እንዲሁም በራስ የመጨነቅ እና የመተማመን መንፈስ ደብዝዞ ባለበት፣ በዚህ ትኩረትን በሚከፋፍል ሟች በሆነው ቦታ ደቀ መዝሙርትነታችንን መሸከም ሌላ ነገር ነው። ወጣቶቻችን ልባቸውን እና አዕምሯቸውን ቀና አድርገው በዘመናችን ካለው ተለዋዋጭ የምግባር አስተያየት በተጻራሪ ጎራ ሲቆሙ ያሳዩት የጀግኖችን ነገር መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።

በቤተክርስቲያን ተግባራት ላይ የተፈጠረውን መነሳሳት ለማስቀጠል ቤተሰቦች በቤት ውስጥ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?

በአንድ ወቅት ለካስማ ወጣት ሴቶች ፕሬዘደንት እንደባል ሆኜ አገልግያለሁ። አንድ ምሽት ባለቤቴ በፀሎት ቤቱ ውስጥ በሚቀጥለው ሳምንት በወጣት ሴቶች ካምፕ ላይ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ላሉት ወላጆች እና ሴቶች ልጆቻቸው መንፈሳዊ ስብሰባ ስታካሂድ፣ በቤተክርስቲያኑ መግቢያ አካባቢ ውስጥ ብስኩቶችን የማዘጋጀት ኃላፊነት ተሰጥቶኝ ነበር። የት መሆን እንዳለባቸውና ምን ማምጣት እንዳለባቸው ከገለጸች በኋላ፣ “እንግዲህ ማክሰኞ ጠዋት ውድ ሴት ልጆቻችሁን አውቶብሱ ጋር ስታወርዷቸው አጥብቃችሁ እቅፏቸው። እናም ተመልሰው ስለማይመመጡ፣ ደህና ሁኑ ብላችሁ ሳሟቸው።”

አንድ ሰው በድንጋጤ ሲተነፍስ ሰማሁ፣ ያም እኔ መሆኔን ተረዳሁ። “አይመለሱም?”

ነገር ግን እንዲህ ስትል ቀጠለች፣ “እነዚያን የማክሰኞ-ማለዳ ሴት ልጆች ትታችሁ ትስሄዱ፣ ትናንሽ የሚከፋፍሉ ነገሮችን ይተዋሉ እናም ለአንድ ሳምንት አብረው በመማርና በማደግ እንዲሁም በጌታ ላይ በመተማመን ያሳልፋሉ። ሳምንቱን ሙሉ፣ እስከ አጥንታችን እስኪገባ ድረስ፣ አብረን እንጸልያለን እና እንዘምራለን እና አብረን ምግብ አብስለን እናቀርባለን እናም ምስክርነቶቻችን እናካፍላለን እንዲሁም የሰማይ አባት መንፈስ እንዲሰማን የሚፈቅዱልንን ነገሮች እናደርጋለን። ቅዳሜም፣ ከዚያ አውቶብስ ሲወርዱ የምታዩአቸው እነዚያ ልጃገረዶች ማክሰኞ ትታችኋቸው የሄዳችኋቸው አይነት አይሆኑም። አዳዲስ ፍጥረታት ይሆናሉ። እና ከዚያ ከፍ ካለ ቦታ እንዲቀጥሉ ከረዳችኋቸው፣ እነርሱም ያስደንቋችኋል። እነርሱም መለወጣቸውን ይቀጥላሉ። ቤተሰቦቻችሁም እንዲሁ ይሆናሉ።”

በዚያ ቅዳሜ የሆነውም፣ ልክ እንደተነበየችው ነበር። ድንኳንን እየጫንኩ እያለሁ፣ ወደ ቤት ከመሄድ በፊት ልጃገረዶቹ በተሰበሰቡበት ትንሽ ጫካ ባለው መሰብሰቢያ ቦታ ውስጥ የሚስቴን ድምፅ ሰማሁ። እንዲህ ስትል ሰማኋት፣ “ኦህ፣ መጣችሁ። ሳምንቱን ሙሉ ስንጠብቃችሁ ነበር። የእኛ የቅዳሜ ልጃገረዶች።”

ፅኑ የፅዮን ወጣቶች በአስደናቂ ጊዜ ውስጥ እየተጓዙ ናቸው። የዚያ ዓለም ክፍል ሳይሆኑ፣ በቅድስናው ላይ ዕውር በሆነው በዚህ በትንቢት በተነገረለት ረብሻ ዓለም ውስጥ ደስታን ማግኘት ልዩ ኃላፊነታቸው ነው። ከአንድ መቶ አመት በፊት፣ ጂ. ኬ. ቸስተርተን እንዲህ ሲል፣ ይህን ፍለጋ በቤት ውስጥ የተመሰረተ እና በቤተክርስቲያን የሚደገፍ አድርጎ ያየው ይመስል ነበር፣ “አጽናፈ ዓለሙን ልክ መጠቃት እንዳለበት እንደ ጭራቅ ቤተ መንግስት፣ ሆኖም በምሽት ላይ መመለስ እንደሚገባን የራሳችን ጎጆ እንደሆነ አይነት አድርገን የመመልከት ስሜት ሊኖረን ይገባል” (Orthodoxy [1909], 130)።

ደግነቱ፣ ብቻቸውን አይወጡም። እርስ በርሳቸው ይደጋገፋሉ። እናንተም ለእነርሱ አላችሁላቸው። እናም እስራኤልን የመሰብሰብ የእነዚህን ጊዜያት ታላቅ ጥረት—ትልቅ እና ግርማ ሞገስ ያለው እንደሚሆን በማወጅ ብሩህ ተስፋ የሚመሩትን ባለ ራእዩን በህይወት ያሉ ነቢይ ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰንን ይከተላሉ (“የእስራኤል ተስፋ” [ዓለም አቀፍ የወጣቶች እምነት፣ ሰኔ 3፣ 2018 (እ.አ.አ)]፣ HopeofIsrael.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ)።

በዚህ በጋ፣ እኔና ባለቤቴ ኬሊን ከብዙ ዓመታት በፊት፣ አዲስ ሚስዮናዊ በነበርኩበት በአምስተርዳም አውሮፕላን እየቀየርን ነበር። ደች ለመማር ለወራት ከታገልኩኝ በኋላ፣ የKLM በረራችን እያረፈ ነበር፣ እናም ካፒቴኑ በማስታወቂያ መሳሪያው ግልጽ ያልሆነ ማስታወቂያ ተናገረ። ከትንሽ ዝምታ በኋላ፣ የሚስዮን ጓደኛዬ፣ “ይህ ደች ይመስለኛል” አለ። አንዳችን የሌላውን ሀሳብ እያነበብን ተያየን፦ ሁሉም ጠፋ።

ነገር ግን ሁሉም አልጠፋም። እንደ ሚስዮናውያን በላያችን ላይ ወደሚያዘንቡት ተአምራት በምንሄድበት በዚህ አየር ማረፊያ ውስጥ ስንጓዝ የወሰድናቸውን ትልቅ የእምነት እርምጃዎች ሳደንቅ፣ ወደ አገር ቤት ለመሄድ በአውሮፕላኑ ላይ በመሳፈር ላይ የነበረን ህያው እና እስትንፋስ ያለውን ሚስዮናዊ በማየት በድንገት ወደ አሁኑ ጊዜ አመጣኝ። ራሱን አስተዋወቀና እንዲህ ጠየቀ፣ “ፕሬዘደንት ለንድ፣ አሁን ምን ላድርግ? ጠንካራ በመሆን ለመቀጠል ምን ላድርግ?

እንግዲህ፣ ይህም ከለወጣቶች ጥንካሬ ጉባኤዎች፣ ከወጣቶች ካምፖች፣ ከቤተመቅደስ ጉዞዎች ሲወጡ እና የመንግሥተ ሰማያት ኃይላት በተሰማቸው በማንኛውም ጊዜ፣ በወጣቶቻችን አእምሮ ውስጥ የሚኖር ተመሳሳይ ጥያቄ ነው፦ “እግዚአብሔርን መውደድ ወደ ዘላቂ ደቀመዝሙርነት እንዴት ይቀየራል?።

የሚስዮኑን የመጨረሻ ሰአታት ለሚያገለግል ለዚህ የዋህ ሚስዮናዊ የፍቅር መነቃቃት ተሰማኝ፣ እና በዚያ የመንፈስ ጸጥታ፣ ድምፄ ሲሰነጠቅ እየተሰማኝ እንዲህ አልኩት፣ “ስሙን ለመሸከም አርማውን መልበስ አያስፈልግህም።”

እጆቼን በትከሻው ላይ በማድረግ እንዲህ ልለው ፈለግሁ፣ “እንዲህ ነው የምታደርገው። ወደ ቤት ሂድ እና ይሄ ብቻ ሁን። በጣም ጥሩ ነህ በጨለማ ውስጥ ታበራለህ። የአንተ የሚስዮን ስነ ምግባር እና መስዋዕትነቶች ድንቅ የእግዚአብሔር ልጅ አድርገውሀል። እዚህ በጠንካራ ሁኔታ ለአንተ የሰራውን በቤትህ ማድረግህን ቀጥል። መጸለይን እና ለማን እንደምትጸልይ እና የጸሎት ቋንቋን ተምረሃል። ቃሉን አጥንተሃል እናም እርሱን ለመምሰል በመሞከር አዳኝን ለማፍቀር ችለሀል። አባቱን እርሱ እንደሚወደው አንተም የሰማይ አባትን ወደሀል፣ ሌሎችን እንደሚያገለግል አንተም አገልግለሀል፣ እናም እርሱ እንደኖራቸው አንተም ትእዛዛትን ኖረሀል—እናም ባፈረስክ ጊዜም፣ ንስሃ ገብተሀል። ደቀመዝሙርነትህ በቲሸርት ላይ ያለ መፈክር ብቻ አይደለም—ህይወትህ ሆን ተብሎ ለሌሎች የሚኖር የህይወትህ ክፍል ሆኗል። ስለዚህ፣ ወደ ቤት ሂድ እና ያንን አድርግ። እንደዛ ሁን። በቀሪው የህይወትህ ጊዜ ውስጥ ይህን መንፈሳዊ ግስጋሴ ውሰድ።

በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በቃል ኪዳኑ መንገድ በመታመን፣ የእምነታችንን እሳት የሚደግፉ እና የሚያቀጣጥሉ ቅዱሳን ልማዶችን እና የጽድቅ ስራዎችን ስናዳብር፣ መንፈሳዊ መተማመን እና ሰላም ማግኘት እንደምንችል አውቃለሁ። እያንዳንዳችን ወደ ሞቃት እሳቶች እንቅረብ እና ምንም ይሁን ምን በዚያ እንቆይ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።