አለምን ማሸነፍ እና እረፍትን ማግኘት
አለምን ከእግዚአብሔር ጋር በገባችሁት ቃል ኪዳኖች በኩል በማሸነፍ ከዚህ አለም ጥንካሬ፣ ጥርጣሬ እና ጭንቀት እረፍት አግኙ።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በዚህ በሰንበት ጠዋት ሰላምታ ስሠጣችሁ እደሰታለሁ። ሁልጊዜም በአዕምሮዬ ውስጥ ናችሁ። ሌሎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ስታዩ እንዴት ወዲያው ለመስራት በመነሳታችሁ እደነቃለሁ። በደጋጋሚ በምታሳዩት እምነት እና ምስክርነትም እደነቃለሁ። በከባድ ሀዘናችሁ፣ በተስፋ መቁረጣችሁ፣ እና በጭንቀታችሁ ምክንያት አለቅሳለሁ። እወዳችኋለሁ። የሰማይ አባታችሁና የእርሱ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚወዳቹም አረጋግጥላችኋለሁ። ስለጉዳዮቻችሁ፣ ስለመልካምነታችሁ፣ ስለፍላጎቶቻችሁ፣ እና ለእርዳታ ስለምታደርጉት ጸሎታችሁ እነርሱ ያውቃሉ። በተደጋጋሚም፣ የእነርሱ ፍቅር እንዲሰማችሁ እጸልያለሁ።
የእነርሱን ፍቅር መቅመስ ዋና ነው፣ በሚያሳዝን ዜናዎች ሁልጊዜም ስለምንጠቃ። በአንዳንድ ቀናት የመኝታ ልብሳችሁን ለብሳችሁ፣ ተጠቅልላችሁ፣ እና ብጥብጥ ሲጠፋ ከእንቅልፍ እንዲያስነሷችሁ ለመጠየቅ የምትፈልጉበት ጊዜ ይኖራል።
ነገር ግን፣ ውድ ወንድሞቼ እን እህቶቼ፣ ብዙ አስደናቂ ነገሮች ወደፊት አሉ። በሚመጡት ቀናት፣ አለም በምንም አይቶት ከማያውቀው በላይ የሆኑ የአዳኝ ታላቅ መግለጫዎችን እናያለን። በአሁን እና እርሱ “በሀይል እና በብዙ ክብር”1 በሚመለስበት ጊዜ፣ መቆጠር የማይችሉ መብቶች፣ በረከቶች፣ እና ተዓምራቶች በሚያምኑት ላይ ይፈሳሉ።
ይህም ቢሆን፣ በአለም ታሪክ ውስጥ ከሁሉም በላይ በተወሳሰብ ጊዜ ውስጥ ነው የምንኖረው። ውስብስቦቹ እና ተግዳሮቶቹ ብዙ ሰዎችን የመጨናነቅ እና የድካም ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋሉ። ሆኖም፣ እናንተ እና እኔ እንዴት እረፍትን ለማግኘት እንድምንችል ግልጽ የሚያደርጉልንን በቅርብ የከሰቱትን ነገሮች አስቡባቸው።
በዋሽንግተን ዲሲ ቤተመቅደስ ከመቀደሱ በፊት በነበረው ጉብኝት፣ ከጉብኝቱ ኮሚቴ አባል አንዱ ብዙ ታዋቂ ጋዜጠኞችን በቤተ መቅደሱ ሲያጅብ አስተዋይ የሆነ ንግግሮችን ተመልክቷል። እንደምንም አንድ ወጣት ቤተሰብ ከዚህ የሚዲያ ጉብኝት ጋር ተጣበቀ። አንድ ዘጋቢ የቤተመቅደስ ተሳታፊ በቤተመቅደስ ውስጥ ሲዘዋወር ስለሚኖራቸው “ጉዞ” ደጋግሞ ይጠይቅ ነበር። የቤተ መቅደሱ ጉዞ በአንድ ሰው የህይወት ጉዞ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶች ምሳሌ መሆኑን ማወቅ ፈልጎ ነበር።
አንድ ትንሽ ልጅ ንግግሩን ያዳምጥ ነበር። የጉብኝት ቡድኑ ወደ መንፈሳዊ ስጦታ ክፍል በገቡበት ጊዜ፣ ይህ ልጅ ሰዎች ተንበርክከው ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ወደሚገቡበት መሰዊያው አመለከተና እንዲህ አለ፣ “ያም ደስ ይላል። ሰዎች በቤተመቅደስ ጉዞአቸው የሚያርፉበት ቦያ ይሀው ነው።”
ያል ልጅ እህ አስተያየቱ እንዴት ትአላቅ ትርጉም እንዳለም እንደገባው አልገምትም። እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር በቤተመቅደስ ውስጥ ቃል ኪዳን በመግባት እና ከአዳኝ አስደናቂ የተስፋ ጋር ያለውን ግንኙነት ላይ ምንም አያውቅም ይሆናል፦
“እናንተ ደካሞች ሸከማችሁ የከበደ ሁሉ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
ቀንበሬንም በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
“ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።”2
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ አባልነታቸው ብዙ እንደሚጠይቅባቸው በማሰብ ከቤተክርስቲያኗ ለሚወጡት በጣም አዝናለሁ። ቃል ኪዳኖችን መግባት እና ማክበር ህይወትን ቀለን እንደሚያደርገው ገና አላወቁም። በጥምቀት ገንዳ እና በቤተመቅደስ ውስጥ ቃል ኪዳን የሚገባ—እና የሚያከብር—እያንዳንዱ ሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ሀይልን ለማግኘት ተጨማሪ ችሎታ አለው። ያን አስደናቂ እውነት እባካችሁ አሰላስሉ።
ቃል ኪዳኖችን የመጠበቅ ሽልማት የሰማይ ሀይል ነው—ያም ሀይል መከራዎቻችንን፣ ፈተናዎቻችንን፣ እና ከባድ ሀዘኖቻችንን በተሻለ ሁኖእታ እንድንቋቋም ያጠናክረናል። ይህም ሀይል በመገዳችንን ያቀልላል። የኢየሱስ ክርስቶስን ከፍተኛ ህግጋት የሚኖሩትም የእርሱን ከፍተኛ ሀይል ያገኛሉ። ስለዚህ፣ ቃል ኪዳን ጠባቂዎች ከእግዚአብሔር ጋር በሚገኝ የቃል ኪዳን ግንኙነት በኩል የሚመጣ ልዩ የሆነ እረፍት ለማግኘት መብት ይኖራቸዋል።
አዳኝ በጌቴሴማኒ እና በቀራንዮም ላይ ለስቃይ ራሱን አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት ለሐዋሪያቱ እንዲህ አውጇል፣ “በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዧችሁ፤ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ።”3 ቀጥሎም፣ እያንዳንዳችን እንዲሁም እንድናደርግ ነበር ኢየሱስ እንዲህ በማለት የለመነን፣ “አለምን እንድታሸንፉ እፈልጋለሁ።”4
ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ በዛሬ የማቀርብላችሁ መልዕክት ቢኖር ኢየሱስ ክርስቶስ ይህችን የወደቀች አለም እንዳሸነፈ እና እርሱ ለእያንዳንዳችን የኃጥያት ክፍያ ስለከፈለ፣ እናንተም ይህችን በኃጢያት የተሞላች፣ ራስ ወዳጅ፣ እና በአብዛኛው አድካሚ የሆነችን አለም ለማሸነፍ እንደምትችሉ ነው።
አዳኝ፣ መጨረሻ በሌለው የኃጥያት ክፍያ በኩል፣ እያንዳንዳችንን ከደካማነት፣ ከስህተቶች፣ እና ከኃጥያት ስላዳነንና ይኖራችሁ የነበሩትን ህመሞች፣ ሀሳቦች፣ እና ሽክሞች ስለነበረው፣5 እናንተ በእውነት ንስሀ ስትገቡና እርዳታውን ስትሹ፣ ከዚህች አስጨናቂ አለም ከፍ ለማለት ትችላላችሁ።
አለምን በወርሸኝ የሚሸፍኑትን መንፈሳዊ እና ስሜታዊ ድክማትን፣ እንዲሁም ትዕቢት፣ ኩራት፣ ቁጣ፣ ብልግና፣ ጥላቻ፣ ስግብግብነት፣ ቅናት እና ፍርሃት ለማሸነፍ ትችላላችሁ። በዙሪያችን የሚሽከረከሩ ነገሮች እና የተዛቡ ነገሮች ቢኖሩም፣ በጣም በሚያስጨንቁ ችግሮቻችሁ ውስጥ እንኳን እውነተኛ እረፍት ማለትም እፎይታ እና ሰላም ማግኘት ትችላላችሁ።
ይህ አስፈላጊ እውነት ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን ያነሳሳል፦
መጀመሪያ፣ አለምን ማሸነፍ ማለት ምንድን ነው?
ሁለተኛ፣ ያንን እንዴት ማድረግ እንችላለን?
እና ሶስተኛም፣ አለምን ማሸነፍ እንዴት ህይወታችንን ለመባረክ ያስችላል?
አለምን ማሸነፍ ማለት ምንድን ነው? ይህም በዚህች አለም ነገሮችን ከእግዚአብሔር ነገሮች በላአይ ለማሰብ ያሉን ፈተናዎችን ማሸነፍ ማለት ነው። ይህም የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ከሰዎች ፍልስፍና በላይ ማመን ማለት ነው። ይህም በእውነት መደሰት፣ ማታለልን ማውገዝ፣ እና “ትሁት የክርስቶስ ተከታዮች”5 መሆን ማለት ነው። ይህም መንፈስ እንዲሸሽ ከሚያደርገው ለመቆጠብ መምረጥ ማለት ነው። ይህም የምንወዳቸው ኃጥያቶቻችንን “ለመተው” ፈቃደኛ መሆን ማለት ነው።7
አሁን፣ አለምን ማሸነፍ ማለት በዚህ ህይወት ፍጹም መሆን ማለት አይደለም፣ ወይም ችግሮቻችሁ በአስማት ሁኔታ ይወገዳሉ ማለት አይደለም—ምክንያቱም እንደዚህ አይጠፉምና። ይህም ስህተት አትሰሩም ማለት አይደለም። ነገር ግን አለምን ማሸነፍ ማለት ኃጢያትን ለመቋቋም ያላችሁ ሀይል ይጨምራል ማለት ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ያለችሁ እምነት ሲያድግ ልባችሁም ይለሰልሳል።8 አለምን ማሸነፍ ማለት እግዚአብሒእርን እና ውድ ልጁን ከማንም ሰው ወይም ነገር በላይ ማፍቀር ማለት ነው።
ስለዚህ፣ ዓለምን እንዴት እናሸንፋለን? ንጉስ ቢንያም እንዴት እንደምናደርገው አስተምሮናል። እንዲህም አለ፣ “ተፈጥሮአዊው ሰው ለእግዚአብሔር ጠላት [ነው]፣ እናም እርሱም ቅዱስ የሆነውን መንፈስ ወደራሱ ካልጋበዘ፣ እናም ስጋዊ ሰውነቱን ካልቀየረ እናም በጌታ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ቅዱስ አማካኝነት ቅዱስ ካልሆነ”9 በስተቀር እንደዚህም ለዘለአለም ይቀራል። የመንፈስን ማነሳሻ በምንፈልግበት እና በምትከተሉበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣ “ተፈጥሮአዊ ሰም የማያደርገውን ማንኛውንም በምታደርጉበት ጊዜ፣ አለምን አሸንፋችኋል።
አለምን ማሸነፍ ማለት በአንድ ወይም ሁለት ቀን የሚከሰት አይደለም። የሚከሰተው የክርስቶስ ትምህርትን በተደጋጋሚ በምንቀበልበት በህይወት ሙሉ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ያለን እምነት የምናሳድገው በየእለቱ ንስሀ በመግባት እና በመንፈስ በረከት በኩል ሀይል የሚሰጡንን ቃል ኪዳኖች በማክበር ነው። በቃል ኪዳን መንገድ ላይ እንቆያለን እና በመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ በግል ራዕይ፣ በተጨማሪ እምነት፣ እና በሚያገለግሉ መላዕክት እንባረካለን። በክርስቶስ ትምህርት መኖር በህይወታችን ውስጥ መንፈሳዊ መነቃቃትን በመፍጠር እጅግ በጣም ኃይለኛ፣ በጎ አዙሪትን ይፈጥራል።10
በኢየሱስ ክርስቶስን ከፍተኛ ህግጋት ለመኖር ስንጥር፣ ልባችን እና ተፈጥሮአችን መቀየር ይጀምራሉ። አዳኝም እኛን በከፍተኛ ልግስና፣ ትህትና፣ ደግነት፣ ራስን መግዛት፣ ሰላም፣ እና እረፍት፣ ከወዳቂ አለም ጉተታ በላይ ከፍ ያደርገናል።
አሁን፣ ይህ ከባድ መንፈሳዊ ስራ እንጂ እረፍት እንዳልሆን ይሰማችሁ ይሆናል። ሆኖም ታላቁ እውነት እዚህ አለ፦ ዓለም ኃይል፣ ሀብት፣ ተወዳጅነትና የሥጋ ደስታ ደስታን እንደሚያመጡ አጥብቆ ቢናገርም፣ አያደርጉትም! ለማድረግ አይችሉም! የሚያፈሩት ነገር “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለሚጠብቁ” “የተባረከና ደስተኛ ሁኔታ” ምትክ ሊሆን ከማይችል በስተቀር ሌላ አይደለም።11
እውነትም ቢኖር ለመገኘት በማይቻልበት ላይ ደስታን መፈለግ በጣም አድካሚ ነው። ነገር ግን፣ ራሳችሁን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስታቀናብሩ እና አለምን ለማሸነፍ የሚያስፈልገውን መንፈሳዊ ስራ ስትሰሩ፣ እርሱ ብቻ ነው እናንተን ከአለም ጉተታ ከፍ ለማድረግ ሀይል ያለው።
አሁን፣ አለምን ማሸነፍ እንዴት ህይወታችንን ለመባረክ ያስችላል? መልሱ ግልፅ ነው፦ ከእግዚአብሔር ጋር የቃል ኪዳን ግንኙነት ውስጥ መግባታችን ስለ ሕይወት ሁሉንም ነገር በሚያቀልል መንገድ ከእርሱ ጋር ያገናኘናል። እባካችሁ ባልኩት አለመግባባት አይኑራችሁ፦ ቃል ኪዳን መግባት ህይወትን ቀላል ያደርገዋል አላልኩም። እንዲያውም ተቃውሞን ጠብቁ፣ ምክንያቱም ተቃዋሚው የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይል እንድታውቁ አይፈልግም። ነገር ግን ራስችሁን ከአዳኝ ጋር ማጣመር ማለት የእሱን ጥንካሬ እና የመቤዠት ሃይል ማግኘት ትችላላችሁ ማለት ነው።
የፕሬዘዳንት ኤዝራ ታፍት ቤንሰንን ጥልቅ ትምህርት በድጋሚ አረጋግጣለሁ፦ “ህይወታቸውን ለእግዚአብሔር አሳልፈው የሰጡ ወንዶች እና ሴቶች፣ እርሱ በህወታቸው ለማድረግ ከሚችሉት በላይ ሊያደርግበት እንደሚችል ይገነዘባሉ። ደስታቸውን ያጎላል፣ ራዕያቸውን ያሰፋል፣ አእምሮአቸውን ያነቃቃል፣ … መንፈሳቸውን ያነሳል፣ በረከታቸውን ያበዛል፣ እድሎቻቸውን ያሳድጋል፣ ነፍሳቸውን ያፅናናል፣ ጓደኞችን ያነሳል፣ እና ሰላምን ያፈሳል።”12
እነዚህ መመዛዘን የማይቻሉ መብቶች አለምን ለማሸነፍ የሰማይ ደጋፊ እርዳታን የሚሹ ተከትለው ይመጣሉ። በዚህም ምክንያት፣ ባለፈው ግንቦት ለወጣት ጎልማሶች የሰጠሁትን ሀላፊነት ለቤተክርስቲያኑ አባላት በሙሉ አቀርባለሁ። በዚያ ጊዜ እኔ እንዳበረታታቸኋቸው፣ እናም አሁን እናንተን እንደምለምናችሁ፣ የራሳችሁን የኢየሱስ ክርስቶስ እና የወንጌሉ ምስክርነት አጥብቃችሁ ያዙ። ይህንንም ስሩበት። ያድግ ዘንድ መግቡት። እውነትን መግቡት። በማያምኑ ወንዶችና ሴቶች ሀሰታዊ ፍልስፍናዎች አታበክሉት። በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ምስክርነት ማጠናከር ከሁሉም በላይ ቅድሚያ ስታደርጉ፣ ተዓምራትን በህይወታችሁ እንዲከሰቱ ጠብቁ።13
ዛሬ ጥዋት የማቀርበው ልመና አለምን ከእግዚአብሔር ጋር በገባችሁት ቃል ኪዳን በማሸነፍ ከዚህ አለም ጥንካሬ፣ ጥርጣሬ እና ጭንቀት እረፍት እንድታገኙ ነው። ዓለምን ለማሸነፍ በቁም ነገር እንዳላችሁ በጸሎታችሁ እና በድርጊታችሁ እንዲታወቁ አድርጉ። አዕምሮአችሁን እንዲያበራ እና የምትፈልጉትን እርዳታ እንዲልክ ጠይቁት። በየቀኑም በምትጸልዩበት ጊዜ ወደ እናንተ የሚመጡትን ሃሳቦች መዝግቡ፤ ከዚያም በትጋት ተከተሉ። በቤተመቅደስ ውስጥ ብዙ ጊዜ አሳልፉ እና ቤተመቅደሱ እንዴት ከዚህች ከወደቀች አለም በላይ እንድትወጡ እንደሚያስተምር ለመረዳት ፈልጉ።14
ከዚህ በፊት እንዳልኩት፣ እስራኤልን መሰብሰብ ዛሬ በምድር ላይ ከሚካሄዱት ሁሉ በላይ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የዚህ መሰብሰብ አንዱ ወሳኝ አካል ጌታ በዳግም በሚመጣበት ጊዜ ለመቀበል የሚችሉ፣ ዝግጁ እና ብቁ የሆኑ ሰዎችን፤ በዚህ በወደቀው ዓለም ላይ ኢየሱስ ክርስቶስን የመረጡ ህዝቦች፤ ከፍ ያለ፣ ቅድስተ ቅዱሳን የሆኑትን የኢየሱስ ክርስቶስ ህግጋትን ለመኖር በመረጣቸው የሚደሰቱ ሰዎችን ማዘጋጀት ነው።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ጻድቃዊ ህዝቦች እንድትሆኑ እጠራችኋለኁ። ቃል ኪዳኖቻችሁን ከሌሎች ቃል ከገባችኋቸው ነገሮች ሁሉ በላይ ተንከባከቡ እና አክብሩ። እግዚአብሔር በህይወታችሁ እንዲያሸንፍ ስትፈቅዱ፣ ታላቅ ሰላም፣ ልበ ብርቱነት፣ ደስታ፣ እናም አዎን፣ እረፍትም እንደምታገኙ ቃል እገባላችኋለሁ።
በተሰጠኝ ቅዱስ ሐዋርያነት፣ አለምን ለማሸነፍ በምትጥሩበት እባርካችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን እምነት እንድታጠናክሩ እና የእርሱን ሀይል ወደራሳችሁ ለመሳብ እንድትማሩም ይባርካችኋለሁ። እውነትን ከስህተት ለመለየት እንድትችሉ እባርካችኋለሁ። ከዚህች አለም ነገሮች በላይ የእግዚአብሔርን ነገሮች እንድታስቡባቸው እባርካችኋለሁ። በአካባቢዎቻችሁ ላሉት ሰዎች ፍላጎቶች እንድትመለከቱና የምታፈቅሯቸውን እንድታጠናክሩም እባርካችኋለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ስላሸነፈ፣ እናንተም እንዲሁ ትችላላችሁ። ይህንን የምመሰክረው ቅዱስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።