አጠቃላይ ጉባኤ
እውነትን የማወጅ ብርታት
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:26

እውነትን የማወጅ ብርታት

እውነትን ከተማርን በኋላ፣ ጌታ ዛሬ እዚህ ቢሆን ኖሮ የሚያደርገውን ነገሮች እንድናደርግ እድልን ይሰጠናል።

በ1982 (እ.አ.አ) በቴክኒካል ትምህርት ቤት ውስጥ የአሶሼት ዲግሪዬን በቶፖግራፊ እየጨረስኩኝ ነበር።

በዓመቱ መጨረሻ ላይ የክፍል ጓደኛዬ እንድንወያይ ጋበዘኝ። ሌሎቹን የት/ቤት አባሎች ትተን ወደ ስፖርት ሜዳው አጠገብ እንደሄድን አስታውሳለሁ። እዚያ ስንደርስ ስለሃይማኖቱ ያለውን እምነት አጫወተኝ እንዲሁም አንድ መጽሐፍ አሳየኝ ማሳየት ብቻም ሳይሆን፣ መጽሐፉን ሰጠኝ። እውነቱን ለመናገር፣ የተናገራቸውን ሁሉንም ቃላት አላስታውስም፣ ነገር ግን ያንን ክስተት እና “ይህ መጽሐፍ እውነት እንደሆነ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንደተመለሰ ልመሰክርልህ እወዳለው” ብሎ ሲለኝ የተሰማኝን ስሜት በደንብ አስታውሳለሁ።

ከውይይታችን በኋላ ወደ ቤት ሄድኩኝ፣ የተወሰኑ ገፆችን ገለጥኩኝ ከዚያም በመደርደሪያው ላይ አስቀመጥኩት። በዓመቱ መጨረሻ ላይ ስለነበርን እና የቶፖግራፊ ድግሪዬ የመጨረሻ ዓመት ስለነበረ፣ ለመጽሐፉም ሆነ ላካፈለኝ የክፍል ጓደኛዬ ብዙ ትኩረት አልሰጠሁም ነበር። የመጽሐፉን ስም እናንተ መገመት ትችላላችሁ። አዎ፣ መፅሐፈ ሞርሞን ነበር።

ከአምስት ወራት በኋላ፣ ሚስዮናውያን ወደ ቤቴ መጡ፣ ልክ ከስራ ወደ ቤት ስመለስ እነሱ እየሄዱ ነበር። እንዲመለሱ ጋበዝኳቸው። ከቤቴ ፊለፊት ካለው በረንዳ ላይ ተቀምጠን አስተማሩኝ።

እውነትን ለማግኘት በማደርገው ፍለጋ ላይ፣ የትኛው ቤተክርስቲያን ትክክለኛ እንደሆነ እና እንዴት ላገኘው እንደምችል ጠየኳቸው። ሚስዮናውያኑ የዚያን ጥያቄ መልስ እኔ በግሌ ማግኘት እንደምችል አስተማሩኝ። ከመጽሐፈ ሞርሞን ብዙ ምዕራፎችን እንዳነብ የሰጡኝን ሃላፊነት በታላቅ ተስፋ እና ፍላጎት ተቀበልኩኝ። ከልብ እና እውነተኛ በሆነ ስሜት ጸለይኩኝ (ሞሮኒ 10፥4–5 ይመልከቱ)። የጥያቄዬ መልስ ግልፅ ነበር እናም ከብዙ ቀናት በኋላ በትክክል በግንቦት 1 ቀን 1983 (እ.አ.አ)፣ ተጠመኩኝ እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ሆንኩኝ።

ዛሬ፣ ስለተከሰቱት ክስተቶች ቅደም ተከተል ሳስብ፣ የክፍል ጓደኛዬ ስለተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንዲሁም ስለ መጽሐፈ ሞርሞን ሲመሰክር የነበረው ድፍረት እንዴት ጠቃሚ እንደሆነ በግልፅ እመለከታለው። ያ ትንሽ ነገር ግን ለእኔ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ተግባር በእኔ እና በሚሲዮናውያን መካከል ግንኙነትን ፈጠረ።

እውነቱ ለእኔ ተሰጥቶኝ ነበር እናም ከጥምቀቴ በኋላ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆንኩኝ። በሚቀጥሉት ዓመታት በተለዩ ሰዎች ማለትም በመሪዎች፣ በአስተማሪዎች፣ እና በጓደኞች እንዲሁም በግሌ ጥናት እርዳታ አማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን ስወስን እውነትን የመጠበቅ ብቻ ሳይሆን የማወጁንም ሃላፊነት እንደተቀበልኩኝ ተማርኩኝ።

እውነትን ለማመን እና ለመከተል ስንስማማ እና የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀመዛሙርት ለመሆን ጥረት ስናደርግ፣ ስህተት እንደማንሰራ፣ ሰው እንደማይነቅፈን፣ ከእውነት ለመራቅ እንደማንፈተን ወይም ስቃይ እንደማያጋጥመን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት አንቀበልም። ነገር ግን የእውነት እውቀት ወደ የሰማይ አባት መገኛ በሚወስደን ቀጥተኛ እና ጠባቡ መንገድ ውስጥ ስንገባ፣ እነዚህ ችግሮች የማምለጫ መንገድ ሁሌም እንዳለ ያስተምራል (1 ቆሮንጦስ 10፥13)፤ እምነታችንን ከመጠራጠር በፊት ጥርጣሬአችንን የመጠራጠር እድሉ ሁሌም ይኖራል (ዲዪተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “ኑ፣ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 21)፤ እናም በመጨረሻ፣ በስቃይ ውስጥ ስንሄድ በፍፁም ብቻችንን እንደማንሆን ማረጋገጫ አለን ምክንያቱም እግዚአብሔር ህዝቦቹን በስቃያቸው ውስጥ ስለሚጎበኝ (ሞዛያ 24፥14 ይመልከቱ)።

እውነትን ከተማርን በኋላ፣ ጌታ ዛሬ እዚህ ቢሆን ኖሮ የሚያደርገውን ነገሮች እንድናደርግ እድልን ይሰጠናል። በእርግጥ፣ ምን ማድረግ እንዳለብን በትምህርቶቹ አሳየን “እናም እንደ መለከት ድምጽ ድምጻችሁን ከፍ በማድረግ፣ ልክ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ቃሌን በማወጅ፣ በመንፈሴ ኃይል ወንጌሌን በመስበክ ሁለት በሁለት በመሆን ወደፊት ትሄዳላችሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥6)። በወጣትነታችን ጊዜ የምንሰጠው የሚስዮናዊ አገልግሎት እድል ልዩ ነው።

እባካችሁ ወጣት ወንዶች፣ እንደ ጌታ ሚስዮኖች ለማገልገል የምትዘጋጁበትን አታስተላልፉ። ጥናታችሁን ለጊዜው እንደማቋረጥ፣ ተመልሳችሁ አብራችኋት እንደምትሆኑ ምንም ማረጋገጫ የሌላችሁን የሴት ጓደኛ እንደመሰናበት ወይም ከስራ እንደመልቀቅ ያሉ ሚስዮን ለማገልገል በምታደርጉት ውሳኔ ላይ ችግር የሚፈጥሩ ሁኔታዎች ሲያጋጥሟችሁ፣ የአዳኝ ምሳሌ አስታውሱ። በአገልግሎቱ ወቅት፣ እርሱም እንደዚሁ ችግሮች፣ እንዲሁም ትችት፣ ስደት እና በመጨረሻም የኃጥያት ክፍያ መስዋዕቱ መራራ ጽዋን ጨምሮ አጋጥመውታል። ነገር ግን በሁሉም ሁኔታዎች፣ የአብን ፈቃድ ለማድረግ እና ግርማውንም ለእርሱ ለመስጠት ፈለገ። (ዮሀንስ 5፥306፥38–393 ኔፊ 11፥11ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥18–19.ይመልከቱ)።

ወጣት ሴቶች፣ ከፈለጋችሁ እናንተ በጌታ ስራ ላይ ለመሳተፍ በጣም ትበረታታላችሁ፣ እናም እርሱን ለማገልገል ስታዘጋጁ፣ ከተመሳሳይ ተግዳሮቶች ነፃ አትሆኑም።

እርሱን ለማገልገል ለሚወስኑት ሁሉ፣ በሚስዮን ላይ የምታሳልፏቸው የ24 ወይም የ18 ወራት አገልግሎት ልክ እቤት ሆናችሁ እንደሚያልፈው ያልፋል፣ ነገር ግን የዚህን ቤተክርስቲያን ብቁ ወጣት ወንዶች እና ወጣት ሴቶች የሚጠብቋቸው እድሎች ልዩ እንደሆኑ ቃል እገባላችኋለው። አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስን እና ቤተክርስቲያኑን የመወከል እድል ችላ ሊባል አይቻልም። ስፍር ቁጥር በሌላቸው ጸሎቶች ውስጥ መሳተፍ፣ በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ ምስክርነታችሁን መገንባት እና ማካፈል፣ ለብዙ ሰዓታት ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት፣ እና እቤት ብትሆኑ ማግኘት የማትችሏቸውን ሰዎች ማግኘት፣ የማይገለፁ ልምዶች ናቸው። ተመሳሳይ ደረጃ ያለው ልምድ በአገልግሎት ሚስዮን ላይ ጌታ እንዲያገለግሉ ለጠራቸው ወጣቶች የተጠበቀ ነው። እናንተም ተጋባዝ እና አስፈላጊ ናችሁ። እባካችሁ የአገልግሎት ተልዕኮን አስፈላጊነት አትቀንሱ፣ ምክንያቱም የአገልግሎት ተልእኮዎች ሊገለጹ የማይችሉ ልምዶችን ይሰጣሉ። “የነፍስ ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10)፣ የነፍሳችሁን ዋጋም ጨምሮ።

ከአገልግሎታችሁ መልስ፣ ምናልባት የሴት ወይም የወንድ ጓደኛችሁ ላትጠብቃችሁ/ላይጠብቃችሁ ትችላለች/ይችላል፣ ነገር ግን ውጤታማ የሆነ ግንኙነት እንዴት ማድረግ እንዳለባችሁ ትማራላችሁ። አካዳሚያዊ ጥናታችሁ ለስራው በበለጠ ሁኔታ በብቃት ካደረጋችሁት ዝግጅት ጋር የበለጠ ትርጉም ይኖረዋል እንዲሁም በመጨረሻ ላይ፣ የተመለሰውን እውነት በመመስከር የሰላምን ወንጌል በብርታት ስለማወጃችሁ ሙሉ እርግጠኝነት ይኖራችኋል።

ላገባችሁ በተለያየ የህይወታቹ ደረጃ ላይ ላላችሁ ሰዎች፣ በጌታ ስራ ውስጥ በጣም ታስፈልጋላችሁ። እራሳችሁን አዘጋጁ። ስጋዊ እና መንፈሳዊ እራስን መቻልን በመሻት ጤናማ ህይወትን ምሩ፣ ምክንያቱም ጌታ ለልጆቹ የሚያደርግላቸውን የማድረግ እድሎች በአንድ የእድሜ ክልል ውስጥ የተገደበ አይደለም። ባለቤቴ እና እኔ በቅርብ አመታት ያጋጠሙን የሚያስደስቱ ልምዶች የመጡት ልዩ ከሆኑ ጥንዶች ጋር፣ በልዩ ቦታዎች እና የተለዩ ሰዎችን ስናገለግል ነበር።

በቶፖግፊ ድግሪዬ መጨረሻ ላይ የነበረኝ ልምድ እውነትን ስናውጅ ሁሌም እውነትን እንደምንጠብቅ እና እውነትን መጠበቅ ንቃትን የሚጠይቅ እንደሆነ አስተማረኝ። እውነትን መጠበቅ በመቆጣት መደረግ የለበትም፣ ነገር ግን እውነትን ለምንመሰክርላቸው ሰዎች በፍቅር፣ በማካፈል እና በመጋበዝ የአፍቃሪውን የሰማይ አባት ልጆች ስጋዊ እና መንፈሳዊ ደህንነት በማሰብ ብቻ መደረግ አለበት (ሞዛያ 2፥41)።

በጥቅምት 2021 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ውድ ነብያችን ፕሬዝዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን አንዳንዶች ከሚያስቡት በተቃራኒ በእርግጥ ትክክል እና ስህተት ብለን የምንጠራው ነገር እንዳለ አስተምረዋል። ፍፁም የሆነ እውነት አለ—ዘላለማዊ እውነት። (ራስል ኤም. ኔልሰን. “ንጹህ እውነት፣ ንጹህ ትምህርት፣ እና ንጹህ ራዕይ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 6 ይመልከቱ።)

ቅዱሳት መጻህፍት እንዲህ ያስተምሩናል፣ “እውነት ነገሮች እንዳሉ፣ እንደነበሩ፣ እናም ወደፊት እንደሚሆኑት የሚታወቅበት እውቀት ነው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥24)።

የእውነት እውቀቱ ከሌሎች ሰዎች የተሻልን አያደርገንም፣ ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር መገኛ ለመመለስ ምን ማድረግ እንዳለብን ያስተምረናል።

እውነትን ለማስተማር ብቻ ሳይሆን ነገር ግን እውነትን ለመኖር በክርስቶስ እና በብርታት ስትቀጥሉ፣ በእነዚህ ቀናት ውስጥ በሚያጋጥማችሁ መናወጥ ወቅት መፅናናትን እና ሰላምን ታገኛላችሁ።

የህይወት ተግዳሮቶች እንድንወድቅ ሊያደርጉን ይችላሉ፣ ነገር ግን እምነትን በኢየሱስ ክርስቶስ ስንለማመድ በዘለአለማዊ አስተያየት “[ስቃያችን” ለጥቂት ጊዜ ቢሆን ነው” በዘላለም እይታ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥7 ይመልከቱ)። እባካችሁ፣ ለችግራችሁ እና ተግዳሮቶቻችሁ ማብቂያ የጊዜ ገደብ አታብጁላቸው። በሰማይ አባት እመኑ እና ተስፋ እትቁረጡ፣ ተስፋ ከቆረጥን በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ የመንገዳችን ፍፃሜ ምን እንደሚሆን መቼም ማወቅ አንችልም።

ከእውነት ምንጮች በመማር እውነትን ያዙ፦

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነቴን እሰጣለው እናም ይህ የእርሱ ቤተክርስቲያን ነው። በህይወት ያሉ ነብይ አሉን እናም እውነትን በብርታት ስናውጅ ሁሌም ነፃነት ይሰማናል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።