አጠቃላይ ጉባኤ
የቃል በጎነት
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:16

የቃል በጎነት

ስለዚህም በጥንቶቹ እና በዘመናችን ነቢያት ቃላት ውስጥ በጎነት እንዳለ እንማራለን ምክንያቱም ቃላቶቻቸው የጌታ ቃላት በመሆናቸው ነው።

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ በተወዳጅ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅስ ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነ ውሳኔ በነቢዩ አልማ ተደርጎ ነበር። እነዚህ የምናውቃቸውን ቃላት ከመገምገም በፊት፣ እባካችሁ ያ ውሳኔ የተደረገባቸውን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ከእኔ ጋር አስቡበት።

ራሳቸውን ዞረማውያን ብለው የሚጠሩ ሰዎች ከኔፋውያን ተነጥለው1 እና በላማናውያን ምድር ዳርቻ ላይ ተሰብስበው ነበር።2 ታይቶ በማይታወቅ ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የተገደሉበት ኔፋውያን በቅርቡ ላማናውያንን አሸንፈው ነበር፣3 እናም “ዞራማውያን ከላማናውያን ጋር የህብረት ስምምነት ያደርጋሉ፣ እናም ይህም ለኔፋውያን የታላቅ ጥፋት መንስኤ ይህናል” ተብሎ ይፈራ ነበር።4 ከጦርነት ሀሳብ በላይ፣ “የእግዚአብሔር ቃል ተሰብኮላቸው” 5 የነበሩት ዘረማውያን ጣኦት ለማምለክ እየዞሩ እና “የጌታ ጎዳናን መበከላቸውን”6 አልማ አስተውሎ ነበር። ይህ ሁሉ በአልማ ላይ ከባድ ነበር እናም ለእርሱም “ታላቅ ሀዘን” ነበር።7

በእነዚህ ውስብስብ እና ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እራሱን በማግኘቱ፣ አልማ ምን መደረግ እንዳለበት አሰላሰለ። በውሳኔው ውስጥ፣ በዘመናችን ያሉትን ውስብስብ እና ፈታኝ ሁኔታዎች በምንመራበት ጊዜ፣ እኛን ለማነሳሳት እና ለማስተማር ተጠብቀው የቆዩ ቃላትን እናነባለን።8

“እናም አሁን፣ የቃሉ መሰበክ ህዝቡ ትክክለኛውን እንዲሰራ የሚመራ ታላቅ ዝንባሌ ስላለው—አዎን፣ ይህም ከጎራዴ፣ ወይም ከሚሆንባቸው ማንኛውም ነገር፣ የበለጠ በአዕምሮአቸው ላይ ውጤት ይኖረዋል—ስለዚህ አልማ ኃያል ውጤት ያለውን የእግዚአብሔር ቃል በጎነት መሞከራቸው አስፈላጊነቱን አሰበ።”9

ከብዙ መፍትሄዎች መካከል፣ የአልማ እምነት በቃሉ ኃይል እንዲታመኑ አድርጓቸዋል። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ በየትኛውም ቦታ ከሚገኙት በጣም ኃይለኛ የሆኑ አንዳንድ ስብከቶች የተሰበኩት ከውሳኔው በኋላ መሆኑ በአጋጣሚ አይደለም። በአልማ ምዕራፍ 32 እና 33 ውስጥ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስላለ እምነት የሰጠውን የተዋጣለት ንግግር እናነባለን፣ እንዲሁም በምዕራፍ 34 ውስጥ አሙሌቅ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ያቀረበውን አነሳሽ ትምህርት እናገኛለን።

የቃል በጎነት ምሳሌዎች

በህይወታቸው ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል በጎነት ለመሞከር በመረጡት ላይ ተአምራዊ በረከቶችን እንደፈሰሰ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እናነባለን።10 ትኩረታችንን ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንደ “የኋለኛው ቀን የመዳን መመሪያ”11 ብለው ወደገለጹት ወደ መፅሐፈ ሞርሞን ስናዞር፣ ከእኔ ጋር ሶስት ምሳሌዎችን እንድታሰላስል እጋብዛችኋለሁ።

መጀመሪያ፣ ጌታ አባቶቻቸውን እንዳዳነ ህዝቡ እንዲያስታውሱ በማድረግ፣ አልማ እንዲህ አስተማረ፦ “እነሆ፣ እርሱ ልባቸውን ለውጧል፣ አዎን፣ ከጥልቁ እንቅልፋቸው ቀስቅሶአቸዋል፣ እናም ወደ እግዚአብሔር ነቅተዋል። እነሆ፣ በጨለማው መካከል ነበሩ፣ ይሁን እንጂ ነፍሳቸው በዘለአለማዊው ቃል ብርሃን በርቷል።”12 ምናልባት በጨለማ ውስጥ እንዳላችሁ ሆኖ ይሰማችሁ ይሆናል። ነፍሳችሁ ብርሃንን በጥብቅ ትፈልጋለችን? ከሆነ እባካችሁ የእግዚአብሔርን ቃል በጎነት ሞክሩ።

ሁለተኛ፣ ሚስዮናዊ እያለ የተመለተውን የጌታን ላማናውያንን መለወጥ ላይ በማሰላሰል፣ አሞን እንዲህ አለ፣ “እነሆ፣ ስንት ሺህ ወንድሞቻችንን ነው እግዚአብሔር ከሲኦል እስራት የፈታው፣ እናም የቤዛነትን ፍቅር እንዲዘምሩ ተደረጉ፣ እናም ለዚህም ምክንያቱ በውስጣችን ባለው በቃሉ ኃይል የተነሳ ነበር።13 ወንድሞች እና እህቶች፣ የሚወዱት ሰው ቤዛዊ ፍቅር እንዲዘምር የሚናፍቁ በጣም ብዙ በመካከላችን ይገኛሉ። በጥረታችን ሁሉ፣ በውስጣችን ያለውን የእግዚአብሔርን ቃል በጎነት መሞከርን እናስታውስ።

ሶስተኛ፣ በመፅሐፈ ሔላማን ውስጥ እንደምናነበው፣ “አዎን፣ ማንም ቢሆን ህያው የሆነውንና ኃያል የሆነውን፣ የዲያብሎስን ዕቅድ፣ ብልጠትና ወጥመድ የሚበታትነውን፣ እናም የክርስቶስ የሆኑትን ሰዎች በቀጭኑና ጠባብ በሆነው ጎዳና፣ ኃጢአተኞችንም ሊውጣቸው ከተዘጋጀው ከዘለዓለማዊው ጉስቁልና ባሻገር የሚመራቸውን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቆ የያዘ … ነፍሳቸውም፣ … በመንግስተ ሰማያት በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ [እንደሚያስቀምጥ]፣ … እንመለከታለን።”14 በዘመናችን በፍልስፍና የተንሰራፋውን ተንኮል እና ወጥመዶች እና የዲያብሎስ ሽንገላዎችን ሁሉ ለማጥፋት እየፈለጋችሁ ነውን? በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ብቻ ለማተኮር በተትረፈረፈ መረጃ ምክንያት የተፈጠረውን የግራ መጋባት ደመና መበተን ትፈልጋላችሁን? እባካችሁ የእግዚአብሔርን ቃል በጎነት ሞክሩ።

በቃሉ ሃይል የተለወጠ እንደመሆኔ፣ እኔ በግሌ በተወዳጁ ነቢያችን፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ስለተማረው ይህን እውነት እመሰክራለሁ፦ “ለእኔ፣ የመፅሀፈ ሞርሞን ሃይል ‘በቅን ልባችሁ፤ ከእውነተኛ ፍላጎት፣ በክርስቶስ [በማመን]’ በሚያነቡት ሰዎች ሕይወት ውስጥ በሚመጣው ታላቅ ለውጥ ምክንያት በጣም ግልፅ ነው። ብዙ አማኞች የመጽሐፉን ትእዛዛት ለማክበር ብለው በአንድ ወቅት ውድ አደርገው ይዘዋቸው የነበሩትን ብዙ ነገሮች ይተዋሉ። … ይህም ነፍሳትን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለማምጣት በጣም ውጤታማ መሳሪያህ ይሆናል።”15

የበጎነት ምንጭ

በእነዚህ እና በሌሎች ምሳሌዎች ውስጥ፣ የእግዚአብሔር ቃል በልጆቹ ህይወት ውስጥ ያለውን በጎነት እንመሰክራለን። የዚያ በጎነት ወይም ኃይል ምንጭ ምንድን ነው ብለን ልንጠይቅ እንችላለን?

ይህን ጥያቄ በምንመረምርበት ጊዜ፣ “ቃል” የሚለው ሐረግ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ቢያንስ ሁለት ትርጉም እንዳለው ማስታወሱ አስፈላጊ ነው። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር በቅርብ እንዳስተማሩት፣ “ከኢየሱስ ክርስቶስ ስሞች አንዱ ‘ቃል’ ነው፣ እንዲሁም “በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እንደተመዘገበው የአዳኝ ትምህርቶችም እንዲሁ ‘ቃል’ ናቸው።”16

ነቢዩ ኔፊ በእነዚህ ሁለትትርጉሞች መካከል ስላለው ግንኙነት እንዲህ ብሎ ገለጿል፦ “እነዚህን ቃላት አድምጡም፣ በክርስቶስም እመኑ፤ እንዲሁም በእነዚህ ቃላት የማታምኑ ከሆነ በክርስቶስ እመኑ። እናም በክርስቶስ የምታምኑ ከሆነ በእነዚህ ቃላት ታምናላችሁ፣ እነርሱ የክርስቶስ ቃላት ናቸውና፣ እነርሱንም ለእኔ ሰጠኝ።”17 ስለዚህም በጥንቶቹ እና በዘመናችን ነቢያት ቃል ውስጥ በጎነት እንዳለ እንማራለን ምክንያቱም ቃላቶቻቸው የጌታ ቃል በመሆናቸው ነው።18 ውድ ጓደኞቼ ፣ እንደተተነበየው “በምድር ላይ ራብ [በሚመጣበት] … እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል [የ]መስማት እንጂ እንጀራን [የ]መራብና ውኃን [የ]መጠማት”19ባልሆነው በኋለኛው ቀናት 20ይህን ዘላለማዊ እውነት መቀበል ለመንፈሳዊ ህልውናችን በጣም አስፈላጊ ነው።

በመጨረሻም፣ የእግዚአብሔር ቃል በጎነት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው21 ይህንን የበለጠ በተሟላ ሁኔታ ስንረዳ፣ በነቢያቱ ሚና እና በራሱ በአዳኙ መካከል ዘላለማዊ ጉልህ የሆነ ግንኙነት መፍጠር እንችላለን። ለእርሱ ያለን ፍቅር፣ ወደ እርሱ ለመቅረብ እና በፍቅሩ ለመኖር ያለን ፍላጎት፣22 የቃሉን በጎነት በህይወታችን እንድንሞክር ያበረታታናል—እንደግል አዳኛችን እና ቤዛችን23 የሚፈሰውን በጎነት እና “በእግዚአብሔር በተመረጡት ዕቃዎች” ቃላቶች በኩል ከእርሱ የሚፈሰውን በጎነት።24 አዳኙን እና የነቢያቱን ቃላት ለማጥናት ሌሎች ምንጮች አጋዥ ቢሆኑም፣ እነርሱን የሚተኩ መሆን እንደሌለባቸው ወደ ማስተዋል እንመጣለን። በቀጥታ ከምንጩ በጥልቅ እና ብዙ ጊዜ መጠጣት አለብን25

ለእያንዳንዳችሁ፣ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ያለኝን ፍቅሬን እገልጻለሁ። በዚያ ፍቅር ውስጥ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በጎነት እንድትለማመዱ እለምናችኋለሁ፣ በተለይም በህይወታችሁ በየእለቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ። ይህንን ስታደርጉ፣ ከፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን የተሰጡትን እነዚህን ነቢያዊ ተስፋዎች ታገኛላችሁ፦ “መፅሐፈ ሞርሞንን በጸሎት መንፈስ በየቀኑስታጠኑበየቀኑየተሻሉ ውሳኔዎችን እንደምታደጉ ቃል እገባለሁ። በምታጠኑት ነገር ላይ ስታሰላስሉ፣ የሰማይ መስኮቶች እንደሚከፈቱ፣ እንዲሁም ለራሳችሁ ጥያቄዎች መልስ እና ለግል ህይወታችሁ መመሪያ እንደምትቀበሉ ቃል እገባለሁ። በየቀኑ ራስችሁን በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ስታጠልቁ፣ ከእለቱ ክፋት መከላከያ እንደሚነራችሁ ቃል እገባለሁ።”27

የሰማይ አባታችን ቃሉን እንደሰጠን እመሰክራለው ምክንያቱም እርሱ በፍጹም ይወደናል እና እያንዳንዳችን ከእርሱ ጋር ለዘለአለም ለመኖር ወደ ቤት እንድንመለስ ይፈልጋልና። “ቃልም ሥጋ [ስለሆነው]”፣28 ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና እኛን ስለሚያደን እና ስለሚቤዥ ኃይሉ እመሰክራለሁ። የእርሱ በጎነት በቀደሙትም ሆነ በአሁኑ ዘመን ነቢያቱ ቃል በኩል እንደሚፈስ አውቃለሁ።

የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀን ለመያዝ29 እና ወደ ክብር እና ወደ ዘለአለማዊ ህይወት በሚያመራው የቃል ኪዳን መንገድ ላይ እንድንቆይ30ጥበብ እና የዋህነትን እንድንይዝ የልቤ ጸሎት ነው። የቃሉ በጎነት ለእያንዳንዳችን ያለውን ታላቅ ለውጥ ያለማቋረጥ እንለማመድ።31 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. አልማ 30፥59 ይመልከቱ።

  2. አልማ 31፥3 ይመልከቱ።

  3. አልማ 28፥2 ይመልከቱ።

  4. አልማ 31፥4። እባካችሁ አልማ እና ህዝቦቹ ቀደም ሲል በአምሊኪውያን እና ላማናውያን መካከል እንዲህ ያለ “ተዛማጅነት” አጋጥሟቸዋል፣ ይህም ወደ ታላቅ ሀዘን እና ኪሳራ እንዳስከተለ አስታውሉ።(አልማ 2፥21–38 እና አልማ 3፥1–3 ይመልከቱ)።

  5. አልማ 31፥8

  6. አልማ 31፥1

  7. አልማ 31፥2

  8. ሞርሞን 8፥34–35 ይመልከቱ።

  9. አልማ 31፥5፤ ትኩረት ተጨምሯል።

  10. ለምሳሌ 1 ኔፊ 15:24አልማ 32:41–4336:2637:844–45ይመልከቱ።

  11. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Embrace the Future with Faith፣” ሊያሆና፣ ሀዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 75።

  12. አልማ 5፥7፤ ትኩረት ተጨምሯል።

  13. አልማ 26፥13፤ ትኩረት ተጨምሯል።

  14. ዮሀንስ 21፥29–30፤ ትኩረት ተጨምሮበታል።

  15. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “መፅሐፈ ሞርሞን፥ ተዓምራዊ ተዓምር” (ንግግሩ የቀረበው፣ ሞሮኒ 10፥4ን በከፊል በመጥቀስ፣ በአዲስ የሚስዮን ፕሬዘዳንቶች ሴሚናር ላይ፣ በሰኔ 23 ቀን 2016 (እ.አ.አ) ነበር።)

  16. ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “But We Heeded Them Not፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022፣ 16።

  17. 2 ኔፊ 33፥10፤ አትኩሮት ተጨምሮበታል።

  18. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥38 ይመልከቱ።

  19. ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 1፥14–18 ይመልከቱ።

  20. አሞፅ 8፥11

  21. አልማ 34፥6 ይመልከቱ።

  22. ዮሀንስ 15፥10 ይመልከቱ።

  23. ማርቆስ 5፥25–34 ይመልከቱ።

  24. ሞሮኒ7፥31

  25. “ለመዘጋጀት የተሻለ መንገድ አለ፣ ምክንያቱም ታላቅ እምነት አጭር የመደርደሪያ ህይወት አለው። በቅዱሳት መጻህፍት እና በህያዋን ነቢያት ትምህርቶች ውስጥ ያሉትን የክርስቶስን ቃላት በማጥናት ለመጽናት መወሰን እንችላለን። እኔ የማደርገው ይህንን ነው። ወደ መጽሐፈ ሞርሞን እመለሳለሁ እናም በጥልቅ እና ብዙ ጊዜ እጠጣለሁ” (ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “Spiritual Preparedness: Start Early and Be Steady፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2005 (እ.አ.አ)፣ 39)።

  26. “ለእኔ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ማንበብ እውቀትን ለማግኘት የሚጣጣርበት አይደለም። ይልቁንም ከጌታና ከእርሱ ነቢያት ቃል ጋር ያለ ፍቅር ነው። …

    በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የሚገኘውን በሰፊው ለማስፋት የተነደፉ ረጅም የሐተታ ጥራዞችን ለማንበብ ብዙም አላስብም። ይልቁንስ የእውነትን መሠረት የሆነውን፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሰጠው እና እንደ ቅዱሳት መጻህፍት በምንቀበላቸው መጻህፍት ውስጥ እንደተመዘገበው፣ ያልተበረዘ ውሆችን እየቀመስኩ መኖርን እመርጣለሁ - ። ቅዱሳት መጻህፍትን በማንበብ፣ ያነበብነው ለልጆቹ ብርሃን፣ በረከት እና ደስታ ይሆኑ ዘንድ ከእግዚአብሔር እንደመጣ የመንፈስን ማረጋገጫ ማግኘት እንችላለን” (ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “Feasting upon the Scriptures፣”ታምቡሊ፣ ሰኔ 1986 (እ.አ.አ)፣ 2፣4)

  27. ራስል ኤም. ኔልሰን “መፅሐፈ ሞርሞንን፦ ያለሱ ሕይወታችሁ ምን ይሆናል?ሊያሆና, ህዳር. 2017, 62–63.

  28. ዮሀንስ 1:14

  29. 1 ኔፊ 8፥30ይመልከቱ።

  30. “የቃል ኪዳን መንገድ ወደ ከፍተኝነት እናአ ዘለዓለማዊ ህይወት የሚመራ ብቸኛ መንገድ ነው፣” (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የመንፈሳዊ ፍጥነት ሃይል፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 98)።

  31. አልማ 5፥11–13ይመልከቱ።