አጠቃላይ ጉባኤ
ምስክርነታችሁን መመገብ እና ማካፈል
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


13:15

ምስክርነታችሁን መመገብ እና ማካፈል

ምስክርነታችሁን በቃል እና በተግባር ለማካፈል እድሎችን እንድትሹ እጋብዛችኋለሁ።

መግቢያ

ወጣት ብትሆኑም እንኳን በሕይወት ውስጥ ወሳኝ ወቅቶች ብዙ ጊዜ እና ሳይጠበቁ ይመጣሉ። ለተማሪ መሪ ክስተት ከስቴት ውጪ ለመጓዝ ስለመረጠው የአጠቃላይ ት/ቤት ተማሪ ስለሆነ ስለ ኬቨን ታሪክ እንዳካፍል ፍቀዱልኝ፣ በራሱ ቃላት የተነገረ።

“በሰልፉ ላይ ተራዬ ደረሰ እና የምዝገባ ጸሐፊዋ ስሜን ጠየቀችኝ። የስም ዝርዝሯን ተመለከተች እና ‘አንተ ከዩታ የመጣህ ወጣት ሰው ነህ።’

“‘እኔ ብቻ ነኝ ማለትሽ ነው?’ ብዬ ጠየኩኝ።

“‘አዎ፣ አንተ ብቻ ነህ።’ ከስሜ ስር “ዩታ” ተብሎ የተፃፈ የስም ማስታወቂያን ሰጠችኝ። የስም ታጉን ሳደርገው የተለየው ያህል ተሰማኝ።

“እንደኔ የስም ታግ ካደረጉ ከአምስት የአጠቃላይ ት/ቤት ተማሪዎች ጋር በሆቴሉ ሊፍት ውስጥ ገባው” ‘ሰላም ነው፣ ከዩታ ነህ። ሞርሞን ነህን?’ ብሎ ጠየቀ አንድ ተማሪ።

“ከመላው አገር በመጡ ከእነዚህ የተማሪ መሪዎች መካከል ካለቦታዬ ያለው መስሎ ተሰማኝ። ‘አዎ፣’ አልኩኝ በማመንታት።

“‘እናንተ መላዕክቶችን አየሁ ባለው በጆሴፍ ስሚዝ የምታምኑት ናችሁ። ያንን በእርግጥ አታምንም አይደል?’

“ምን ማለት እንዳለብኝ አላወኩም። በሊፍቱ ውስጥ ያሉት ተማሪዎች በሙሉ እኔን እያዩ ነበር። ገና መድረሴ ነበር፤ ሁሉም ሰው የተለየሁ እንደሆንኩኝ አሰቡ። ትንሽ ተከላካይ ሆንኩ ነገር ግን “ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑን አውቃለሁ” አልኩ።

“‘ያ ከየት ነው የመጣው?’ ብዬ አሰብኩኝ። በውስጤ ያለኝ አልመሰለኝም። ነገር ግን ቃላቶቹ እውነት መስለው ተሰሙኝ።

“‘አዎ፣ እናንተ ሁሉ አክራሪ ሐይማኖተኛ እንደሆናችሁ ተነግሮኛል’ አለ።

“የሊፍቱ በር ሲከፈት የማይመች ፀትታ ነበር። ሻንጣችንን ስንሰበስብ፣ እየሳቀ ሄደ።

“ከዛ፣ ‘ሞርሞኖች የተለየ መጽሐፍ ቅዱስ የላቸውም እንዴ?’ የሚል ድምፅ ከጀርባዬ መጣ።

“አዪ። እንደገና። በሊፍቱ ውስጥ ከእኔ ጋር የነበረን ሌላ ተማሪ ክርስቶፈርን ለማየት ዞርኩኝ።

“‘መጽሐፈ ሞርሞን ይባላል፣’ ብዬ አልኩኝ ሃሳብ ለመቀየር በመፈለግ። ሻንጣዬን አንስቼ መራመድ ጀመርኩኝ።

“‘ጆሴፍ ስሚዝ የተረጎመው መጽሐፍ ነውን?’ ብሎ ጠየቀ።

“‘አዎ፣ ነው’ ብዬ መለስኩኝ። መራመዴን ቀጠልኩኝ መዋረድን ለማስወገድ ተስፋ በማድረግ።

“‘እንዴት ማግኘት እንደምችል ታውቃለህን?’

“በሴሚነሪ ውስጥ የተማርኩት ጥቅስ በድንገት መጣልኝ። ‘በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አላፍርም።’1 ይህ አዕምሮዬ ውስጥ ሲገባ፣ በጣም በመዋረዴ አፈርኩኝ።

“በቀሪው ሳማንት ውስጥ ያ ጥቅስ ከውስጤ ሊጠፋ አልቻለም። እሰከምችለው ድረስ ስለ ቤተክርስቲያኗ ብዙ ጥያቄዎችን መለስኩኝ እና ብዙ ጓደኞችን አፈራው።

“በሐይማኖቴ እንደምኮራ አወኩኝ።

“ለክርስቶፈር አንድ መጽሐፈ ሞርሞን ሰጠሁት። ከዛ ሚስዮኖችን ወደ ቤቱ እንደጋበዘ ፃፈልኝ።

“ምስክርነቴን ለማካፈል ማፈር እንደሌለብኝ ተማርኩኝ።”2

ኬቨን ምስክርነቱን በማካፈሉ ብርታት ተነሳስቻለው። በመላው ዓለም በአማኝ የቤተክርስቲያን አባሎች በእየቀኑ የሚደጋገም መበረታታት ነው። ሃሳቤን ሳካፍል፣ በእነዚህ አራት ጥያቄዎች ላይ እንድታስቡ እጋብዛለው፦

  1. ምስክርነት ምን እንደሆነ አውቃለውን እና እረዳለውን?

  2. ምስክርነቴን እንዴት እንደማካፍል አውቃለውን?

  3. ምስክርነትን የማካፈል እንቅፋቶች ምንድን ናቸው?

  4. ምስክርነቴን እንዴት መጠበቅ እችላለሁ?

ምስክርነት ምን እንደሆነ አውቃለውን እና እረዳለውን?

ምስክርነታችሁ በጣም ውድ የሆነ ሃብታችሁ ነው፣ ብዙ ጊዜ ዝልቅ በሆነ የመንፈስ ስሜት ይገለፃል። እነዚህ ስሜቶች ብዙ ጊዜ የሚነገሩት በፀጥታ ነው እና “ዝግ ባለ በትንሽ ድምፅ” ይገለፃሉ።3 በመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ አማካኝነት እንደ መንፈሳዊ ምስክርነት የተሰጠ የእውነት እምነታችሁ ወይም እውቀታችሁ ነው። ይህን ምስክር ማግኘት የምትሉትን ነገር እና የምትተገብሩበትን መንገድ ይቀይራል። በመንፈስ ቅዱስ የተረጋገጠው የምስክርነታችሁ ዋና ክፍሎች እነዚህን ይጨምራሉ፦

  • እግዚአብሔር የሰማይ አባታችሁ ነው እናንተ የእርሱ ልጆች ናችሁ። ያፈቅራችኋል።

  • ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው ነው። እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ፣ እናም አዳኛችሁ እና ቤዛችሁ ነው።

  • ጆሴፍ ስሚዝ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን እንዲመልስ የተጠራ የእግዚአብሔር ነብይ።

  • የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር የተመለሰ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ነች፡፡

  • የኢየሱስ ክርስቶስ የተመለሰው ቤተክርስቲያን ህያው በሆነ ነቢይ ይመራል ዛሬ።

ምስክርነቴን እንዴት እንደማካፍል አውቃለውን?

ከሌሎች ጋር መንፈሳዊ ስሜቶችን ስታካፍሉ ምስክርነታችሁን ታካፍላላችሁ። እንደ ቤተክርስቲያን አባል፣ ምስክርነትን የመስጠት እድሎች በመደበኛ የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ወይም ብዙም መደበኛ ባልሆነ ከቤተሰብ፣ ከጓደኞች እና ከሌሎች ጋር ባለ የአንድ ለአንድ ንግግሮች ይመጣል።

ሌላ ምስክረነታችንን የምንካፈልበት መንገድ ጻድቃዊ ባህሪ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁ ምስክርነት የምትሉት ብቻ አይደለም—ይህም ማንነታችሁ ነው።

ምስክርነታችሁን ስታካፍሉ ወይም ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ቁርጠኝነታችሁን በተግባራችሁ ስትገልፁ ሌሎችን “ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ” ትጋብዛላችሁ።4

የቤተክርስቲያን አባሎች በሁሉም ሰዓት፣ በሁሉም ነገርች እና በሁሉም ቦታዎች እንደ የእግዚአብሔር ምስክሮች ይቆማሉ።5 በዚህ በዲጂታል ዓለም ውስጥ የገዛ የሚያነሳሳ ጉዳይን የመጠቀም ወይም በሌሎች የተዘጋጀ ከፍ የሚያደርግ ጉዳይን የማካፈል እድሎች ማለቂያ የላቸውም። በኦንላይንም ቢሆን እንኳን ስንወድ፣ ስናካፍል እና ስንጋብዝ እንመሰክራለን። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ህይወታችሁን እንዴት እንደሚቀርጽ ለማሳየት ማህበራዊ ሚዲያ ስትጠቀሙ ትዊቶቻችሁ፣ ቀጥታ መልእክቶቻችሁ እና ልጥፎቻችሁ ከፍ ያለ እና የተቀደሰ አላማ ይኖራቸዋል።

ምስክርነትን የማካፈል እንቅፋቶች ምንድን ናቸው?

ምስክርነታችሁን የማካፈል እንቅፋቶች ስለምትናገሩት ነገር እርግጠኛ አለመሆንን ያካትታል። ማቲው ካውሊ፣ የቀድሞ ሐዋርያ በ17 ዓመት ወደ ኒው ዚላንድ ለአምስት ዓመት የሚስዮን አግልግሎት ሲሄዱ ይህን ልምድ አካፈሉ።

“በሄድኩበት ቀን አባቴ ያደረገውን ጸሎት መቼም አልረሳውም። በህይወቴ ከዚህ የበለጠ የሚያምር በረከት ሰምቼ አላውቅም። ከዚያ በባቡር ጣቢያው ለእኔ የተናገራቸው የመጨረሻ ቃላት፣ ‘ልጄ፣ ወደዚያ ሚስዮን ትሄዳለህ፤ ታጠናለህ፤ ትምህርትህን ለመዘጋጀት ትሞክራለህ፣ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ስትጠራ በሚያስደንቅ ሁኔታ እንደተዘጋጀህ ታስባለህ ነገር ግን ለመናገር ስትቆም አዕምሮህ ይጨልምብሃል።’ … እንደዚያ ዓይነት ተሞክሮ ከአንድ ጊዜ በላይ አጋጥሞኛል።

“እንዲህ አልኩኝ፣ ‘አዕምሮህ ሲጨልምብህ ምን ታደርጋለህ?’

“እንደዚህ አለ፣ ‘እዛ ትቆምና በመላ ነፍስህ ጆሴፍ ስሚዝ የሕያው እግዚአብሔር ነብይ እንደሆነ ትመሰክራለህ እና ለሚሰሙ ልቦች በሙሉ ሃሳቦች ወደ አዕምሮህ ቃላቶች ደግሞ ወደ አፍህ ይጎርፋሉ።’ እና በሚስዮኔ ብዙ ጊዜ አዕምሮዬ ስለጨለመብኝ ከጌታ ስቅለት ጀምሮ በዓለም ታሪክ ውስጥ ለታላቁ ክስተት ምስክርነት ለማካፈል እደል ሰጠኝ። ወንዶች እና ሴቶች፣ ይህን ሞክሩት። የምትሉት ነገር ከሌላችሁ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚአብሔር ነብይ እንደነበር መስክሩ እና የቤተክርስቲያኗ ታሪኮች በሙሉ ወደ አዕምሮአችሁ ይጎርፋል።”6

ልክ እንደዚህ፣ ፕሬዝዳንት ዳለንኤች. ኦክስ እንዲህ አስተማሩ፣ “የተወሰኑ ምስክርነቶች ተንበርክኮ ለእነሱ ከመፀለይ ይልቅ በእግር ተሆኖ ሲመሰከሩ የበለጠ ይገኛሉ።”7 መንፈስ ለተናጋሪ እና ለአድማጭ በተመሳሳይ ሁኔታ ይመሰክራል።

ሌላኛው እንቅፋት፣ በኬቨን ታሪክ ላይ እንደተገለፀው፣ ፍርሃት ነው። ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንደፃፈው፦

“እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም። …

“እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት አትፍራ።”8

የፍርሃት ስሜት ከጌታ አይመጣም ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የሚመጣው ከተቃዋሚ ነው። ልክ እንደ ኬቨን እምነት መኖር፣ እነዚህን ስሜቶች ለማሸነፍ ይፈቅድላችኋል እናም በልባችሁ ውስጥ ያለውን በነፃነት ታካፍላላችሁ።

ምስክርነቴን እንዴት መጠበቅ እችላለው?

ምስክርነት በውስጣችን እንደተፈጠረ አምናለው፣ ነገር ግን ለመጠበቅ እና በይበልጥ ለማዳበር “[ምስክርነታችንን] በታላቅ ጥንቃቄ [መንከባከብ]” እንዳለብን አልማ አስተምሯል።9 ይህን ስናደርግ፣ “ስር ያገኛልም፣ ያድጋልም፣ እናም ፍሬን ያስገኛል።”10 ከዚህ ውጪ “ይደርቃል።”11

እያንዳንዱ ተወዳጅ የቀዳሚ አመራር አባል ምስክርነታችንን እንዴት እንድምንጠብቅ መመሪያ ሰጥተውናል።

ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ በፍቅር እንዳስተማሩን፣ “ምስክርነታችሁ እንዲያድግ እና እንዲበለፅግ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መመገብ፣ ልባዊ ጸሎት እና የጌታን ትእዛዛት መታዘዝ በእኩል እና በቀጣይነት መተግበር አለበት።”12

ፕሬዘደንት ዳለን ኦክስ እንድናስታውስ እንዳደረጉን፣ ምስክርነታችንን ለመጠበቅ፣ “ቅዱስ ቁርባንን በየሳምንቱ በመቀበል (ት&ቃ 55፥9) ‘በመንፈሱ ሁልግዜም [ከእኛ] ጋር ይሆን ዘንድ’ (ት&ቃ 20፥77) ለሚለው ውድ የተስፋ ቃል ብቁ መሆን ያስፈልገናል።”13

እናም ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በደግነት ይህን ምክር በቅርብ ሰጡ፦

“[ምስክርነታችሁን] እውነት መግቡት። …

“… በጥንት እና በዘመናዊ ነቢያት ቃል እራሳችሁን መግቡ። እርሱን የበለጠ እንዴት እንደምትሰሙት ጌታን እንዲያስተምራችሁ ጠይቁት። በቤተመቅደስ ውስጥ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ ላይ ብዙ ጊዜ አሳልፉ።

“… ምስክርነታችሁን ከሁሉም በላይ ከፍተኛ አድርጉት።”14

መደምደሚያ

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ የምስክርነት ትርጉምን የበለጠ ስትገነዘቡ እና ስታካፍሉ፣ የመጠራጠርን እና የፍርሃትን እንቅፋቶችን ታሸንፋላችሁ ምስክርነታችሁን እንድትንከባከቡ እና እንድትጠብቁ እንደሚያስችላችሁ ቃል እገባለው።

ቁጥር ስፍር የሌላቸውን የጥንት እና የዘመናዊ የኋኛው ቀን ነብያት በድፍረት ምስከራቸውን ያካፈሉበት ምሳሌዎች ስላሉን ተባርከናል።

የክርስቶስን ሞት ተከትሎ፣ ጴጥሮስ ቆሞ እንደዚ መሰከረ፦

“እናንተ በበሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሳው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደህና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።

“መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”15

አሙሌክ የአልማን የእምነት ትምህርት በመከተል፣ በኃይል እንደዚህ አለ፦ “እኔ ራሴ እነዚህ ነገሮች እውነት መሆናቸውን እመሰክራለሁ። እነሆ፣ እንዲህም እላችኋለሁ፥ ክርስቶስ በሰው ልጆች መካከል እንደሚመጣ፣ እናም ለዓለም ኃጢያት ክፍያን እንደሚከፍል አውቃለሁ፤ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሯልና።”16

ጆሴፍ ስሚዝ እና ሲድኒ ሪግደን ከሞት የተነሳውን አዳኝ ራዕይ ከተመለከቱ በኋላ መሰከሩ።

“እናም አሁን፣ ስለ እርሱ ከተሰጡት ከብዙ ምስክርነቶች በኋላ፣ ይህ ስለ እርሱ የምንሰጠው፣ የሁሉም መጨረሻ ምስክርነት ነው፥ እርሱ ሕያው ነው!

“በእግዚአብሔር ቀኝ አይተነዋልና፤ እናም እርሱ የአብ አንድያ ልጅ እንደሆነም ሲመሰክርም ድምፅ ሰምተናል።”17

ወንድሞች እና እህቶች፣ ምስክርነታችሁን በቃል እና በተግባር ለማካፈል እድሎችን እንድትሹ እጋብዛችኋለሁ። በደቡብ አሜሪካ ውስጥ ከዋና ከተማ ከንቲባ እና ከካቢኔው ጋር ስብሰባ መጨረሻ ላይ እንደዚህ ዓይነት እድል በቅርቡ ወደ እኔ መጣ። በጨዋነት ስሜቶች ስንቋጭ፣ እርግጠኛ ባለመሆን ምስክርነቴን ማካፈል እንዳለብኝ አስብኩ። መነሳሳቱን በመከተል፣ ኢየሱስ ከርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እና የዓለም አዳኝ እንደሆነ መሰከርኩኝ። በዛ ወቅት ሁሉም ነገር ተቀየረ። በክፍሉ ውስጥ መንፈሱ እንደነበር የማይካድ ነበር። ሁሉም የተነኩ ይመስል ነበር። “አጽናኙ … ስለአብ እና ስለወልድ ይመሰክራል።18 ምስክርነቴን ለመስጠት ብርታቴን ስለሰበሰብኩኝ ደስተኛ ነኝ።

እንደዚህ ዓይነት ጊዜ ሲመጣ፣ ውሰዱት እና ተቀበሉት። ይህን ስታደርጉ፣ የአፅናኙን ሙቀት በውስጣችሁ ይሰማችኋል።

ምስክርነቴን እሰጣችኋለሁ፣ እግዚአብሔር የሰማይ አባታችን ነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው ነው፣ እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዛሬ በውዱ ነቢያችን፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን የምትመራ በምድር ላይ ያለች የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ናት። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።