አጠቃላይ ጉባኤ
የማበረታታት ቅርስ
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


14:29

የማበረታታት ቅርስ

ወደ ሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ለመመለስ ብቁ ለመሆን መጣራችሁን እንድትቀጥሉ አበረታታችኋለው።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በዚህ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርሰቲያን ጉባኤ ከእናንተ ጋር በመሆኔ አመስጋኝ ነኝ። ባለንበት ቦታ እምነታችሁ እና ፍቅራችሁ ተሰምቶናል። በተነሳሱት ትምህርቶች፣ በኃይለኛ ምስክርነቶች እና በድንቅ መዝሙሮች ታንፀናል።

ወደ ሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ለመመለስ ብቁ ለመሆን መጣራችሁን እንድትቀጥሉ አበረታታችኋለው። በቃልኪዳኑ መንገድ ላይ በየትኛውም ቦታ ብትሆኑም፣ የሟችነት አካላዊ ፈተናዎች ትግል እና የሴጣን ተቃርኖ ያጋጥማችኋል።

የሆነ ነገር እንዴት ከባድ እንደሆነ ሳጉረመርም እናቴ እንደነገረችኝ “ኦ፣ ሃል፣ በእርግጥ ከባድነው።” መሆንም ነበርበት። ህይወት ፈተና ነች” አለች ።

ያንን በተረጋጋ መልኩ በፈገግታ ልትናገር ትችላለች ምክንያቱም ሁለት ነገሮችን ታውቃለች። ምንም ትግል ቢኖርም አስፈላጊው ነገር ከእሷ ሰማይ አባት ጋር ለመሆን ወደ ቤት መድረሷ ነው። በእሷ አዳኝ እምነት አማካኝነት ማድረግ እንደምትችል አወቀች።

እርሱ ለእሷ ቅርብ እንደሆነ ተሰማት። እንደምትሞት ባወቀችበት ቀናት ውስጥ መኝታ ቤቷ ስትተኛ ከእኔ ጋር ስለ አዳኝ አወራች። ከአልጋዋ አጠገብ ወደ ሌላ ክፍል የሚወስድ በር ነበር። እርሱን በቅርቡ እንደምታየው በእርጋታ ስታወራ ወደ በሩ እያየች ፈገግ አለች። በሩን በመመልከት በስተጀርባው ያለውን ክፍል ማሰቤን እስካሁን አስታውሳለው።

አሁን በመንፈስ ዓለም ነው ያለችው። ለዓመታት በአካላዊ እና ግለሰባዊ ፈተና ውስጥ በፈለገችው ሽልማት ላይ አይኖቿን ለመጠበቅ ችላለች።

ለእኛ ትታው የሄደችው የማበረታታት ቅርስ ሞርሞን ልጁን ሞሮኒን እና ህዝቦቹን ባበረታታቸው በ በሞሮኒ 7 ውስጥ የበለጠ ይጠቀሳል። ለትውልዶች የማበረታታት ቅርስ ነው ልክ እናቴ ለቤተሰቧ እንዳደረገችው። ሞርሞን ያንን የማበረታታት ቅርስ በሟች ህይወት ፈተናቸው ሁሉ ለዘላለም ሕይወት ብቁ ለመሆን ቆራጥነቱ ላላቸው አሳለፈ።

ሞርሞን በሞሮኒ 7 መጀመሪያ ቁጥሮች በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በመላዕክቶች እና መልካሙን ከመጥፎ እንድናውቅ እና ትክክልን እንድንመርጥ በሚፈቅደው በክርስቶስ መንፈስ ምስክርነት ጀመረ።

ወደ ሰማይ ቤታቸው ወደሚመራው መንገድ ላይ የሚታገሉትን ሰዎች ማበረታቻ በመስጠት ኢየሱስ ክርስቶስን አስቀደመ፣ ልክ እሱን የተከተሉት ሁሉ እንዳደረጉት።

እንደ ክርስቶስ ቃል በእርሱ እምነት ከሌላቸው ማንም ሰው ለመዳን አይችልም፤ ስለሆነም፣ እነዚህ ነገሮች ከቆሙ፣ እምነትም ደግሞ ይቆማል፤ እናም የሰዎች ሁኔታ አሰቃቂ ይሆናል፣ ምክንያቱም ቤዛነት እንዳልተፈፀመ ሆነው ይቆያሉና።

ነገር ግን እነሆ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፤ ስለእናንተ የተሻሉትን ነገሮች እፈርዳለሁ፤ ምክንያቱም እናንተ የዋህ በመሆናችሁ በክርስቶስ እምነት እንዳላችሁ እፈርዳለሁ፤ ምክንያቱም በእርሱ እምነት ከሌላችሁ ከቤተክርስቲያኑ ሰዎች ጋር ለመቆጠር ብቁ አትሆኑምና።1

ለእምነታቸው ጥንካሬ ማረጋገጫ ሞርሞን ትህትናን ተመለከተ። በአዳኙ ላይ ጥገኝነት እንደተሰማቸው ተመለከተ። ያንን እምነት በመገንዘብ አበረታታቸው። ሞርሞን እምነታቸው እና ትትናቸው በትግላቸው ውስጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ማረጋገጫቸውን እና መተማመናቸውን እንደሚገነባ እንዲዩ በመርዳት ማበረታቻ መስጠቱን ቀጠለ።

“እናም የተወደዳችሁ ወንድሞቼ በድጋሚ ተስፋን በተመለከተ እናገራችኋለሁ። ተስፋ ከሌላችሁ እምነትን እንዴት ለማግኘት ይቻላችኋል?

“እናም ተስፋ የምታደርጉበት ምንድን ነው? እናም ተስፋ የምታደርጉበት ምንድነው? እነሆ በክርስቶስ የኃጢአት ክፍያ እናም በትንሳኤው ኃይል ለዘለዓለም ህይወት እንዲኖራችሁ ተስፋ ይኑራችሁ እላችኋለሁ፤ እናም ይህም በእርሱ ባላችሁ እምነት ለእናንተ በገባላችሁ ቃል ኪዳን መሰረት ነው።

“ስለሆነም፣ አንድ ሰው እምነት ካለው ተስፋ ሊኖረው ይገባል፤ ያለ እምነት ምንም ዓይነት ተስፋ ሊኖር አይችልም።

“እናም በድጋሚ፣ እነሆ እንዲህ እላችኋለሁ፣ የዋህ እና በልቡ የሚራራ ካልሆነ በስተቀር እምነት እና ተስፋ ሊኖረው አይችልም።”2

ከዛ ሞርሞን የልባቸው ስጦታ በክርስቶስ ንፁህ ፍቅር በሚሞላበት መንገድ ላይ እንደሆኑ በመመስከር አበረታታቸው። እምነት በኢየሱስ ክርስቶስ፣ የዋነት፣ ትህትና፣ መንፈስ ቅዱስ እና የዘላለም ሕይወትን ለመቀበል የማሳካት ጥልቅ ተስፋ ግንኙነቶችን ለእነሱ አስተካከለላቸው። በዚህ መልኩ አበረታታቸው።

“ምክንያቱም በልቡ የሚራራ እናም የዋህ ካልሆነ በጌታ ፊት ተቀባይነት አይኖረውምና፤ እናም ሰው የዋህ እናም በልቡ የሚራራ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ከሆነ እርሱ ልግስና ሊኖረው ይገባዋል፤ ልግስና ግን ከሌለው እርሱ ከንቱ ነውና፤ ስለሆነም ልግስና ሊኖረው ይገባል።”3

ወደኋላ በመመልከት፣ ያ የልግስና—የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር—ስጦታ እናቴን ወደ ቤቷ በመሄድ ትግሏ ውስጥ እንዴት እንዳጠነከራት፣ እንደመራት፣ እንደጠበቃት እና እንደቀየራት አሁን አያለው።

“እናም ልግስና ትታገሳለች፣ እናም ደግ ናት፣ እናም አትቀናም፣ እናም በኩራት አትወጠርም፣ የራሷን አትፈልግም፤ በቀላሉ አትቆጣም፣ ክፉ አታስብም፣ እናም በመጥፎ ስራ አትደሰትም፣ ነገር ግን በእውነት ትደሰታለች፣ ሁሉንም ነገሮች ትታገሳለች፣ በሁሉም ነገሮች ታምናለች ሁሉንም ነገሮች ተስፋ ታደርጋለች፣ በሁሉም ነገሮች ትፀናለች።

“ስለዚህም፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ልግስና ከሌላችሁ ከንቱዎች ናችሁ፣ ልግስና አትወድቅምና። ስለሆነም ከሁሉም በላይ ታላቅ የሆነችውን ልግስናን ያዙ፤ ሁሉም ነገሮች መውደቅ አለባቸውና—

“ነገር ግን ልግስና ንፁህ የክርስቶስ ፍቅር ነው፤ እናም እስከዘለዓለም ይፀናል፤ እናም በመጨረሻው ቀንም እርሱን የያዘ መልካም ይሆንለታል።

“ስለሆነም የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ሁሉ ላይ በሚያፈሰው በዚህ ፍቅር ትሞሉ ዘንድ በኃይል ከልባችሁ ወደ አብ ፀልዩ፤ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆኑ ዘንድ፣ እርሱ በሚመጣበትም ጊዜ እንደእርሱ ሆነን እንዳለ እናየዋለንና፣ ይህ ተስፋም ይኖረናልና፣ ልክ እርሱ ፍፁም እንደሆነ እኛም ፍፁማን እንሆናለንና።4

ለሞርሞን ምሳሌ እና ትምህርት ማበረታቻ አመስጋኝ ነኝ። በእናቴ ቅርስ እኔም ተባርኬአለው። ከአዳም አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ያሉ ነብያት በትምህርታቸው እና በምሳሌዎቻቸው አጠንክረውኛል።

በግል እና ቤተሰባቸውን ለማውቃቸው ሰዎች ላለኝ ክብር ስል፣ የትግላቸውን ዝርዝር ወይም ታላቅ ስጦታቸውን በገሃድ ላለማረጋገጥ ወይም ላለመናገር መርጫለው። ነገር ግን ያየሁት ነገር ለመልካም ነገር አበረታቶኛል እና ለውጦኛል።

የእሷን ግላዊነት መጋራትን በመስጋት የባለቤቴን ማበረታቻ አጭር ዘገባ አክላለው። ይህንንም በጥንቃቄ አደርጋለው። ውደሳን የማትፈልግ እንዲሁም የማታደንቅ ሰው ነች።

ለ60 ዓመታት ተጋብተናል። በዛ ልምድ ምክንያት ነው አሁን እነዙህን የመጽሐፍ ቅዱሳት ቃላት ማለትም፦ እምነት፣ ተስፋ፣ የዋነት፣ መፅናት፣ የራስ ያልሆነን ነገር አለመፈለግ፣ በእውነት መደሰት፣ ክፋትን አለማሰብ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ልግስናን ትርጉም የምረዳው።5 በዚህ አጋጣሚ ተራ የሰው ዘሮች ከሕይወት እንግልታቸው ሲነሱ እነዛን ድንቅ ተስማሚዎች ወደ ቀን ተቀን ሕይወታቸው ለመውሰድ እንደሚችሉ መመስከር እችላለሁ።

በማዳመጥ ላይ ያላችሁ ሚሊዮኖች እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ታውቃላችሁ። ብዙዎቻችሁ እንዚህ ዓይነት ሰዎች ናቹ። ሁላችንም እንደዚህ ዓይነት አበረታች እና ወዳጅ ጓደኞች እንፈልጋለን።

እንደ የአገልግሎት እህት ወይም የአገልግሎት ወንድም ከአንድ ሰው ጋር ስትቀመጡ ጌታን ትወክላላችሁ። እርሱ የሚያደርገውን ወይም የሚለውን ነገር አስቡ። ወደ እርሱ እንዲመጡ ይጋብዛቸዋል። እርሱ ያበረታታቸዋል። ማድረግ ያለባቸውን የመለወጦች መጀመሪያ ይገነዘባል እና ያደንቃል። እና ለእነሱ ሊከተሉት የሚችሉት ፍፁም ምሳሌ ይሆናቸዋል።

ያንን ሙሉ በሙሉ ማድረግ ማንም አይችልም፣ ነገር ግን ይህን ጉባኤ በመስማት በመንገድ ላይ እንዳላችሁ ማወቅ ትችላላችሁ። አዳኝ ትግላችሁን በጥልቅ ያውቃል። በእምነት፣ ተስፋ እና ልግስና የማደግ ታላቅ ችሎታችሁን ያውቃል።

እርሱ የሚሰጣችሁ ትዕዛዛት እና ቃልኪዳኖች እናንተን የመቆጣጠር ፈተናዎች አይደሉም። ወደ ሚወዷችሁ ወደ ሰማይ አባታችሁ እና ወደ ጌታችሁ ቤት እንድትመለሱ እና ሁሉንም የእግዚአብሔርን ስጦታዎች እንድትቀበሉ ከፍ ሊያደርጓችሁ ያሉ ስጦታ ናቸው።

ኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያታችንን ዋጋ ከፈለ። ንስሃ ለመግባት እና እንደ ልጅ ንፁህ እና ከእግዚአብሔር ስጦታዎች መካከል ታላቁን ለመቀበል ዝግጁ ለመሆን በእርሱ በቂ እምነት ካለን ያንን የዘላለም ሕይወት በረከትን እንቀበላለን።

የእርሱን ግብዣ እንድትቀበሉ እና ለሰማይ አባታችን ልጆች እንድትሰጡ እጸልያለው።

በዓለም ዙሪያ ላሉ ሚስዮናችን እጸልያለው። እያንዳንዱን ግለሰብ ግብዣው ስሙን በራሳቸው ላይ በወሰዱት በአገልጋዮቹ አማካኝነት ከኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ እንዲፈልጉ እና እንዲያምኑ እንዲያበረታቱ ይነሳሱ።

ህያው እንደሆነ እና ቤተክርስቲያኑን እንደሚመራ እመሰክራለሁ። የእርሱ ምስክር ነኝ። ፕሬዝደንት ረስል ኤም.ኔልሰን ለመላው ምድር ሕያው የእግዚአብሔር ነብይ ናቸው። ያ እውነት እንደሆነ አውቃልሁ። በተቀደሰው በእየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን፡፡