አጠቃላይ ጉባኤ
የደቀ መዝሙርነት መንገዶች
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:4

የደቀ መዝሙርነት መንገዶች

ስለ ክርስቶስ እና ስለ መንገዶቹ መማር እርሱን ወደማወቅ እና ወደመውደድ ይመራናል።

የእምነት መንገድ

ዛሬ ጠዋት በሰሜን አሜሪካ ውስጥ ያሉ ሁለቱ ልጆቻችን እና ሶስቱ የልጅ ልጆቻችን እና ግማሽ የሚሆነው የዓለም ህዝብ የፀሀይን ብርሃንን በክብር በምስራቅ በኩል ስትነሳ ተመለከቱ። በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ሌሎቹ ሶስቱ ልጆቻችን እና ሰባቱ የልጅ ልጆቻችን እንዲሁም በሌላኛው የዓለም አጋማሽ ያሉ በምዕራብ በኩል ፀሀይ ስትጠልቅ ጨለማ ቀስ እያለ ሲመጣ ተመለከቱ።

ይህ ጊዜ የማይገድበው የቀን እና ማታ መፈራረቅ መቀየር የማንችለው ሕይወታችንን የሚመራ እውነታ የቀን ተቀን ማስታወሻ ነው። እነዚህን ዘላለማዊ እውነታዎች ስናከብር እና የምንሰራውን ነገር ከእነርሱ ጋር ስናስተካክል፣ ውስጣዊ ሰላም እና ስምምነት እናገኛለን። ያንን ሳናደርግ ስንቀር አንረጋጋም እንዲሁም ነገሮች እንደጠበቅነው አይሆኑም።

ቀን እና ማታ በምድር ላይ ለኖረ ለማንኛውም ሰው እግዚአብሔር ከሰጣቸው መንገዶች መካከል አንዱ ምሳሌ ነው። እንደየፍላጎታችን ልንደራደርበት እና ልናሸንፍበት የማንችለው የሰውነት ተፈጥሮአችን ፍፁም እውነታ ነው። ከአፍሪካ ወደ አጠቃላይ ጉባኤ ለመምጣት አውሮፕላን ስይዝ እና በአንድ ቀን ውስጥ ባዮሎጂያዊ ሰዓቴን በ10 ሰዓት ወደኋላ ባስተካከልኩኝ ጊዜ ሁሉ ይህንን አስታውሳለሁ።

ለመገንዘብ ስንሻ የሰማይ አባት እርሱን እንድናውቀው እና የሰላም እና የደስታ በረከቶችን እንድናገኝ ህይወታችንን ለመምራት በቂ የእውነት ምስክሮችን እንደሰጠን እናያለን።

በነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት የጌታ መንፈስ እንዲህ ያረጋግጣል፣ “እና ደግሞም፣ እንዳትታለሉም ለሁሉም ነገሮች ንድፍን እሰጣችኋለሁ፤ ሰይጣን በምድር ላይ አለና፣ እና አገሮችን እያሳታቸውም ይሄዳል።”1

የክርስቶስ ጠላት የሆነው ቆሪሆር የእግዚአብሔርን መኖር እና የክርስቶስን መምጣት ባለማመን በዚህ ዓይነት መታለል ወደቀ። ነብዩ አልማ ለእሱ እንዲህ መስክሮለት ነበር፦ “ሁሉም በምድር ገፅ ላይ ያሉት ነገሮች በሙሉ፤ አዎን እናም የምድር እንቅስቃሴ፣ አዎን፣ እናም ደግሞ በተለመደው ሁኔታ የሚንቀሳቀሱት ፕላኔቶች ታላቅ ፈጣሪ እንዳለ ያመለክታሉ።”2

ቆሪሆር ከማመኑ በፊት ምልክት እንዲሰጠው ሲጠይቅ አልማ ዱዳ እንዲሆን አደረገው። በመከራው ምክንያት ትሁት በመሆን ቆሪሆር በሰይጣን እንደተታለለ በነፃነት ተናዘዘ።

ለመታለል አንፈልግም። የብልህ ሕይወት ተዓምር በተደጋጋሚ በፊታችን ይካሄዳል። ስፍር ቁጥር የሌላቸው ክዋክብቶች እና ጋላክሲዎች የያዘውን ሰማይ ለቅፅበት መመልከት እና ስለእርሱ ማሰብ የአማኞች ልብ ነፍስ “የእኔ እግዚአብሔር እንዴት ታላቅ ነህ!” እንዲሉ ያነሳሳል።3

አዎን፣ የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር ሕያው ነው እና እራሱን በብዙ መንገዶች ለሁላችንም ይገልፃል።

የትህትና መንገድ

ነገር ግን እግዚአብሔርን ለመቀበል፣ ለማመን እና ለመከተል ልባችን ለእውነት መንፈስ ክፍት መሆን አለበት። ትህትና እምነትን እንደሚከተል አልማ አስተምሯል።4 “ትሁት እና ልበ ቀና” ላልሆነ ሰው እምነት እና ተስፋን ለማግኘት እና የእግዚአብሔርን መንፈስ ለመቀበል የማይቻል እንደሆነ ሞርሞን ጨምሮ ተናገረ።5 የዓለምን ክብር የሚያስቀድም ማንኛውም ሰው “የእግዚአብሔር ጠላት” እንደሆነ ንጉሥ ቢኒያም ተናግሯል።”6

ምንም እንኳን ፃድቅ እና ቅዱስ ቢሆንም ሁሉንም ጽድቅ ለማሟላት ለመጠመቅ እራሱን በመስጠት ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ፊት ትሁት መሆን የእርሱ ደቀ መዝሙርነት መሰረት እንደሆነ ገለፀ።7

ሁሉም አዲስ ደቀ መዛሙርት የጥምቀት ስርዓትን በማከናወን በእግዚአብሄር ፊት ትህትናን ማሳየት ይኖርባቸዋል። ስለዚህ፣ “ራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት ትሁት የሚያደርጉ እናም ለመጠመቅ ከፈለጉ እናም በተሰበረ ልብ እና በተዋረደ ምንፈስ ከመጡ … ወደ እርሱም ቤተክርስቲያን በጥምቀት ይወሰዳሉ።”8

ትህትና የደቀ መዛሙርትን ልብ ወደ ንስሃ እና መታዘዝ እንዲያዘነብል ያደርጋል። ከዚያም የእግዚአብሔር መንፈስ ለዚያ ልብ እውነትን ያመጣል እናም መግቢያውን ያገኛል።9

የሐዋርያ ጳውሎስን ትንቢት በእነዚህ የመጨረሻው ቀናት ውስጥ እንዲተገበር አስተዋፅኦ እያደረገ ያለው የትህትና አለመኖር ነው።

“ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና ገንዘብን የሚወዱ ትምክህተኞች ትዕቢተኞች ተሳዳቢዎች ለወላጃቸው የማይታዘዙ የማያመሰግኑ፣

ቅድስና የሌላቸው ፍቅር የሌላቸው ዕርቅን የማይሰሙ ሐሜተኞች ራሳቸውን የማይገዙ ጨካኞች መልካም የሆነውን የማይወዱ።”10

ከእርሱ እንድንማር የቀረበልን የአዳኙ ግብዣ ከዓለማዊ ፈተናዎች የመሸሽ እና እንደ እርሱ የዋህ፣ ልበ ቀና እና ትሁት የመሆን ግብዣ ነው። ከዚያም ፕሬዝደንት ረስልኤም. ኔልሰን በርቱዕ አንደበት ደጋግመው እንዳስተማሩን የእርሱን ቀንበር ለመሸከም እና ቀላል እንደሆነ ለማወቅ፣ ደቀ መዝሙርነት ሸክም እንዳልሆነ ነገር ግን ደስታ እንደሆነ ለመገንዘብ እንችላለን።

የፍቅር መንገድ

ስለ ክርስቶስ እና ስለ እርሱ መንገዶች መማር እርሱን ወደማወቅ እና ወደመውደድ ይመራናል።

በትህትና ባህሪ እግዚአብሔር አብን በሙሉ ማንነታችን መውደድ እና ሌሎችን እራሳችንን እንደምንወደው መውደድ በእርግጥ እንደሚቻል በምሳሌ አሳይቷል። ፍቃዱንም አካሉንም በመሰዊያው ላይ የያደረገበት ምድራዊ አገልግሎቱ፣ ወንጌሉ የተመሰረተበት እነዚህን መርሆዎች የመተግበሪያ መንገድ ነበር። ሁለቱም መርሆዎች ከራስ ውጪ የሚመለከቱ እና ከሌሎች ጋር እንዴት እንደምንዛመድ የሚገልጹ ናቸው፣ ግላዊ እርካታን ወይም ክብርን የምንሻበት አይደሉም።

ታዓምራዊው ምጸት ከሁሉም የተሻለ ጥረታችንን እግዚአብሔርን እና ሌሎችን በማፍቀር ላይ ስናተኩር፣ ይህ ልምድ ከሚያመጣው ፍፁም ሰላም እና ደስታ ጋር እንደ እግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ያለንን እውነተኛ መለኮታዊ ዋጋችንን ለማግኘት እንችላለን።

በፍቅር እና በአገልግሎት አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር እና እርስ በእርስ አንድ እንሆናለን። ከዚያም ሌሂ “ከቀመስኩት የበለጠ በጣም ጣፋጭ” ብሎ የተናገረውን የዚያን ንፁህ ፍቅር ከመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት መቀበል እንችላለን።11

አብን እና እኛን የመውደድ መንገድን ለማሳየት የተቻለውን ሁሉ በመስጠት እና በማድረጉ ክርስቶስ የተቀበለው አክሊል ሁሉንም ኃይል እግዚአብሔር ያለውን ኃይል በሙሉ መቀበል ነበር እሱም ከፍ ማለት ነው።12

የእግዚአብሔር እና የጎረቤታችን ዘለቄታ ያለው ፍቅር የመመገብ እድል ከእግዚአብሔር ጋር በአንድያ ልጁ በእየቀኑ በግል እና በቤተሰብ ጸሎት በመገናኘት ቅዱስ ልምዶች፣ ስለእነሱ በግል እና በቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በጋር በመማር፣ ሰንበትን በጋራ በመቀደስ እና በግል ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን በመያዝ እና እስከተቻለ ድረስ በጋራ በመጠቀም ከቤት ይጀምራል።

እያንዳንዳችን እንደ ግለሰብ በእውቀታችን እና ለአብ እና ለወልድ ባለን ፍቅር ስናድግ፣ በምስጋና እና እርስ በእርስ ባለን ፍቅር እናድጋለን። ከቤት ውጪ ያሉትን ሌሎችን የመውደድ እና የማገልገል ችሎታችን የበለጠ ያድጋል።

እቤት የምናደርገው ነገር እውነተኛ የሚፀና እና የሚያስደስት ደቀ መዝሙርነት ነው። ባለቤቴ ግላዲስ እና እኔ በቤታችን ውስጥ ያጣጣምነው የተመለሰው ወንጌል ጣፋጭ በረከቶች የመጣው በቤት ውስጥ እግዚአብሔርን በማወቅ እና በማክበር ከመማር እና የእርሱን ፍቅር ለትውልዳችን ከማካፈል የመጣ ነው።

የአገልግሎት መንገድ

ለእግዚአብሔር ያለ ፍቅር እና በቤት ውስጥ ያደገ እርስ በእርስ አገልግሎት እና ከቤት ውጪ ሌሎችን ማገልገል በጊዜ ውስጥ ወደ በጎነት ባህሪ ያድጋል።

በሕይወት ባሉ የጌታ ነብያቶች እና ሐዋርያቶች ከተቀመጠው በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ከተቀደሰ አገልግሎት መንገድ ጋር ይዛመዳል። ከእነርሱ ጋር አንድ እንሆናለን።

ከዚያም “በማንኛውም ሃሳብ” “እንዳንጠራጠር” እና “እንዳንፈራ” በእነርሱ አማካኝነት ወደጌታ ለመመልከት እንችላለን።13

እንደ ህያው የጌታ ነብያት እና ሐዋርያት፣ “ለሁሉም ሰው ቸርነት በማሳየት እና ለእምነት ቤተሰቦች በጎ ሃሳቦቻችንን ካለማቋረጥ እያስዋብን እና በእግዚአብሔር ፊት እና በክህነት ትምህርት በራስ መተማመናችን እያጠነከርን እንደሰማይ ጤዛ ነፍሳችንን እያጠራን” ወደፊት መሄድ እንችላለን።

በሕይወት ካሉት ከጌታ ነብያት እና ሐዋርያት ጋር፣ እኛም በተቀደሰ አገልግሎት “መንፈስ ቅዱስ ዘላቂ ጓደኛችን የሚሆንበት፣ በትራችን የማይለወጥ የጽድቅ እና የእውነት በትር የሚሆንበት እና ግዛታችን ዘላለማዊ የሚሆንበት እናም ወደ እኛ ካለምንም ግዴታ ለዘላለም የሚፈስበት” የጠነከረ የእምነት ኡደትን መቀላቀል እንችላለን፣ 14 ይህም የአብ ዕቅድ ቃል ኪዳን ነውና። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።