አጠቃላይ ጉባኤ
በሙሉ ልብ
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


በሙሉ ልብ

በግል የደቀመዛሙርትነት ጉዞአችን ትእደሳች እና ሙሉ ልብ ያእን የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች መሆን ይገባናል።

አንዳንዴ፣ ምን እንደሚጠበቅ ማወቅ ይረዳል።

በተልዕኮው መጨረሻ አካባቢ፣ ኢየሱስ ሐዋሪያቱን አስቸጋሪ ጊዜዎች እንደሚመጡ ነገራቸው። ነገር ግን፣ “አትጨነቁ” አላቸው።1 አዎን፣ ትቶአቸው ይኄዳል፣ ነገር ግን ብቻቸውን አይተዋቸውም።2 እነርሱም እንዲያስታውሱ፣ በፅናት እንዲቆሙ፣ እና ሰላይ እንዲያገኙ ይረዳቸው ዘንድ መንፈሱን ይልክላቸዋል። አዳኝ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመሆን የገባውን ቃል እንደሚፈጽም ነው፣ ነገር ግን የእርሱን መገኘት እንድናውቅ እና እንድንደሰት እንዲረዳን በቀጣይነት እርሱን መፈለግ እንዳለብን ነው።

የክርስቶስ ደቀመዛሙርቶች ሁልጊዜም አስቸጋሪ ጊዜዎች አጋጥሟቸዋል።

ውድ ጓደኛዬ በመካከለኛው ምዕራብ ዩናትድ ስቴትስ ውስጥ በሐምሌ 7 ቀን 1857 (እ.አ.አ) በነብራስካ አድቨርታይዘር የታተመ የድሮ አንቀፅን ላከችልኝ። ምንባቡን እንዲህ ይላል፦ “ዛሬ ጠዋት አንድ የሞርሞኖች ቡድን ወደ ሶልት ሌክ በሚጓዙበት ወቅት በዚህ አለፉ። ሴቶች (በእርግጠኝነት በጣም ስሱ አይደሉም) የእጅ ጋሪዎችን እንደ አውሬ እየጎተቱ፣ አንድ [ሴት] በዚህ ጥቁር ጭቃ ውስጥ ወድቃ ሰልፉ ላይ ትንሽ እንዲቆም አድርጓል፣ ትንንሽ ልጆች እንደ እናቶቻቸው ቆራጥ መስለው የውጭ አገር ልብሳቸውን ለብሰው ይሄዳሉ።”3

ስለዚህች በጭቃ ስለተሸፈነች ሴት ብዙ አስቤ ነበር። በብቻዋ የምትጎትተው ለምን ነበር? ነጠላ እናት ነበረችን? አንዳንድ ጊዜ ታዛቢዎች እየተሳለቁባት፣ ንብረቶቿን በሙሉ ወደ ማይታወቅ የበረሃ ቤት በሠረገላ እየጎተተች፣ ይህን የመሰለ አሰቃቂ ጉዞ ለማድረግ ውስጣዊ ጥንካሬን፣ ብርቱነት፣ ጽናትን ምን ነበር የሰጣት?4

ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ስለ ፈርቀዳጅ ሴቶች ውስጣዊ ጥንካሬ እንዲህ አሉ፦ “ከእነዚህ ሴቶች አንዷን በኋለኛው ቀን ቅዱሳን በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከነበራቸው እምነት ልትመልሱ ትችላላችሁን? ስለ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ተልዕኮ አእምሮአቸውን ልታጨልሙ ትችላላችሁን? የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስን መለኮታዊ ተልእኮ በመጥቀስ ልታወርሯቸው ትችላላችሁን? አትችሉም፣ በዓለም ውስጥ በጭራሽ ማድረግ አትችሉም። ለምን? ምክንያቱም ይህን ያውቁታል። እግዚአብሔር ይህን ገለጠላቸው፣ እነርሱም ተረዱት፣ እናም በምድር ላይ ያለ ምንም ሃይል እውነት እንደሆነ ከሚያውቁት ሊመልሳቸው አይችልም።”5

ወንድሞች እና እህቶች፣ በምድረ በዳ እንዲሄዱ በተጠሩበት ጊዜ እየጎተቱ ለመቀጠል የሚያስችል ጥንካሬ ለማግኘት በጥልቀት የሚቆፍሩ ደቀ መዛሙርት፣ በእግዚአብሔር የተገለጠልን እምነት ያላቸው ደቀ መዛሙርት፣ በራሳችን የግል የደቀመዝሙርነት ጉዞ ደስተኛ እና በሙሉ ልብ ኢየሱስ የሚከተሉ እንዲህ ያሉ ወንዶች እና ሴቶች መሆን የዘመናችን ጥሪ ነው። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቶች፣ እናምናለን እናም በሶስት አስፈላጊ እውነቶች ለማደግ እንችላለን።

መጀመሪያ፣ ቀላል በማይሆንበትም ጊዜ፣ ቃል ኪዳኖቻችንን እናከብራለን

እምነታችሁ፣ ቤተሰባችሁ ወይም የወደፊት ህይወታችሁ ሲፈተን—ወንጌልን ለመኖር የምትችሉትን ሁሉ በምታደርጉበት ጊዜ ህይወት ለምን ከባድ እንደሆነ ስታስቡ—ጌታ ችግሮችን እንድንጠብቅ እንደነገረን አስታውሱ። ችግሮች የእቅዱ አካል ናቸው እና እናንተ ተጥላችኋል ማለት አይደለም፤ እነዚህ የእርሱ መሆን ማለት አካል ናቸው።6 እርሱ ከሁሉም በላይ “ህማምና ሀዘንን የሚያውቅ ሰው ነው።”7

የሰማይ አባት ከምቾቴ በላይ እኔ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በማድግበት ላይ ክኡረት እንዳለው ተምሬአለሁ። ሁልጊዜም እንዲህ እንዲሆን ባልፈልግም—እንዲህ ነው።

በተመቻቸ ሁኔታ መኖር ሀይል አያመጣም። የቀኑን ፈተና ለመቋቋም የሚያስፈልገን ሀይልም የጌታ ሀይል ነው፣ እናም የእርሱ ሀይል ከእርሱ ጋር ባለን ቃል ኪዳን በሙል ይመጣል።8 ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ሲያጋጥመን በእምነታችን መደገፍ—እንደምናደርገ ከአዳኝ ጋር ቃል የገባነውን ለማድረግ በየቀኑ መትጋት፣ በተለይም ስንደክም፣ ስንጨነቅ እና ከአስጨናቂ ጥያቄዎች እና ጉዳዮች ጋር ስንታገል—ቀስ በቀስ ብርሃኑ፣ ብርታቱን፣ ፍቅሩን፣ መንፈሱን፣ ሰላሙን መቀበል ነው።

የቃል ኪድን መንገን መጓዝ አላማ ወደ አዳኝ ለመቅረብ ነው። እርሱ ነው አላማው፣ ፍጹም እድገታችን ሳይሆን። ድርድር አይደለም፣ እናም ጉዞአችንን ከሌሎች ጋር ማነጻጸር አያስፈልገንም። ስንደናቀፍም፣ እርሱ አለ።

ሁለተኛ፣ በእምነት መተግበር እንችላለን

እንደ ኢየሱስ ክስርሶስ ደቀ መዛሙርቶች፣ እምነት እርሱ የሚጠይቅብን ስራ ነው—በልዮም በአስቸጋሪ ጊዜዎች።9

ከብዙ አመታት በፊት፣ ወላጆቼ ቤታቸውን እንደገና በምንጣፍ ለመሸፈን ወሰኑ። አዲሱ ምንጣፍ ከመምጣቱ አንድ ምሽት በፊት፣ እናቴ ወንድሞቼን የቤት እቃዎችን እንዲያወጡ እና አዲሱን ምንጣፍ እንዲነጠፍ ዘንድ የመኝታ ክፍል ምንጣፎችን ቀድደው እንዲያወጡ ጠየቀቻቸው። በዚያ ጊዜ ሰባት አመት የነበረችው እህቴ፣ ኤመሊ፣ ተኝታ ነበር። ስለዚህ፣ ተኝታ እያለች፣ እነርሱ በጸጥታ ከመኝታ በስተቀር የቤት እቃዎችን በሙሉ አውጥተው፣ ምንጣፉንም ቀደው አወጡ። ልክ ታላቅ ወንድሞች አንዳንዴ እንደሚያደርጉት፣ ለመቀልድ ወሰኑ። ንብረቶቿን በሙሉ ከፍሏ እና ከግድግዳዎ ላይ በማውጣት፣ ክፉን በሙሉ ባድ አደረጉት። ከዚያም ማስታወሻ ጻፉና ግድግዳው ላይ ለጠፉት፦ “ውድ ኤሚሊ፣ ትተንሽ ሄደናል። ከትንሽ ቀናት በኋል ደብዳቤ ጽፈን የት እንዳለን እንነግርሻለን። በፍቅር፣ ቤተሰብሽ።”

በሚቀጥለው ጠዋት ኤሚሊ ቁርስ ለመብላት ስላልመጣት፣ ወንድሞቼ እርሷን ለማግኘት ሄዱ—እርሷም ብቻዋን በሯን ዘግታ በሀዘን አገኟት። ኤሚሊ ስለዚህ አጋጣሚ በኋላ እንዲህ አሰላስላለች፦ “በጣም ሀዘን ተሰምቶኝ ነበር። በሩን ብከፍት ኖሮ ምን ይደርስ ነበር? ምን እሰማ ነበር? ምን አሸት ነበር? ብቻዬን እንዳልሆንኩኝ አውቅ ነበር። እንደምወደድም አውቅ ነበር። ባለሁበት ሁኔታ ላይ አንድ ነገር ለማድረግ ሀሳብም በአዕምሮዬ አልገባም ነበር። ተስፋ ቆረጥኩኝ እናም በቁም ሳንጣ ውስጥ በማልቀስ ቆየሁ። ግን በሩን ብከፍተውስ ኖሮ።”10

እህቴ ባየችው ነገር ላይ ተመርኩዞ ግምቷን ሰጠች፣ ነገር ግን ነገሮች በትክክል የነበሩበትን የሚያንፀባርቅ አልነበረም። አንድ ነገር ለማድረግ፣ በሩን ለመክፈት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ለመስራት ሳንሞክር፣ እኛ ልክ እንደ ኤሚሊ በሀዘን ወይም በመጎዳታችን ወይም በተስፋ መቁረጥ ወይም በጭንቀት ወይም ብቸኝነት ወይም ንዴት ወይም ብስጭት መጨቆናችን አስደናቂ አይደልምን?

ቅዱሳት መጻህፍት የማይቻል ነገር ሲያጋጥማቸው፣ በቀላሉ እርምጃ የወሰዱ፣ በእምነት ተነስተው ወደፊት በገፉ በክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ወንዶችና ሴቶች ምሳሌዎች ተሞልተዋል።11

መፈወስ ለፈለጉት ለማጻሞች፣ ክርስቶስ እንዲህ አላቸው፣ “ሂዱ፥ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ አላቸው። እነሆም፥ ሲሄዱ ነጹ።”12

ሄዱ እና ልክ እንደተፈወሱ አይነት ለካህናት ራሳቸውን አሳዩ፣ እናም በስራቸውም ተፈወሱ።

እንዲሁም በህመምዎ ውስጥ እርምጃ ለመውሰድ ማሰብ የማይቻል ሆኖ ከተሰማችሁ፣ እባካችሁ እርምጃዎቻችሁ እርዳታ ለማግኘት ወደ ጓደኞቻችሁ፣ ወደቤተሰብ አባል፣ ወደ ቤተክርስትያን መሪ፣ ወደባለሙያ የሚደርሱ አድርጉ። ይህ ለተስፋ የመጀመሪያ እርምጃ ሊሆን ይችላል።

ሶስተኛ፣ በአምልኮአችን ሙሉ ልብ እና ደስተኛ ለመሆን እንችላለን13

አስቸጋሪ ጊዜያት ሲመጡ፣ ወደ ምድር ከመምጣቴ በፊት ክርስቶስን ለመከተል እንደመረጥኩ እና በእምነቴ፣ በጤንነቴ እና በፅናቴ ላይ ያሉ ተግዳሮቶች እዚህ ያለሁበት ምክንያት እንደሆኑ ለማስታወስ እሞክራለሁ። እናም የዛሬው ፈተና እግዚአብሔር ለእኔ ያለውን ፍቅር አጠራጣሪ ያደርገዋል ወይም በእርሱ ላይ ያለኝን እምነት ወደ ጥርጣሬ እንዲለውጠው ፈጽሞ ማሰብ የለብኝም። ሙከራዎች እቅዱ አልተሳካም ማለት አይደለም፤ ይህም እግዚአብሔርን እንድፈልግ ለመርዳት የታሰበው እቅድ አካል ናቸው። በትዕግሥት ስጸና፣ እንደ እርሱ፣ በሥቃይ ጊዜ አብዝቼ በትጋት ስጸልይ፣ እንደ እርሱን እሆናለሁ።14

ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችንን በፍጹም ልቡ የመውደድ—በምንም ይሁን ምን ፈቃዱን በመፈጸም ፍፁም ምሳሌ ነበር።15 እኔም ተመሳሳይ ነገር በማድረግ የእሱን ምሳሌ መከተል እፈልጋለሁ።

ሁለቱን ሳንቲም ወደ ቤተመቅደስ ግምጃ ቤት በወረወረችው መበለት ሙሉ ልብ፣ ሙሉ ነፍስ ደቀመዝሙርነት ተነሳስቻለሁ። ያላትን ሁሉ ሰጠች።16

ሌሎች የእርሷን ጉድለት ብቻ በሚያዩበት ቦታ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሷ ያላትን ሁሉ ብዛት አውቆ ነበር። ይህም በእያንዳንዳችን ላይ ተመሳሳይ ነው። እሱ የእኛን ጉድለት እንደ ውድቀት ሳይሆን እምነትን ለመለማመድ እና ለማደግ እንደ እድል አድርጎ ይመለከታል።

መደምደሚያ

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ወገኖቼ፣ በሙሉ ልቤ ከጌታ ጋር መቆምን መርጫለሁ። ከተመረጡት አገልጋዮቹ—ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እና ከሌሎች ሐዋሪያት—ጋር ለመቆም እመርጣለሁ ምክንያቱም ለእርሱ ስለሚናገሩ እና ከአዳኝ ጋር ለሚያስሩኝ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች መጋቢዎች ናቸውና።

በምሰናከልበት ጊዜ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ኃይል ላይ በመታመን መነሣቴን እቀጥላለሁ። ከእርሱ ጋር በገባሁት ቃል ኪዳን እቆያለሁ እናም የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት፣ በእምነት እና መመሪያው ላይ በምመካበት በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ በኩል ጥያቄዎቼ ላይ እሰራለሁ። ትንንሽ እና ቀላል ነገሮችን በማድረግ መንፈሱን በየቀኑ እፈልጋለሁ።

ይህም ተደቀ መዛሙርትነት መንገዴ ነው።

እናም የእለት ተእለት የሟችነት ቁስሎች እስከሚፈወሱበት ቀን ድረስ፣ ጌታን እጠብቃለሁ እናም እርሱን እንዲሁም ጊዜውን፣ ጥበቡን፣ እቅዱን እታመናለሁ።17

ከእናንተ ጋር ክንድ በክንድ በመያያዝ፣ ከእርሱ ጋር ለዘለአለም ለመቆም እፈልጋለሁ። በሙሉ ልብ። ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሉ ልብአችን ስናፈቅር፣ ሁሉንም በምላሽ እንደሚሰጠን በማወቅ።18 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

አትም